TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
''...ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው'' - አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሶስተኛ የዘፈን አልበም ምርቃትና የአንደኛ ዓመት ሙት ዓመት መታሰቢያ ፕሮግራም ትላንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተው ነበር።

አርቲስቱ በህይወት እያለ ያዘጋጀው ሶስተኛው የዘፈን አልበም፤ 'ማል መሊሳ' በሚል ርዕስ ታትሞ ለአድማጮች ቀርቧል። የዘፈኑ 300 ሺህ ቅጂ በመጀመሪያ ዙር የተዘጋጀ ሲሆን አልበሙም 14 ዘፈኖችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

ትናንት ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ለአርቲስቱ ሙት ዓመት መታሰቢያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአርቲስቱ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ''ሀጫሉ በህይወት ቢለይም ትውስታውና ስራዎቹ ህያው ናቸው'' ብለዋል።

ከአርቲስቱ ህልፈት ቦኃላ ከቤተሰቡ ጎን ሆነው በተለያየ መልኩ ድጋፍ ላደረጉላቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም የአርቲስቱን ስም ባልተገባ መንገድ ለመጠቀም የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ወላጅ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ''ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው'' ብለዋል። ''የልጄ ገዳዮች ህግ ፊት ቀርበው ፍትህ እንዲያገኙ ሁሉም እንደየ ሀይማኖቱ ጸሎት ያድርግልኝ'' ሲሉም ጥ አቅርበዋል።

በመርሃ-ግበሩ የጥበብ ስራዎችን የሚያግዝና በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመ ፋውንዴሽን ተቋቁሟል።

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለፈው ዓመት ሰኔ 22 በአዲስ አበባ በሰው እጅ በጥይት ተመቶ መገደሉ አይረሳም።

#ENA

@tikvahethiopia
ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈረደባቸው።

የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል።

የ79 ዓመቱ ጃኮብ ዙማ በአገሪቱ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ፍ/ቤት መገኘት ሲኖርባቸው ባለመገኘታቸው ከህግ ተቋማት ትችቶች ሲቀርብባቸው ነበር።

ይህ እውነትን አፈላላጊ ኮሚሽን አቋቁሞ የዙማን ጉዳይ እየተመለከተ የነበረ ሲሆን ጃኮብ ዙማ ግን በዚህ ፍርድ ቤት አልቀርብም ሲሉ በይፋ ተቃውመው ነበር።

ዙማ በዚህ የኮሚሽኑ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ፍቃደኛነት ባለመሆናቸው ባለፈ ፈርድ ቤቱ ገለልተኛ አይደለም በማለታቸው ፍርድ ቤት ተዳፍረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

የዙማ ድርጊት ፍርድ ቤቱን መናቅና መድፈር በመሆኑ ሕግ አለማክበርን ያበረታታል፤ ሌሎችን ለህግ ተገዢ እንዳይሆኑ ያደርጋል የሚሉ ሀሳቦች ሲነሱ ቆይቷል።

የአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤትም በቀድሞው ፕሬዘዳንት ድርጊት ጃኮብ ዙማ የ15 ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል።

ዙማ እስሩ የተላለፈባቸው በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ቀጣይ የፍርድ ክርክር ላይ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አላከበሩም በሚል ነው።

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia
ችሎት !

በእነ አቶ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ጉዳዩን በዋነኛነት የያዘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የምስክር አቀራረብ ሒደት ላይ የግራና ቀኝ የህግ ክርክር በመመርመር ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ እንዲመሰክሩ ያዘጋጃቸው 16 ምስክሮች #በግልጽ_ችሎች እንዲመሰክሩ ወስኗል ።

የከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ውሳኔውን ያሳለፈው፤ ምስክሮች “ለደህንነታቸው” ሲባል በዝግ ችሎት ከመጋረጃ ጀርባ እንዲሰሙ በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን ጥያቄ በተከሳሾች እና በደጋፊዎቻቸው በኩል ለዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ምንም አይነት በቂ የሆነ በምክንያት እና በእውነት አስረጂ የሆኑ የደህንነት ስጋት አላገኘሁም ፤ በማለት ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ሕግ የመጋረጃ ጀርባ ምስክርነት ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ሐምሌ 8 እና 9 እንዲሁም ሐምሌ 14 ፣15 እና 16 በአምስት ቀናት ውስጥ እንደሚሰማ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።

መረጃው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ባልደራስ) ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ነው።

@tikvahethiopia
#Update

ከሳዑዲ አረቢያ 1 ሺህ 777 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ::

ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን የማስወጣት የተጠናከረ ዘመቻ እያደረገች መሆኑ ይታወቃል::

በዚህ መሰረትም በትናትናው ዕለት 1 ሺህ 777 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል::

@tikvahethiopia
የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች !

የፊታችን እሁድ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም "መንገድ ለሰው” ከተሽከረካሪ ነፃ መንገዶች ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት በእለቱ ፕሮግራሙ የሚካሄድበት እና ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው ፡-

1. ከልደታ ኮንደሚኒያም ጌጃ ሰፈር፣
2. ቤተል ወይራ ሰፈር ፊት ለፊት፣
3. ቤተል ከወረዳ 5 እስከ ታክሲ ተራ፣
4. ቤተል ከኪዳነምህረት እስከ ቤተል አደባባይ፣
5. ከሜክሲኮ አደባባይ በሸበሌ እስከ ብሄራዊ ትያትር፣
6. ከስድስት ኪሎ እስከ ሚኒሊክ ፣
7. በስፔን ኤምባሲ መነን ት/ቤት፣
8. መካኒሳ ከአምጎ ካፌ እስከ ቆሬ አደባባይ፣
9. ገላን ኮንደሚኒየም አካባቢ፣
10. ከለቡ ጀሞ፣
11. ከፊጋ ሳሚት መብራት፣
12. ሳሚት ኮንደሚኒየም፣
13. የካ አባዶ፣
14. ቀይ ባህር ኮንደሚኒየም፣
15. ጎተራ ኮንደሚኒየም

#AMN

@tikvahethiopia
#BritishEmbassy

ብሪታንያ የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይ ክልል ውስጥ የአንድ ወገን/የተናጠል በሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ማድረጉን በደስታ እንቀበላለን ብላለች::

ለዚህም ሁሉም ወገኖች ዕውቅና እንዲሰጡ ፣ ግጭት ለማቆም እና ሕይወት አድን ሰብዓዊ ዕርዳታ በክልሉ በፍጥነት እንዲያደርስ ጠይቃለች::

ብሪታኒያ ይህን ያሳወቀችው እዚህ አዲስ አበባ በሚገኙው ኤምባሲዋ በኩል ነው::

ትላንት ምሽት የኢትዮጵያ ፌዴራሉ መንግስት ትግራይ ክልል ውስጥ የተናጠል በሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ማወጁ ይታወቃል::

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከጥቂት ደቂቃ በኃላ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን የሚከታተሉ የቲክቫህ አባላት በቦታው ይገኛሉ።

መግለጫውን በቀጥታ በ Voice Chat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

@tikvahethiopia
Live stream started
#LIVE

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

ከላይ ባለው Voice Chat 'Join' በማለት በቀጥታ ማድመጥ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
#Live

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተረጋገጡ የምርጫ ክልሎችን ውጤት እያሳወቀ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ከላይ በ Voice Chat አድምጡ።

@tikvahethiopia
#Update

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከ942 የምርጫ ክልሎች መካከል እስካሁን የ618ቱ ውጤት ወደ ማዕከል መድረሱን አስታውቀዋል።

160 ምርጫ ክልሎች ላይ የተለያዩ ፓርቲዎች የቅሬታና አቤቱታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡

ከአቤቱታዎቹ ከፊሉ በተደራጀ መልኩ ስላልቀረቡ ተስተካክሎ እንዲቀርብ ለፓርቲዎች ጥሪ ተደርጓል ብለዋል።

@tikvahethiopia
Live stream finished (1 hour)
#Tigray

የትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

- የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት በትላንትናው ዕለት የተናጠል በሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ካወጀ በኃላ በተለያዩ ሀገራት የተሰጡ አስተያየቶች።

- UNICEF ያሰማው ክስ።

- በኔትዎርክ መቋረጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወላጆች እና ትግራይ ክልል ውስጥ ቤተስብ ያላቸው ዜጎች ጭንቀት።

-የአሜሪካ ትግራይን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች እንደምትገኝ መግለጿ።

- የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰን ስለ ትግራይ ጉዳይ የሰጡት አስተያየት።

- የህወሓት ኃይሎች ሽረን መያዛቸው፣ የኤርትራ ሰራዊት ከሽረ መውጣቱ።

- የህወሓት ኃይሎች በሰጧቸው አስተያየቶች ላይ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ያወጣው ጠንከር ያለመግለጫ።

- የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ስለቀረበለት ጥሪ።

.
.
.
ሌሎችም ጉዳዮች!

(ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የተዘጋጁ)

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tigray-Update-06-29-2