TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Gambella

በትላንትናው ዕለት ከጋምቤላ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ 5 ግለሰቦች በከፈቱት ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የጋምቤላ ክልል የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት አስታወቁ።

ጉዳቱን ተከትሎ በከተማው በተከሰተው ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

በግጭቱ ባጠቃላይ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

ጥፋተኞቹን ወደህግ ለማቅረብ የፀጥታ አካላት ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ሲሉ ገልፀዋል።

ከግጭቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ አስር የሚደርሱ ግለሰቦች ቀደም ብሎ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ማጣራት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ግጭቱ በተፈጠረበት በጋምቤላ ከተማ ያለው ሰላም ወደ ነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ከጋምቤላ ከተማ ወደ ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲገቡ ተደርጓል፤ ለጊዜው በፀጥታ አካላት እጀባ እንዲሄዱ እየተደረገ ነው ብለዋል።

መረጃው የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው::

@tikvahethiopia
ዛሬ በቡለን ወረዳ 5 ሚሊሻዎች ተገደሉ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ስር ወዳለችው ቡለን ወረዳ ዛሬ ረፋዱን በባጃጅ ሲጓዙ የነበሩ 5 ሚሊሺያዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ፤ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የጉሙዝ ታጣቂዎች አምስት ሚሊሺያዎችን መግደላቸውን አረጋግጠዋል።

ሚሊሺያዎቹ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው “ለአካባቢ መጠበቂያ የሚሆን [ትጥቅ] ሊታጠቁ ወደ ከተማው ማዕከል በመጓዝ ላይ እያሉ” መሆኑን አቶ አብዮት ገልጸዋል።

በመተከል ዞን ከምትገኘው ዶቤ ቀበሌ እንደተነሱ የተነገረላቸው ሚሊሺያዎች፤ ወደ ቡለን ከተማ ሲጓዙ የነበረው በሶስት ባጃጆች ተሳፍረው ነበር ተብሏል።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የሰነዘሩት በአንደኛው ባጃጅ ውስጥ በነበሩ ሰባት ሚሊሺያዎች ላይ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።

በጥቃቱም አምስት ሚሊሺያዎች ሲገደሉ፤ ሁለቱ መቁሰላቸውን በቡለን ወረዳ የሚኖሩ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የመንግስት ሰራተኛ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘገባ በዚህ ይገኛል : https://telegra.ph/Ethiopia-Insider-08-31

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Djibouti

ከሰሞኑን በዩጋንዳ እና ሩዋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት እና ከሀገራቱ መሪዎች ጋር የመከሩት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሁን ደግሞ ከጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ፕሬዜዳንታ ጋር በስልክ ተወያያተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌ ጋር የተወያዩት በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ነው። በውይይታቸው የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ተብሏል።

ዶ/ር ዐቢይ እና ኢማኤል ኡመር ጌሌ በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል ፥ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነትን በጠበቀ መልኩ የሁለትዮሽና የቀጠናዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ተነጋግረዋል።

በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደተገኘው መረጃ።

@tikvahethiopia
የመንግስት ምስረታ የሚካሄድበት ቀን ታወቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጪው መስከረም 24 ቀን 2014 ስድስተኛው ዙር የመንግስት ምስረታ እንደሚካሄድ ዛሬ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,324 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ15 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 8,430 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,324 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 15 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ከትላትናው በ30 ጨምሮ ዛሬ 630 ደርሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ሠመራ እና ዱብቲ ከተሞች ላይ ከፍተኛ የሆነ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት ፦ - ሠመራ፣ - ዱብቲ፣ - አይሳኢታ፣ - ሎጊያ እና ሚሌ ከተሞች ላይ ዛሬ በ23/12/2013 ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል። የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመመለስ የጥገና ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቁሟል። በሠመራና ዱብቲ…
#Update

በአፋር ክልል ነፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ጥገና ተደርጎ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በ23/12/2013 ምሽት ላይ ከፍተኛ የሆነ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ጥገና ተደርጎለት ፦
- ሠመራ፣
- ዱብቲ፣
- አይሳኢታ፣
- ሎጊያ እና ሚሌ ከተሞችን ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ መደረጉን የአፋር ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
* TPLF

የ " ህወሓት ኃይሎች " ባለፉት ቅርብ ሳምንታት የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (USAID) የሆኑ የእርዳታ መጋዘኖችን መዝረፋቸው ተገለጸ።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳሬክተር ሾን ጆንስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት ፥ "የህወሓት አማጺያን በደረሱባቸው ስፍራዎች የሚገኙ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል" ብለዋል።

የUSAID የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ፥ "የታጠቁ ሰዎች ከዜጎች ምግብ ሰርቀዋል። ህወሓት በገባባቸውና ጦርነት በከፈተባቸው ሁሉም የአማራ አካባቢዎች መጋዘኖችን ዘርፏል፤ ተሽከርካሪዎች ዘርፏል። ውድመት ፈፅሟል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሾን ጆንስ አክለው ፤ "በተለይ የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካበቢዎች በርካታ የእርዳታ መጋዘኖቻችን ስለመዝረፋቸው እና መጋዘኖቹ ባዶ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አለን" ብለዋል።

በተጨመሪ ፥ "ህወሓት ሁኔታዎችን ያለአግባብ እየተጠቀመ እንደሆነ አምናለሁ። ከተረጂዎች ላይ በኃይል እርዳታ እየነጠቀ አንደሆነ ይሰማናል፤ የምናውቀው ሃቅ ግን የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖቻችን ዘርፈዋል" ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት በተባበሩት መንግሥት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ የአሜሪካ ተወካይ በተመሳሳይ "በአማራ ክልል ውስጥ የእርዳታ መጋዘን በህወሓት ኃይሎች መዘረፉን" ተናግረው እንደነበር ቢቢሲ አስነብቧል።

#EBC #BBC #AFP

@tikvahethiopia
#UNSC

የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የወርሃ መስከረም ሰብሳቢ አየርላንድ 🇮🇪 ሆና ተመረጠች፡፡

አየር ላንድ ሰብሳቢነቱን ከህንድ 🇮🇳 ነው የተረከበችው፡፡

የወርሃ ነሃሴ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የነበረችው ህንድ ም/ቤቱ በትግራይ ጉዳይ በተወያየበት ጊዜ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውን በመቃወም ኢትዮጵያን መደገፏ የሚታወስ ነው፡፡

ወቅታዊ የኢትዮጵያን ሁኔታዎች በአሳሳቢነት ስትገልጽ የሰነበተችው አየርላንድ በበኩሏ ከአሁን ቀደም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ ስብሰባን እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቧ የሚታወስ ነው፡፡

መረጃው የአል ዓይን ነው።

@tikvahethiopia
ለተፈናቃዮች የሚደረግ ድጋፍ ...

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እያደረገ ነው።

በክልሉ ከ112 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሉ የገለጸው ድርጅቱ ለ30 ሺህ ዜጎች የምግብ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

በአምስት ቀጠናዎች ከአፋር ክልል እና ከፌደራል መንግስት ጋር በመቀናጀት አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ስንዴ እና ዘይት ማድረሱን ገልጿል፡፡

#WFPEthiopia

@tikvahethiopia
የተፈናቃዮች ድጋፍ ሁኔታ በአማራ ክልል...

ትላንት የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ከተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ማዕከል የኢትዮጵያ ሃላፊ አዴል ከድር ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህ ውይይት ላይ ህወሓት በሀይል በወረራቸው አካባቢዎች ግማሸ ሚሊየን ዜጎች መፈናቀላቸውን 4 ሚሊየን የሚደርሱት ደግሞ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ሪፖርት አቅርበዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት ግማሽ ሚሊዮን ሰው እንደተፈናቀለ የገለፁት ወረራ በተደረገባቸው በሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም ዋግኸምራና ሰሜን ወሎ ዞኖች ነው።

በተጨማሪ ወረራ ተፈፅሞባቸወል ባሏቸው አካባቢዎች የማህበራዊ ተቋማት ትምህርት ቤቶች እና ጤና ተቋማትን ወድመዋል፤ ዜጎች ላይ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ተፈፅሟል ሲሉ ሪፖርት አድርገዋል።

UNICEF አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዴል ኮድር በሰሜን ጎንደርና አካባቢው ጉብኝት ማድረጋቸውን ገልፀው በርካታ ህፃናት በምግብ እጥረት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡

ታዳጊዎች በመጭው የትምህርት ዘመን በትምህርት ገበታ ለመታደም አሳሳቢ ሁኔታ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

ዳይሬክተሯ በቀጣይ ጊዜያት ወደ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እንደሚሄዱም ገልፀዋል፡፡

ከተባበሩት መንግስታት እህት ድርጅቶችና ከሌሎች ረድኤት ድርጅቶች ጋር በመሆን ችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች በአፋጣኝ እርዳታ እንዲደርሳቸው እንሰራለን ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ UNICEF በአማራ ክልል በጦርነት ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።

UNICEF ድጋፍ ያደረገው ለተማሪዎች ደብተርና ስኪርቢቶ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እንዲሁም ፍራሾች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ነው።

ፎቶ፦ UNICEF & AMC

@tikvahethiopia
41 ሺህ ተፈናቃዮች የሚገኙባት ደባርቅ...

በደባርቅ 41 ሺህ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ይገኛሉ። ከቀናት በፊት የUNICEF የኢትዮጵያ ኃላፊ አዴል ከድር ደባርቅ ከተማ በመገኘት ተፈናቃዮችን ተመልክተዋል። በዚህ ወቅት ፍራሾችን ፣ ከፍተኛ የኃይል ሰጪ ብስኩቶችን፣ ውሃ ፣ የአካባቢ ጽዳትና ንፅህና አቅርቦቶችን ጨምሮ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ አቅርቦቶችን አስረክበዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጰያ ኢንተርፕሩነርስ ማህበር ተቋቋመ።

በአገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው አገር አቀፍ “የኢትዮጰያ ኢንተርፕሩነርስ ማህበር” ተቋቋመ፡፡

ኢንተርፕሩነርስ በስራ ፈጠራና ሀገር ግንባታው ዘርፍ ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጠንቅቀው ቢረዱም ዘርፉ የሚጠይቀውን ግብዓትና እገዛ ግን በሚፈለገው ደረጃ አቅርበዋል ለማለት አያስደፍርም፡፡

ማህበሩ ኢንተርፕሩነርስ ሥራቸውን በሚጀምሩበት ወይም በሚሠሩበት ጊዜ የሚያጋጥማችውን ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እንዲሁም የሥራ ፈጠራን (ኢንተርፕሩነርሽፕን) ባህል ለማበረታታት ጠንክሮ እንደሚስራ መመስርቱን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በኤልገሌ ሆቴሌ በተካሄደው ይፋዊ ማብሰሪያ መርሀ ግብር ላይ ተገልጿል።

@tikvahethiopia