TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ህፃን ልጁ ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡

ተከሳሽ (ለተጎጂው ሲባል ስሙ ያልተጠቀሰ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 631/1/ለ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በጥቅምት እና ህዳር ወር 2011 ዓ.ም በተለያዩ ቀናት በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታዉ ኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ዉስጥ ዕድሜዉ 7 ዓመት የሆነዉን የራሱን ልጅ የግብረሰዶም ጥቃት ወንጀል የፈፀመበት በመሆኑ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ወንጀል ችሎት በአቃቤ ህግ ክስ ቀርቦባታል፡፡

ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ የዓቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ቀርበው ተከሳሽ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ እንደክስ አመሰራረቱ ያስረዱ በመሆኑ እንዲከላከል ችሎቱ ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ ባቀረባቸዉ የሰነድና የሰዉ መከላከያ ማስረጃዎች መከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ መዝገቡን መርምሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቶ ነበር ለመስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ መዝገቡ ያደረው፡፡

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ከላይ በተገለጸው እለት በዋለው ችሎት ተከሳሽ በአስራ ስድስት (16) ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* ኒውዮርክ በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ እየተካሄደ በመገኘው የተመድ (UN) 76ተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተለያዩ ሀገራት ባለስጣናት/ተቋማት ጋር የጎንዮሽ ምክክር እያደረጉ ይገኛሉ። ትላንት ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ ጋር መምከራቸው ይታወሳል። አቶ ደመቀ መኮንን ከባስሌይ ጋር…
አቶ ደመቀ መኮንን ከማርቲን ግሪፍትስ ጋር መከሩ።

በኒውዮርክ ከሚካሄደው የተመድ ስብሰባ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት ባለስልጣናት እና ተቋማት ጋር እየመከሩ የሚገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከUNOCHA ዋና አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ ጋር መክረዋል።

በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ተከትሎ በአጎራባች አከባቢ የሚኖሩ ወገኖች ለችግር ተጋላጭነታቸው እየጨመረ በመምጣቱ ሁሉአቀፍ የሰብዓዊ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እንደሚጠይቅ አቶ ደመቀ ጠቁመዋል።

"በሁሉም አከባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖችን በተሟላ አግባብ ተደራሽ ለማድረግ በእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በፍጥነት መፍታት ይገባል" ብለዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት እና አቅርቦት ባለው መስተጋብር የሚገጥሙ ክፍተቶችን ለመድፈን ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠይቅ አስምረውበታል።

ሁሉአቀፍ የሰብዓዊ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የሚያደርገውን ርብርብ የዓለምአቀፉን ማህበረሰብ ሚዛናዊ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ UNOCHA ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

UNOCHA በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ከመንግስት ጎን በመቆም ለሚያደርገው ድጋፍ አቶ ደመቀ አመስግነዋል።

በውይይቱ ላይ መንግስት ለሰብዓዊ አገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ ባደረገው ርብርብ ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ጉዳዮች እንደተሻሻሉ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል።

Credit : Deputy PM Office

@tikvahethiopia
#Gambella : የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ መሆኑ አሳውቋል። ቢሮው የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ከ97 በመቶ በላይ ማለፋቸውን ገልጿል።

ትምህርት ቢሮው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት ለወንዶች 44 በመቶ እንዲሁም ለሴቶች 42 በመቶ እንዲሆን መወሰኑን ገልጾ ፤ በክልሉ ለፈተናው ከተቀመጡ አጠቃላይ 13 ሺህ 674 ተማሪዎች 7,715 ወንዶችና 5,626 ሴት ተማሪዎች ወደቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን ይፋ አድርጓል።

ከመስከረም 20 እስከ መስከረም 30 ባሉት ቀናት የተማሪዎች ካርድ ይሰጣልም ብሏል።

መረጃው የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው።

@tikvahethiopia
" እናቶች፣ ህፃናትና አቅመ ደካሞች እንዲሁም በርካታ ዜጎች የምግብ አቅርቦትና የጤና አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል " - የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል

- በኢትዮጵያ የUNICEF ተወካይ አዴል ኮደር፣
- የብሪታኒያ ልዩ መልዕክተኛ ኒክ ዳየር፣
- የUNICEF ዋናው መስሪያ ቤት የአቅርቦት ክፍል ኃላፊ ኢትሌቫ ካድሊል፣
- በUNICEF የባህርዳር ፊልድ ኦፊሰር ባልደረቦችና ሌሎም ደሴ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጎበኙ።

የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል ለስራ ኃላፊዎቹ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ፤ ህወሃት ወረራ በፈፀመባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የUNICEF ተወካዮች በስፍራው በመገኘት ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ በመጎብኘታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ አበበ ገ/መስቀል ፥ የተፈናቀሉ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር እና እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ገልፀው በውጭም በአገር ወስጥም ያሉ ረጂ ደርጅቶች፣ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ባለሃብቶችና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የምግብ ፣ አልባሳት እና ሌሎችንም ቁሳቁሶች እንዲለግሱ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይ ደግሞ እናቶች፣ ህፃናትና አቅመ ደካሞች እንዲሁም “በርካታ ዜጎች የምግብ አቅርቦትና የጤና አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል” ብለዋል።

UNICEF እና ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለእነዚህ ዜጎች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እናቶች፣ ህፃናትና አቅመ ደካሞች እንዲሁም በርካታ ዜጎች የምግብ አቅርቦትና የጤና አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል " - የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል - በኢትዮጵያ የUNICEF ተወካይ አዴል ኮደር፣ - የብሪታኒያ ልዩ መልዕክተኛ ኒክ ዳየር፣ - የUNICEF ዋናው መስሪያ ቤት የአቅርቦት ክፍል ኃላፊ ኢትሌቫ ካድሊል፣ - በUNICEF የባህርዳር ፊልድ ኦፊሰር ባልደረቦችና ሌሎም ደሴ የሚገኙ…
ፎቶ : የUNICEF አመራሮች በደሴ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ በአካል ተገኝተው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የደሴ ከንቲባ አበበ ገብረመስቀል በሰጡት ማብራሪያ ፥ በደሴ ከተማ ከ300 ሺ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ ገልጸው ለተፈናቃዮች መንግሥት የሚችለውን እያደረገ ቢሆንም ሁሉንም ማዳረስ እንዳልተቻለ አሳውቀዋል።

የደሴ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ኀላፊ አቶ አብዱልሃሚድ ይመር ደግሞ የተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የUNICEF ተጠሪ የሆኑት አዴል ኮደር ደግሞ፥ ተፈናቃዮችን ባስጠለሉ መጠለያዮዎች ተገኝተው ባዩት ነገር ማዘናቸውን ገልፀው ፥ በቀጣይ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል።

Credit : AMC

@tikvahethiopia
#Egypt #Ethiopia

ግብፅ በኢትዮጵያ🇪🇹የሾመቻቸው አዲሱ አምባሳደር ዛሬ ረቡዕ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጅ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የግብፅ 🇪🇬 አምባሳደር ዶክተር መሐመድ ኦማር ጋድ ሲሆኑ የሹመት ደብዳቤያቸዉን ቅጅ ለዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዴይሬክተር ጄኔራል አቶ ፈይሰል አልይ አቅርበዋል።

Photo Credit : MFA Ethiopia

@tikvahethiopia
#DrLiaTadesse #DrMariaVanKerkhove

የዓለም ጤና ድርጅት በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ እየተዘዋወሩ ካሉት አሳሳቢ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ሁሉ በብዛት እየተዛመተ ያለው #ዴልታ የተባለው በፍጥነት ተላላፊው ዝርያ መሆኑን አስታውቋል።

የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካዊ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ማሪያ ቫን ኼርኾቭ በሰጡት ቃል አልፋ ፥ ቤታ እና ጋማ የሚባሉት የቫይረሱ ዝርያዎች እያንዳንዳቸው ከአንድ ከመቶ ባነሰ ደረጃ እየተዛመቱ መሆኑን በብዛት እየተስፋፋ ያለው ዴልታው ዝርያ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ መረጃ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፥ በኢትዮጵያ አዲሱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዝርያ (ዴልታ) በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረው በዚህም በዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚያገኝ ተናግረዋል።

የቫይረሱ ስርጭት መስፋፋት በቫይረሱ የሚያዙ ፣ በፅኑ የሚታመሙና ህይወታቸው የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን ገልፀው ፤ ለአዲሱ ቫይረስ መስፋፋት ቫይረሱን ለመከላከል ሚተገበሩ "የጥንቃቄ እርምጃዎች መቀዛቀዝ ምክንያት አንዱ ነው" ብለዋል።

ህዝባዊ ጥንቃቄ የጎደላቸው መሰባሰቦች መብዛታቸውና የህብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን ክትባት አለመከተብ ተጨማሪ ምክንያቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።

Credit : MoH/ENA & WHO/VOA

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ47 ዜጎች ህይወት አለፈ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 47 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,379 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,489 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 789 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በየዕለቱ በኮቪድ19 ምክንያት ህይወታቸው የሚያጡ ዜጎች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ በመሆኑ መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጥንቃቄያችሁን እንድታጠናክሩ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
* China

ቻይና የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ለመጣል ያሰበውን ማዕቀብ አጥብቃ ተቃወመች።

ቻይና የአሜሪካንን አቋም የተቃወመችው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል በሰጠችው መግለጫ ነው።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን፤ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ከመንቀሳቀስ እንድትቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።

ሀገራቸው ቻይና በማዕቀቦች አማካኝነት የሚደረግን ጫና እንዲሁም በሌሎች ሀገሮች የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ለመግባት ማዕቀብ የመጣል ድርጊት እንደምትቃወም ተናግረዋል።

አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ልትጥለው የወሰነችውን ማዕቀብ ቻይና እንደማትቀበለውም ቃል አቀባዩ አሳውቀዋል።

የቻይና ወዳጅ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የገጠማትን የውስጥ ችግር ለመፍታት የሚያስችል አቅም እና ጥበብ እንዳላት ቻይና ታምናለች ብለዋል።

ቻይና ፤ "አሜሪካ አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮችን በጥንቃቄ ማስተናገድ እና የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት ወደነበረበት መመለስ ገንቢ ሚና መጫወት አለበት" ሲሉም ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ቻይና በተለያዩ ጉዳዮች በተለይ በተመድ (UN) የፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ድጋፏን ስትሰጥ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
የ4G LTE አገልግሎት በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ከተሞች ጀመረ።

ኢትዮ-ቴሌኮም በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ከተሞች የ4G LTE Advanced አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደብረ ብርሃን እያከናወነ ይገኛል።

አገልግሎቱ ፦
- ደብረ ብርሀን፣
- ፍቼ፣
- ሸዋሮቢት፣
- ሱልልታ፣
- ሰንዳፋ፣
- ገርበ ጉራቻና ለገጣፎ ከተሞች ነው ተደራሽ የሚያደርገው።

በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው ይፋዊ የማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተገኝተዋል።

Photo Credit : North Shewa Communication

@tikvahethiopia
#BaankiiRaammis

ራሚስ ባንክ በቂ ሃብት በማሰባሰቡ ወደ ምስረታ ተሸጋገረ።

በምስረታ ሂደት ሁለት አመታትን ያስቆጠረው ራሚስ ባንክ ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ ባገናዘበ መልኩ ወደ ምስረታ ሂደት መሸጋገሩን አስታወቀ።

ባለፈው ሚያዝያ ብሄራዊ ባንክ ባስተላለፈው ትእዛዝ በምስረታ ላይ የሚገኙ ባንኮች 500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዘው እና የመስራች ጉባኤ አድርገው እስከ ጥቅምት 2 ለፈቃድ እንዲያመለክቱ ቀነ ገደብ ማስቀመጡ ይታወሳል።

በዚህም ራሚስ 724 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ እውን ለመሆን ተቃርቧል። ራሚስ መስከረም 22 የመስራች ጉባኤ ያደርጋል።

Credit : Capital Newspaper

@tikvahethiopia