TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba 4 ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ በንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ የተቀመጡ ከ 1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ህዳር 8 ቀን 2014 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። በቤተ ክህነቱ ግቢ በሚገኝ…
የፖሊስ ማብራሪያ ፦
አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች እንደተያዙ የአ/አ ፖሊስ መግለፁ ይታወሳል።
ፖሊስ ስለጉዳዩ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት የፀጥታ አካላት ከህዝብ ጋር በመተባበር እያከናወኑ የሚገኙትን ውጤታማ ተግባር ለማጣጣል እና ትክክለኛውን መረጃ ከእውነት ሰውረው የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ውሸቶችንና ሌሎች ተገቢነት የሌላቸውን ወሬዎች እያሰራጩ ይገኛሉ ብሏል።
መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የተቋማቸውን ደህንነት ለመጠበቅ ጦር መሳሪያ እንዲጠቀሙ ሊፈቀድላቸው እንደሚችል ፖሊስ ገልጿል።
ነገር ግን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ ከተገኙት ጥይቶች መካከል ከ1 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑት የቡድን መሳሪያ የሆነ የብሬን ጥይቶች መሆናቸውንና እነዚህ ጥይቶች ሊገኙ የሚገባው በፀጥታ ተቋማት እጅ ብቻ ከመሆኑም ባሻገር ለተቋማት ጥበቃ አገልግሎት በፍፁም የማይፈቀዱ ናቸው ብሏል።
ይህንን በምርመራ ለማጣራትና ለማረጋገጥ ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ ማጣጣል እና ህዝብ በፀጥታ ስራ ላይ እያደረገ የሚገኘውን ተሳትፎ ዋጋ ማሳጣት አግባብ የለውም ብሏል ፖሊስ።
በወቅቱ በቁጥጥር ስር የዋለው የንብረት ግምጃ ቤቱ ሰራተኛ የክላሽ-ኮቭ ጥይቶች ናቸው ተብሎ በመዝገብ ፈርሞ እንደተረከበ ለፖሊስ ቃሉን መስጠቱ ተገልጿል።
በብረበራው ወቅት የተቀረፀውን ምስል ፖሊስ ለህዝብ አሰራጭቷል።
ቪድዮውን ያሰራጨው ፥ " እውነትን ክደው የሃሰት ወሬ እየፈበረኩ ህዝብን ለማደናገር የሚፈልጉ አካላትን ሴራ ለማጋለጥ ነው " ብሏል።
@tikvahethiopia

"ድሽታ ግና" ዘንድሮ ለ6ኛ ዙር በአደባባይ ይከበራል።
በየዓመቱ ታህሳስ 1 የሚከበረው የአሪ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ "ድሽታ ግና" በዓል አንድነትንና አብሮነትን የሚሰብክ እሴት ያለው ባህላዊ ክዋኔ መሆኑን በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲከበር እናደርጋለን ሲሉ የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ገልጸዋል።
በዘንድሮው አመት ለ6ኛ ዙር በአደባባይ የሚከበረው የድሽታ ግና በዓል የአደባባይ በዓል ሁኖ እንዲከበር የዞኑ አስተዳደርና የየወረዳ መንግስት መዋቅሮች ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር አንስተው በዘንድሮውም የዞኑ አስተዳደር ያልተቆጠበ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የብሔረሰቦች ቋንቋና ባህል ማክበር ህገመንግስታዊ መብት ሁኖ ሳለ በአንዳንድ የአሪ ኤሊቶች አማካይነት የዲሽታ ግና በዓል እንዳይከበር መንግስት ተፅእኖ እንደፈጠረበት በማድረግ ለህዝቡ የተሳሳተ መልእክት በማስተላለፍ ግጭት ለመፍጠር የተሞከረ ቢሆንም እንዳልተሳካ ገልፀዋል።
የአሪ ማህበረሰብ ለዘመናት ከሚታወቅበት ማንነቱ በተቃረነ ሁኔታ ጥቂት ተማርን በሚሉ አካላት ማህበረሰቡን የማይወክሉ ነገሮች እየተነሱ ይገኛሉ እና እነዚህን አካላት በተባበረ ሁኔታ ልናርማቸው ይገባል ብለዋል።
ከዚህ ጋር አያይዘውም ለሀገር አንድነት ለሀገር እድገትና ለህዝቦች ትስስር ጠቃሚ የሚሆኑ ባህላዊ እሴቶች ጎልብተው አደባባይ ወጥተው እንዲከበሩ ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርጉ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
በዞኑ ውስጥ ያሉ ማህበረሰቦችም ከውስጥ በመነጨ ፍቅር በነቂስ በመውጣት በአሉን በጋራ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
አስተዳዳሪው በመጨረሻም ለብሔረሰቡ አባላት በዓሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት እንዲሆን በመመኘት እስከበአሉ ፍፃሜ ድረስ ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
መረጃው የደቡብ ኦሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።
@tikvahethmagazine

#ECAA
" በኢትዮጵያ አየር ክልል ላይ የሚደረግ በረራ ደህንነቱ የተጠበቀና ከስጋት ነጻ ነው " - የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን
ወደ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም ሆነ በየትኛውም የኢትዮጵያ አየር ክልል ላይ የሚደረግ በረራ ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከስጋት ነጻ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በውጭ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ አየር ክልል የሚደረግ በረራ ስጋት እንዳለበት ተደርጎ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረተ ቢስና ከእውነታው የተቃረነ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የአገሪቷ የአየር ክልል እና አየር መንገዱ ፍጹም ደህንነቱ የተጠበቀ ለመሆኑ ለተጠቃሚዎቻችን እናረጋግጣለንም ብሏል።
ዓለም አቀፍ የጥንቃቄ እና ደህንነት ደረጃ መስፈርት በሚያዘው መሰረትም የተጠቃሚዎቻችን ምቾትና ደህንነት ተጠብቆ ከሥጋት ነጻ የሆነ በረራ እንዲያደርጉ የጥንቃቄ መስፈርቶችን እንደወትሮው ሁሉ እንደሚተገብርም ባለስልጣኑ አስታወቋል።

" የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወደ ታህሳስ ወር ተራዝሟል " - የጤና ሚኒስቴር
በኅዳር 2014 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ የነበረው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወደ ታህሳስ ወር መራዘሙን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የፈተናው ምዝገባ ለሁለት ጊዜ በመራዘሙ ምክንያት ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ወደ ታህሳስ መሸጋሸጉን በሚኒስቴሩ የብቃት ምዘና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አበባው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።
የምዘና ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከጥቅምት 05/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል።
የግል አመልካቾች የትምህርት ማስረጃ ሕጋዊነትና ትክክለኛነት ማረጋገጫ እንዲያገኙ ለማስቻል ምዝገባው ሁለት ግዜ መራዘሙን አስታውሰዋል።
ተማሪዎች ለሙያ ብቃት ምዘና ፈተናው ዝግጅት ተጨማሪ ጊዜ መጠየቃቸውንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በመሆኑም የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተናው በታህሳስ ወር እንደሚሰጥ ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።
More : @tikvahuniversity

#ማሳሰቢያ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ የህልውና ዘመቻ ላይ መሆኗ በማስታወስ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመከላከል፣ ኢትዮጵያ የተደቀነባትን የግዛት አንድነት ስጋትና ሉአላዊነት ጥሰት ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የጥንቃቄ እርምጃዎች መውስድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮሙዩኒኬሽንና የመገኛኛ መሳሪያዎች በእጁ የሚገኝ ማንኛዉም ግለሰብ፣ ተቋም፣ ኤምባሲ ወይም ዲፕሎማት፣ በመንግስታዊም ሆነ በግል ተቋማት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በዘርፉ የተሰማሩ አስመጪዎች እና ላኪዎች በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እንዲያሳዉቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
1. ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች ፦
• የጦር ሜዳ መነጽር (binokular)
• ኮምፓስ (Compass)
• የጂፒኤስ መሳሪያ (GPS)
2. ወታደራዊ እና ሲቪል የመገናኛ መሳሪያዎች ፦
• መገናኛ ሬዲዮ (Walkie Talkies radio)
• ሳተላይት ስልክ (satellite phone)
3. ቪሳት እና ቢጋን (A very small aperture terminal (VSAT) and Broadband Global Area network (BGAN))
4. ድሮኖች (Drones)
እነዚህን የመገናኛ እና ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጅንሲ በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0113851193 ፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ እንደሚጠበቅበት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳውቋል።

#EMA : ሲኤንኤን ፣ ቢቢሲ ፣ ሮይተርስ እና ኤፒ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለአራት የውጭ ሚዲያዎች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፅፏል።
እነዚህ ሚዲያዎች ሲኤንኤን (CNN)፣ ቢቢሲ (BBC)፣ ሮይተርስ (Reuters) እና አሶሺየትድ ፕሬስ (AP) ናቸው።
በማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ላይ ሚዲያዎቹ ፦
- TPLFን ዓላማ ለማገዝ በኢትዮጵያ ላይ የሀሰት ዜናዎች እና የዜና ትንታኔዎችን ማዘጋጀታቸው እና ማሰራጨታቸው ፥
- የህግ ማስከበር ዘመቻውን የዘር ማጥፋት (Genocide) ዘመቻ አድርገው ሪፖርት ማድረጋቸው ፥
- በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት መንግስት የሚያደርገውን ጥረት የሚያበላሽ ዘገባዎችን መስራታቸው፣
- በትግራይ ክልል መንግስት ረሃብንን እና አስገድዶ መድፈር እንደጦር መሳሪያ እንደተጠቀመበት ሪፖርት ማድረጋቸው ፤
- በሀገሪቱ መሪ ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ሪፖርቶችን ማዘጋጀታቸው፤
- የሀገሪቱን መሪ በዓለም አቀፍ መድረክ ለማጣጣል እና ሀገሪቱን ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ውሥጥ የሚከቱ ዜናዎችን ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።
ተቋማቱ የጋዜጠኝነት መርህን አክብረው እንዲሰሩ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ መልኩ ተደጋጋሚ ምክርና ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱን የጠቀሰው ባለስልጣኑ፤ መገናኛ ብዙኃኑ ከድርጊታቸው ከመታቀብ ይልቅ አባብሰው መቀጠላቸውን አስታውቋል።
ለኢትዮጵያዊያን ደህንነት ሲባል የሚዲያ ተቋማቱ በቀጣይ ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ባለስልጣኑ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት በመጠቀም የሰጣቸውን የሥራ ፈቃድ ለመሰረዝ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል።
በኢመብባ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ኢድሪስ ተፈርሞ የወጣው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

#ካማላ_ሃሪስ
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል ላይ በመሆናቸው ምክትላቸው ሥልጣን ተረክበዋል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል እያደረጉ በመሆኑ ምክትላቸው የሆኑት ካማላ ሃሪስን ፕሬዝዳንትነት ሥራውን መረከባቸውን ዛሬ የዋይትሐውስ ቃላቀባይ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ የጤና ምርመራቸውን ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ያቀኑት ዛሬ ሲሆን ከማደንዘዣው እስኪነቁ ድረስ ነው ምክትላቸው የፕሬዝዳንቱን ሥራ እንዲሰሩ የወከሉት።
በአሜሪካ ታሪክ ካማላ ሀሪስ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን የያዙ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል።
አሜሪካን እስካሁን ከመሯት ፕሬዝዳንቶች ጆ ባይደን በእድሜ የመሪውን ደረጃ ይይዛሉ ፤ በነገው ዕለት 79 ዓመታቸውን ይደፍናሉ።
NB : በአሜሪካ ፕሬዘዳንትነት ታሪክ እኤአ ከ2002 እስከ 2007 ዓመት ስልጣነ ላይ የነበሩት ፕሬዘዳንት ደብሊው ቡሽ ለህክምና ክትትል ሆስፒታል ሲገቡ ስልጣናቸውን ለምክትላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አሳልፈው ሰጥተው ነበር።

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 7 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,830 የላብራቶሪ ምርመራ 200 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 265 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#Soamlia
ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ያለው የድርቅ ሁኔታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተባባሰ መሆኑን UN አስጠንቅቋል።
በዚህም ተነሳ ሶማሊያ ውስጥ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች የውኃ እና የምግብ እጥረት ሊገጥማቸው እንደሚችል ተገልጿል።
UNOCHA በድርቁ የተነሳ ወደ 100,000 የሚጠጉ ሰዎች ከቀዬያቸው መፈናቀላቸውን ማስታወቁን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

#SouthOmoZone
በድርቅ ምክንያት ከብቶች እየሞቱ ነው።
በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ላይ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 98 ሺህ ሄ/ር ለግጦሽ ሲውል የነበረው መሬት ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመያዙ በተከሰተ ድርቅ የአርብቶ አደሩ የኢኮኖሚ ምንጭ የሆኑ ከብቶቻቸው በግጦሽ ሳር እጦት እየሞቱ ነው።
በዛሬው እለት የዞኑ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ምህረት አስራቱ የተመራ ቋሚ ኮሚቴ የመስክ ምልከታ በማድረግ ይህንን አረጋግጧል።
በአካባቢው ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ፎቶ ከላይ ተያይዟል።
Photo Credit : የደቡብ ኦሞ ዞን ኮሚኒኬሽን