" የምንሰራው ስራና የሚከፈለን ወርሃዊ ደመወዝ አይመጣጠንም ፤ ድካማችንን የሚመጥን ክፍያ አናገኝም " - ሰራተኞች
በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራው ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ድርጅት አንዱ በሆነ መስፍን ኢንዳትሪያል ኢንጅነሪነንግ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የመብት ጥያቄ እንዳላቸው ገለጹ።
ሰራተኞች ዛሬ ስራ በማቆም ወደ ትእምት ( ትግራይ መልሶ ግንባታ) ዋና ቢሮ በመጓዝ " የመብት ጥያቂያችን ይመለስ " ብለዋል።
ብዛታቸው ከ150 በላይ የሆኑ ሰራተኞቹ ፦
➡️ የሚሰሩት ስራና የሚከፈላቸው ወርሃዊ ደመወዝ እንደማይመጣጠን፤
➡️ በድርጅቱ በቀን አስከ 20 ሰዓታት የሚሰሩ ሰራተኞች ቢኖሩም የሚያከፈላቸው ከፍያ እጅግ አነስተኛ መሆኑ፤
➡️ ደርጅቱ አትራፊ ቢሆንም ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ፤
➡️ ከጥቅማጥቅም ፣ ያልተከፈለ ውዙፍ ደመወዝና የሰራተኛ ቅጥር ጋር የተያየዘ ጥያቄ እንዳላቸው ገልጸዋል።
" ለረጅም ጊዜ የመብት ጥያቄያችንን የሚመጥን አስቸኳይ መልስና መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።
ለሰራተኞቹ ዘግይተው መልስ የሰጡት የትእምት የሰው ሃይል አስተዳደር ተኽለወኒ ገ/መድህን ፥ " ቀጣዩ አርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ከትእምት ኢንደውመንት አመራሮች በጋራ በመሆን ጥያቄያችሁ እናደምጣለን " በማለት ሸኝተዋቸዋል።
መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪነንግ በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራ ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ካምፓኒዎች አንዱ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
መቐለ ? የመቐለ ከተማ ም/ቤት ዛሬ አካሂዶታል በተባለ ሰብሰባ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ህወሓት ውስጥ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው የተመረጡትን ዶ/ር ረዳኢ በርሀ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖው እንዲያገለግሉ በ1 የተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ እንደመረጣቸው ተሰምቷል። የከተማዋ ም/ቤት ከተማዋ በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት በዶ/ር ደብረፅዮን በሚመራው ህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑትን አቶ…
#መቐለ
" የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አዲሱን የመቐለ ከንቲባ ከስራ አገዱ።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " ለዶ/ር ረዳኢ በርሀ " በማለት ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ፤ አዲሱ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ህጋዊ ያልሆነ ተግባራቸውን እንዲያቆሙ አሳስበዋል።
" የመቐለ ከተማ ምክር ቤት መጠቀምያ በማድረግ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ የሚፃረር ተግባር መፈፀም አይቻልም " ያለው የፕሬዜዳንቱ ደብዳቤ የአዲሱ ከንቲባ ሹመት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል።
አቶ ጌታቸው " የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚፃረር አቋም በመያዝ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ስር ያለን መዋቅር መምራት አትችሉም ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩም ከእርስዎ ጋር መሰራት አይችልም " ብለዋል።
በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት መዋቅሮች " ህጋዊ አይደሉም " የተባሉት ከንቲባ የሚሰጡዋቸው አመራሮች እና ትእዛዞች ተቀብለው እንዳይፈፅሙ ፕሬዜዳንቱ አስጠንቅቀዋል።
አዲሱ የመቐለ ከንቲባ ዶ/ር ረዳኢ በርሀ ፤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት የስራ አስፈፃሚ ሆነው የተመረጡ ናቸው።
በያዝነው ወር መጀመሪያ ሳምንት ደግሞ የቀድሞውን ከንቲባ አቶ ይትባረክ አምሃ በመተካት ከንቲባ ሆነው እንዲመሩ በመቐለ ከተማ ምክር ቤት መሾማቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።

Photo
" ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ምሽት ብዙዎችን ያነጋገር መልእክትና ፎቶ በይፋዊና በተረጋገጠ የX ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።
ፎቶው ከደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር አብረው ያሉበት ነው።
አቶ ጌታቸው ፤ " ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም ለመቀራረቡ እኛ እንቀርባለን ብላችሁ እኛን ለማገናኘት በመጣር ላይ ያላችሁ ትግራዎት ክብር ይስጣችሁ። ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " ብለዋል ከፎቶው ጋር ባያያዙት ፅሁፍ።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጋራ የተነሱትን ፎቶ ብዙዎች በመጋራት አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
አብዛኞቹ ምስሉ በአውንታ ተቀብለው ሲያስተጋቡ ፤ ጥቂት የማይባሉት ደግሞ " ከአንገት በላይ " ያሉትን ፎቶና መልእክት ንቅፈው እየጻፉ ነው።
አቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለበርካታ ሳምንታት በሚዲያ እና በፅሁፍ መግለጫ ብዙ ሲባባሉ እንደነበር አይዘነጋም።
ምንም እንኳን ዛሬ በምን ጉዳዮች ላይ እንደተነጋገሩ በዝርዝር ባይታወቅም አቶ ጌታቸው ረዳ ያጋሩት ፎቶ ብዙዎችን እያነጋገረ ሲሆን ለአንዳንዶችም ' መካረሩ ያበቃለት ይሆናል ' የሚል ተስፋ የሰጠ ሆኖ ታይቷል።

" ሌሊት 10 ሰዓት ነው በትዳር አጋሯ የተገደለችው ፤ አንቆ ነው የገደላት " - የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ በትግራይ፣ በውቕሮ ከተማ ድል ባለ ሰርግ ከተሞሸረች በኃላ በአራተኛው ቀን በትዳር አጋሯ ታንቃ ስለተገደለችው ሊዲያ ዓለም ጉዳይ የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ አስተያየቱን ሰጥቷል። ለቢቢሲ አማርኛው ቃላቸውን የሰጡት የትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ሙሉ ብርሃን ካህሳይ ፥ " ሊዲያ ረቡዕ፣ጥቅምት…
#መቐለ
መቐለ ከተማ ውስጥ በጭካኔ የተገደለች እንስት አስከሬንዋ ከ2 ቀን በኋላ መገኘቱን ፓሊስ አስታውቋል።
የጭካኔ ተግባሩ የት ፣ መቼ ፣ እንዴት ተፈፀመ ?
የጭካኔ ተግባሩ በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነው የተፈፀመው።
ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል #በቢላዋ ተገድላ መገኘትዋና ጥቅምት 20 /2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቀብርዋ ስነ-ሰርዓት መከናወኑ ተሰምቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የጭካኔ ተግባሩ የሚመለከት ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት ወደ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ፅህፈት ተጉዟል።
ፓሊስ የጭካኔ ተግባሩ የሚመለከት ዝርዝር መረጃ በማሰብባሰብ ላይ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የጭካኔ ግድያ ተግባሩ በፍቅኛሞች መካከል መፈፀሙን እና በግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ዳዊት ዘርኡ የተባለ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጠይቋል።
በተያያዘ በያዝነው ወር የመጀመሪያ ሳምንት ውቕሮ ከተማ ላይ እሁድ ጥቅምት 5 ተድራ ሓሙስ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም በባሏ በጭካኔ የተገደለችው ሙሽሪት ሊድያ ጉዳይ ተጣርቶ ወደ አቃቤ ህግ መተላለፉን የወቕሮ ከተማ ፓሊስ አሳውቋል።

#ትግራይ " ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች ከ51 በላይ ወገኖች ሲቀጠፉ ፤ ከ286 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ሰለባ ሆኗል " - በትግራይ ማእከላይ ዞን የየጭላ አበርገለ ወረዳ የፀጥታ ፅ/ቤት በትግራይ በነበረው አውዳሚ እና አሰቃቂ ጦርነት ወቅት ተቀብረው እና ተጥለው ያልመከኑ ተተኳሾች የንፁሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፍና አካል ማጉደል ቀጥለዋል። በየጭላ አሸርገለ ወረዳ የእምባ…
#ትግራይ
ያልመከነ ተተኳሽ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ቀጠፈ።
ጥቅምት 21 /2017 ዓ.ም በትግራይ ማእከላይ ዞን አበረገለ ጭላ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዘገልዋ መንደር ውስጥ ባልመከነ ተተኳሽ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው ጠፍቷል።
ህይወታቸው የጠፋው ባል እና ሚስት ከ5 ዓመት ልጃቸው ጋር ነው።
የወረዳው ፓሊስ አከባቢው በትግራዩ ጦርነት ከባድ ውግያ የተካሄደበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያልመከኑ ተተኳሾች አደጋ ሲያደርሱ ቆይቷል እያደረሱም ይገኛሉ ብሏል።
ፓሊስ እንዳለው ህይወቱ የተቀጠፈው ህፃን ወድቆ ያገኘውን ተተኳሽ ወደ ቤቱ ወስዶ ከእሳት በማነካካቱ ፈንድቶ ሦስቱ የቤተሰቡ አባላት ወድያውኑ ሞተዋል።
በወረዳው ከፕሪቶሪያ ስምምነት ወዲህ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች የአሁኑን ጨምሮ ከ53 ሰዎች በላይ መሞታቸው ያስታወቀው የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት በበኩሉ አሁንም የሚመለከተው አካል አከባቢው ካልመከኑ ተተኳሾች በማፅዳት ህዝቡ እንዲታደግ ተማጽኗል።
መረጃው ከወረዳው የህዝብ ግንኙነት ፅህፈት ቤት ነው የተገኘው።

#Afar #Tigray " የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ ነው " - ሀጂ አወል አርባ የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከፍተኛ አመራርን ላካተተዉ ሉዑካን ቡድን ምን አሉ ? " የአፋርና ትግራይ ህዝቦች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው። በሁለቱ ክልሎች…
#አፋር #ትግራይ
የትግራይ እና የዓፋር አጎራባች ዞኖች አመራሮች ዛሬ ጥቅምት ለሁለተኛ ጊዜ በዓፋርዋ የአብዓላ ከተማ ተገናኝተዋል።
ለግማሽ ቀን በተካሄደው የሁለቱ ክልል አጎራባች ዞኖች አመራሮች ግንኙነት ፦
- የሁለቱም ክልል ህዝቦች የፊት ለፊት ግንኙነት እንዲጀመር፤
- የተከለከሉ መንገዶች ተከፈትው ነፃ የህዝቦች ግንኙነት እንዲቀጥል፤
- ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ ክልል ህዝቦች የሰላም እና የልማት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፡
- ሁለቱም ክልሎች ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ፤
- ሁለቱም ክልሎች የሰላምና የፀጥታ እቅድ በማውጣት በየወሩ እየገመገሙ እንዲጓዙ፤
ተወያይተው መግባባት ላይ ደርሰዋል።
ግንኙነቱ በማስመልከት አስተያየት የሰጡት የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ሰላምና ልማት መሰረት እንዲይዝ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የላቀ ዝግጁነት አለው " ብሏል።
በያዝነው ጥቅምት ወር መጀመሪያ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ዓፋር ሰመራ ድረስ በመጓዝ ከርእሰ መስተዳደር ሃጂ ኣወል ኣርባ ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት ማካሄዳቸው መዘገባችን ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
Photo Credit - Tigrai Television

ፎቶ ፦ የህወሓት አመራሮች ዛሬ በመቐለ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኝተዋል። የፊት ለፊት ግንኙነቱ በክልሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች የተመራ ነበር። ጥዋት በመቐለ ኖርዘርን ስታር ሆቴል አዳራሽ የነበረው የፊት ለፊት ውይይት ግማሽ ቀን የፈጀ እንደነበር ታውቋል። የሃይማኖት አባቶቹ ፥ " ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ባቀረብናላቸው ጥሪ መሰረት ተገናኝተው ችግራቸውን በፓለቲካዊ እና በህጋዊ አሰራር እንፈታለን…
" ' ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል ' ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " - በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትናንት በትግራይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ያደረጉት የፊት ለፊት ግንኙነት ከብፁአን የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅና ምክር የዘለለ ውጤት እንደሌለው ተናገረ።
የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ዛሬ ምሽት አጭር መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም ፥ " በብፁአን አበው የተዘጋጀው ፊት ለፊት የማገናኘት መርሃ ግብር ልዩነቶች በህግ ፣ ተቋማዊ ስርዓት ማእከል በማድረግ ህዝብን ከአደጋ መታደግ በሚችል የሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችን እንድንፈታ ያለመ የምክርና የተግሳፅ መድረክ ነበር " ብሏል።
" መድረኩን ተከትሎ የተለያዩ ውዥንብሮች መፈጠራቸው ለመረዳት ችለናል " ያለው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፥ "ብፁአን አበው ላቀረቡልን ምክርና ተግሳፅ ያለን ክብር እና ድጋፍ ገልፀናል ፤ ከዚህ በዘለለ የተለያዩ አካላትና ሚዲያዎች ' ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል ' በማለት የሚያሰራጩት መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " ሲል ገልጿል።

#መቐለ መቐለ ከተማ ውስጥ በጭካኔ የተገደለች እንስት አስከሬንዋ ከ2 ቀን በኋላ መገኘቱን ፓሊስ አስታውቋል። የጭካኔ ተግባሩ የት ፣ መቼ ፣ እንዴት ተፈፀመ ? የጭካኔ ተግባሩ በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነው የተፈፀመው። ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል #በቢላዋ ተገድላ መገኘትዋና ጥቅምት 20 /2017…
#መቐለ
" ተጠርጣሪው ተይዞ ለክልሉ ፖሊስ ተላለልፎ ተሰጥቷል " - ፖሊስ
የ19 ዓመትዋን ወጣት በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በፓሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
የመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ፥ ጥቅምት 19 /2017 ዓ.ም ሓበን የማነ የተባለች ፍቅረኛውን በተከራዩት የሆቴል ክፍል በጬቤ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ከቀናት ፍለጋ በኃላ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
በአሰቃቂ የግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ዳዊት ዘርኡ ተወልደ የተባለው ግለሰብ አሰቃቂ ተግባሩን ፈፅሞ በመሰወሩ ሲፈለግ ቆይቷል።
የሟች ቤተሰብ ጨምሮ በርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች በከባድ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ ከትግራይ ክልል ወጥቶ በአማራ ክልል በኩል ሊያመልጥ ሲል በደሴ ከተማ መያዙን ፅፈዋል።
የመረጃው ትክክለኝነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያረጋገጡት የሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፓሲስ አዛዥ ሞገስ ወርቁ ፥ ተጠርጣሪው በዛሬው ቀን ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም ለክልሉ ፓሊስ ተላለልፎ መሰጠቱን ገልፀዋል።
ግለሰቡ ደሴ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ለፖሊስ ጥቆማ በመድረሱ ነው ሊያዝ የቻለው።
ከክልል ፖሊስ በተገኘው መረጃ ደግሞ ግለሰቡ በአላማጣ አድርጎ ነው ወደ ደሴ የተጓዘው። ወደዛ የሄደውም በረዳት ሹፌርነት ነው።
አንድ ለሊትም በደሴ ከተማ ካሳለፈ በኃላ ሰውነቱ ላይ ያለውን ንቅሳት የሚሸፍን ልብስ ገዝቶ ወደ ያዘው መኝታ ክፍል ሲገባ በደረሰ ጥቆማ ሊያዝ ችሏል። ከዛም መቐለ ፖሊስ አባላቱን በመላክ ተጠርጣሪው ወደ መቐለ እንዲመጣ አድርጓል።
የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የደሴ ህዝብ ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርቧል።
በከባድ የግድያ ተግባር የተጠረጠረው ግለሰብ አስመልክቶ በማህበራዊ የትስስር ገፆች የተሰራጨው አጭር ቪድዮ እንደሚያመለክተው ፥ ተጠርጣሪው ፍቅረኛውን በጬቤ ከገደላት በኋላ ተፀፅቶ ራሱ ለመግደል ሞኩሮ ሳይሳካለት መቅረቱ በአንደበቱ ይገልፃል።
የሟች ወጣት ሓበን የማነ አባት አቶ የማነ ንጉስ ልጃቸው በጭካኔ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ በአጭር ጊዜ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ለተባበሩ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
የፎቶ ባለቤት ፦ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን

#ትግራይ " ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ህጋዊ ያልሆነው ቡድን የሚመድባቸው አስተዳዳሪዎች እና የስራ ሃላፊዎች የሚያስተዳድሩት ሃብት የለም " ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። ጊዚያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው በፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በኩል ባወጣው መግለጫ ነው። " ህጋዊ ያልሆነው ቡድን " ሲል የገለፀው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ግልፅ የመንግስት ግልበጣ አካሂደዋል…
#ትግራይ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደተር በ4 ከተሞች የጠራቸው የህዝብ ስብሰባዎች በአንዱ ሲካሄድ በሦስቱ ተስተጓጉሏል።
ለስብሰባዎች መሰተጓጎል የፀጥታ ስጋት እንደ ምክንያት መቀመጡ አንዳንድ የከተሞቹ ነዋሪዎች ይገልፃሉ።
ባለፈው እሮብ ህዳር 4/2017 ዓ.ም የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተሾሙት ሰለሙን ትኩእ በዓዲግራት ከተማ ከዛላኣንበሳ ከተማ ተፈናቃዮች ለመወያየት እና በህዝብ የተመረጠ አዲስ አስተዳዳሪ ለመሾም የጠሩት ስብሰባ ፈተና የበዛበት ነበር።
ስብሰባ ከተከናወነበት አዳራሽ የወጡ የቪድዮ እና ድምፅ ፋይሎች እንደሚያሳዩት የማይናቅ ቁጥር ያላቸው እናቶች በስድብ ፣ ጩኸት እና ዋይታ ሰብሰባው እንዳይካይሄድ ሲከላከሉ ታይተዋል።
ቢሆንም የእናቶቹ ረብሻ በፀጥታ አካላት እንዲረገብ ሆኖ ወይይቱ ተካሂዶ የዛላምበሳ ከተማ አስተዳዳሪ በህዝብ ድምፅ እንዲመረጥ ሆኗል።
በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የጉሎመኸዳ ወረዳ ሦስተኛ ከተማ የሆነችው የዛላኣንበሳ ከተማ እስካሁን በኤርትራ ስራዊት ቁጥጥር ስር እንደምትገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የወረዳው አስተዳዳሪዎችን ዋቢ በማድረግ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
እሁድ ህዳር 8 /2017 ዓ/ም በትግራይ ምስራቃዊ እና ማእከላዊ ዞኖች በሚገኙ ውቕሮ ፣ ዓብዩ ዓዲ እና አክሱም ከተሞች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተጠሩ ህዝባዊ ስብሰባዎች መሰረዛቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል።
ስብሰዎቹ ከፀጥታ ስጋት ጋር በተገናኘ የተሰረዙ እንደሆነ የገለጹ አሉ።
ከዚህ ተቃራኒ አስተያያት የሰጡ ደግሞ " በተለይ በዓብዩ ዓዲ እና አክሱም ከተሞች ሊካሄዱ ታቅተደው የተሰተጓጎሉት ህዝባዊ ስብሰባዎች በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በዞኑ ያካሄደው የአስተዳደር የስልጣን ግልበጣ አካል ናቸው " ብለዋል።
ዛሬ ሊካሄድ የታሰበው ስብሰባ የተሰተጓጎለባቸው የውቕሮ ፣ የተምቤን ዓብዩ ዓዲ እና የአክሱም ከተሞች በአሁኑ ሰዓት ከወትሮ የተለየ የፀጥታ ስጋትና መደፍረስ እንደሌለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ወደ ከተሞቹ ስልክ በመደወል አረጋግጧል።

#Tigray
🔴 " ተኩስ ተከፍቶብኝ መኪናዬ ላይ ጉዳት ደርሷል " - አቶ ሰለሙን መዓሾ
🟠 " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " - አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት
🔵 " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " - ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ተሰምቷል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ የማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ባለፈው እሁድ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከስራ ባለደርቦቻቸው ጋር ከአክሱም ወደ መቐለ ሰጓዙ የግድያ ሙከራ እንደ ተቃጣባቸውና ከግድያ ሙከራው እንደተረፉ ተናግረዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ከአክሱም ወደ መቐለ ሲመለሱ ማይቅነጣል ፈላፍል በተባለ ቦታ ሲደርሱ መኪናቸው ላይ ተኩስ እንደተከፍተባቸው ገልጸዋል።
ለጊዜው እነማን እንደተኮሱባቸው ማንነታቸውን / የታጣቂዎችን ማንነት ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸው በተተኮሰባቸው ጥይቶች መኪናቸው ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል።
በጥይት የተመታው መኪናቸውን የሚያሳይ ፎቶም ይፋ አድርገዋል።
በመኪናው ውስጥ ከእሳቸው በተጨማሪ ጥበቃቸው እና የመኪናው ሹፌር ነበሩ።
ዋና አስተዳዳሪው የደረሰባቸው አካላዊ ጉዳት እንደሌለ አረጋግጠዋል።
እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የመግደል ሙከራ መደረጉ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኃላ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ማይቅነጣል ወረዳ ስልክ ቢደውልም ጉዳዩ የሚያረጋግጥ አካል አልተገኘም ነበር።
የዞኑ መቀመጫ ወደሆነችው አክሱም የሚገኝ ፓሊስ ማዘዣ ስልክ ቢደወልም የተጣራ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።
ይህ በእንዲህ እያለ የመግደል መከራ ተቃጥቶበታል የተባለው ቦታ የሚያስተዳድረው የማይ ቅነጣል ወረዳ " ጉዳዩ አልተፈፀመም " የሚል መግለጫ አውጥቷል።
የማይቅነጣል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ደግሞ ፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " ብለዋል።
ከዚህ ባለፈ " በአከባቢው አለ ጉዳዩ ፈፅሞታል " ተብሎ በማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ተደጋግሞ የተጠቀሰው የትግራይ ሰራዊት አርሚ 60 አዛዥ ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ እሳቸው የሚያዙት በፀሃፊዎቹ የተገለፀው ሰራዊት በአከባቢው እንደሌለ በመግለፅ " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " ሲሉ ተጠምደዋል።
ከአሁን በፊት በተለያዩ ጊዚያት መሰል የግደያ ሙከራዎች በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሹማመንት በየነ መኩሩ ፣ ነጋ ኣሰፋ ፣ ሰሎሙን ትኩእ እንዲሁም በአክሱም ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር መደረጋቸው የተነገረ ቢሆንም እስካሁን የድርጊቱ ፈፃሚዎች ተጣርተው የተወሰደ እርምጃ የለም።
#VOATigrigna #TikvahEthiopiaFamilyMekelle