TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ECAA

" በኢትዮጵያ አየር ክልል ላይ የሚደረግ በረራ ደህንነቱ የተጠበቀና ከስጋት ነጻ ነው " - የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን

ወደ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም ሆነ በየትኛውም የኢትዮጵያ አየር ክልል ላይ የሚደረግ በረራ ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከስጋት ነጻ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በውጭ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ አየር ክልል የሚደረግ በረራ ስጋት እንዳለበት ተደርጎ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረተ ቢስና ከእውነታው የተቃረነ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የአገሪቷ የአየር ክልል እና አየር መንገዱ ፍጹም ደህንነቱ የተጠበቀ ለመሆኑ ለተጠቃሚዎቻችን እናረጋግጣለንም ብሏል።

ዓለም አቀፍ የጥንቃቄ እና ደህንነት ደረጃ መስፈርት በሚያዘው መሰረትም የተጠቃሚዎቻችን ምቾትና ደህንነት ተጠብቆ ከሥጋት ነጻ የሆነ በረራ እንዲያደርጉ የጥንቃቄ መስፈርቶችን እንደወትሮው ሁሉ እንደሚተገብርም ባለስልጣኑ አስታወቋል።

@tikvahethiopia