#Irreecha2014
ኢሬቻ መስከረም 22 እና መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ/ም ይከበራል።
የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ፥ የኦሮሞ ህዝብ የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት የሆነውን የኢሬቻን በዓል ያለ ምንም እንከን ለማክበር ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል።
ህብረቱ ይህን ያሳወቀው መስከረም 22 እና 23 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከበረውን የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል በማስመልከት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
የአባገዳዎች ህብረት ምክር ቤት ሰብሳቢ አባገዳ ጂሎ ማኖ ፥ በኢሬቻ ውስጥ ፖለቲካ የለም፣ ሰላምና ምስጋና ነው ያሉ ሲሆን “ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ የአንድነትና የሰላም ተምሳሌት ነው፤ በዓሉን ያለምንም እንከን ለማክበር ተዘጋጅተናል ነው” ብለዋል።
ዕለቱ የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት በመሆኑ በዓሉ ያለምንም ችግር በሰላም እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አስገንዝበዋል።
የህብረቱ ፀሐፊና የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ ደግሞ ፤ “በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ ባህልና ትውፊቱን፣ ማንነቱ፣ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት መሆኑን የሚያሳይበት ነው” ያሉ ሲሆን የበዓሉ ታዳሚ ህዝብ በዓሉን ሲያከብር ከኮሮና ወረርሽኝ ራሱን በመጠበቅ መሆን ይገባዋል ብለዋል።
በዓሉ የፖለቲካ ትርፍ ይገኝበታል ብለው ለሚያስቡ ሃይሎች መጠቀሚያ እንዳያደርጉት የኦሮሞ ቄሮዎች፣ ቀሬዎችና ፎሌዎች በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች ጋር በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
Credit : ENA
@tikvahethiopia

በመዲናዋ የ2014 ትምህርት ዘመን ፕሮግራም ይፋ ተደረገ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ይፋ ያደረገ ሲሆን ከጥቅምት 1 ቀን ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርት እንደሚጀምር ተገልጿል።
ከጥቅምት 1 በፊት ፤ ከመስከረም 24 እስከ 28 ድረስ የትምህርት ሳምንት እንደሚካሄድ ተገልጿል። ሁሉም መምህራን እስከ መስከረም 18 ድረስ ሪፖርት ያድርጉ ተብሏል።
የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርት 99 ቀናት ሲሆን የማጠቃለያ ፈተናው ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 18 ድረስ እንደሚሠጥ ተገልጿል።
የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ትምህርት ከየካቲት 28 እስከ ሀምሌ 15 ይሰጣል ተብሏል፤ ይህም መንፈቅ በተመሳሳይ 99 የትምህርት ቀናት አሉት።
የ8ኛ ክፍል ፈተና በወቅቱ ሲወሰን ለሶስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን የማስፈተኛ ጣቢያ የሆኑ ትምህርት ቤቶች ብቻ ዝግ ይደረጋሉ ፤ በተመሳሳይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ተወስኖ ሲሰጥ ለ2013 እና ለ2014 ለእያንዳዳቸው 4 ቀናት የመፈተኛ ናቸው፤ የማስፈተኛ ጣቢያ የሆኑ ትምህርት ቤቶች ብቻ ዝግ ይደረጋሉ ተብሏል።
የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 30 እስከ ሃምሌ 5 ድረስ የሚሰጥ ሲሆን የ2014 ትምህርት ዘመን ሃምሌ 15/2014 በየትምህርት ቤቱ በመዝጊያ ስነስርዓት የትምህርት ማስረጃ ሰርተፊኬት በመስጠት ይጠናቀቃል።

* አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ 5 ሺህ አልፏል !
በሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ በሽታው የገደላቸው አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሺህ አልፏል።
ባለፉት 24 ሰዓት የተመዘገቡ 34 ሟቾችን ጨምሮ በሽታው በአጠቃላይ የ5,001 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1664 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በፅኑ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል፤ አሁን ላይ 783 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ጥቁር ገበያው...
በመደበኛው የባንኮችና የጥቁር ገበያ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የተጋነነ የምንዛሪ የዋጋ ልዩነት አሁን ማሽቆልቆል ጀምሯል።
www.wazemaradio.com አሰባሰብኩት ባለው መረጃ በመደበኛው የባንኮችና የጥቁር ገበያ መካከል የነበረው የተጋነነ የምንዛሬ የዋጋ ልዩነት እያሽቆለቆለ ነው።
የበዓላት ወቅት መጠኑ ከፍ ያለ የውጪ ምንዛሪ ወደ ጥቁር ገበያው የሚገባበት የነበረ ቢሆንም የዘንድሮው የዘመን መለዋጫ የጥቁር ገበያ ከበፊቱ ተቀዝቅቅዞ ታይቷል ብሏል ድረገፁ።
በጥቁር ገበያው 74 ብር ደርሶ የነበረው የአንድ ዶላር ምንዛሬ ወደ 59 ብር ከ50 ሳንቲም ዝቅ ብሎ ሲመነዘር እንደነበት ድረገፁ በአካል ተዘዋውሮ መመልከቱን ገልጿል።
የምንዛሪ አገልግሎት ከሚሰጡ ስውር አቀባባዮች ቁጥራቸው ቀንሶ መታየቱንም ጠቁሟል።
ድረ ገፁ የጥቁር ገበያው ማሽቆልቆል የተከሰተው መንግስት መውሰድ በጀመራቸው አንዳንድ የገንዘብ ፖሊሲ እርምጃዎች ሳቢያ ስለመሆን / አለመሆኑ የተጠየቁ ስማቸውን እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የብሄራዊ ባንክ የስራ ሀላፊ፥ ባንኩ ጠበቅ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ መከተሉ በጥቁር ገበያው ለታየው መቀዛቀዝ ምክንያት መሆኑን እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ከቅርብ ወራት ወዲህ ቁጥራቸው ቀላል ማይባሉ ግለሰቦች ንብረታቸውን በማስያዣነት ተጠቅመው ከባንክ በሚያገኙት ገንዘብ የውጭ ምንዛሬን ከጥቁር ገበያ ገዝቶ ከሀገር በማስወጣት እንዲሁም በሀገር ውስጥ ሲደብቁ እንደነበርና ይህም ለጥቁር ገበያ መናር እንድ ምክንያት ሆኖ ሰንብቷል ብለዋል።
ይህ ብቻ ሳይሆን ቤት ንብረትን እየሸጡ የውጭ ምንዛሬን የመግዛት እንቅስቃሴ በሰፊው ሲታይ እንደነበርም አንስተዋል።
ያንብቡ: telegra.ph/Wazema-Radio-09-15
Credit: Wazema Radio (wazemaradio.com)

በ1 አመት ከግማሽ ይጠናቀቃል የተባለው የሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት በ #Hawassa ፦
ትላንት በሐዋሳ እንዱስትሪ ፓርክ ለሰራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
ኘሮጀክቱ 13 ህንጻዎች ያሉትና ለ6, 500 ሰራተኞች መኖሪያነት የሚያገለግል ነው።
በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ንግግር ያደረጉህ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ፣ ኘሮጀክቱ ለከተማዋ ትልቅ ሀብትና አቅም ነው ሲሉ ገልፀዋል፤ ከከተሞች እድገትና ስፋት ጋር ተያይዞ ለነዋሪው ምቹ የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት እና ሌሎችንም አገልግሎት ለማቅረብ አስተዳደሩ አቅም በፈቀደ መልኩ ጠንክሮ የሚሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ስራአስኪያጅ የሆኑት አቶ ፍጹም ከተማ የመኖሪያ ቤት ኘሮጀክቱ በግቢው መገንባት ለሰራተኞች ከገቢያቸው ጋር የተመጣጣነ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ተቋሙን ውጤታማ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
የኮርነርስቶን ዴቨሎኘመንት መስራች እና ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ሲራክ አምባዬ ኘሮጀክቱ በ1 አመት ከግማሽ እንደሚጠናቀቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ ኘሮጀክት ስኬት በመነሳት በሐዋሳ ተጨማሪ የሰራተኞች መኖሪያ ግንባታ የሚኖር ሲሆን ወደ ሌሎች ከተሞችም ለማስፋት እቅድ መኖሩን አቶ ሲራክ አስረድተዋል።
መረጃው የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው።

#Chena
የጭና ተፈናቃዮች ከዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ጠይቀዋል።
በአማራ ክልል ዳባት ወረዳ ጭና ተክለሃይማኖት ቀበሌ የሚገኙ ተፈናቃዮች እንዲሁም የአካባቢው ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ እርዳታ ተቋማት አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
በጭና አካባቢ ከተፈፀመው ጭፍጨፋ አምልጠው ጫካ እንደገቡ የሚናገሩት ተፈናቃዮች (እናቶች ከነልጆቻቸው) የሚበሉት እንደሌላቸው፣ በበርድ እንኳን የሚለበስ እንደሌላቸው ተናግረው የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲደርስላቸው ተማፅነዋል።
ወደጫካ ከገቡ 11 ቀናት መሆናቸውን የጠቆሙ አንዳንድ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
ከጭና ተፈናቅለው ወቅን ከተማ የሚገኙ አርሶ አደሮች ያሉ ሲሆን ማደሪያ አጥተው በየበረንዳው ለማደር መገዳዳቸውን እነሱንም ለማቋቋም እንዳልተቻለ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወቅን ንዑስ ወረዳ አስተዳዳሪ ካሳ ማሸሻ ለቪኦኤ አሳውቀዋል።
ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንደሚሰጡ የሚናገሩ ተቋማት በጦርነት ምክንያት በችግር ላይ ለወደቁ ዜጎች ሊደርሱላቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ከጭና የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማት ቦታው ድረስ መጥተው እንዲያዩ የጠየቁት ባለስልጣኑ ይህ ማድረግ ካልተቻለ በወኪላቸው በኩል እርዳታቸውና ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ከእስር ያመለጠው ግለሰብ ከ28 ዓመታት በኃላ ተላልፎ ተሰጠ።
#ፓናማ ከእስር ካመለጠ 28 ዓመታት ያለፈውን #የእስራኤል እስረኛ አሳልፋ ሰጥታለች።
ፓናማ የእስራኤል እስረኛ የሆነውን ዮሲ ቤን-ኤሪን አሳልፋ መስጠቷን KAN ሪፖርት አድርጓል።
ቤን-ኤሪ የተባለው ግለሰብ 5 ኪሎግራም የሚጠጋ #ሄሮይን ከኔዘርላንድ ወደ እስራኤል በማስገባቱ ጥፋተኛ ተብሎ 12 ዓመት እንዲታሰር ተፈርዶበት ነበር።
ይህ ግለሰብ ከ28 ዓመት በፊት ነበር ከእስር ያመለጠው ፤ እንሆ ከ28 ዓመት በኃላ ፓናማ እስረኛውን አሳልፋ ለእስራኤል ሰጥታለች።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጉዳዩን የሰሙ ሰዎች ማንም ግለሰብ ጥፋተኛ ከሆነ የፈጀውን ጊዜ ይፈጃል እንጂ ከህግ እንደማያመልጥ ማሳያነው ሲሉ ገልፀውታል።

#NorthWollo
የጦርነት ቀጠና በሆኑ የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በራሱ አርማ መለያ ድጋፍ ማቅረብ መጀመሩ ተገልጿል።
በትግራይ ክልል ድጋፍ ሲያቀርቡ የነበሩ አጋር አካላት ከዛሬ ጀምሮ ተመሳሳይ እርዳታ ወደአማራ ክልል ለማቅረብ ከመንግስት ጋር ውል መፈፀማቸው ተነግሯል።
የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል ፥ WFP በራሱ አርማና መለያ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እና ማከፋፈል ስለሚችል ድርጅቱ ይህን እንዲሰራ እየተደረገ ነው ብለዋል።
ከአጋር አካላት ጋር በተደረገ ስብሰባ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውል ገብተው እስከሰሩ ድረስ ወደአካባቢው የግድ መግባት አለባቸው በሚል እነሱም በተቻላቸው አቅም ተጨማሪ ሃብት ከሌሎች ፕሮግራሞች ወደዚህ በማምጣት ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ስምምነት ላይ መደረሱን አስረድተዋል።
አቶ ደበበ ፥ "ከዛሬ ጀምሮ በእያንዳንዱ የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል ICP አቋቁመናል፤ ሰዎች እዛ ሁሉ እንዲመድቡ ስምምነት ተደርሷል ፤ ስለዚህ እነሱ ከሚቀርባቸው ዋና መስሪያ ቤት ጋር በመገናኘት እንዲሰሩ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል" ብለዋል።
በሌላ በኩል የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ለደቡብ እና ሰሜን ወሎ አጎራባች ከሆኑ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎች 270,318 መሆናቸውን ጠቁሞ ተፈናቃዮቹ ደሴ እንደሚገኙ አመልክቷል።
ለተፈናቃዮቹ በመንግስት እና አጋር አካላት በኩል ድጋፍ እየተደረገ ነው ብሏል ፥ ድጋፍ ከሚደረግላቸው መካከል 118,000 በመንግስት በኩል 60 ሺ ደግሞ Joint Emergancy Operation (JEOP) በሚባል አጋር አካል የሚሰጥ መሆኑን ኮሚሽኑ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።
Credit : Sheger FM

በደቡብ ክልል የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የሚጀምርበት ቀን ይፋ ሆነ።
በቀን 04/01/2014 ዓ/ም ከሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የትምህርት መምሪያ እና የፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት የመማር ማስተማር ስራ የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን ጠብቆ ፡
- በመንግስት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ/ም እንዲጀመር፤
- በሁሉም የግል ትምህርት ቤቶች መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ/ም እንዲጀመር ስምምነት ላይ መደረሱን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
ከዚህ ቀደም የ2014 ትምህርት ዘመን መስከረም 3 ይጀመራል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የተማሪዎች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ አለመጠናቀ እንዲሁም አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሰረተ የተማሪዎች መማሪያ እና የመምህራን መምሪያ መፅሀፍት ዝግጅት ያላለቀ በመሆኑ በተባለው የጊዜ ሰሌዳ ትምህርት ማስጀመር አልተቻለም።

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የDAS ተሸላሚ ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የዘንድሮው የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን (DAS) ተሸላሚ ሆነዋል።
ፋውንዴሽኑ በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው ዶ/ር ዳንኤል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ላበረከቱት የህይወት ዘመን አስተዋፅኦ ከፍተኛውን ሽልማት ለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል።
ዶ/ር ዳንኤል ከ30 ዕጩዎች መካከል #በሙሉ_ድምፅ የተመረጡ ሲሆን ሽልማታቸውንም በኅዳር ወር እንደሚቀበሉም ተገልጿል።
ዶ/ር ዳንኤል ኮሚሽኑ ነፃ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ፋውንዴሽኑ አሳውቋል።
ሽልማቱ "የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በከፍተኛ ደረጃ እንዲለወጥና ገለልተኝነቱ እንዲረጋገጥ ፣ ሥልጣንና ኃላፊነቱ እንዲሰፋ ለተጫወቱት ቁልፍ ሚና እውቅና የሚሰጥ" መሆኑ ተገልጿል።
ከ25 ዓመታት በላይ በየዓመቱ ሲካሄድ የቆየው ይህ ሽልማት ፣ በሙያቸው የላቀ አመራር ላሳዩና ለእድገትና ለመሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አፍሪካውያን እውቅና የሚሰጥ ነው።
Credit : EHRC

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል።
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ።
የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፤ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል ብለዋል።
የመፈተኛ ወይም የአድሚሽን ካርድ ከመስከረም 24 እስከ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ለተማሪዎች እንደሚሰጥም ገልፀዋል።
ከ618 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም ፈታኝ መምህራንን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን በማሟላት በቂ ዝግጅት ተደርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል(Rotar) የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት ተከናውኗል።
በቅርቡ ኃይል እንደሚያመነጭ ከሚጠበቁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ዩኒቶች መካከል በዩኒት 10 ላይ የተርባይን ጀነሬተር ተሽከርካሪ አካል (Rotar) በቦታው ላይ የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት ተከናውኗል።
ሮታሩና አብረው ያሉት አካላት 840 ቶን ክብደት ያላቸው ሲሆን ሮተሩ ብቻውን 780 ቶን ይመዝናል።
ሮተሩ ከአንድ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ድረስ ያለው አጋማሽ ርዝመት ወይም ዳያሜትር 11 ነጥብ 7 ሜትር ነው።
የሮተሩና የተርባይን አካላቶች በአግባቡ መገጠም የኃይል ማመንጨት የሙከራ ስራ ለመጀመር መቃረቡ አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
Credit : Ethiopian Electric Power

#ETHIOPIA😷
በሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 34 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 34 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,488 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,687 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 778 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ በመሆኑ መላው የቲክቫህ አባላት ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድታጠናክሩ አጥብቀን አደራ እንላለን።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከት ትላንት የተካሄዱ 3 አበይት ክንውኖች ፦
(በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የቀረበ)
1. የመጀመርያው ተርባይን Unit 10 በመባል የሚታወቀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል (Rotar) የማስቀመጥ ሥራ በስኬት ተከናውኗል። ይህም በቅርቡ ኃይል እንደሚያመነጭ ከሚጠበቁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2 ዩኒቶች መካከል አንዱ ሲሆን ሮታሩና አብረው ያሉት አካላት 840 ቶን ክብደት አላቸው፤ ሮተሩ ብቻውን 780 ቶን ይመዝናል። ሮተሩ ከአንድ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ድረስ ያለው አጋማሽ ርዝመት ወይም ዳያሜትር 11 ነጥብ 7 ሜትር ነው። ይህም የስራውን ግዝፈት ያሳያል::
2. የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ/ር እና የውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን የዲሞክራቲክ ኮንግ አቻቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል:: በውይይታቸውም ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ተገኝተው ነበር። የዲሞክራቲክ ኮንግ ም/ጠ እና ው/ጉ ሚ/ሩም አመጣጥ በግድቡ ዙሪያ የሚደረገው የ3ዮሽ ድርድር የሚጀምርበትን ለመምከር ሲሆን፤ ሚ/ሩ ድርድሩን የሚያግዝ ዶክመንት ይዘው መጥተዋል።
3. የተ.መ. ድ. (UN) በJuly 8 ለተካሄደው የፀጥታው ምክር ቤት open debate ከ9 ሳምንት በሁዋላ የም/ቤቱን ፕሪዚዳንት statement ማምሻውን አውጥቶአል:: ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ እና ድርድሩ በሶስቱ አካላት ኢትዮጵያ: ግብፅ እና ሱዳን እንዲቀጥል ተገልጿል:: ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የተመድ ፀጥታ ም/ቤት እንዲህ አይነት ጉዳዮችን ማየት እንደሌለበት አምባሰደር ታዬ በኩል ለሚዲያ በስፍራው ተገኝተው ገለፃ አድርገዋል::
@tikvahethiopoa

#MoH
የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ላይ ያለውን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል አጋር ድርጅቶች እገዛቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ከአጋር ድርጅቶች ተወካዮች ጋር የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ያለውን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ በተመለከተ ትላንት ውይይት አደርገዋል።
ውይይቱን የመሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ አጋር ድርጅቶች እየሰጡ ላለው ሰብዓዊ እርዳታ አመስግነው የፀጥታ ችግር ባለባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የጤና አገልግሎት በመጓደሉ የእናቶች እንዲሁም ህፃናት ጤና ችግር ላይ መውደቁን ፣ የውሃ እጥረት በመኖሩም ኮቪድና ኮሌራን ጨምሮ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊጋለጡ እንደሚችሉ ጠቁመው ችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በጤና ሚኒስቴር የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን ዳይሬክተር ዶክተር አለኝታ ገ/የሱስ የጤና ተቋማትና አምቡላንሶች ያሉበትን ሁኔታ የገለፁ ሲሆን ፥ በግጭት አካባቢዎች አብዛኞቹ ተቋማትና አምቡላንሶች አገልግሎት እየሰጡ አለመሆናቸውን፤ አገልግሎት የሚሰጡትም ያሉባቸውን ዕጥረቶች በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች በየአካባቢዎች እያደረጉ ያሉትን አስተዋፅኦ አብራርተው በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
Via MoH Ethiopia

#ICRCEthiopia
በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ግጭት በርካታ ሰዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዳይኖራቸው አድርጓል።
ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ #በንፋስ_መውጫ አካባቢ የተጎዳውን የውሃ አቅርቦት ለመጠገን የሚረዱ ቁሳቁሶችን ማቅረቡን አሳውቋል።
በዚህም ከ50 ሺ በላይ የሚሆኑ በደቡብ ጎንደር የሚገኙ በብጥብጥ የተጎዱ ሰዎች የውሃ አቅርቦት እንደሚኖራቸው አይሲአርሲ ጠቁሟል።

TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል። የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ። የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፤ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ…
#Update
ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና #በወረቀት እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለ @tikvahuniversity ገልጿል።
የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ በ @tikvahuniversity በኩል ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናው በወረቀት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
አቶ ረዲ ፤ በዘንድሮው ፈተና የኢኮኖሚክስ የትምህርት አይነት እንደማይኖር የገለፁ ሲሆን የመልቀቂያ ፈተናው ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች ይሰጣል ብለዋል።
በተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው የሚገኙ ተማሪዎችን በተመለከተም ለተነሳላቸው ጥያቄ ፥ "ሁኔታው ተጠንቶ ወደ ፊት አቅጣጫ ይቀመጣል" የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h