TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ ጥዋት የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ የጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩርሱላ ቮን ደር ላየን ማድረሳቸው መገለፁ ይታወሳል። የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን ስለማድረሳቸው ተሰምቷል። ደብዳቤውን…
#Update

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን መልዕክትን ለተለያዩ ሀገራት /ተቋማት እያደረሱ መሆኑን በተለያዩ መረጃዎች ተለዋውጠናል።

ለማስታወስ ያህል ፦

- የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን አድረሳዋል።

- የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን የተላከ መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት የስራ ሃላፊዎች አድርሰዋል።

- የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አድርሰዋል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የተመራ ልዑክ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልእክት ለፈረንሳይ ፕሬዚደንት አድርሷል።

መልእክቱን የተቀበሉት የፈረንሳይ ፕሬዚደንት የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ አማካሪ ሚንስትር ፍራንክ ፓሪስ ናቸው።

ሚኒስትሯ መልዕክቱን ባስተላለፉበት ወቅት በሀገሪቱ ውሥጥ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ ከእሳቤው ጀምሮ ሂደቱና ውጤቶቹ ላይ ያተኮረ ገለጻ አድርገዋል።

በትግራይ ስላሉ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የመልሶ ማቋቋም ተግባራት ላይ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸው ታውቋል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,405 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 274,028 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 2 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,237 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,936,566 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ! የመስቀል አደባባይና እስከ ማዘጋጃ ቤት ድረስ የተከናወነው የመንገድ ግንባታ ምረቃ ምክንያት በማድረግ ሰኔ 6/2013 የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። የምረቃ ስነ ስርዓቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦ - ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የላይኛው አደባባይ - ፒያሳ ጣሊያን ሰፈር መግቢያ - ሱማሌ ተራ አካባቢ የሚገኘው አደባባይ -…
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል።

2.6 ቢሊዮን ብር ወጥቶበት የተገነባው የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ነገ እንደሚመረቅ ይጠበቃል።

ፕሮጀክቱ እስከ ማዘጋጃ ቤት የሚዘልቅ የመንገድ ግንባታን ያካተተ ነው።

በተለይ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት በተጀመረበት ወቅት በአንዳንድ አካላት ከፍተኛ የሆነ ቅራኔ እና ተቃውሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርቦ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

ከሰሞኑ በተሰራጨው የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ "ቃልን በተግባር" በተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ላይ ጠ/ሚስትሩ ይህንን ጉዳይ አንስተውት ነበር።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ ስራው ሲጀመር ቅራኔዎች እና ተቃውሞዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። አሁን ላይ ስራው ተሰርቶ መጠናቀቁን በመግለፅ ሁሉም ዜጋ ቦታውን የመጠበቅ ፣የማሳመር፣ የማስዋብ፣ ከዚህም የተሻለ ቦታ የመስራት ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

መስቀል አደባባይ ፥ የህዝብ በዓላት ፣ የሙዚቃ ኮንሰርት ፣ ሃይማኖታዊ በዓላት፣ የመንግስት ፕሮግራሞች፣ የተለያዩ አይነት ትርዒቶች ሊታዩበት በሚያስችል መልኩ የተሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

እስከ 1 ሚሊዮን ሰዎችን ማስተናገድ የሚችልበት አቅም እንዲኖረው መደረጉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የመስቀል አደባባይ ፓርኪንግ እጅግ ሰፊ እና ለአይንም ማራኪ ሆኖ የተሰራ እስከ 1450 ገደማ መኪና መያዝ የሚችል መሆኑን ገልፀዋል።

Photo Credit : Tikvah Family

@tikvahethiopia
ለምርጫ ቅስቀሳው የቀረችው የመጨረሻዋ እሁድ!

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከየካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅቶች ነበሩ።

ግንቦት 28 ይደረጋል በተባለው ምርጫ የምርጫ ቅስቀሳው የሚያበቃው በግንቦት 23 ነበር። ሆኖም ምርጫው ወደ ሰኔ 14 መዛወሩን ተከትሎ የመርጫ ቅስቀሳውም አብሮ መራዘሙ ይታወሳል።

ብዙዎች የምርጫ ቅስቀሳዎቹ በተለይ በጅምሩ ጊዜያት ተቀዛቅዞ እንደነበር ይጠቅሳሉ።

አንዳንድ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ያላቸውን አማራጭ ኃሳብ ባገኙት አጋጣሚ በአግባቡ አለማድረሳቸው ይገለፃል።

በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት በአንዳንድ አከባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው፤ አባሎቻቸውም የታሰሩባቸው ስለመኖሩ ከፖርቲዎች የሚቀርብ ክስ ነው።

በአንጻሩ በዚህ ወቅት ምርጫው በበርካቶች ዘንድ ትኩረት ማግኘቱ እሙን ነው። ከአላስፈላጊ ቃላት ልውውጥ ውጪ ዜጎች አማራጭ ኃሳቦችን እንዲመለከቱ፤ እንዲያወዳድሩና እንንዲመርጡ ቀላል የማይባሉ ሥራዎች ተሰርተዋል።

የምርጫ ቅስቀሳው ከመጭው አርብ በፊት ተጠናቆ ምንም ቅስቀሳ ወደማይካሄድበት ወደ የጥሞና ጊዜ ለመግባት የዛሬዋ እሁድና ጥቂት ቀናት ቀርተዋል።

@tikvahethiopia
#Afar

በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲን አማካኝነት ግንባታው ተጀምሮ በመሃል ግንባታው ለረጅም አመታት እንዲቋረጥ ተደርጎ የቆየው ግዙፉ የኢስላማዊ ማእከል የተቋረጠውን ግንባታ ዳግም ለማስጀምር እና ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እንዲቻል በዛሬው ዕለት በአሳይታ ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በአሳይታ ከተማ ለሱልጣን አሊ ሚራህ መድረሳ ማስቀጠያ ዝግጅት ፦
- የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፣
- የፌዴራልና የክልል መጅሊስ አመራሮች ፣
- የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

መረጃው ከሀሩን ሚድያ እና ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (#ICRC) ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ በላይላይ ማይጨው ወረዳ 5 ቀበሌዎች ለሚገኙ ለ5,251 ቤተሰብ ፣ እንዲሁም በዓድዋ ወረዳ 4 ቀበሌዎች ለሚገኙ 6,907 ቤተሰብ የዘር እና ማዳበሪያ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ ወዳቋረጡት እርሻቸው እንዲመለሱ ያግዛቸዋል ተብሎ ታምኗል።

@tikvahethiopia
#UNHCR #Ethiopia #UN

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጋር እደተወያዩ በትዊተር ገፃቸው አሳወቁ።

ውይይቱ የነበረው ስደተኞችን ከመጠበቅ ፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለስደተኞች እየተሰጠ ስለሚገኘው የኮቪድ 19 ምላሽን በተመለከተ መሆኑን በመልዕክታቸው ገልፀዋል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፥ ኢትዮጵያ የስደተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለመከላከል ለረጂም ጊዜ የሚዘልቅ ዝግጁነት እንዳላት ለፊሊፖ ግራንዴ ነግረዋቸዋል።

@tikvahethiopia
"...የተለያዩ ሰበቦችን በመደርደር የዞኑን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማወክ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል" - የሰሜን ሸዋ ዞን

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች ጥቂት ግለሰቦች ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 11/2013 ዓ/ም የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ በማለት በድብቅ የተለያዩ ደብዳቤዎችን በመበተን ላይ መጠመዳቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ገለፀ።

ግለሰቦቹ አድማውን ፥" አጣየና አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም ስራ እየተሰራ አይደለም" በሚል እንደተጠሩት ነው የተገለፀው።

የዞኑ አስተዳደር ፥ መንግስት በአጣየ እና በአካባቢውን መልሶ ለማቋቋምና ለመገንባት በዞኑ አስተዳዳሪ የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አስታውሷል።

የክልሉ መንግስትም አካባቢውን በዘመናዊ መልኩ መልሶ ለመገንባት የተሻሉ ነገሮችን ለመስራት በትኩረት እየሰራ ይገኛል ለዚህም የተለያዩ ግብአቶች እየተማሉ ነው ብሏል።

ነገር ግን ይላል የዞኑ አስተዳደር ፥ "የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላም መሆንና የክልሉ ሰላም መሆን የእግር እሳት የሆነባቸው ፣ በደም የሚነግዱ እና ደም ያሰከራቸው ፣ የዞኑን ህዝብ በኢኮኖሚው እንዲሽመደመድ አልመው የሚሰሩ ጥቂት ግለሰቦች አጣየና አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም ስራ እየተሰራ አይደለም በሚል ከ9 እስከ 11/10/2013ዓ.ም የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ በማለት በድብቅ የተለያዩ ደብዳቤዎችን በመበተን ላይ ተጠምደዋል" ሲል ገልጿል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ፥ የተለያዩ ሰበቦችን በመደርደር የዞኑን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማወክ የተለያየዩ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ጥቂት ግለሰቦች ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ዛሬ ባሰራጨው ፅሁፍ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines #OpenUniversity

ትላንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሽን አካዳሚ በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ኦፕን ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን የአየር መንገዱን የማኔጅመንት አባላት አስመርቋል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተገኝተው ለተመራቂዎቹ የ "እንኳን ደስ አላችሁ" መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።

ያንብቡ : https://bit.ly/3wnTdUQ

@tikvahethiopia