" ዓይናችንን እንከባከብ "
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል ከዓይን ሃኪሞች እና ኦፕቲሜትሪስት ማህበር ጋር በመተባበር የአለም የዕይታ ቀንን ምክንያት በማድረግ ለባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ማህበር ነፃ የዓይን ህክምና አገልግሎት ሰጡ።
የትምህርት ክፍሉ ሃላፊ ዶ/ር ሳድቅ ታጁ ፥ "የህክምና አግልግሎቱ ሰዎች ስለ ዓይን ህክምና እውቀት እንድኖራቸው እና ህክምና እንዲወስዱ ለማበረታታት እንድሁም መምህራንም ተማሪዎችም በጎ ማድረግን እንድለማመዱና በጎነትን ባህሉ ያደረግ ትውልድ ለመገንባት በማሰብ የተደረገ ነው ብለዋል"
ዶ/ር ሳድቅ ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አይነስውርነቶች ከ80-90 ፐርሰንት የሚሆኑት ታክመው የሚድኑ እንደሆኑ ገልፀው በግንዛቤ ማነስ ምክንያት መታታከም የማይችሉበት ደረጃ ይደርሳሉ ብለዋል።
የአለም የጤና ቀንን በማክበር የሰዎችን እውቀት በማሳደግ የዓይን በሽታን ለመከላከል ለማከምም የሚያስችል መሰረት ማስቀመጥ እና በጎ አግልግሎትን ማስፋፋት የዚህ ፕሮግራም ዋና አላማ ነው ብለዋል።
ዛሬ እስከ ሶስት መቶ ሃምሳ ለሚደርሱ አቅመ ደካሞች ህክምና የተሰጠ ሲሆን መድሃኒት እና መነፀር በነፃ ተሰጥቷቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪም በ " ባቡል ኸይር " ውስጥ መታከም የማይችሉት ሪፈር ተብለው በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተሻለ ህክምና እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።
የዓለም የዕይታ ቀን በሃገር አቀፍ ደረጃ ሀሙስ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ/ም በጅግጅጋ ከተማ ይከበራል።
መረጃው ከኢትዮጵያ አይን ባንክ የተላከ ነው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም (1922 -2013) - ከዛሬ 91 ዓመት በፊት አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፣ - የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እትጌ መነን ተምረዋል፣ - ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ በለንደንና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርት ተከታትለዋል፣ - በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ውስጥ በጂኦግራፊ ዲፓርትመንት በመምህርነት ና በትምህርት…
#ProfMesfinWoldemariam
መምህር፣ ተመራማሪ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም ደራሲ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በህይወት ዘመን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም ራእያቸውን ለማስቀጠል በስማቸው ፋውንዴሽን ተመስርቶላቸዋል።
የፋውንዴሽኑ ዋና የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ፤ ፕሮፌሰር መስፍን የሰብዓዊ መብት ትግል ማዕተም የሆነው ስማቸው እንዳይደበዝዝ በማሰብ ፋውንዴሽኑ ሊቋቋም እንደቻለ አሳውቀወል።
ዶ/ር በድሉ ፥ " ... ይህ የሰብዓዊ መብት መከበር ትግል እንዳይደበዝዝ ፣ እንዳይገፈፍ ለማድረግ ነው። ለወጣቶች እንዲደርስ ፣ በጎልማሶች እንዳይዘነጋ፣ ለእውነት የቆሙ ለጭቆና ያልገበሩ ፣ ግላዊነት ያለጎማቸው ፤ ለምን ? ብለው የሚጠይቁ ሰዎች እስካለን ድረስ መስፍን ወልደማርያም የሰብዓዊ መብት መከበር ፣ የፀረ ጭቆና ግፍ ማህተም ሆኖ ይኖራል" ብለዋል።
የፕሮፌሰር መስፍን ልጅ ዶ/ር መቅደስ መስፍን ፥ ፋውንዴሽኑ እንዲመሰረት፣ የፕሮፌሰር መስፍን ስራ በከንቱ እንዳይቀር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፤ የተመሰረተውን ፋውንዴሽን ወደትልቅ ደረጃ ለማድረስ በመተጋጋገዝ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን ከመንግስት ፣ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ከጎሳ እንዲሁም ከማንኛውም አይነት የፖለቲካ አመለካከት ገለልተኛ ሆኖ መቋቋሙን በፋውንዴሽኑ ምስረታ ማብሰሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጿል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአ/አ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሹን በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስም እንደሚሰየም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አሳውቀዋል።
በፕሮፌሰር መስፍን ስም የተሰየመው መሰብሰቢያ አዳራሽ የምርቃት ስነ ስርዓት ወደፊት ይካሄዳል።
Photo Credit : AMN

ሱማሊያውያን ደህንነትን ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ ነው።
UNHCR በሱማሊያ እየጨመረ በመጣው አለመረጋጋት ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱማሊያውያን ወደ ኢትዮጵያ 🇪🇹 እየተሰደዱ መሆኑን አሳውቋል።
UNHCR ለስደተኞች መጠለያ በቡራሚሮ እና መልካዲዳ በተባሉ ቦታዎች እየገነባ መሆኑንም አሳውቋል።
በዚሁ የUNHCR መረጃ ከሱማሊያ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት ሱማሊያውያን ቁጥር አልተገለፀም ፤ መጠለያዎቹ ለምን ያህል ሰዎች እየተገነቡ እንደሆነም አልተብራራም።
Photo Credit : UNHCR Ethiopia

ተጠናቀቀ | ኢትዮጵያ 1 - 3 ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል የተካሄደው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድቡ 3ኛ ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ለደ/አፍሪካ ጎሎቹን ሞኩዌና ፣ ሞቶቢ ምቫላ እና ኢቪደንስ ማኮፓ ሲያስቆጥሩ ብቸኛውን የኢትዮጵያ ጎል ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ ነው። More : @tikvahethsport
የኢትዮጵየ ብሄራዊ ቡድን ደ/አፍሪካ ገባ።
ትላንት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ 🇪🇹 ብሄራዊ ቡድን ለመልስ ጨዋታ ደ/አፍሪካ (ጆሀንስበርግ) ገብቷል።
Photo Credit : EFF

#Dessie : የደሴ ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት ከዚህ ቀደም ካሳለፋቸው ውሳኔዎች በተጨማሪ ሌሎች ውሳኔዎችን በዛሬው ዕለት አሳልፋል።
ከዚህ ቀደም የተላለፈው የሰዓት እላፊ ገደብ ባለበት የሚቀጥል ሲሆን ማንኛውም የንግድ ድርጅትም ሆነ የሰዎች እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በተጣለው የሰአት እላፊ ገደብ መሠረት ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ስለሚቀጥል ማህበረሰቡ ለፀጥታ ሃይሎች ተባባሪ እንዲሆን ተጠይቋል።
የፀጥታ ም/ቤት በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ በመኖሩ እና የከተማውን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ያልተፈቀዱ ስብሰባዎች እና ህገ-ወጥ ሰልፎች ማድረግ በጥብቅ መከልከሉ አሳውቋል።
ማንኛውም ሰው ከተፈቀደለት የፀጥታ ሃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ በመዝናኛ ቦታ ይዞ መገኘት የተከለከለ መሆኑን ም/ቤቱ አሳስቧል።
በተከለከለ ቦታ ባጃጅ ማሽከርከር፣ ያለ ሰሌዳ ተሽከርካሪ ማሽከርከርና ከተፈቀደላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ሰአት እላፊ ማሽከርከር በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ የደሴ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ም/ቤት አሳውቋል።
* ሙሉ የደሴ ከተማ ፀጥታ ም/ቤት መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

#Attention
" በዕየለቱ የሟቾች ቁጥር አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ስለመጣ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንጠንቀቅ " - EPHI
በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ - 19 ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒሲትዩት አሳውቋል።
በበሽታው የሚያዙ፣ በፅኑ ሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን ቁጥር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ መጠን እየጨምረ እንደሚገኝም ገልጿል።
ወረርሽኙ አሁንም በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ስጋት ሆኖ መቀጠሉንም አመልክቷል።
እየአንዳንዱ ግለሰብ በሀላፊነት ስሜት እራሱን ፣ ቤተሰቡን ፦
- ማስክ በማድረግ፣
- የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ በመጠበቅ ፣
- በማንኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ
- የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስቧል።

' አዲሱ የትምህርት ስርዓት '
በዘንድሮ 2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን በሙከራ ደረጃ እንዲሁም በ2015 ዓ/ም ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ የሚገባው አዲሱ የኢትዮጵያ 🇪🇹 የትምህርት ስርዓት ምን ምን ጉዳዮችን አካቷል ?
- አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለሀገር በቀል እውቀት ትኩረት የሰጠ ነው።
- ከመዋለ ህፃናት አንስቶ የግብረገብ ትምህርት መስጠት የሚያስገድድ ነው።
- በብቃት ላይ የተመሰረተ ፣ የሞያ እና የቀለም ትምህርትንም አብሮ በሚያስኬድ መልኩ የተቀረፀ ነው።
- ከምርት እና ከተግባር ጋር የተሳሰረ ብቃትን 21ኛው ክ/ዘመን የሚፈልገውን እውቀት የሚያስጨብጥ ፣ በቴክኖሊጂ ተደግፎ እንዲሰጥ የሚያስችል ነው።
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተማሪዎች ከቅድመ መደበኛ እስከ 6ኛ የግብረገብ ትምህርት አይነት፣ ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ የስነዜጋ ትምህርት እንዲወስዱ ያስገድዳል።
ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጥ የነበረው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ከ7ኛ ክፍል እንዲጀመር ያደርጋል።
የጤና፣ የግብርና ትምህርት አይነቶችም ተካተዋል።
12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ተማሪ በመለስተኛ ባለሞያነት በዲፕሎማ ተመርቆ ወደስራ እንዲገባም ያስችለል። ለዚህም ከ11ኛ ክፍል ጀምሮ ከመደበኛ ትምህርቶች በተጨማሪ ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ በተግባር የተደገፈ ስልጠና የሚያገኙበት እንድል ተመቻችቷል።
11ኛ እና 12ኛ ክፍል በሁለት ይከፈላሉ የማህበራዊ (ሶሻል) እና የተፈጠሮ (ናቹራል) ሳይንስ በሚል።
ተፈጥሮ ሳይንስ (ናቹራል) የመረጠ ተማሪ ሰባት (7) ትምህርቶችን ለአካዳሚክስ ይጠቀምበታል፤ ይህም ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚቀመጥበት ነው።
እነዚህም የትምህርት አይነቶች ፦
- እንግሊዘኛ
- ሂሳብ
- ፊዚክስ
- ኬሚስትሪ
- ባይሎጂ
- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
- #ግብርና ናቸው።
" ግብርና " 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲማሩ ይደረጋል ፤ በብሄራዊ ፈተናም (የ12ኛ ክፍል ፈተና) እንዲመጣም ይደረጋል።
ከ7ቱ ውጭ ደግሞ በምርጫ ተማሪዎች 5 የትምህርት መስኮችን መምረጥ ይችላሉ፤ እነዚህ መርጠው የሚማሩት ሲሆን ፤ የትምህርት መስኮቹ ፦
- ማኑፋክቸሪንግ
- ኮንስትራክሽን
- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
- ጤና ሳይንስ እና ግብርና ሳይንስ ናቸው። ከአምስቱ አንዱን መርጠው ይማራሉ።
የማህበራዊ (ሶሻል) ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ 6 የጋራ ትምህርቶች አላቸው ለ12ኛ ክፍል ፈተና የሚያቀመጡበት / ጥሩ ነጥብ ካላቸው ወደዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ነው።
ከዚህ ውጭ ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ፦
- ከቋንቋ እና ማህበራዊ ሳይንስ
- ቢዝነስ
- ስነ ጥበባት መካከል አንዱን መርጠው ይማራሉ።
ከላይ የተገለፁት ኮርሶች የሁሉም ሞጁሎች ተዘጋጅተው አልቀዋል።
በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠነ 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ ተማሪ ለማፍራት ትምህርት ሚኒስቴር ከተለያዩ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነትን ተፈራርሟል።
ሰባቱ ተቋማት የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ ተግባራዊ ትምህርት እንዲያገኙ ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ትምህርት ስርዓት በዘንድሮው ዓመት 2014 ዓ/ም እስከ ስምንተኛ ለሙከራ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ፣ 11ኛ ክፍል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ባሉ ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል።
የ8ኛ ክፍል እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለክልላዊ እና ብሄራዊ ፈተና የሚዘጋጁበት ዓመት ስለሆነ እነሱ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም። በ2015 ሙሉ በሙሉ በመላው ሀገሪቱ በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች ተግባራዊ ይደረጋል።
#NB : ከላይ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ የተገኘው ከ30ኛው የሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ነው።
"በ2014 #በሙከራ ደረጃ ይትገበራል " ማለት ምን ማለት ነው ?
በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋል ማለት ነው።
ለምሳሌ ፦ አንደኛ ደረጃ ከ40 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች አሉ ከነዛ ውስጥ የተወሰኑ (በሺዎች የሚቆጠሩ) ተመርጠው ሙሉ ትግበራ ይደረግባቸዋል።
አንድ ትምህርት ቤት ከ1 እስከ 12ኛ ክፍል ቢኖረው ከ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጭ በትምህርት ቤቱ ሙሉ ትግበራ ይደረጋል።
በዚህም ሙከራ ተብሎ የተገለፀው በሁሉም የሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለማይተገበር ነው።
ነገር ግን በተመረጡት ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል።
ሙከራ ይደረግባቸዋል በተባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ደግሞ ለተወሰኑ ክፍሎች የድሮው ለተወሰኑ ክፍሎች አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል ማለትም አይደለም ፤ በትምህርት ቤቱ ሙሉ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል።
(11ኛ ክፍል ግን በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ ይደረጋል) - ይህን መረጃ ከቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ነው ያገኘነው)
በስርዓተ ትምህርቱ ዝግጅት ላይ ፦
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- በመቐለ ዩኒቨርሲቲ (መጀመሪያ አካባቢ-ከግጭቱ በፊት)
- በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
- በጅማ ዩኒቨርሲቲ
- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ከ200 በላይ ምሁራን ተሳትፈውበታል።
#TikvahFamily

#Amhara : በአማራ ክልል ትላንት ለዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አመራሮች ሹመት ተሰጥቷቸዋል።
አጠቃላይ የተሿሚዎች ስም ዝርዝር እንዲሁም የተሾሙበት የኃላፊነት ቦታ ከላይ ተያይዟል።
የብሄረሰብ ዞኖች እና የሜትሪፖሊታንት ከተሞች የየራሳቸው ምክር ቤት ያላቸው በመሆኑ ሹመታቸው በየምክርቤቶቹ ቀርቦ ሲፀድቅ ይገለፃል ተብሏል።

#Shashemene : በቀን 27/01/2014 ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ የኢትዮጲያ ምግብና መደኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከሻሸመኔ ጤናና ጤና ነክ የስራ ሂደት ተቆጣጣሪ ጋር በጋራ በመሆን በምግብ ዘይት ላይ የገበያ ቅኝት አድርገው ነበር።
በዚህም ፦
• ከሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል የዘይት ምርት ለማምረት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው፤
• የምርት ማሸጊያ መስፈርት ባላሟላ ፣ ንጽህናዉ ባልጠበቀ የአመራረት ሂደት ፤
• ዘይት ለማምረት ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረቱ ለህብረተሰቡ እየሸጡ የተገኙ ድርጅቶች ላይ ምርት የማምረት ስራዉን እንዲያቆሙ ተደርጓል።
ድርጅቶቹ ከተመረተው የዘይት ምርትና ለዘይት ምርት የሚገለገሉበት የቅባት እህል (ጎመንዘር) ጋር እንዲታሸጉም ተደርጓል።
በገበያ ቅኝቱ ወቅት ባጠቃላይ በግምት 150 ኩንታል በላይ የጎመንዘር እህል እና #በዛገ_በርሜል የተከማቸ 80 በርሜል ህገወጥ ዘይት አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋው 2,244,000 ብር የሚያወጣ ህገወጥ የዘይት ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው መደረጉም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ፤ ከድርጅቶቹ ጋር በተያያዘ ቀጣዩ የክትትል ስራ ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ጤ/ጤ/ግ/ጥ/ቁ/የስራ ሂደት እና ከሻሸመኔ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ጋር በጋራ ይሰራል ሲል አሳውቋል።

14ኛው የሰንደቅ ዓላማ 🇪🇹 ቀን እየተከበረ ነው።
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ግቢ ፥
- የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣
- የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ፣
- የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።
የ14ኛው የሰንደቅ ዓለማ ቀን መሪ ቃል " በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉአላዊነት ለሰንደቅ አላማ ከፍታ " የሚል ነው።
በዓሉ በተመሳሳይ ሰዓት በመላ ሃገሪቱ በመከበር ላይ ነው።

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 59 ስደተኞችን ከሜድትራኒያን ባሕር ላይ መታደጉን አንድ የጣልያን መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አስታወቀ።
ከስደተኞቹ መካከል 17ቱ ታዳጊዎች ሲሆኑ አንድ እርጉዝ ሴት እንደምትገኝበት ረስኪዩ ቻሪቲ የተባለው የነፍስ አድን ድርጅት አስታውቋል።
በመግለጫው መሠረት በእንጨት በተሰራ ጀልባ ተጭነው ከ #ሊቢያዋ ዘውራ ከተነሱ ከ24 ሰዓታት በኋላ በጭንቀት ላይ ሳሉ በባሕር አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመድረስ የሚሞክሩ ስደተኞችን ለመታደግ የተቋቋመው " ረስኪዩ ቻሪቲ " የተባለ ድርጅት ያሰማራው መርከብ ታድጓቸዋል።
በጀልባው ከተጫኑት መካከል ፦
- ኢትዮጵያውያን፣
- ሶማሊያውያን፣
- ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን ይገኙበታል።
ከአፍሪካ እንዲሁም ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በመነሳት የሜድትራኒያን ባሕርን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ በርካታ ሰዎች በሚገጥማቸው አደጋ በተደጋጋሚ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ መሠረት እኤአ 2021 ዓ.ም 480 ሰዎችበሜድትራኒያን ባሕር መካከለኛ ክፍል ጠፍተዋል።
በእንዲህ አይነቱ አስቸጋሪ መንገድ ለጉዞ የሚነሱት አብዛኞቹ በአገሮቻቸው ያለውን አለመረጋጋት የሚሸሹ እና በአውሮፓ የተሻለ ምጣኔ ሐብታዊ ዕድል ለማግኘት ተስፋ የሚያደርጉ ናቸው።
በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት አድን ድርጅት ልጆች እና ያለ ጠባቂ የሚጓዙ አዳጊዎች ጭምር የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመሻገር እንደሚሞክሩ ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር።
መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
Video Credit : ShamshadTV