TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች📌ነገ በመስቀል አደባባይ ለኦነግ አመራሮች የሚደረገው አቀባበል ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በአዲስ አበባ #ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ።

በዚህም መሰረት፦

▪️ከቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣

▪️በኡራኤል፣ ባምቢስ አብዮት አደባባይ፣ ከአራት ኪሎ፣ ብሄራዊ ቤተመንግስት ወደ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ከካዛንቺስ፣ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ፍል ውሃ፣

▪️ከንግድ ማተሚያ ቤት ኦርማ ጋራዥ፣ ፍልውሃ፣ ሃራምቤ ሆቴል፣ ከቴድሮስ አደባባይ፣ ኢሞግሬሽን፣ ፣ ሀራምቤ ሆቴል፣ ስታዲየም፣

▪️ከጎማ ቁጠባ፣ ብሄራዊ ትያትር፣ ስታዲየም፣ ሜክሲኮ፣ ከሰንጋ ተራ፣ በድሉ ህንፃ ስታዲየም፣

▪️ከሰንጋ ተራ፣ በለገሃር፣ ስታዲየም፣
በቂርቆስ አዲሱ መንገድ፣ በለገሃር ስታዲየም፣

በሀራምቤ ሆቴል፣ ጋንዲ ሆስፒታል፣ ወደ መስቀል አደባባይ፣

▪️ከአጎና ሲኒማ፣ በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መሰቀል አደባባይ ያሉ መንገዶች #ለጊዜው የተዘጉ መሆናቸውን አስታውቆአል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ 6 አመራሮቹን ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ አቶ አራርሶ ቢቂላ ፣ አቶ ቶሌራ አዳባና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ ስድስት ከፍተኛ አመራሮቹን #ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል፡፡

በእግዱ ተካተዋል የተባሉ አመራሮች ነሐሴ 4 ቀን የድርጅቱ አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫ በሂልተን ሆቴል መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳዎድ ኢብሳ በበኩላቸው የተሰጠው መግለጫ የፓርቲያቸው እውቅና እንደሌለውና እርሳቸውም ስለ መግለጫው መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ከዚህም አስቀድሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ስብሰባ በኀላ በተነሱ ጉዳዮችና ልዩነቶች ላይ የፓርቲው የህግና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲያጣራ መወሰኑን አመራሮቹ ገልጸው ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot