TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢቦላ⬆️

በኮንጎ #የኢቦላ በሽታ እንደገና በማገረሸቱ የተነሳ ወላጆች በፍርሃት ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት #እያስቀሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው በኢቦላ ቫይረስ በሽታ ምክንያት በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #የትምህርት ተሳትፎ መቀነሱ ተገልጿል፡፡

የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ወረርሽኙ በነሐሴ ወር ከተከሰተ ወዲህ በኢቦላ #የሞቱ ሰዎች ቁጥር 75 ደርሷል፡፡

ይሄን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረትም በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው መላክ መጀመሩን አልጀዝራ በዘገባው አመልክቷል።

@tsegawolde @tikvahethiopia
#update የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎች ኮሚቴ በኮንጎ #የኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ ሊወያይ ነው። ኮሚቴው በመጪው ረቡዕ ተሰብስቦ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ ተወያይቶ ዓለም አቀፋዊ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ላይ መድረስ አለመድረሱን ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ሰባት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #መገደላቸው ተገለፀ።

በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላም አስከባሪ ሃይሉ ከመንግስት ሃይሎች ጋር በመተባበበር አዲኤፍ በተባለው አማጺ ቡድን ላይ በከፈቱት ጥቃት ወቅት ሰባት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት መሞታቸው ነው የተገለጸው፡፡

#የኢቦላ በሽታ ተጠቂ የሆነው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኒ ግዛትን ከአማፂ ቡድኑ ነጻ ለማድረግ በተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል እና የመንግስት ወታደሮች በጋራ ዘመቻ ማድረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ #ስቴቨን_ዱጃሪክ አስታውቀዋል፡፡

በዘመቻው አስር የሚሆኑ የሰላም አስከባሪ ሃይሎች መቁሰላቸውን እና አንድ ሰላም አስከባሪ መሰወሩን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል፡፡

ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የአማፂ ቡድኑ በርካታ አባላት ተገድለዋልም ነው ያሉት፡፡

ከሞቱት የተባባሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት ስድስቱ የማላዊ ተዋላጆች ሲሆኑ አንዱ ታንዛንያዊ ነው ተብሏል፡፡

በማዓድን ሃብታም የሆነው ምስራቃዊ የዲሞክራቲክ ኮንጎ አካባቢን ለመቆጣጠር አዲኤፍ የተባለ አማፂ ቡድንን ጨምሮ በርካታ ታጣቂዎች ከመንግስት ሃይል ይዋጋሉ፡፡

ምንጭ፦ አልጃዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢቦላ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 782 ሰርሷል!

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተውን #የኢቦላ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በጥምረት ሊሠራ እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ጥሪ አቅርቧል። ኅብረቱ ጥሪውን ያቀረበው በወረርሽኙ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 782 መድረሱን ተከትሎ ነው።

በወረርሽኙ ላይ የሚደረገው ዘመቻ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ከሀገሪቱ ጋር በሚያወሳኑ ሀገሮች እና ቀጠናው ውስጥ በሚገኙ ሌሎች ሀገራት ጭምር የሚደረግ መሆኑን ኅብረቱ ገልጿል።

የኅብረቱ አባል ሀገራትም የጤና ጥበቃ ባለሙያዎችን በአፋጣኝ በመላክ የኅብረቱን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርቧል።

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ የተስፋፋው የኢቦላ ወረርሽኝ በእጅጉ እንዳሳሰበው የገለጸው ኅብረቱ፣ በመጪው መስከረም የመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ "አፍሪካ የፀረ-ኢቦላ አጋርነት ትረስት ፈንድ" በሚል መሪ ቃል አህጉር አቀፍ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ ገልጿል። የመድረኩ ዓላማም በአህጉር አቀፍ ደረጃ ኢቦላ ላይ ለሚደረገው ዘመቻ ገቢ ለማሰባሰብ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ሽንዋ/#ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia