#Shashemene : በቀን 27/01/2014 ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ የኢትዮጲያ ምግብና መደኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከሻሸመኔ ጤናና ጤና ነክ የስራ ሂደት ተቆጣጣሪ ጋር በጋራ በመሆን በምግብ ዘይት ላይ የገበያ ቅኝት አድርገው ነበር።
በዚህም ፦
• ከሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል የዘይት ምርት ለማምረት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው፤
• የምርት ማሸጊያ መስፈርት ባላሟላ ፣ ንጽህናዉ ባልጠበቀ የአመራረት ሂደት ፤
• ዘይት ለማምረት ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረቱ ለህብረተሰቡ እየሸጡ የተገኙ ድርጅቶች ላይ ምርት የማምረት ስራዉን እንዲያቆሙ ተደርጓል።
ድርጅቶቹ ከተመረተው የዘይት ምርትና ለዘይት ምርት የሚገለገሉበት የቅባት እህል (ጎመንዘር) ጋር እንዲታሸጉም ተደርጓል።
በገበያ ቅኝቱ ወቅት ባጠቃላይ በግምት 150 ኩንታል በላይ የጎመንዘር እህል እና #በዛገ_በርሜል የተከማቸ 80 በርሜል ህገወጥ ዘይት አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋው 2,244,000 ብር የሚያወጣ ህገወጥ የዘይት ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው መደረጉም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ፤ ከድርጅቶቹ ጋር በተያያዘ ቀጣዩ የክትትል ስራ ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ጤ/ጤ/ግ/ጥ/ቁ/የስራ ሂደት እና ከሻሸመኔ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ጋር በጋራ ይሰራል ሲል አሳውቋል።
@tikvahethiopia

14ኛው የሰንደቅ ዓላማ 🇪🇹 ቀን እየተከበረ ነው።
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ግቢ ፥
- የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣
- የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ፣
- የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።
የ14ኛው የሰንደቅ ዓለማ ቀን መሪ ቃል " በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉአላዊነት ለሰንደቅ አላማ ከፍታ " የሚል ነው።
በዓሉ በተመሳሳይ ሰዓት በመላ ሃገሪቱ በመከበር ላይ ነው።

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 59 ስደተኞችን ከሜድትራኒያን ባሕር ላይ መታደጉን አንድ የጣልያን መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አስታወቀ።
ከስደተኞቹ መካከል 17ቱ ታዳጊዎች ሲሆኑ አንድ እርጉዝ ሴት እንደምትገኝበት ረስኪዩ ቻሪቲ የተባለው የነፍስ አድን ድርጅት አስታውቋል።
በመግለጫው መሠረት በእንጨት በተሰራ ጀልባ ተጭነው ከ #ሊቢያዋ ዘውራ ከተነሱ ከ24 ሰዓታት በኋላ በጭንቀት ላይ ሳሉ በባሕር አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመድረስ የሚሞክሩ ስደተኞችን ለመታደግ የተቋቋመው " ረስኪዩ ቻሪቲ " የተባለ ድርጅት ያሰማራው መርከብ ታድጓቸዋል።
በጀልባው ከተጫኑት መካከል ፦
- ኢትዮጵያውያን፣
- ሶማሊያውያን፣
- ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን ይገኙበታል።
ከአፍሪካ እንዲሁም ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በመነሳት የሜድትራኒያን ባሕርን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ በርካታ ሰዎች በሚገጥማቸው አደጋ በተደጋጋሚ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ መሠረት እኤአ 2021 ዓ.ም 480 ሰዎችበሜድትራኒያን ባሕር መካከለኛ ክፍል ጠፍተዋል።
በእንዲህ አይነቱ አስቸጋሪ መንገድ ለጉዞ የሚነሱት አብዛኞቹ በአገሮቻቸው ያለውን አለመረጋጋት የሚሸሹ እና በአውሮፓ የተሻለ ምጣኔ ሐብታዊ ዕድል ለማግኘት ተስፋ የሚያደርጉ ናቸው።
በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት አድን ድርጅት ልጆች እና ያለ ጠባቂ የሚጓዙ አዳጊዎች ጭምር የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመሻገር እንደሚሞክሩ ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር።
መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
Video Credit : ShamshadTV

#ThomasSankara
በቶማስ ሳንካራ ግድያ ተባባሪ በመሆን አስራ አራት ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ከ34 ዓመታት በፊት ነበር የወቅቱ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ " የአፍሪካው ቼ ጉቬራ" አስደንጋጭ የሆነ ግድያ የተፈጸመባቸው።
የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ ሳንካራ እአአ ጥቅምት 15/1987 በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት ነው በወታደሮቹ በጥይት ተገደሉት።
እንሆ ከ34 ዓመት በኋላ የቶማስ ሳንካራ ግድያ ተባባሪ በመሆን 14 ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የቶማስ ሳንካራ ግድያን ተከትሎ ፥ የቅርብ ጓደኛቸው ብሌዝ ኮምፓዎሬ ነበሩ ወደ ሥልጣን የመጡት።
ከግድያው ከአራት ዓመታት ቀድም ብሎ ሳንካራና ካምፓዎሬ ሳንካራን ለፕሬዝዳንትነት ያበቃውን መፈንቅለ መንግሥት መርተው ነበር።
ኮምፓዎሬ ከ14ቱ ተከሳሾች መካከል ናቸው።
በጎረቤት ሀገር አይቮሪ ኮስት በግዞት የሚገኙት ኮምፓዎሬ እአአ በ2014 በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሥልጣን ለቀው ነው የተሰደዱት።
ነገር ግን በቶማስ ሳንካራ ግድያ ውስጥ እጃቸው እንደሌለበት በተደጋጋሚ አስተባብለዋል። በፍርድ ሂደቱ እንደማይገኙም አስታውቀዋል።
• የፍርድ ሂደቱ ለምን ረዥም ጊዜ ፈጀ ?
• የፍርድ ሂደቱ በሀገሪቱ ላይ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል ?
#ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/Thomas-Sankara-10-11-2
Credit : BBC

TIKVAH-ETHIOPIA
ሱዳን ኢትዮጵያ አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንድትሸጥላት ጠየቀች። ሱዳንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት ፍላጎት አሳይተዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ተናግረዋል። በቅርቡ ሱዳን አንድ ሺህ ሜጋዋት ሃይል እንደምትፈልግ ማሳወቋን ተከትሎ ባለፈው ወር የተቋሙ ሠራተኞች ወደ ካርቱም አቅንተው እንደነበረና…
የሱዳን ኤሌክትሪክ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ ገቡ።
በሱዳን ኤሌክትሪክ ኩባንያ (ሱዳን ኤሌክትሪክ ትራንስሚሽን ኮርፖሬሽን) ዋና ሥራ አስፈጻሚ የቴክኒክ አማካሪ የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል በቀጣይ ስለሚኖረው የኃይል ትስስር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች ጋር ለመደራደር አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
በዋና ሥራ አስፈጻሚው የቴክኒክ አማካሪ ሚስተር አህመድ አደም ኡመር የተመራዉና 5 አባላትን ያካተተው የልዑካን ቡድን ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስትራቴጂና ኢንቨስትመንት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ተሾመ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
አቶ ወንድወሰን የልዑካን ቡድኑን በተቀበሉበት ወቅት እንደተናገሩት የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ የገባው በሁለቱ ሃገራት መካከል የኃይል ትስስሩን ለማጠናከር እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ ድርድር ለማድረግ ነው፡፡
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በመገኘት ከኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች ጋር ድርድር መካሄዱን አስታውሰዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚካሄደው ድርድር ከዚህ በፊት በነበሩ ድርድሮች የተነሱ ጉዳዮች እልባት እንዲያገኙና በቀጣይ ስለሚኖረው የአሰራር ሁኔታ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል፡፡
ድርድሩ የሱዳን የኤሌክትሪክ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ባቀረበው ጥያቄ ላይ እንዲሁም ተጨማሪ ኃይል ለማቅረብ መከናወን ባለበት የመስመር ዝርጋታ እና ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታዎች ላይ ትኩረት የሚያደርግ እንደሚሆን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
ድርድሩ ከጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
#EEP

" ጊዜው እየረዘመ በመጣ ቁጥር የሚደርስብን ጫና እየከፋ ነው " - ተማሪዎች የትግራይ ክልል ጦርነት ከፍተኛ ቀውስ ከፈጠረባቸው ሴክተሮች አንዱ የትምህርቱ ዘርፉ ነው። ይኸው አንድ አመት ሊሞላው አንድ ወር ብቻ የቀረው የትግራይ ክልል ቀውስ በሺዎች የሚቆጠሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው አስቀርቷል። የዚህ ከፍተኛ ችግር ገፈጥ ቀማሾችም አንድም በትግራይ ክልል ነዋሪ ሆነው…
የተማሪዎቹ እና ወላጆቹ ጥያቄ እና ቅሬታ !
• " ሌላ ነገር እንኳን እንዳንጀምር ፣ ትምህርትም ሌላ ቦታ ተመዝግበን እንዳንጀምር ማነቆ ሆኖብናል " - ተማሪዎች
• " ልጆቻችን በስነልቦና ተጎደተዋል፤ በጣም እየተጨነቁም ነው፤ በእነሱ ምክንያት እኛም በእጅጉ እየተጨነቅን ነው" - ወላጆች
• በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተቋሙ አመራሮች ስልጠና ላይ ናቸው የሚል ምላሽ ተሰጥቷል።
ዛሬ ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የተመለሱ ተማሪዎች "ድምጻችን ይሰማ፣ መፍትሔ ይሰጠን" በማለት ከወላጆቻቸው ጋር በትምህርት ሚኒስቴር ቅሬታቸውን ለማሰማት ተገኝተው ነበር።
ትምህርት ካቋረጡ 2 ወር ያለፋቸው ተማሪዎች "የቀድሞው ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የገባላቸውን ቃል እንዳልፈጸመላቸው" ገልፀዋል።
ዛሬ በትምህርት ሚኒስቴር የተገኙት ተማሪዎች ፥ በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ 10,500 ተማሪዎችን በመወከል ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ መሆኑን ገልፀው የተለያዩ አካላት ኮሚቴውን እንኳን ለማናገር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ አሁን በትምህርት ሚኒስቴር ስር የተጠቃለለው ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ቢሄዱም ስብሰባ ናቸው የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው አንዳንድ ጊዜ ከበር እንደሚመልሷቸውና ብዙ እንዳጉላሏቸው አስረድተዋል።
" ከዚህ ቀደም መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ወደተለያዩ ተቋማት እንደሚመድቡን ነግረውን ነበር" ያሉት ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎቹ "እስካሁን ድረስ ምንም ማላሽ አላገኘንም" ብለዋል።
ተማሪዎቹ በዛሬው ዕለት በትምህርት ሚኒስቴር የተገኙት የሚያናግራቸው አካል ካለ እንዲያናግራቸውንና የታሰበውን ነገር እንዲያሳውቋቸው መሆኑን ገልፀዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/MoE-10-11

የተማሪዎቹ እና ወላጆቹ ጥያቄ እና ቅሬታ ! • " ሌላ ነገር እንኳን እንዳንጀምር ፣ ትምህርትም ሌላ ቦታ ተመዝግበን እንዳንጀምር ማነቆ ሆኖብናል " - ተማሪዎች • " ልጆቻችን በስነልቦና ተጎደተዋል፤ በጣም እየተጨነቁም ነው፤ በእነሱ ምክንያት እኛም በእጅጉ እየተጨነቅን ነው" - ወላጆች • በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተቋሙ አመራሮች ስልጠና ላይ ናቸው የሚል ምላሽ ተሰጥቷል። ዛሬ ከትግራይ ክልል…
" ከትግራይ የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ መፍትሔ ያገኛሉ" - የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች
ከ150 በላይ ከትግራይ ክልል የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በማቅናት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ይሁን እንጂ "ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ" የተማሪዎቹ ተወካዮች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጸዋል።
በመቀጠልም በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ስር ወደተጠቃለለው የቀድሞው ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በማምራት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የተቋሙ ሁለት ከፍተኛ አመራሮች የተማሪዎቹ እና የወላጆች ተወካዮችን አነጋግረዋል።
"ሚኒስቴሩ ከትግራይ ክልል የተመለሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጉዳይ ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ እየሰራበት እንደሚገኝ" አመራሮቹ ለተወካዮቹ ገልጸዋል።
"ተማሪዎቹ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ መፍትሔ እንደሚያገኙም " አመራሮቹ ተናግረዋል።
በትግራይ ክልል ከሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች በነሐሴ መጀመሪያ ተጠቃለው የወጡ ሲሆን ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ካቋረጡ ሁለት ወር አልፏቸዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች በቲክቫህ ዩኒቨርሲቱ በኩል ተከታተሉ : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h
@tikvahuniversity @tikvahethiopia

አቶ ግርማ ሰይፉ የስራ ርክክብ አደረጉ። በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተሾሙት አቶ ግርማ ሰይፉ የስራ ርክክብ አደረጉ። በባለፈው ሳምንት በይፋ ምስረታውን ያደረገው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ ግርማ ሰይፉን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርጎ መሾሙ…
#Update
በአዲስ አበባ ከተማ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት የኢዜማ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ቃለመሃላ መፈፀማቸውን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት አሳውቋል።
አቶ ግርማ ሰይፉ የአዲስ አበባ ከተማ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር በተገኙበት ነው በዛሬው ዕለት ቃለ መሀላ የፈፀሙት።

#ETHIOPIA😷
ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 36 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 36 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,727 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 945 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 735 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#Amhara የትግራይ ክልል ጦርነት ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች ከሰፋ በኃላ ህወሓት የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎችን ፣ በርካታ ህዝብ የሚኖርባቸውን ከተሞች እንደተቆጣጠረ ይገኛል። መንግስት አካባቢዎቹን ከቡድኑ ለማስለቀቅ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ከዚህ ቀደም ሲገልፅ ነበር። ከሰሞኑ የህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ይዘዋቸዋል በተባሉ ቦታዎች ላይ የአየር ድብደባ እየተፈፀመ…
የህወሓት በ #አማራ_ክልል በያዛቸው አካባቢዎች የኢትዮጵያ ጦር ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ "ሙሉ የማጥቃት" እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ዛሬ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘገብ ውሏል።
ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ጦር ተከፈተብኝ ያለውን ጥቃት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርቧል።
ህወሓት የኢትዮጵያ ሠራዊት የተቀናጀ ጥቃት ከፍቶብኛል ያለ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅረሰብ ይህንን እርምጃ እንዲያወግዝ ጠይቋል።
ህወሓት በኢትዮጵያ ሰራዊት እየተሰነዘረበት ያለው ጥቃት "በከባድ ጦር መሳሪያ፣ በታንክ፣ በሮኬቶች፣ በድሮኖች እና በተዋጊ ጀቶች" የታገዘ እንደሆነ ገልጿል።
ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ጦር በህወሓት ታጣቂዎች በተያዙ ቦታዎች ላይ "ከባድ" የተባለ ጥቃት መፈፀም እንደጀመረ መገለፁ አይዘነጋም።
ካለፉት ቀናት አንስቶ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ ለነበሩ መረጃዎች ቃሉን ያልሰጠው የመከላከያ ሰራዊት በይፋዊ ገፁ ላይ ዛሬ ምሽር መግለጫ አውጥቷል።
ሰራዊቱ ፥ "ህወሓት ውሸት ቀለቡ ነው ያለ ሲሆን ፤ በአንድ በኩል "ተጠቃሁ" ድረሱልኝ ፤ በሌላ በኩል ደግሞ "የትግራይ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሰራዊት ባለበት ተኮማትሮ እንዲቀመጥ አድርገነዋል" ሲል ይገልጻል ብሏል።
አክሎ ፥ የዛሬው ፈሊጥ ለጋላቢዎቹ "መጠነ ሰፊ ጥቃት" ተሰነዘረብኝ እባካችሁ አድኑኝ እያለ ሲማፀን ለሚጋልባቸው ደግሞ "አኮማትሬያለሁ" እያለ መዘላበድ ሆኗል ብሏል።
መከላከያ ሰራዊት በራሱ ዕቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ " ተጠቃሁ " ብሎ ለመናገር እንኳን ጊዜ ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ አለበት ያለ ሲሆን ህዝቡ በወሬ ሳይደናገር የቁርጥ ቀን ልጆቹ በመንግስት ትዕዛዝ አይቀሬውን ድል እስኪያበስሩ የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ሲል ጠይቋል።
* መግለጫው ከመከላከያ ሰራዊቱ ገፅ ተነስቷል።