TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ ሌንጮ ለታ⬇️

#ኦነግ ትጥቅ አልፈታም በማለት ለተጀመረው ሰላማዊ የፖለቲካ ሂደት እንቅፋት መሆን የለበትም መንግስትም በጉዳዩ ላይ ግልፅ መረጃ ማቅረብ አለበት ሲሉ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ተናገሩ።

አዲስ አበባ በሚገኘው አሐዱ በተባለው ሬድዮ ከአቶ #በቀለ_ገርባ ጋር እንግዳ ሆነው የቀረቡት አቶ #ሌንጮ_ለታ በሀገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ሁሉን አካታችና የማይቀለበስ እንዲሆን ሁሉም አካል በሀላፊነት መንቀሳቀስ አለበት ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከኦነግ ጋር የደረሰበትን ስምምነት ይፋ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ሌንጮ ለታ የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምን ተነስተው ትጥቅ አንፈታም እንዳሉ መረዳት ይቸግረኛል ብለዋል።" ወጣቶች ባዶ እጃቸውን ወጥተው ታንክ ፊት ቆመው ሲታገሉ የኦነግ ሰራዊት የት ነበረ? አሁንስ ትጥቅ አልፈታም ማለት ማንን ለመውጋት ነው?" ሲሉ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦዴፓ እና ኦዴግ ተዋሀዱ‼️

በአቶ #ሌንጮ_ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ODF) ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ODP) ጋር መዋሃዱ እየተነገረ ነው።

ይኸው የሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት በዛሬው ዕለት ለህዝብ #ይፋ እንደሚደረግም ተሰምቷል።

የአርትስ ቴሌቪዥን ምንጮች እንደጠቆሙት የሁለቱን ፓርቲዎች ውህደት በተመለከተ የፓርቲዎቹ አመራሮች አቶ ለማ መገርሳ እና አቶ ሌንጮ ለታ ዛሬ ከቀትር በኋላ በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ቢሮ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መከፋፈል በኋላ የቀድሞ አመራሩ አቶ ሌንጮ ለታ አሁን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ጋር ሊዋሃድ መሆኑ የተነገረውን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) መስርተው መንቀሳቀስ መጀመራቸው ይታወሳል።

በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደሃገር ቤት ከገቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀዳሚውም ይኸው የአቶ ሌንጮ ፓርቲ ኦዴግ ነው።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከመንግስት ጋር በተደረገ ድርድር ትጥቅ ፈትቶ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ በመወሰን ወደኢትዮጵያ መግባቱም አይዘነጋም።

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia