TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ህወሓትን የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ፥ "የሀገርን ህልውናን እየተፈታተነ ያለውን ሽብርተኛውን የህወሃት ቡድን ለማውገዝ እና የሀገርን አንድነት ለማስከበር የሚፋለመው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ለመደገፍ ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል" ሲል አሳውቋል።

ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረሰ በመስቀል አደባባይ እና በዙሪያው የሚገኙ መንገዶች ለተወሰነ ሰዓት ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፦

• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ

• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይና ታች

• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት

• በቸርችልር ጎዳና ወደ መ/አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል

• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደመ/አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት

• ከሜክሲኮ አደባባይ፣ በሰንጋ ተራ በድሉ ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መ/ቤት

• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መ/ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ ለቀላል ተሽከርካሪዎች ደግሞ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ ዝግ ይሆናሉ።

መንገዶቹ የሚዘጉት ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ነው። ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ተሽከርካሪ ለእረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ የሚዘጉ መንገዶች ! ነገ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ህወሓትን የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ፥ "የሀገርን ህልውናን እየተፈታተነ ያለውን ሽብርተኛውን የህወሃት ቡድን ለማውገዝ እና የሀገርን አንድነት ለማስከበር የሚፋለመው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ለመደገፍ ነገ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ…
#HappeningNow

በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ህወሓትን እና ሸኔን የሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው።

በሰልፉ ላይ የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትንና የውጭ ሀገር መገነኛ ብዙሃንን አጥብቀው የሚተቹ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተፃፉ የተለያዩ መፈክሮች በሰልፈኞች ተይዘዋል።

ሰልፈኞች ካያዟቸው መፈክሮች መካከል ፦

- የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች ከኢትዮጵያ ይውጡና ቦታው ለልማት ይዋል።

- CNN ፣ BBC በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ ዜናዎቻችሁን አቁሙ።

- የአውሮፓ መንግስታት መሰሪነታችሁን አቁሙ ፤ በግልፅ ግቡኑና ህወሓትን በጦር ሜዳ አግዙት።

- ኢትዮጵያ በውክልና ጦርነት አትንበረከክም።

- SHAME ON YOU USA !

- You are liar you can't repeat #Libya in Ethiopia again.

- Americans don't come back we are better off without you.

- #No_More የሚሉት ይገኙበታል።

በተጨማሪም ሰልፈኞቹ ከያዟቸው ሌሎች መፈክሮች መካከል ፦

- ይህ ትውልድ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ያስከብራል።

- የቀኝ ገዢዎች ሀሳብ ይመክናል ፤ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

- ክብር ለመከላከያ ሰራዊት

- ኢትዮጵያን ማሸነፍ አይቻልም።

- እኔ የሀገሬ ጠባቂ ነኝ።

- ከኢትዮጵያዬ 🇪🇹 የሚበልጥብኝ የለም።

- እኛ እያለን ኢትዮጵያ ሀገራችን በፍፁም አትፈርስም፤ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ፎቶ ፦ ከአ/አ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ህወሓትን እና ሸኔን የሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው። በሰልፉ ላይ የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትንና የውጭ ሀገር መገነኛ ብዙሃንን አጥብቀው የሚተቹ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተፃፉ የተለያዩ መፈክሮች በሰልፈኞች ተይዘዋል። ሰልፈኞች ካያዟቸው መፈክሮች መካከል ፦ - የአሜሪካ…
#Update

" ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

በመስቀል አደባባይና በዙሪያው የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ #በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማው ነዋሪ በተለይ ደግሞ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር በማድረጋቸው ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።

በተጨማሪ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ላሉ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሰልፉን ላስተባበሩ እና ለመሩ አካላት በሙሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
#ETHIOPIA

አሜሪካን ጨምሮ 16 የዓለማችን ሀገራት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተካሄደውን ጥምር ምርመራ ሪፖርት እንደሚቀበሉት በጋራ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

የጣምራ ሪፖርቱን እንደሚቀበሉ ያሳወቁት፦
• አሜሪካ
• አውስትራሊያ
• ቤልጂየም
• ካናዳ
• ዴንማርክ
• ፊንላንድ
• ፈረንሳይ
• ጀርመን
• አይስላንድ
• አየርላንድ
• ሉግዘንበርግ
• ኔዘርላንድ
• ኒውዝላንድ
• ኖርዌይ
• ስዊድን እና እንግሊዝ ናቸው።

ሀገራቱ በመግለጫቸው ሁለቱ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተቋማት በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ዙሪያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ያወጡት ሪፖርት ገለልተኛ እና ተጠያቂነትን ሊያሰፍን የሚችል መሆኑን አስታውቀዋል።

በሪፖርቱ መሰረት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁሉም አካላት መሳተፋቸው በመረጋገጡ ሁሉም ተሳታፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ሀገራቱ አሳስበዋል።

በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹ ላይ የተሳተፉ ሁሉም አካላት በሪፖርቱ ግኝቶች መሰረት ወደ መፍትሄ እንዲመጡም ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል 16ቱ አገራት የኢትዮጵያ መንግስት በጦርነቱ ለተጎዱ አካላት እያደረገ ያለው ድጋፍ፣ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በተጠረጠሩ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ምርመራ መጀመሩ ና እያደረጋቸው ላለው ሌሎች ጥረቶች እውቅና እንሰጣለን ብለዋል።

መንግስት የጀመረውን ጥረት እንዲቀጥልበት የጠየቁ ሲሆን በተለይ ለተጎጂዎች ተጨማሪ የሰብዓዊ መብት ድጋፎች እንዲደርሱ፣ በወንጀል ፈጻሚዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲካሄዱና ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም ብሄራዊ ውይይት እንዲያካሂድ ጠይቀዋል።

ሀገራቱ ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ሰላሟና መረጋጋቷ እንድትመለስ ድጋፍ እንደሚያደርጉና የግዛት አንድነቷን እንደሚያከብሩም አሳውቀዋል።

https://telegra.ph/ETHIOPIA-11-07

#አልዓይን

@tikvahethiopia
Audio
#Audio : ዛሬ አ/አ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ታዳሚው እነ CNN፣ አልጀዚራ፣ BBC ፣ ሮይተርስ በመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እጅግ ኃይለኛ ትችት እና ወቀሳን ሰንዝሯል።

የሚዲያ ተቋማቱ እጃቸውን ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ላይ እንዲሰበስቡ ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም ውሸቶችን ለዓለም ህዝብ ከማሰራጨት እንዲታቀቡ ሰልፈኞች አሳስበዋል።

ህወሓት /TPLF/ አሸባሪ ድርጅት ነው ያሉት የሰልፉ ታዳሚዎች አሜሪካ ለቡድኑ የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆምም ጠይቀዋል።

የሰልፉ ታዳሚያን በአሜሪካው ፕሬዜዳንት #ጆ_ባይደን አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ወቀሳን በእንዲሁም ትችት የሰነዘሩ ሲሆን ሀገራቸው አሜሪካ እጇን ከኢትዮጵያ ላይ እንድታነሳ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ታዳሚያኑ TPLF ሆነ ማንኛውም የውጭ አካል ኢትዮጵያን የማፍረስ አንዳችም አቅም የላቸውም ያሉ ሲሆን ፥ " ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ! ህዝቧም ይወክለኛል ያለውን መንግስት መርጧል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"እንፀልይ" ፖፕ ፍራንሲስ ፥ ዛሬ እሁድ ባስተላለፉት መልዕክታቸው በከባድ ሰብአዊ ቀውስ ለተጎዳው ለኢትዮጵያ ፣ የትግራይ ህዝብ ቅርብ ነኝ ብለዋል። ግጭት እንዲቆም ፣ የምግብና ጤና ዕርዳታ ተደራሽነት ለሁሉም እንዲረጋገጥ እና ማህበራዊ መግባባት በተቻለ ፍጥነት እንዲመለስ በጋራ #እንፀልይ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። @tikvahethiopia
ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ።

በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲደረግ ብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዛሬ ጥሪ አቀረቡ።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት የሰላም ጥሪያቸውን ሲያሰሙ ነበር።

ዛሬ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በነበረ መርሃ ግብር ላይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ባሰሙት ንግግር ከኢትዮጵያ የወጡትን ዜናዎች እየተከታተሉ መሆኑን ገልፀዋል።

“ከ1 ዓመት በላይ በዘለቀው ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎጂ መሆናቸው እና ግጭቱ ከባድ ሰብዓዊ ቀውስን ያስከተለ መሆኑን የሚገልፁ ዜናዎችን “በአሳሳቢነት” እየተከታተልኩ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ወንድማማችነት መግባባትና ሰላማዊ የውይይት መንገድ እንዲሰፍን ጥሪዬን አቀርባለሁ" ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Mekelle

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ እና የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ማርቲን ግሪፊትስ እና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ዛሬ የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መግባታቸውን ሮይተርስ ከአንድ የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ምንጭ እና ጉዳዩን ከሚያውቅ አንድ ሰው መስማቱን ዘግቧል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የUN የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ቃል አቀባይ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ አልሰጠም።

በኒውዮርክ የሚገኙ የUN ባለስልጣናት ስለጉዳዩ መረጃ እንዲሰጡ ወዲያውኑ ማግኘት እንዳልተቻለ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ቃል አቀባይ ኢባ ካሎንዶ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በባለስልጣናቱ ጉብኝት ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ አለመስጠታቸውን ዜና ወኪሉ ዘግቧል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ዘግይቶ በወጣ መረጃ ሁለቱም ባለስልጣናት በመቐለ ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውና ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊና የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ማርቲን ግሪፊትስ ከቀናት በፊት አዲስ አበባ መግባታቸው እና ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት እና የአሁኑ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ቆሞ ሰላም እንዲወርድ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ህወሓትን እና ሸኔን የሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው። በሰልፉ ላይ የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትንና የውጭ ሀገር መገነኛ ብዙሃንን አጥብቀው የሚተቹ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተፃፉ የተለያዩ መፈክሮች በሰልፈኞች ተይዘዋል። ሰልፈኞች ካያዟቸው መፈክሮች መካከል ፦ - የአሜሪካ…
" ... ሕዝብ ተናግሯልና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሊያዳምጥ ይገባል " - የመንግስት ኮሚኒኬሽን

ሰሞኑን በተለያዩ ክልሎች ከ30 ሚልዮን በላይ ሕዝብ ዐደባባይ ወጥቶ ስለሀገሩ ተናግሯል ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን " ህዝቡ ኢትዮጵያን ለማዳን እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት እንደሚከፍል፣ ለጸጥታ ኃይሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ፣ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማይቀበል፣ የሕወሐትንና አጋር ጽንፈኛ ኃይሎችን ሀገር የማፍረስ የሽብር ተግባራት አጥብቆ እንደሚያወግዝ በግልጽ ተናግሯል" ሲልም አክሏል።

አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች፣ ዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ስለ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፉትን የተዛባ መረጃ ሕዝቡ መኮነኑንም ገልጿል።

" የሚያስተዳድረውን መንግሥት ነጻ፣ ገለልተኛና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መምረጡንና ይህንን ውሳኔውንም ዓለም እንዲያከብርለት ሕዝቡ አጥብቆ ጠይቋል። ሕዝቡ ሀገሩን ለማዳን ማንኛውንም መሥዋዕትነት እንደሚከፍል በተግባር አሳይቷል " ብሏል።

ሕዝቡ በወራሪው በተያዙ አካባቢዎችም በከፍተኛ ግለት እየተነሣ ነው ያለው የመንግስት ኮሚኒኬሽን " በተወረሩ አካባቢዎች የሚገኘው ሕዝብ ጽንፈኛውን ሕወሐት ምቾት ተሰምቶት እንዳይቀመጥ እያደረገው ይገኛል" ብሏል።

አክሎ ፥ " ይህ የሕዝብ ንቅናቄ አሸባሪውን በሁሉም ቦታዎች እግር በእግር እየተከታተለ ርምጃ በመውሰድ አከባቢዎችን ተገድዶ እንዲለቅ እያደረገው ይገኛል " ሲል ገልጿል።

ያንብቡ : telegra.ph/ETHIOPIA-11-07-2

ፎቶ ፦ አቤል ጋሻው

@tikvahethiopia