TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EskinderNega

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የፓርቲው ፕሬዘዳንት እና እጩ የሆኑት እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ውስጥ ታስረው የሚገኙበት ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረበት አመልከተ።

የአቶ እስክንድር ነጋ አያያዝ ሲከታተል መቆየቱን የገለፀው ባልደራስ ፥ በተለይ ከግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ቀድሞ ታስረውበት ከነበረው "ዋይታ" ተብሎ ከሚጠራው ዞን በደረሰባቸው የሰብዓዊ በደል ምክንያት 8ኛ ዞን ተብሎ ወደሚጠራው ቦታ እንዲዘዋወሩ ተደርጓል ብሏል።

አቶ እስክንድር አሁን ታስረውበት ባለበት ቦታ በእስረኞች የደህንነታቸው ሁኔታ፣ አደጋ ላይ እንደወደቀ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ማረሚያ ቤቱ ድረስ በመሄድ ለማረጋገጥ እንደቻሉ ፓርቲው ገልጿል።

አቶ እስክንድር እየገጠማቸው ያለውን የደህንነት አደጋ፣ ማረሚያ ቤቱ ሆነ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ እያወቁ መፍትሄ ለመስጠት ባለመፈለጋቸው አዝኛለሁ ብሏል ባልደራስ።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Balderas-06-09

@tikvahethiopia