TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 20 ሺህ ሰራተኞችን ሊቀጥር ነው ?

ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ !

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገፁ 20 ሺህ #ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን መቅጠር እንደሚፈልግ አስታወቀ ፤ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን የሚቀጥረው ትግራይ ፣ አፋር፣ ሶማሌ ክልሎችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች የቴሌኮም አገልግሎቱን ለማስፋፋት በማቀድ ነው ፤ የስራ ቅጥሩ ዲግሪ አይጠይቅም 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ማመልከት ይችላሉ " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም #ሀሰተኛ መሆኑን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገልጾልናል።

ከጥዋት አንስቶ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨውን የ20 ሺህ ሰራተኞች ቅጥር መረጃ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሚመለከተው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ክፍል " በየትኛው የማህበራዊ ትስስር ገፃችሁ ላይ ነው ይህ ያሳወቃችሁት ? መረጃው እውነት ከሆነስ በየትኛው መንገድ ነው ማመልከት የሚቻለው ? " ስንል ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን መረጃው #ሀሰተኛ ነው የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል።

" እኛ 20 ሺህ ሰራተኞች ለመቅጠር በየትኛውም የማህበራዊ ትስስር ገፃችን ላይ ጥሪ አላቀረብንም ፤ መሰል ሀሰተኛ መረጃዎች የሚሰራጩት ሆን ተብሎ ተመሳስለው በተከፈቱ #ሀሰተኛ_ገፆች ነው " ሲል የሚመለከተው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ክፍል ገልጾልናል።

በመሆኑም " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 20 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ሊቀጥር ነው " በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopia