TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሳዑዲ አረቢያ ባሉ ዜጎቻችን ላይ የሚፈፀመውን በደል የሚቃወም ሰል በአሜሪካ ተደረገ።

በአሜሪካን ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት መበቃወም ሰልፍ ወጥተዋል።

በአሜሪካን ሃገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት አስተባባሪነት በሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት መበቃወም በዋሽንግተን የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ ወጥተው ድምፃቸው አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት ‘በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲቆም' ጠይቀዋል፤ ‘ሕጻናትና ሴቶች ጥበቃን እንጂ የመብት ጥሰትን አይፈልጉም' ብለዋል።

ሰልፈኞቹ 'በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየደረሰባቸው ያለው በደልና ግፍ አይገባቸውም' ብለዋል።

በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን "ሥቃያቸው ፣ እንግልታቸው እና መከራቸው እየበዛ መሆኑን ሪፖርት እያሰረጉ ይገኛሉ።

ሕፃናት እየሞቱባቸው እንደሆነ ፣ እህት ወንድሞቻቸውም እየተሰቃዩ እንደሆነ፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች እየተሰቃዩ እንደሆነ እያሳወቁ ይገኛሉ።

መረጃው ከኢትዮጵያ ዳያስፓራ ኤጀንሲ እና የጀርመን ድምፅ ሬድዮ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
የቀድሞ የህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ስመኘው በቀለ 3ኛ ዓመት መታሰቢ ተከናወነ።

የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብን ፕሮጀክት በመምራት በሀገሪቱ ታሪክ የማይፋቅ አሻራቸውን ያሳረፉት የቀድሞው የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ስመኘው በቀለ 3ኛ አመት መታሰብያ በትላንትናው ዕለት በጎንደር ከተማ ሀይሌ ሪዞርት ተከናውኗል።

በአባታቸው አባ በቀለ አይናለም ቤትም የፍታት ስርዓት ተዘጋጅቶ እንደነበር ተገልጿል።

ፕሮግራሙ ተዘጋጅቶ የነበረው ዘወትር በማትለያቸው እና በደጋፊያቸው #ሰሎሜ እንደነበር ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በማህበራዊ የትስስር ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"እናቴ በጭንቀት ታማለች" ከሳምንታት በፊት የታሰሩት የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች እስካሁን ያሉበትን እንደማያውቁ ቤተሰቦቻቸው ዛሬ በስልክ ሪፖርት አድርገውልናል። እስር ላይ ካሉ የአውሎ ሰራተኞች መካከል የአንድ ታሳሪ የቤተሰብ አባል የሆነች እንስት ጋዜጠኞቹና የሚዲያ ሰራተኞቹ የት እንዳሉ ቤተሰብ ባለማወቁ ለከፍተኛ ጭንቀት መዳረጋቸውን ገልፃለች። ቤተሰብ ስላለበት ሁኔታ እንደሚከተለው አስረድታለች፦…
የሚዲያ ሰራተኞቹ አዋሽ 7 እንደሚገኙ ታወቀ።

አካልን ነፃ የማውጣት ማመልከቻ አስገብተው የነበሩት 14 የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ወደ አዋሽ 7 መዘዋወራቸውን ፖሊስ ፍርድ ቤት አሳወቀ።

ፖሊስ ለልደታ ዘጠነኛ የፍትሐ ብሔር ችሎት ትላንት በጽሁፍ ባቀረበው ምላሽ ተጠርጣሪዎቹ በቦታ ጥበት ምክንያት አፋር ክልል፣ ፈንታሌ ወረዳ አዋሽ ሰባት ኪሎ ወደሚገኘው ቅርንጫፍ ወስጃቸዋለሁ ብሏል።

ለፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀረበ አቤቱታ እስከ ሐምሌ 26 ድረስ ለምርመራ ጊዜ መፈቀዱን ፖሊስ አክሏል።

ለችሎቱ በማስረጃነት የተያያዘው ለፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረበው የፖሊስ ማመልከቻ እንደሚያመለክተው ጋዜጠኞቹ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ፥ "በማኅበራዊ ድረ ገጽ ፤ ማለትም በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም እና ዋትስአፕን በመጠቀም በውጭ አገር ከሚገኙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን፤ ሕብረተሰቡ ላይ ጫና ለመፍጠር፤ ብሔር ብሔረሰቦች እንዲጋጩ፣ ሕዝቡ ተረጋግቶ ሥራውን እንዳይሰራ፤ ጦርነት ቀስቃሽ መልዕክቶችን አሰራጭተዋል" የሚሉትን ጨምሮ በተመሳሳይ ወንጀሎች ጠርጥሬያቸዋለሁ ሲል ለፈንታሌ ወረዳ ችሎት አመልክቷል።

የመገናኛ ብዙኃን አዋጁን በመጣስ ብሎም ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የሚያስረዳው ክሱ እነዚህን ወንጀሎች ለመመርመር ጊዜ ይሰጠኝ ሲል አመልክቶ ነበር።

ሐምሌ 12 ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል የጠየቀው ፖሊስ በተሰጠኝ ጊዜ ውስጥ አከናወንኩ ያላቸውን ተግባራት ዘርዝሮ ለችሎቱ አቀርቧል።

ያንብቡ : telegra.ph/BBC-07-27 [ቢቢሲ]

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ይፋ ከሆነ ቀናትን ብቻ ባስቆጠረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የድጋፍ ማድረጊያ ድረገፅ www.mygerd.com ከ90 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ ተሰበሰበ።

በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚያደርጉበት እና ታሪካዊ አሻራቸውን የሚያሳርፉበት ድረገፅ ከ2 ቀናት በፊት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ባለፉት ቀናት ብቻ በ737 ሰዎች ድጋፍ 90,845 ዶላር መገኘቱን ከድረገፁ ላይ መመልከት ችለናል። 38 ሰዎች ለሌሎች በማስተዋወቅ ዘመቻ እያካሄዱ ነው።

@tikvahethiopia
#WFP #Tigray

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ ፥ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ትግራይ ውስጥ የሚያደርሰው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት በዚህ አርብ እንደሚያልቅበት ገለፁ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በትግራይ ውስጥ ሊመግብ ላሰባቸው ሰዎች ሁሉ ለመድረስ በቀን 100 የጭነት ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልገው አንስተዋል።

ባስሌይ ፥ "ለትግራይ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶች የያዙ 170 ተሽከርካሪዎች በአሁን ሰዓት አፋር ይገኛሉ፤ መንቀሳቀስም አልቻሉም ፤ አሁኑኑ እነዚህ ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ መፈቀድ አለበት ፤ ሰዎች እየተራቡ ነው" ብለዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbabaPolice

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ170 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በህገ ወጥ መንገድ የአሜሪካ ዶላር ሲያዘዋውር የነበረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-57949 ኢት/ተሳቢ 17713 ኢት የሆነ ከባድ ተሽከርካሪ ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋለው ሃምሌ 7 ቀን 2013 ዓ/ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቱሉ ዲምቱ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ተሽከርካሪው ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ እየተጓዘ ነበር ፤ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በተደረገበት ፍተሻ ከጋቢናው መቀመጫ ወንበር ጀርባ በሚገኝ ሳጥን ውስጥ በላስቲክ ተጠቅልሎ የተደበቀ 170 ሺህ 700 የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ አንድ ተጠርጣሪ ተይዞ ምርመራው እየተከናወነ ይገኛል።

የአ/አ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት ህገ-ወጥ የገንዘብ እንዲሁም የጦር መሳሪያ ዝውውር የሃገርን ሰላም እና የተረጋጋ ኢኮኖሚን በማናጋት በህዝብ ኑሮ ላይ የሚፈጥረው ቀውስ ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ መረጃ እና ጥቆማ በመስጠት ለፀጥታ አካላት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹 #Tokyo2020

ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን ዲፕሎማ አግኝታለች።

በወርልድ ቴኳንዶ የመጀመሪያ ተሳትፎን በኦሎምፒክ ያደረገው ሰለሞን ቱፋ 7ኛ ደረጃን በ መያዝ ዲፕሎማውን መረከቡን #EOC አሳውቋል።

Via @tikvahethsport
#Tigray

የፌዴራል መንግስት "የሰብአዊ ዕርዳታ እንዲርደስ ለማስቻል አልሜ ያደረኩት የተናጠል የተኩስ አቁም በሕወሃት ትንኮሳ መደናቀፉን ቀጥሏል" ብሏል።

በትግራይ ክልል በሚገኙ መጋዘኖች ውስጥ ከ400,000 ኩንታል የሚበልጥ ስንዴ እና ከ2.5 ሚሊዮን ሊትር የሚበልጥ የምግብ ዘይት መቀመጡን ገልጿል።

የፌዴራል መንግስት ፥ "በትግራይ ክልል ያሉት ዜጎቻችን ደህንነት ያሳስበኛል" ያለ ሲሆን "ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በተለይም ደግሞ በትግራይ ድጋፍ በመስጠት ላይ የሚገኙት፣ ህወሓት የአፋርን ክልል መተናኮሱን አቁሞ ሰብዓዊ እርዳታ ለያዙ ተሽከርካሪዎች መንገዱን እንዲከፍት ግፊት ማሳደር አለባቸው" ብሏል።

ይህ መረጃ ይፋ የሆነው በ"ወቅታዊ ሁኔታ የመረጃ ማጣሪያ ገፅ" በኩል ነው።

ከሰዓታት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ ድርጅታቸው ትግራይ ውስጥ የሚያደርሰው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት በዚህ አርብ እንደሚያልቅበት ገልፀዋል።

ዴቪድ ባስሌይ በአፋር አካባቢ ስላለው ሁኔታ ዝርዝር መረጃዎች ባይሰጡም ለትግራይ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶች የያዙ 170 ተሽከርካሪዎች በአሁን ሰዓት አፋር እንደሚገኙና መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ገልፀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ፥ ተሽከርካሪዎች አሁኑኑ እንዲንቀሳቀሱ መፈቀድ እንዳለበት በመግለፅ ትግራይ ውስጥ ሰዎች እየተራቡ መሆኑን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#SaudiArabia

'በሳዑዲ አረቢያ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድምጽ እንሁን' በሚል የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ወጣቶች ህብረት ባዘጋቸው የበይነ መረብ ውይይት ኢትዮጵያዊያኑ ''ድምጻችሁን አሰሙልን በጣም እንግልታችን እየበዛ ነው። ህጻናቱ እየሞቱብን ነው እህት ወንድሞቻችን እየተሰቃኑ ነው ነፍሰጡር ሴቶች እየተሰቃዩ ነው'' ሲሉ ችግራቸውን አስረድተዋል።

''ገንዘባችንን ከፍለን ወደ ሀገር ቤት መመለስ የምንችል ዜጎች በህጋዊ መንገድ እንድንወጣ የኢትዮጵያ መንግስት ህጋዊ መንገዶችን ያመቻችልን'' ሲሉም ጠይቀዋል።

በሳዑዲ አረቢያ የስደተኞች ህግ መቀየሩ ችግሩን አወሳስቦታል ሲሉ በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል።

ስምንትና ዘጠኝ ዓመት ከህግ ውጪ የሰሩ ሰዎች ወደ 100 ሺ ሪያል የሚጠጋ ካልከፈሉ መውጣት አይችሉም፤ ይህንን የሚከፍሉ ከሆነ ራቁታቸውን ነው የሚወጡት ሲሉ የገለፁት አምባሳሰር ሌንጮ ፥ ምህረት እንዲደረግ በመጠየቁ ባለፈው ሳምንት ምህረት መደረጉን ንጉሱ ማሳወቃቸውን አንስተዋል። ነገር ግን ወከባውና አሰሳው ካላቆመ በስተቀር ዜጎች ኤምባሲ ድረስ መጥተው ሊመዘገቡ እንደማይችሉ አስረድተዋል።

ዜጎችን ወደሃገር የመመለስ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያስገነዘቡት አምባሳደሩ ፥ ''ሴቶችና ህጻናትን ቅድሚያ መስጠት አለብን ይሄ ካልሆነ ሦስት ወር ስድስት ወር ሬሳ በሬሳ ነው የሚሆነው ለዚህ ደግሞ የሚጠየቁት እነሱ ብቻ አይደሉም እኛም ተጠያቂ ነን'' ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 5,386 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 203 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሶስት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 43 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia