TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ukraine #Russia

በሩስያ እና ዩክሬን መካከል ያለው ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ሰላማዊ መፍትሄ ካላገኘ በበርካታ ታዳጊ ሀገራት እንዲሁም ባደጉት ሀገራት ጭምር የሚያሳድረው ተፅእኖ የበረታ እንደሚሆን እየተገለፀ ነው።

በተለይ በጦርነቱ ከ2ቱ ሀገራት ውጭ NATO የመሰሉ ኃይሎች የሚቀላቀሉ ከሆነ ዓለማችን እጅግ የከፋ ቀውስ ውስጥ ትገባለች ተብሎ ተፈርቷል።

እስካሁን ምዕራባውያን ከሩስያ ጋር ጦር ባይማዘዙም የማዕቀብ ናዳ ሩስያ ላይ እያወረዱ ዩክሬንን በመሳሪያ እያስታጠቁ የሚያስፈልግሽን ሁሉ ድጋፍ እናደርግልሻለን እያሉ ይገኛሉ።

ጦርነቱ እንዲሁ በቀላሉ የማታይ አይደለም፤ በተዋጊዎቹ ሀገራት መካከል የሚረግፈው የሰው ህይወት እንደተጠበቀ ሆኖ ኢኮኖሚያቸው ይዳከማል። በርካታ ሀገራትን ችግር ላይ ሊጥል ይችላል። እስካሁን በነዳጅ፣ በስንዴ፣ በተፈጥሮ ጋዝ...ዋጋ ንረት ላይ ያሳደረው ተፅእኖ የሚታይ ነው።

ተጎጂዎቹ ግን ታዳጊ ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ ያደጉትንም ያካትታል።

ለምሳሌ፦ ዩናይትድ ኪንግደምን ብንመለከት ተንታኞች በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ባለፉት አሥርተ ዓመታት ባልታየ ፍጥነት የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል ይጠቁማሉ።

ካረን ዋርድ የተባሉ አንድ ተንታኝ በግጭቱ ምክንያት የሚከሰቱ ኢኮኖሚያዊ ውድቀቶች የዋጋ ግሽበት 8 በመቶ ሊያደርስ ይችላል ብለዋል።

የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጨምሯል ያሉት ተንታኙ ይህም የዩናይትድ ኪንግደም የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አድርጓል ብለዋል።

ሩሲያ ትልቅ #የማዳበሪያ ላኪ በመሆኗ የምግብ ምርት ዋጋ ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋትም አለ።

ጦርነቱ ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ይገኝ እንደሆነ አንዳችም ፍንጭ ማየት አልተቻለም። በየዕለቱ እየተባባሰ ዓለምን ህዝብ ስጋት ከፍ እንዳደረገ ቀጥሏል።

@tikvahethiopia