TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... በምርጫ ክልል ደረጃ ያለው የውጤት ድመራ እነዲቋረጥ እና የድመራ ሂደቱ በቦርዱ ኦፕሬሽን መዕከል በአዲስ አበባ እንዲከናወን ተወስኗል " - ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ካከናወነባቸው ቦታዎች መካከል ድጋሚ ምርጫ እንዲከናወን የተወሰነበት የምስቃን እና ማረቆ 2 ምርጫ ክልል አንዱ ነው።

በዚሁ ምርጫ ክልል የመራጮች ድምጽ አሰጣጥ በሰላም የተጠናቀቀ ቢሆንም ቦርዱ በእለቱ የተለያዩ አቤቱታዎችን ሲቀበል የዋለ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምጽ ቆጠራ ተጠናቆ ለምርጫ ክልል ከደረሰ በኋላ ምርጫ ክልሉ ሃላፊዎች #በጸጥታ_ስጋት የተነሳ ውጤት ድመራን ማከናወን እንደሚቸግራቸው ሪፓርት አድርገዋል።

ምርጫ ቦርድም ሁኔታውን ገምግሞ የምርጫ ክልል ላይ የውጤት ድመራን ማከናወን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ተረድቻለሁ ብሏል።

በምርጫ ክልል ደረጃ ያለው የውጤት ድመራ እነዲቋረጥ እና የድመራ ሂደቱ በቦርዱ ኦፕሬሽን መአከል በአዲስ አበባ እንዲከናወን መወሰኑንም ቦርዱ ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ ፤ ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የድምጽ አሰጣጥ ቁሳቁሶችን በሙሉ ወደ ማእከል እንደሚጓጓዙ ገልጿ ይህ ተግባራዊ እስኪደረግ ድረስ ቁሳቁሶች በህጉ መሰረት ታሽገው እንዲቀመጡ መመሪያ አስተላልፏል።

የእጩዎች ወኪሎች እና የፓርቲ ወኪሎች ውጤት ድመራው በማእከል በሚከናወንበት ወቅት ወኪሎቻቸውን በመላክ መታዘብ እንደሚችሉም ተገልጿል።

@tikvahethiopia