TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update BiT-ባህር ዳር⬇️

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የ3ኛ ዓመት ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች አጠቃላይ ፈተና (Holistic Exam ) አንፈተንም በማለታቸው የባሕር ዳር ቴከኖሎጅ ኢንስቲትዩት የአካዳሚክ ካውንስል የ3ኛ አመት ተማሪዎች ለአንድ አመት ማለትም 2011 የትምህርት ዘመንን ከትምህርት ገበታ እንዲታገዱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ይህ ግን የዩንቨርሲቲው ሴኔት ውሳኔ
አለመሆኑን #ተረጋግጧል

አሁን ላይ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው በባሕር ዳርና አካባቢው ያሉ የተማሪዎች ወላጆችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ሊያወያይ ነው። ውይይቱ ነገ ሰኞ
ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. በቴክኖሎጄ ኢንስቲትዩት ፖሊ ግቢ ከቀኑ 8፡00 ይጀመራል። አወያዩም የዩኒቨርሰቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ ናቸው።

ዶክተር ፍሬው ተገኘ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ በተማሪዎቹ እና በቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩቱ መካከል የተፈጠረውን ችግር ትክክለኛ ምክንያት ለወላጆች ለማስረዳት እና መፍትሄ ለመሰጠት ነው።

በምዘና መመሪያው ላይ ግን #ማሻሻያ አልተደረገም ነው ያሉት። በመሆኑም ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ፈቃደኛ ከሆኑ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት #ይቅርታ ሊያደርግላቸው እንደሚችል ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት።

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብሄር ብሄረሰቦች ቀን⬇️

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል #የተራራቁና #የተኳረፉ ሕዝቦችን በማስታረቅና በማቀራረብ #ይከበራል ተባለ፡፡

የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዓሉ እስካሁን ሲከበርበት የቆየው መንገድ የተለያዩ #ክፍተቶች እንዳሉበት በጥናት #ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

በሕዝቦች መካከል የቆየውን አብሮ የመኖር፣ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች ከማስጠበቅ አንፃር ክፍተቶች ነበሩ ብለዋል፡፡

አሁን ኢትዮጵያ ላይ እየታየ ያለው ሁኔታም ለዚህ ማሳያ ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ የብሔር ማንነትንና ኢትዮጵያዊነትን በማጣመር የዘንድሮውን በዓል ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ሰው በብሔሩ ብቻ የሚፈናቀልበት፣ የሚጠቃበትና የሚገደልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ያሉት አፈ ጉባኤዋ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል መጠራጠርና አለመተማመን ተፈጥሯል፣ በህብረተሰቡ ውስጥም በርካታ ቁስል አለ ብለዋል፡፡

የዘንድሮ በዓል የተራራቁ የሚቀራረቡበትና ለመፃኢ የጋራ ተስፋቸው የሚተባበሩበት መንገድ የሚታሰብበት ሆኖ እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡

በተለይም የጎላ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ የሰላምና የማረጋጋት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ሳይንሳዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ዘላቂነት ያለው ሰላም ለመፍጠር ከወዲሁ ስራዎችን ጀምረናል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

በበዓሉ ዝግጅት ወጣቶችና የኪነ ጥበብ ሰዎች እንደሚሳተፉ የተናገሩት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ እለቱን የኢትዮጵያውያን ቀን አድርጎ ያከብራል ብለዋል፡፡

ለበዓሉ አከባበር የሚወጣው ወጪም ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የሚውል ሲሆን ድግስ የማይበዛበት ዝግጅት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በብዝሃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊነት በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድብቅ እስር ቤቶቹ‼️

በአዲስ አበባ የተገኙት 7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች #ንብረትነታቸው የቤቶች ኮርፖሬሽን መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለሸገር ራድዮ ተናገረ፡፡

ዜጎች የተለያየ ስቃይ እና እንግልትን አሳልፈውባቸዋል የተባሉት እነዚህ ድብቅ እስር ቤቶች በቀድሞው የኪራይ ቤቶች ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በአሁኑ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሲተዳደሩ እንደቆዩ #ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ እንደነገሩን ከ7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች መካከል የሚደረግባቸው
ምርመራ ተጠናቆ የተወሰኑት ለቤቶች ኮርፖሬሽን ተመልሰዋል፡፡ የቀሩት ግን የሚካሄደው ምርመራ ስላላለቀ ታሽገው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በድብቅ እስር ቤትነት ሲያገለግሉ የቆዩት ቤቶች በየትኛው ክፍለ ከተማና ወረዳ የሚገኙ እንደሆኑ ግን አቶ ዝናቡ በግልፅ ለመናገር #አልፈቀዱም፡፡

#የቤቶች_ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የሚያስተዳድራቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶቹን ገሚሱን ለመንግስት ሹማምንት በመስጠት የተረፉትንም ለተለያዩ ግለሰቦች በዝቅተኛ ዋጋ #በማከራየት ያስተዳድራል፡፡

ድብቅ እስር ቤት ሆነው ቆይተዋል የተባሉት ቤቶች ኮርፖሬሽኑ ለባለስልጣናት ከሰጣቸው መኖሪያዎች መካከል ይሁኑ ወይንም ሌላ እስካሁን አልታወቀም፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ ይደረግ...

"የአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት ህመም በአዲስ አበባ እና በአራት ክልሎች ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እና ሶማሌ በአጠቃላይ በ365 ሰዎች ላይ የታየ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ዘጠኝ የሚሆኑት በላቦራቶሪ የኮሌራ በሽታ መሆኑ #ተረጋግጧል። ሁሉም አስፈላጊውን ህክምና እያገኙ ሲሆን በቅርቡ ለበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የክትባት አገልግሎት የምንሰጥ ይሆናል። ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግና ምልክቱ የታየባቸውን ወደ ጤና ተቋማት መውሰድ ይኖርባቸዋል። በየህክምና ተቋማት የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እየሰጡ ላለው የህክምና አገልግሎት በጤና ሚኒስቴር እና በራሴ ስም ማመስገን እወዳለሁ።"

Via ዶክተር አሚር አማን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ከከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር ፦

- ከምባታ ጠምባሮ ዞን በቅርቡ ከሞያሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ተለቆ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንክኪ ያላቸውን ግለሰቦች የማፈላለግ እና ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የማስገባት ተግባር ሲያከናውን ቆይቷል።

- ዛሬ በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ በቅርቡ ከሞያሌ አስገዳኝ ለይቶ ማቆያ ወጥቶ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንክኪ ያለው ነው።

- ግለሰቡ ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ወደ አንጋጫ ለይቶ ማቆያ ማዕከል እንዲገባ ተደርጎ ናሙናው ወደ ደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተልኮ በተደረገው ምርመራ በቫይረሱ መያዙ #ተረጋግጧል

- በአሁን ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል። ከእሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ግለሰቦች በማፈላለግ ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ማዕከል የማስገባት ስራ እየተሰራ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ሰበር ዜና!

የደቡብ ሱዳን ሌላኛው ምክትል ፕሬዘዳንት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ዳግም እንደአዲስ የተዋቀረውን የደቡብ ሱዳን 'የኮቪድ-19 መከላከል ግብረ ኃይል (ታስክ ፎርስ) ሲመሩ የነበሩት ምክትል ፕሬዘዳንት ሁሴን አብድልበጊ አኮል በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው #ተረጋግጧል

ከዚህ ቀደም ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት የሆኑት ዶ/ር ሬክ ማቻር፣ ባለቤታቸው የመከላከያ ሚኒስትር አንጅሊና ቴኒ ፣ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ተማሪዎቹን እንደሚጠራ አስታወቀ!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኮቪድ-19ን በመከላከል ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት የሚጀምሩበትን ቁመና የሚገመግም ቡድን ወደየተቋማቱ መላኩ ይታወቃል፡፡

የግምገማ እና ክትትል ቡድኑ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዝግጁነት በተለያዩ መለኪያዎች መዝኖ ግብረ መልሱን ለመካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ አቅርቦ በስጋትና መልካም አጋጣሚዎች ውይይት እና ምክክር ተደርጓል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅትና የጤና ሚኒስቴርን መመሪያ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ በማድረግ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማሩን እንደገና ለማስቀጠል የሚያስችል አቋም ላይ እንደሚገኝ በቡድኑ ግምገማ ውጤት #ተረጋግጧል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ መደበኛ ትምህርቱን የሚያስቀጥል ይሆናል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
መስከረም25/2013 ዓ.ም
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
" የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል "

13 የ " ቤቲንግ " ሥራ ድርጅቶች እንዲሁም 109 አንቀሳቃሾቻቸው ከህብረተሰቡ የሚሰበስቡትን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በመጠቀም በጥቁር ገበያ የውጭ ሀገር ምንዛሬ ግዢ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን በተደረገ ክትትል በመረጋገጡ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ ተደረገ።

ጉዳያቸውም በህግ እንደሚታይ ተገልጿል።

" ቤቲንግ " በሚል ስያሜ የሚታወቁትና የውርርድ ስራዎችን ላይ የተሰማሩት እነዚህ አካላት #የታክስ_ማጭበርበርን ጨምሮ በህገ-ወጥ የጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ ግዢ ወንጀል ድርጊት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው #ተረጋግጧል ሲል የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ የ13ቱን የቤቲንግ ስራ ድርጅቶች እና የ109 አንቀሳቃሾቻቸውን ስም ዝርዝር በይፋ አልገለፀም።

በእነዚህና በሌሎችም ዘርፎች በሚንቀሳቀሱ እና መሰል የወንጀል ተግባር ላይ በሚሳተፉ አካላት ላይ ቀጣይነት ያለው ክትትልና ህጋዊ የሆነ እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታወቀው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ታሳታፊ እየሆኑ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine