TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* China

ቻይና የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ለመጣል ያሰበውን ማዕቀብ አጥብቃ ተቃወመች።

ቻይና የአሜሪካንን አቋም የተቃወመችው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል በሰጠችው መግለጫ ነው።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን፤ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ከመንቀሳቀስ እንድትቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።

ሀገራቸው ቻይና በማዕቀቦች አማካኝነት የሚደረግን ጫና እንዲሁም በሌሎች ሀገሮች የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ለመግባት ማዕቀብ የመጣል ድርጊት እንደምትቃወም ተናግረዋል።

አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ልትጥለው የወሰነችውን ማዕቀብ ቻይና እንደማትቀበለውም ቃል አቀባዩ አሳውቀዋል።

የቻይና ወዳጅ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የገጠማትን የውስጥ ችግር ለመፍታት የሚያስችል አቅም እና ጥበብ እንዳላት ቻይና ታምናለች ብለዋል።

ቻይና ፤ "አሜሪካ አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮችን በጥንቃቄ ማስተናገድ እና የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት ወደነበረበት መመለስ ገንቢ ሚና መጫወት አለበት" ሲሉም ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ቻይና በተለያዩ ጉዳዮች በተለይ በተመድ (UN) የፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ድጋፏን ስትሰጥ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
የ4G LTE አገልግሎት በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ከተሞች ጀመረ።

ኢትዮ-ቴሌኮም በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ከተሞች የ4G LTE Advanced አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደብረ ብርሃን እያከናወነ ይገኛል።

አገልግሎቱ ፦
- ደብረ ብርሀን፣
- ፍቼ፣
- ሸዋሮቢት፣
- ሱልልታ፣
- ሰንዳፋ፣
- ገርበ ጉራቻና ለገጣፎ ከተሞች ነው ተደራሽ የሚያደርገው።

በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው ይፋዊ የማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተገኝተዋል።

Photo Credit : North Shewa Communication

@tikvahethiopia
#BaankiiRaammis

ራሚስ ባንክ በቂ ሃብት በማሰባሰቡ ወደ ምስረታ ተሸጋገረ።

በምስረታ ሂደት ሁለት አመታትን ያስቆጠረው ራሚስ ባንክ ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ ባገናዘበ መልኩ ወደ ምስረታ ሂደት መሸጋገሩን አስታወቀ።

ባለፈው ሚያዝያ ብሄራዊ ባንክ ባስተላለፈው ትእዛዝ በምስረታ ላይ የሚገኙ ባንኮች 500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዘው እና የመስራች ጉባኤ አድርገው እስከ ጥቅምት 2 ለፈቃድ እንዲያመለክቱ ቀነ ገደብ ማስቀመጡ ይታወሳል።

በዚህም ራሚስ 724 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ እውን ለመሆን ተቃርቧል። ራሚስ መስከረም 22 የመስራች ጉባኤ ያደርጋል።

Credit : Capital Newspaper

@tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት የሚኒስትሮች ምክር ቤት 100ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 100ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮች ፦

1.የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብ፤
2. የመንግሥት ሠራተኞች እና የግሉ ዘርፍ ሠራተኞች ጡረታ ለመደንገግ በቀረቡት ረቂቅ ዐዋጆች ላይ ፤
3. የማዕድን ስምምነቶች
4. የተሐድሶ ሕክምና አገልግሎት ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው።

* ዝርዝር ጉዳዩ ከላይ ተያይዟል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
" የኢትዮጵያ ቡና ማህበር "

በቡና ማልማት፣ ማዘጋጀት እና በማቅረብ ስራ የተሰማሩ ሰባት ማኅበራት ‘የኢትዮጵያ ቡና ማኅበር’ን ለመመስረት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈረማቸውን ኢዜአ አስነብቧል።

ስምምነቱን የፈረሙት ፦
- የኢትዮጵያ ቡና አልሚዎች፣
- የሲዳማ ቡና አቅራቢዎች፣
- የኦሮሚያ ቡና አዘጋጅና አቅራቢዎች፣
- የደቡብ ቡና አቅራቢዎች፣
- የኢትዮጵያ ቡና አልሚዎች፣
- የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች እና የሴቶች ቡና ማኅበራት ናቸው።

የሚመሰረተው ማኅበር ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ፣ የኢትዮጵያን ቡና በዓለም ገበያ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዲኖረው የማድረግ፣ አርሶ አደሩን በጋራ የመደገፍና በምርቱ ልክ ተጠቃሚ የማድረግ ዓላማ አለው ተብሏል።

ማህበሩ ህገወጥ ግብይት በማስቀረት በጋራ መስራት እንደሚያስችልም ተገልጿል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጦርነት ባደቀቃት የመን 16 ሚሊዮን ሰዎች ወደረሃብ እያመሩ መሆኑን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የመናውያን የሚያቀርበው የምግብ አቅርቦት በጥቅምት ወር ማለቅ እንደሚጀምር ገልጿል።

ድርጅቱ ለተቸገሩ ሰዎች ለመድረስ ገንዘብ እያለቀብኝ ነው ብሏል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ ፥ " ከዚህ በፊት ረሃብን አስወግደናል ፤ አሁንም እንደገና ይህን ማድረግ አለብን፤ ነገር ግን በፍጥነት ገንዘብ እንፈልጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።

የተለያዩ የዓለም ሀገራት እንደሳዑዲ አረቢያ ፣ አሜሪካ ፣ ብሪታኒያ ፣ ፈረንሳይ እና ሌሎች የውጭ ኃይሎች እጃቸውን ባስገቡበትን ከስድስት ዓመታት በላይ የዘለቀው የየመኑ ደም አፋሳሽ ጦርነት ከ110 ሺህ በላይ ህዝብ ሲረግፍ ፣ ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል፣ በርካቶች በህክምና እጦት እና ረሃብ ሞተዋል።

አሁን ላይ ድጋፍ ካልተገኘ 16 ሚሊዮን የመናውያን ወደረሃብ እያመሩ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
ፎቶ : የሀዲያ ብሄር ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" ክብረ በዓል ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ እየተከበረ እንደሚገኝ የሀዲያ ዞን አሳውቋል።

የበዓሉ አከባበር በባህል ሽመግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን ክብረ በዓሉም ባህላዊ ይዘትን በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ ነዉ።

@tikvahethiopia
#Attention📣

በወረርባቦ ወረዳ የአንበንጣ መንጋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።

በወረባቦ ወረዳ ባለፋት ሁለት አመታት በተደጋጋሚ የአምበጣ መንጋ ወደ ወረዳው በመግባት ጉዳት አድርሷል።

በተለይ ባለፈው አመት በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ በወረዳው በሚኖረው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል።

በዘንድሮው አመት በአፋር ክልል የአንበጣ መንጋ መፈልፈሉንና ይህም መንጋ እንቅስቃሴ የጀመረ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

የወረዳው ማህበረሰብ መንጋው ጉዳት ከማድረሱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እንዲሁም የአንበጣ መንጋ መከሰቱን ወይም መግባቱን የሚያመላክት ምልክት ካየ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲያድረስ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
"ለሶማሊያ ሕዝብ ታሪካዊ ምሽት ነው" - አብዲካዲር አብዲ ዩሱፍ

በሶማሊያ ከ30 ዓመታት በኋላ ሕዝብ በታደመበት ለመጀመሪያ ጊዜ ፊልም ታይቷል።

ሞቃዲሾ ውስጥ በሚገኘው የአገሪቱ ብሔራዊ ቲያትር የሲኒማ አዳራሽ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዕይታ የቀረቡት 2 አጫጭር ፊልሞች በሶማሊያዊ ዳይሬክተር የተዘጋጁ ናቸው።

በጦርነት ውስጥ ለሶስት አስርት ዓመታት በቆየችው ሶማሊያ ውስጥ እነዚህ ፊልሞች ለሕዝብ ዕይታ የቀረቡት ከባድ የደኅንት ጥበቃ ተደርጎላቸው ነው።

የአገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ-መንግሥት እና ምክር ቤት በሚገኝበት አረንጓዴው ቀጠና ተብሎ በሚታወቀውና ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት አካባቢ ወደሚገኘው ቲያትር ቤት ፊልም ለመመልከት የመጡ ሰዎች በርካታ የፍተሻ ቦታዎችን ማለፍ ይጠበቅባቸው ነበር።

በመዲናዋ የሚገኘው ብሔራዊ ቲያትር ከባድ የእርስ በርስ ጦርነት በሚካሄድበት ዘመን የአጥፍቶ ጠፊ ኢላማ የነበረ ሲሆን የተለያዩ የጦር አበጋዞች መቀመጫ ሆኖ ነበር።

የፊልሙ አዘጋጅ አብዲካዲር አብዲ ዩሱፍ ፊልም መታየት መጀመሩን ተከትሎ "ለሶማሊያ ሕዝብ ታሪካዊ ምሽት ነው" ሲል ገልጾታል።

"ከበርካታ ዓመታት ችግር በኋላ. . . የአገሪቱ ተስፋ እያንሰራራ መሆኑን ያሳያል" ሲል ለAFP ተናግሯል።

"ይህ ለሶማሊያውያን የሙዚቃ ጸሐፊዎች፣ ደራሲያንና የፊልም ዳይሬክተሮች እና ተዋንያኖች ችሎታቸውንና ተሰጥኦአቸውን ለሕዝብ እንዲያቀርቡ መድረክና ዕድልን ይፈጥራል" በማለት የሲኒማ ቤቱ መከፈት የሚያመጣውን ለውጥ ገልጿል።

Credit : BBC / AFP

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 37 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 37 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,481 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,544 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 799 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ደመቀ መኮንን ከማርቲን ግሪፍትስ ጋር መከሩ። በኒውዮርክ ከሚካሄደው የተመድ ስብሰባ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት ባለስልጣናት እና ተቋማት ጋር እየመከሩ የሚገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከUNOCHA ዋና አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ ጋር መክረዋል። በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ተከትሎ በአጎራባች አከባቢ የሚኖሩ ወገኖች ለችግር ተጋላጭነታቸው…
* ኒውዮርክ

የተመድ ስብሰባን ለመካፈል አሜሪካ፣ ኒውዮርክ የሚገኙት የኢትዮጵያ 🇪🇹 ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬም ከተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት አመራሮች ጋር የጎንዮሽ ስብሰባ ሲያደርጉ ነው የዋሉት።

አቶ ደመቀ መኮንን ፥ ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪ ኤሪክሰን ሱሬይድ ጋር ተገናኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

እንዲሁም ከዴኒማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር ተገናኝተው በልማት ትብብር እና በሰብዓዊ አገልግሎት ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር መክረዋል።

በተጨማሪ ከUNDP ዋና አስተዳዳሪ አሺም ስታይነር ጋር በልማት፣ በሰላም ግንባታ እና በልዩ ልዩ የትብብር መስኮች ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል።

ትላንት ደግሞ ከUNHCR ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሌፖ ግራንዴ ጋር ተገናኝተው የመከሩ ሲሆን በስደተኞች አያያዝ ፣ በድጋፍ አሰጣጥ፣ እና በስደተኞች ካምፕ አስተዳደር ዙሪያ ጠቃሚ ሃሳቦችን ተለዋውጠዋል።

በሌላ በኩል ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ፥ የደርባን ዲክላሬሽን እና የድርጊት መርሃ ግብር 20ኛ ዓመት አስመልክቶ በተዘጋጀው መድረክ ለጠቅላላ ጉባኤው ንግግር አድርገዋል።

@tikvahethiopia