TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 45 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 45 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,004 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 888 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 776 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን በየዕለቱ በበሽታው ሳቢያ የሚሞተው የሰው ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ በመሆኑ ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ #እንድታጠናክሩ አደራ እንላለን።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Irreecha2014

ዛሬ በቢሾፍቱ የሆራ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓል በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ ባለፈው ዓመት ልክ እንደ ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ሁሉ በኮቪድ-19 ምክንያት በአነስተኛ የሰው ቁጥር የተከበረ ሲሆን የዛሬው በዓል ላይ ከፍተኛ የሰው ቁጥር ተገኝቷል።

የበዓሉ ተሳታፊዎች ከለሊት ጀምሮ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ በማቅናት በዓሉን እየከበሩት ይገኛሉ። የበዓሉ ታዳሚዎች በባህላዊ ልብስ ተውበው ፥የተለያዩ ባህሉን የሚገልፁ ዜማዎችን በማዜም በዓሉን በድምቀት እያከበሩት ነው።

ኢሬቻ የሰላም፣ የእርቅ፣ የይቅርታ መገለጫ በዓል ነው።

Baga ayyaana Irreecha nagaan geessan !
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው ተገለፀ። ይህ የተገለፀው ዛሬ በአሶሳ በጀመረው 23ኛው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አቀፍ ትምህርት ጉባኤ ላይ ነው።፡ በዚሁ መድረክ ላይ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ እንደተናገሩት ፤ በመተከል ግጭት…
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወደሙትን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ተቀናሽ በማድረግ የተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት በተካሄደው 23ኛው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትምህርት ጉባኤ ላይ በመተከል የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፤ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ፤ 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው በክልሉ ትምህርት ቢሮ ሪፖርት መደረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቋል።

የቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

ቢሮው ፥ በዓሉ ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች እና ከሌሎች ክልሎች እንዲሁም ከመላ አገሪቱ የመጡ ታዳሚዎች በተገኙበት ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፤ በሰላምም ተጠናቋል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BaankiiRaammis ራሚስ ባንክ በቂ ሃብት በማሰባሰቡ ወደ ምስረታ ተሸጋገረ። በምስረታ ሂደት ሁለት አመታትን ያስቆጠረው ራሚስ ባንክ ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ ባገናዘበ መልኩ ወደ ምስረታ ሂደት መሸጋገሩን አስታወቀ። ባለፈው ሚያዝያ ብሄራዊ ባንክ ባስተላለፈው ትእዛዝ በምስረታ ላይ የሚገኙ ባንኮች 500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዘው እና የመስራች ጉባኤ አድርገው እስከ ጥቅምት…
#BaankiiRaammis

ትላንት መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም ራሚስ ባንክ የመስራች ጉባኤውን በኢሊሊ ሆቴል አካሂዷል።

በጉባኤው ላይ 13 የቦርድ አባላት ምርጫ የተካሄደ መሆኑ ታውቋል።

ብሄራዊ ባንክ 500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል በማሟላት በምስረታ ላይ ያሉ ባንኮች ተገቢውን የመስራች ሂደት አልፈው በ6 ወር ውስጥ ማለትም እስክ ጥቅምት 2 ድረስ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ መግለፁ ይታወቃል።

ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚያቀርበው ራሚስ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል አለው።

በቀነ ገደቡ የማይመጡ አዳዲስ ባንኮች የመመስረቻ ካፒታል 5 ቢሊየን ይሆናል።

Credit : Capital Newspaper

@tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ የኢፌዲሪ የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም ይካሄዳል።

የመንግስት ምስረታው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡-

1. ከሚያዚያ 27 አደባባይ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር
2. ከአዋሬ በአዋሬ ገበያ ወደ ፓርላማ
3. ከሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ
4. ከሴቶች አደባባይ በእንድራሴ ሆቴል ወደ ካሳንቺስ ቶታል
5. ከ22 ወደ ቅዱስ ኡራኤል እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላስ ሆቴል ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን
6. ከአትላስ ሆቴል በደሳለኝ ሆቴል ሩዋንዳ
7. ከኤምፔሪያል ሆቴል ወደ ብራስ ሆስፒታል
8. ከገርጂ ኮሪያ ሆስፒታል ውስጥ ውስጡን ወደ ብራስ ሆስፒታል
9. ከጎሮ አዲሱ መንገድ መሄጃ ወደ ብራስ ሆስፒታል
10. ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቀለበት መንገድ እንዲሁም ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሩዋንዳ ማዞሪያ
11. ከካዲስኮ አደባባይ ወደ ቦሌ ሚካኤል ዋናው ቀለበት መንገድ
12. ከቡልቡላ ወደ ቦሌ ሚካኤል
13. ከመስቀል ፍላውር ወደ ጎርጎሪዮስ አደባባይ
14. ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር አጎና ሲኒማ
15. ከጎፋ ማዛሪያ አዲሱ መንገድ መስቀለኛ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያ ለገሃር
16. ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ ገንት ሆቴል እንዲሁም ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
17. ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር እንዲሁም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ኑር ህንፃ በባልቻ መስቀለኛ ወደ አረቄ ፋብሪካ
18. ከሞላ ማሩ ወደ ቅድስት ልደታ ቤተ-ክርስቲያን
19. ከተክለ ሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ወደ ዲ-አፍሪክ ሆቴል
20. ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
21. ከአብነት ፈረሳኛ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
22. ወሎ ሰፈር፣ ኦሎምፒያ፣ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግስት ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ ሸራተን አዲስ አራት ኪሎ
23. ጎርጎሪዮስ አደባባይ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ።

መንገዶቹ ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቅ ድረስ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ነው ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑት።

ፕሮግራሙ በሚካሄድበት መስቀል አደባባይ አካባቢ ከዛሬ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫዎች ግራና ቀኝ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

እንግዶች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
" ... በምርጫ ክልል ደረጃ ያለው የውጤት ድመራ እነዲቋረጥ እና የድመራ ሂደቱ በቦርዱ ኦፕሬሽን መዕከል በአዲስ አበባ እንዲከናወን ተወስኗል " - ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ካከናወነባቸው ቦታዎች መካከል ድጋሚ ምርጫ እንዲከናወን የተወሰነበት የምስቃን እና ማረቆ 2 ምርጫ ክልል አንዱ ነው።

በዚሁ ምርጫ ክልል የመራጮች ድምጽ አሰጣጥ በሰላም የተጠናቀቀ ቢሆንም ቦርዱ በእለቱ የተለያዩ አቤቱታዎችን ሲቀበል የዋለ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምጽ ቆጠራ ተጠናቆ ለምርጫ ክልል ከደረሰ በኋላ ምርጫ ክልሉ ሃላፊዎች #በጸጥታ_ስጋት የተነሳ ውጤት ድመራን ማከናወን እንደሚቸግራቸው ሪፓርት አድርገዋል።

ምርጫ ቦርድም ሁኔታውን ገምግሞ የምርጫ ክልል ላይ የውጤት ድመራን ማከናወን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ተረድቻለሁ ብሏል።

በምርጫ ክልል ደረጃ ያለው የውጤት ድመራ እነዲቋረጥ እና የድመራ ሂደቱ በቦርዱ ኦፕሬሽን መአከል በአዲስ አበባ እንዲከናወን መወሰኑንም ቦርዱ ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ ፤ ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የድምጽ አሰጣጥ ቁሳቁሶችን በሙሉ ወደ ማእከል እንደሚጓጓዙ ገልጿ ይህ ተግባራዊ እስኪደረግ ድረስ ቁሳቁሶች በህጉ መሰረት ታሽገው እንዲቀመጡ መመሪያ አስተላልፏል።

የእጩዎች ወኪሎች እና የፓርቲ ወኪሎች ውጤት ድመራው በማእከል በሚከናወንበት ወቅት ወኪሎቻቸውን በመላክ መታዘብ እንደሚችሉም ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA : በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል። ጉባዔው በዛሬ ውሎው ፦ 1. የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሻሻያ የተጠየቀባቸው አንቀፆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል። 2. በፓርቲው ፕሮግራም ላይ የቀረቡ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል። 3. ከግጭት ቀጠና የመጡ…
#EZEMA : የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ እያካሄደ ይገኛል።

በዛሬው መርሃ ግብር ጉባኤው በፓርቲው መሪ [ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ] ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ ቀርቦለት ካዳመጠ በኋላ ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበው «የአብረን እንሥራ» ጥያቄ ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ውይይቱን ተከትሎ ፓርቲው የሚወስነው ውሳኔ እየተጠበቀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA pinned «ነገ የሚዘጉ መንገዶች ! ነገ የኢፌዲሪ የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም ይካሄዳል። የመንግስት ምስረታው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡- 1. ከሚያዚያ 27 አደባባይ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር 2. ከአዋሬ በአዋሬ ገበያ ወደ ፓርላማ 3. ከሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ 4. ከሴቶች አደባባይ በእንድራሴ ሆቴል ወደ ካሳንቺስ ቶታል 5. ከ22 ወደ ቅዱስ ኡራኤል እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላስ ሆቴል ወደ ቅዱስ ኡራኤል…»
TIKVAH-ETHIOPIA
#EZEMA : የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ እያካሄደ ይገኛል። በዛሬው መርሃ ግብር ጉባኤው በፓርቲው መሪ [ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ] ሪፖርት እና ምክረ ሀሳብ ቀርቦለት ካዳመጠ በኋላ ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበው «የአብረን እንሥራ» ጥያቄ ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል። ውይይቱን ተከትሎ ፓርቲው የሚወስነው ውሳኔ እየተጠበቀ…
#EZEMA : ኢዜማ ከገዢው ፓርቲ ብልፅግና የቀረበለትን "የአብረን እንስራ" ጥያቄ ተቀብሏል።

ጉባዔው ውይይት ካደረገ በኃላ አሁን ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ ለመስራት በ536 ድጋፍ፣ 79 ተቃውሞ እና 25 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላላ ጉባዔ የመጀመሪያ አስቸኳይ ስብሰባ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ 🇪🇹 ነገ አዲስ መንግስት ትመሰርታለች።

ከሰሞኑን የተለያዩ የክልል መንግስታት እንዲሁም ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች አዲስ መንግስት መመስረታቸው ይታወቃል።

ነገ የኢፌዴሪ መንግስት ይመሰረታል።

በዚሁ የመንግስት ምስረታ ላይ ለመታደም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የሚጠበቅ ሲሆን ዛሬ ማምሻውን የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል።

የሌሎችም ሀገራት መሪዎች እንዲሁም እንግዶች ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 47 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 47 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 6,025 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 697 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 771 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን በየዕለቱ በበሽታው ሳቢያ የሚሞተው የሰው ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ በመሆኑ ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ #እንድታጠናክሩ አደራ እንላለን።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
' ጋዜጠኛው የት እንዳለ ማወቅ አልተቻለም '

የኢትዮጵያ ኢንሳይደር መስራች እና ጋዜጠኛ የሆነው ተስፋለም ወልደየስ ከትላንት ጀምሮ የት እንዳለ አይታወቅም።

ጓደኞቹ እና የስራ ባልደረቦቹ በአዲስ አበባ የነበረውን የሆራ ፊንፌኔ የኢሬቻ በዓል ከዘገበ በኃላ ሊያገኙት እንዳልቻሉ አሳውቀዋል።

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ዛሬ በቢሾፍቱ የተከበረውን የሆራ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓል ለመዘገብ እቅድ እንደነበረውም ገልፀዋል።

Credit : Befekadu Z. H.T

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ 🇪🇹 ነገ አዲስ መንግስት ትመሰርታለች። ከሰሞኑን የተለያዩ የክልል መንግስታት እንዲሁም ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች አዲስ መንግስት መመስረታቸው ይታወቃል። ነገ የኢፌዴሪ መንግስት ይመሰረታል። በዚሁ የመንግስት ምስረታ ላይ ለመታደም የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የሚጠበቅ ሲሆን ዛሬ ማምሻውን የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ…
#Update

የአሁኑ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ ገብተዋል።

የነገውን የአዲስ መንግስት ምስረታ ተከትሎ የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃሙድ ቡሃሪ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ አዲስ አበባ ገብተዋል።

@tikvahethiopia