TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም ይፋ ይሆናል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እንዲሁም የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት የጋራ ሪፖርቱን ግኝቶች፣ መደምደሚያዎች…
#ETHIOPIA

ዛሬ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እና የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት የጋራ ሪፖርቱን ግኝቶች ፣ መደምደሚያዎች እና ምክረ ሃሳቦችን ለማቅረብ በአዲስ አበባ እና ጄኔቫ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* ዝርዝር መረጃ ! ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች ከላይ በዝርዝር ተቀምጠዋል ያንብቡ። @tikvahethiopia
#የወንጀል_ተጠያቂነት

መላው ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ድንጋጌዎች እንዲሁም አዋጁን መሰረት አድርጎ የወጡትን መመሪያዎች መተላለፍ የወንጀል ተጠያቂነትን ያመጣል ፤ ቅጣትን ያስከትላል።

ይህም የወንጀል ተጠያቂነት ፦

- የአዋጁን ድንጋጌዎች እና በአዋጁ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ 3 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም እንደጥፋቱ ክብደት እስከ 10 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል።

- የአዋጁን ድንጋጌዎች እና በአዋጁ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ የተፈፀመው ወንጀል በሌሎች ሕጎች ከዚህ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ የከበደው ቅጣት ተፈጻሚ ይሆናል።

- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የተፈፀሙ የአዋጁ እና በአውጁ ማዕቀፍ የወጡ መመሪያዎች ጥሰቶች የአዋጁ ተፈጻሚነት ጊዜ ቢያበቃም፣ የሚያስከትሉት የወንጀል ተጠያቂነት በመደበኛው የወንጀል ሥነ ስርዐት ሕግ መሰረት ይቀጥላል።

#StateofEmergencyEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba መሳሪያ ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ባለጦር መሳሪያ ግለሰቦች በ2 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግቡ የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ደህንነት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አሳሰቡ። የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ወቅታዊ ፀጥታን በተመለከተ መግለጫ ተሰጥተዋል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በመንደር እርስ በርስ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቁ ተፈቅዷል ብለዋል። አደረጃጀቱ ከፀጥታ…
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ማንኛውም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ወይም የፖሊስ አገልግሎትን ማግኘት ስትፈልጉ በ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 ፣ 997 መጠቀም እንደምትችሉ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ትላንት በተቀመጠው የሁለት ቀን ጊዜ ውስጥ በ11ዱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች በስራ ሰዓት በግንባር ቀርቦ ማስመዝገብ አለበት።

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ በማስመዝገብ ህጋዊነቱን ተላብሶ የጦር መሳሪያውን ተጠቅሞ እራሱንና አካከበቢው እንዲጠብቅበት ሲል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአዲሱ ክልል የስልጣን ርክክብ ነገ ይደረጋል። ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔውን ነገ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አስታውቀዋል። የተከበሩ የምክር ቤቱ ዋና አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ ዛሬ እንዳሳወቁት ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂው አስቸኳይ ጉባኤ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ…
#Update

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማከሄድ ጀምሯል።

በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በፌዴረሽን ምክር ቤት 11ኛ ክልል ሆኖ ለጸደቀው ደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል የስልጣን ርክክብ ያደርጋል።

@tikvahethiopia
#ENDF

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ የአየር ኃይል አዲሀገራይ በተባለ አካባቢ በሚገኝ አዲቡክራይ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ማሠልጠኛ ማዕከል ላይ የአየር ድብደባ መፈፀሙን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።

በዚህ ማሠልጠኛው በአሁኑ ወቅት የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ለሽብር ተልዕኮው የመለመላቸው በርካታ ታጣቂዎች እያሠለጠነበት የሚገኝበት ቦታ ነው ሲል የመንግስት ኮሚኒኬሽን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ዛሬ ጥቅምት 24/2014 ዓ/ም የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ይደረጋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ እና የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት የጋራ ሪፖርቱን ግኝቶች ፣ መደምደሚያዎች እና ምክረ ሃሳቦችን…
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
3.8 MB
#የምርመራ_ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (EHRC) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (OHCHR) በትግራይ ግጭት ዙሪያ በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።

የEHRC እና OHCHR የጋራ ሪፖርት በትግራይ ግጭት ላይ የተሳተፉ ሁሉም አካላት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ያሳያል።

* ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING በመላ ሀገሪቱ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያሳለፈው ውሳኔ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን በ48 ሰዓታት ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል። @tikvahethiopia
#Update

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ነገ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይፀድቃል።

በሃገር ህልውናና ሉአላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በኢፌደሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93/1 ፦

• የውጪ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቁም የማይቻል ሲሆን፣

• ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማውጣት ሥልጣን እንዳለው ይደነግጋል፡፡

በዚሁ አንቀጽ 2(ሀ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በታወጀ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መቅረብ አለበት በሚል ተደንግጓል ፡፡

በዚህም በሚኒስትሮች ም/ቤት የተዘጋጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነገ ለም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
" Genocide ተካሂዷል ለማለት መረጃ የለም" - ሚሼል ባሽሌት

ጄኔቫ ላይ መግለጫ የሰጡት የተመድ (UN ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት በተለያየ ደረጃ በሁሉም አካላት የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን መኖራቸውን ገልፀዋል።

ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት እጅግ በተደጋጋሚ ምርመራው ጭብጦች (Facts) ላይ ተመስርቶ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በሁሉም አካላት ቢፈፀሙም #Genocide ዘር ላይ ያተኮረ የጅምላ ፍጅት (የዘር ማጥፋት ወንጀል) ተካሂዷል ለማለት በቂ መረጃ የለም ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
#ሪፖርት

በትግራይ ግጭት ሁሉም አካላት ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈፅመው መገኘታቸውን የጋራ ሪፖርቱ አመላክቷል።

ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶች ፦

• ከሕግ ውጪ ግድያና ርሸና፣
• ማሰቃየት፣
• ወሲባዊና ጾታዊ ጥቃቶች፣
• በስደተኞች ላይ የተፈጸሙ ግፎች እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን በኃይል ማፈናቀል ይገኙበታል።

በጋራ የምርመራ ሪፖርቱ ከቀረቡት ክስተቶች መካካል በጥቂቱ ፦

በማይካድራ "ሳምረ" በተባለ ቡድን የተፈጸመ ጥቃት ይገኝበታል ፤ ምንም እንኳን ቁጥሩን እርግጠኛ ለመሆን ባይቻልም ከ200 በላይ ሰዎች በዚህ ጥቃት ተገድለው በጅምላ መቃብሮች መቀበራቸውን ተመላክቷል።

የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል ከተማውን በተቆጣጠሩባቸው ቀጣይ ቀናት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የበቀል ግድያዎች መፈጸማቸውን እና የፋኖ ሚሊሺያዎችም በግድያው መሳተፋቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል።

በአክሱም ከተማ የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከ100 በላይ ሲቪሎችን መግደላቸውን፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ግድያዎቹ ሲፈጸሙ ጣልቃ ሳይገቡ መቅረታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።

በቦራ አምደውሃ ፣ በቦራ ጫማላ እና ማኢ ሊሃም ከተሞች ከ70 በላይ ሲቪሎች በመከላከያ ሠራዊት መገደላቸውን የጋራ ሪፖርቱ ገልጿል።

እነዚህን እና ሌሎች የግድያ ማስረጃዎችን በመያዝ የሕግ ትንታኔ የሰጠው የምርመራ ቡድኑ በዚህ ጦርነት ውስጥ "የጦር ወንጀሎች" ተፈጽመው ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።

#EHRC #OHCHR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ !

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የወጣውን የጋራ ሪፖርት በተመለከተ ምላሽ ሰጥተዋል።

TPLF በትግራይ ክልል በቀሰቀሰው ግጭት ወቅት የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል በሚል ያናፈሰው የሐሰት ውንጀላ ተጨባጭ መሠረት እንደሌለው በቡድኑ የጋራ ምርመራ በግልፅ ተረጋግጧል ብለዋል።

ቡድኑ ባወጣው ሪፖርት መሰረትም መንግስት ረሃብን 'የጦርነት መሳሪያ' አድርጎ ይጠቀምበታል የሚለውን ተደጋጋሚ ክስ በአሳማኝ ማስረጃ ላይ ያልተመሰረተ ሲል መደምደሙ ይፋ ባደረገው መግለጫ ተመላክቷል ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በትግራይ ውስጥ ሆን ተብሎ መንግስት ለህዝቡ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይደርስ ከልክሏል በሚል የቀረበውን ክስ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዳላገኘ በሪፖርቱ እንደማለከተ አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ''እነዚህ ውንጀላዎች ውሸት መሆናቸውን እናውቃለን፣ ነገር ግን ጠላቶቻችን አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሰርተዋል'' ብለዋል።

በሪፖርቱ ላይ አንዳንድ ጥርጣሬዎች ቢኖሩንም ሪፖርቱን እንደ ጠቃሚ ሰነድ ተቀብለነዋል፤ ለተጎጂዎች መፍትሄ ለመስጠት፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ይሰራል ብለዋል።

አክለውም የሁለቱ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ሙያዊና ተዓማኒ የሆነ የሰብአዊ መብት ምርመራ ለማካሄድ ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

* ሙሉ ምላሻቸው ከላይ ተያይዟል።

#ENA

@tikvahethiopia
#US : በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያን በሚኖሩባት የቨርጂኒያ ምርጫ የሪፐብሊካን ዕጩ ግሌን ዮንከን አሸነፉ።

ግሌን ዮንከን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

ቀድም ብሎ በዚህ ግዛት ላይ ዲሞክራቶች ከተሸነፉ የጆ ባይደን ቅቡልነት ማጣት አንድ ማሳያ እንደሆነ ተንታኞች ሲናገሩ ነበር።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጆ ባይደን ቨርጂኒያን በ10 ነጥብ የበላይነት አሸንፈው ነበር።

ከቨርጂኒያ ሌላ በኒው ጀርሲም በዲሞክቶችና በሪፐብሊካን መካከል ጥብቅ ፉክክር እየተደረገ ነው።

ጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ ከገቡ ወዲህ ፦
- የዋጋ ግሽበት መባባስ፣
- የተቀዛቀዘው የምጣኔ ሀብት ቶሎ አለማንሰራራት - ዝርክርክ የተባለው የአሜሪካ ከአፍጋኒስታን የወጣችበት መንገድ በሕዝብ ዘንድ ለዲሞክራቶች የነበረው ተስፋና እምነትን ሸርሽሯል እየተባለ መሆኑን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

መረጃው ከኤኤፍፒ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማከሄድ ጀምሯል። በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በፌዴረሽን ምክር ቤት 11ኛ ክልል ሆኖ ለጸደቀው ደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል የስልጣን ርክክብ ያደርጋል። @tikvahethiopia
#Update

የደቡብ ክልል ም/ቤት በዛሬው እለት 6ኛ ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤው ከአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር የስልጣን ርክክብ አድርጓል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ሆኖ በፌዴሬሽን ም/ቤት መፅደቁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት ቆሟል፡፡

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፥ " ለህዝቡን ድህንነት ሲባል በተለያዩ መንገዶች ወደ ከተማው የሚገቡ ጸጉረ ልውጦችን እና ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል ሲባል የከተማ አስተዳደሩ ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም ወረዳ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት መስጠት ቆሟል " ብሏል።

የሀገር ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል ከከትላንት ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል::

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጅ መሰረትም የከተማው የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ፡፡

ሆኖም የከተማችን ነዋሪዎች ሆነው በተለያዩ ምክኒያቶች መታወቂያ ያልወሰዱ ነዋሪዎች ካሉ በልዩ ሁኔታ በሚመለከተው አካል ተጣርቶ እና ተረጋግጦ ጊዜያዊ መታወቂያ የሚዘጋጅላቸው ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
ኤርትራ የምርመራ ሪፖርቱን አልቀበልም አለች።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተመድ የጋራ የምርመራ ቡድን ዛሬ ይፋ ያደረጉትን ሪፖርት ኤርትራ እንደማትቀበለው አሳውቃለች።

ዛሬ ከሰዓት የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።

ኤርትራ በምርመራው ላይ የተሳተፉ አካላትን ገለልተኛነት ጉዳይ ያነሳች ሲሆን ምርመራው አካሄድና ትክክለኛነት እንዲሁም ህጋዊነት ላይ ጥያቄዎችን አንስታለች፡፡

ሪፖርቱ ላይ ኤርትራን የተመለከቱ መረጃዎች ተዛብተው መቅረባቸውን ኤርትራ የገለፀች ሲሆን ምርመራው ከምስክሮች ተዓማኒነት፣ ከተደረገበት ጊዜ እና ከሸፈናቸው ቦታዎች አንጻር ውስንነቶች ያሉበት ነው ብላለች።

የኤርትራን ጦር መዳኘትም ሆነ ለተጎጂዎች ፍትህ መስጠት ከተፈለገ የሚቻለ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሌሎች በኤርትራ ህግ መሰረት ገለልተኛ እና እውነተኛ ምርመራን ለማድረግ በሚችሉ አካላት ነው ብላለች።

ኤርትራ ምንም ዐይነት ማረጋገጫና ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ያለቻቸውን የአክሱም ጭፍጨፋና ሌሎች ጾታዊና በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ ጥቃቶችንም አንስታለች።

በእዚህም ጣምራ ሪፖርቱ ተቀባይነት እንደሌለው ገልፃ ፤ ኤርትራ ፈርማ ህግ ያደረገቻቸውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ማክበሯን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። እነዚህን ህጎች በሚጥሱ የሰራዊት አባላት ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂ እንደምታደርግ ኤርትራ ገልፃለች።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

#አልዓይን
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AGOA ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ተጠቃሚ ከነበረችበት የአሜሪካ የንግድ ችሮታ (AGOA) ማስወጣታቸውን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማሳወቃቸውን ኋይት ሃውስን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከንግድ ችሮታው እንዲትወጣ ፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ የጻፉት ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ጋር ተያይዞ መሆኑንም ኋይት ሃውስ አስታውቋል። አሜሪካ ፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ጥልቅ…
#AGOA

" አሜሪካ አጎዋን በተመለከተ ያሳለፈችውን ውሳኔ ልታጤነው ይገባል " - ኢትዮጵያ

የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ከቀረጥ ነጻ ዕድል (አጎዋ) ተጠቃሚነቷ ለማገድ ያስተላለፈችውን ውሳኔ እንድታጤነው ኢትዮጵያ ጠይቃለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካን የአጎዋ ውሳኔ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

ኢትዮጵያ ፥ አሜሪካ ያሳለፈችው ውሳኔ አግባብነት የሌለው እና የአሜሪካ መንግስት አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ መሆኑን ገልፃለች።

በውሳኔው ኢትዮጵያን ከአጎዋ ተጠቃሚነት ውጭ ማድረግ፤ ከግጭቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙት የሌላቸውን ከ200 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የበርካታ ሴቶች ኑሮ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋልም ብላለች።

እንዲሁም በግበዓት አቅርቦት ሰንሰለት የሚሳተፉትን የ1 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት በእጅጉ እንደሚጎዳውም የገለፀው ኢትዮጵያ አሜሪካ ውሳኔውን እንድታጤነው ጥይቃለች።

#ENA

@tikvahethiopia