TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ! የመስቀል አደባባይና እስከ ማዘጋጃ ቤት ድረስ የተከናወነው የመንገድ ግንባታ ምረቃ ምክንያት በማድረግ ሰኔ 6/2013 የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦ - ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የላይኛው አደባባይ - ፒያሳ ጣሊያን ሰፈር መግቢያ - ሱማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው አደባባይ -…
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል።

2.6 ቢሊዮን ብር ወጥቶበት የተገነባው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ነገ እንደሚመረቅ ይጠበቃል።

ፕሮጀክቱ እስከ ማዘጋጃ ቤት የሚዘልቅ የመንገድ ግንባታን ያካተተ ነው።

በተለይ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በተጀመረበት ወቅት በአንዳንድ አካላት ከፍተኛ የሆነ ቅራኔ እና ተቃውሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርቦ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

ከሰሞኑ በተሰራጨው የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ "ቃልን በተግባር" በተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ላይ ጠ/ሚስትሩ ይህንን ጉዳይ አንስተውት ነበር።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ ስራው ሲጀመር ቅራኔዎች እና ተቃውሞዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። አሁን ላይ ስራው ተሰርቶ መጠናቀቁን በመግለፅ ሁሉም ዜጋ ቦታውን የመጠበቅ ፣የማሳመር፣ የማስዋብ፣ ከዚህም የተሻለ ቦታ የመስራት ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

መስቀል አደባባይ ፥ የህዝብ በዓላት ፣ የሙዚቃ ኮንሰርት ፣ ሃይማኖታዊ በዓላት፣ የመንግስት ፕሮግራሞች፣ የተለያዩ አይነት ትርዒቶች ሊታዩበት በሚያስችል መልኩ የተሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

እስከ 1 ሚሊዮን ሰዎችን ማስተናገድ የሚችልበት አቅም እንዲኖረው መደረጉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የመስቀል አደባባይ ፓርኪንግ እጅግ ሰፊ እና ለአይንም ማራኪ ሆኖ የተሰራ እስከ 1450 ገደማ መኪና መያዝ የሚችል መሆኑን ገልፀዋል።

Photo Credit : Tikvah Family

@tikvahethiopia
ለምርጫ ቅስቀሳው የቀረችው የመጨረሻዋ እሁድ!

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከየካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅቶች ነበሩ።

ግንቦት 28 ይደረጋል በተባለው ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳው የሚያበቃው በግንቦት 23 ነበር። ሆኖም ምርጫው ወደ ሰኔ 14 መዛወሩን ተከትሎ የመርጫ ቅስቀሳውም አብሮ መራዘሙ ይታወሳል።

ብዙዎች የምርጫ ቅስቀሳዎቹ በተለይ በጅምሩ ጊዜያት ተቀዛቅዞ እንደነበር ይጠቅሳሉ።

አንዳንድ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ያላቸውን አማራጭ ኃሳብ ባገኙት አጋጣሚ በአግባቡ አለማድረሳቸው ይገለፃል።

በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት በአንዳንድ አከባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው፤ አባሎቻቸውም የታሰሩባቸው ስለመኖሩ ከፖርቲዎች የሚቀርብ ክስ ነው።

በአንጻሩ በዚህ ወቅት ምርጫው በበርካቶች ዘንድ ትኩረት ማግኘቱ እሙን ነው። ከአላስፈላጊ ቃላት ልውውጥ ውጪ ዜጎች አማራጭ ኃሳቦችን እንዲመለከቱ፤ እንዲያወዳድሩና እንንዲመርጡ ቀላል የማይባሉ ሥራዎች ተሰርተዋል።

የምርጫ ቅስቀሳው ከመጭው አርብ በፊት ተጠናቆ ምንም ቅስቀሳ ወደማይካሄድበት ወደ የጥሞና ጊዜ ለመግባት የዛሬዋ እሁድና ጥቂት ቀናት ቀርተዋል።

@tikvahethiopia
#Afar

በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን አማካኝነት ግንባታው ተጀምሮ በመሃል ግንባታው ለረጅም አመታት እንዲቋረጥ ተደርጎ የቆየው ግዙፉ የኢስላማዊ ማእከል የተቋረጠውን ግንባታ ዳግም ለማስጀምር እና ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እንዲቻል በዛሬው ዕለት በአሳይታ ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በአሳይታ ከተማ ለሱልጣን አሊ ሚራህ መድረሳ ማስቀጠያ ዝግጅት ፦
- የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፣
- የፌዴራልና የክልል መጅሊስ አመራሮች ፣
- የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

መረጃው ከሀሩን ሚድያ እና ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (#ICRC) ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ በላይላይ ማይጨው ወረዳ 5 ቀበሌዎች ለሚገኙ ለ5,251 ቤተሰብ ፣ እንዲሁም በዓድዋ ወረዳ 4 ቀበሌዎች ለሚገኙ 6,907 ቤተሰብ የዘር እና ማዳበሪያ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ ወዳቋረጡት እርሻቸው እንዲመለሱ ያግዛቸዋል ተብሎ ታምኗል።

@tikvahethiopia
#UNHCR #Ethiopia #UN

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጋር እደተወያዩ በትዊተር ገፃቸው አሳወቁ።

ውይይቱ የነበረው ስደተኞችን ከመጠበቅ ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለስደተኞች እየተሰጠ ስለሚገኘው የኮቪድ 19 ምላሽን በተመለከተ መሆኑን በመልዕክታቸው ገልፀዋል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፥ ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለመከላከል ለረጂም ጊዜ የሚዘልቅ ዝግጁነት እንዳላት ለፊሊፖ ግራንዴ ነግረዋቸዋል።

@tikvahethiopia
"...የተለያዩ ሰበቦችን በመደርደር የዞኑን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማወክ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል" - የሰሜን ሸዋ ዞን

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች ጥቂት ግለሰቦች ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 11/2013 ዓ/ም የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ በማለት በድብቅ የተለያዩ ደብዳቤዎችን በመበተን ላይ መጠመዳቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ገለፀ።

ግለሰቦቹ አድማውን ፥" አጣየና አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም ስራ እየተሰራ አይደለም" በሚል እንደተጠሩት ነው የተገለፀው።

የዞኑ አስተዳደር ፥ መንግስት በአጣየ እና በአካባቢውን መልሶ ለማቋቋምና ለመገንባት በዞኑ አስተዳዳሪ የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አስታውሷል።

የክልሉ መንግስትም አካባቢውን በዘመናዊ መልኩ መልሶ ለመገንባት የተሻሉ ነገሮችን ለመስራት በትኩረት እየሰራ ይገኛል ለዚህም የተለያዩ ግብአቶች እየተማሉ ነው ብሏል።

ነገር ግን ይላል የዞኑ አስተዳደር ፥ "የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላም መሆንና የክልሉ ሰላም መሆን የእግር እሳት የሆነባቸው ፣ በደም የሚነግዱ እና ደም ያሰከራቸው ፣ የዞኑን ህዝብ በኢኮኖሚው እንዲሽመደመድ አልመው የሚሰሩ ጥቂት ግለሰቦች አጣየና አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም ስራ እየተሰራ አይደለም በሚል ከ9 እስከ 11/10/2013ዓ.ም የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ በማለት በድብቅ የተለያዩ ደብዳቤዎችን በመበተን ላይ ተጠምደዋል" ሲል ገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ፥ የተለያዩ ሰበቦችን በመደርደር የዞኑን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማወክ የተለያየዩ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ጥቂት ግለሰቦች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ዛሬ ባሰራጨው ፅሁፍ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines #OpenUniversity

ትላንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን አካዳሚ በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ኦፕን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን የአየር መንገዱን የማኔጅመንት አባላት አስመርቋል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተገኝተው ለተመራቂዎቹ የ "እንኳን ደስ አላችሁ" መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።

ያንብቡ : https://bit.ly/3wnTdUQ

@tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 22 ተማሪዎቹን ያስመርቃል።

የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ለ @tikvahuniversity እንዳሳወቀው በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠኛቸውን ተማሪዎቹን ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ/ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ 3ኛ ዲግሪ በመደበኛ እና የማታ መርሀ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አህመድ መሀመድ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ትምህርት በመጠናቀቁ ነባር ተማሪዎች (ከተመራቂዎች በስተቀር) ሰኔ 11 እና 12/2013 ዓ.ም እረፍት እንደሚወጡ ኃላፊው ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 25 እስከ 30/2013 ዓ.ም ጥሪ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

#CARD #TIKVAH

@tikvahuniversity
CECOE-2021-Voter-Registration-Observation-Report.pdf
238.2 KB
#CECOE

ከ175 በላይ በምርጫ ዙርያ የተለያዩ ስራዎችን የሚሰሩ አገር በቀል የሲቪል ማህበራትን ያካተተው የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (CECOE) ከሚያዝያ 2 ቀን እስከ ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመራጮች ምዝገባን ታዝቦ ሪፖርቱን አቅርቧል።

ህብረቱ ስልጠና ሰጥቶ ያሰማራቸው 117 ታዛቢዎች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውረው 1,190 የምርጫ ምዝገባ ጣቢያዎች ላይ የታዘቡ ሲሆን ሪፖርቱ በእነዚህ ጣቢያዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጿል።

ሪፖርቱ ከ45,000 በላይ የመራጮች ምዝገባ ጣቢያዎችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከመክፈት አንስቶ ወደ 135,000 የሚጠጉ አስፈፃሚዎችን አሰልጥኖ እስከማሰማራት ድረስ ቦርዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰራው ስራ በመልካም ጐኑ የሚጠቀስ ነው ብሏል።

''ምንም እንኳን የመራጮች ምዝገባን የማደራጀትና የማካሄድ ተግባርን ውስብስብነት ህብረቱ ቢረዳም በምዝገባ ሂደቱ ወቅት የበርካታ ኢትዮጵያውያንን የመምረጥ መብት ሊያጣብቡ የሚችሉ ችግሮች መከሰታቸውን መካድ ግን አይቻልም'' ሲል ሪፖርቱ ይጠቅሳል።

* ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Tigray

"...የሚደርሱን ሪፖርቶች በምግብ እጥረት የተጎዱ የህፃናት ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ያመላክታሉ" - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ደረጃ ምደባ (Integrated Food Security Phase Classification) በቅርቡ ባወጣው ረፖርት እንደተጠቀሰው በትግራይ ክልል ያለው አሳዛኝ ሰብዓዊ ቀውስ ከፍተኛ የድንገተኛ አደጋ ስጋት ላይ መድረሱ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ዛሬ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ከክልሉ ከሚገኙ የጤና ተቋማት ደረሱኝ ባላቸው ሪፖርቶች በምግብ እጥረት የተጎዱ የህፃናት ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ያመላክታሉ ብሏል።

ኮሚሽኑ የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት በአፋጣኝ የማረጋገጥ አስፈላጊነትን እና በአብዛኛው ተደራሽ በሆኑ አካባቢዎች ጭምር ያለው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እጥረት ለሟሟላት ተገቢ ጥረት መደረግ እንዳለበት በአፅንዎት አሳስቧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ያደረጋቸውን ጥሪዎች አስታውሰው "ሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ መቆየት የማይችለው አስቸኳይ ጉዳይ ግን አስፈላጊውን አቅምና ሀብት ሁሉ በማሰባሰብ የሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽነት ማረጋገጥ እና ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ ማድረግ እንደሆነ" ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በዋግኽምራና አካባቢዋ ከትላንት ጀምሮ መብራት ተቋርጧል። በዋግኽምራና አካባቢዋ ከትላንት ግንቦት 21/2013 ዓ.ም ምሳ ሰዓት አካባቢ ጀምሮ የመብራት ሀይል አገልግሎት መቋረጡን ተሰምቷል። መብራት ሀይል አገልግሎት የተቋረጠበት ምክንያት ? የመብራት ኃይል የተቋረጠበት ምክንያት በተመለከተ የ ዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ስለሺ ወርቁና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰቆጣ አገልግሎት…
#Update

ለሁለት ሳምንት በዋግ ኽምራ ዞን የተቋረጠው ኤሌክትሪክ መልሶ ተገናኝቷል።

በምሰሶዎች ላይ በተፈፀመ ስርቆት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ተቋርጦ የቆየው የዋግ ኽምራ ዞን ኤሌክትሪክ የጥገና ስራ ተጠናቆ አካባቢው ኤሌክትሪክ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ከሰዓት አሳውቋል።

በአካባቢው ከግንቦት 21 ቀን 2013 ፣ ጀምሮ ኤሌክትሪክ ተቋርጦ የቆየው በ3 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ስርቆት በመፈፀሙና በመውደቃቸው ነበር።

ወደስፍራው ለጥገና የተንቀሳቀሰው ቡድን የተሰረቁትንና የወደቁትን የብረት ምሰሶዎች አካል በአዲስ በመተካት መልሶ ለመትከል ጊዜ ስለሚወስድ በጊዜያዊነት በእንጨት ምሰሶዎች በመተካት አካባቢው ኤሌክትሪክ እንዲያገኝ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገልጿል።

የጥገና ቡድኑ አባላት ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ አስቸጋሪ በሆነ መልክዓ - ምድር በእግር በመጓዝና ከ36 ሠዓት በላይ ያለምግብ በመስራት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በማሳካት አካባቢው ኤሌክትሪክ እንዲያገኝ በማድረጋቸው ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን አማካኝነት ግንባታው ተጀምሮ በመሃል ግንባታው ለረጅም አመታት እንዲቋረጥ ተደርጎ የቆየው ግዙፉ የኢስላማዊ ማእከል የተቋረጠውን ግንባታ ዳግም ለማስጀምር እና ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እንዲቻል በዛሬው ዕለት በአሳይታ ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል። በአሳይታ ከተማ ለሱልጣን አሊ ሚራህ መድረሳ ማስቀጠያ ዝግጅት ፦ - የአፋር…
የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ ፥ ለሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ጥሪ አቀረቡ።

በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ አማካኝነት ለአፋር ህዝብ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ታላቁን የሱልጣን አሊ ሚራህ ኢስላማዊ ማዕከል ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባት ወደ ስራ ተገብቶ የነበረ ቢሆንም በ "ፖለቲካ አሻጥር" ምክንያት ይህ ፕሮጀክት ግንባታው ከሁለት አስርት አመታት በላይ ቆሟል።

የግዙፉን ማዕከል ሙሉ ወጪ ሸፍነው ለማስገንባት ስራውን ያስጀመሩት እውቁ የሃገራችን ባለሃብት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ብዙ ገንዘባቸውን ውጪ ካደረጉ ቡኃላ በፖለቲካ አሻጥር ግንባታው እንዲቆም እና እሳቸውም ፕሮጀክቱን ፋይናንስ ማድረግ እንዲያቆሙ በመግፋት ግንባታው እንዲቆም ተደርጓል።

ዛሬ በአሳይታ እየተካሄደ በነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አወል አርባ ለሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ ፕሮጀክት በዋናነት ያስጀመሩት እና ብዙ የለፉለት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ እንደመሆናቸው አሁንም ተቋም ተጠናቆ እውን ይሆን ዘንድ ትልቁን ድርሻ ቅድሚያ ለእሳቸው እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

በክልሉ መንግስት ስምም ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ዳግም ተመልሰው ሃገራቸው እንዲያለሙ በይፋ ጥሪ አቅርበውላቸዋል።

ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ይህን ፕሮጀክት እንዳስጀመሩትና ብዙ እንደደከሙበት ሁሉ አሁን ላይ እንደ አዲስ ግንባታው ተጠናቆ ምኞታቸው ተሳክቶ ያዩት ዘንድ እሳቸውም የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

በተጨማሪ ፥ "ለእናት ሃገራቸው እንዲያበቃቸው፣ ያሉበትን ሁኔታ አላህ እንዲያስተካክላቸው በዱዓ ልናግዛቸው ይገባል" ብለዋል።

መረጃው ከኡስታዝ አቡበርክ አህመድ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia