TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#updateሀዋሳ የኢህአዴግ ጉባኤ⬇️

-የኢሕአዴግ ጉባዔ ለውጡን #በአዎንታዊነት የገመገመ መሆኑ ተገለጸ።

- መፈጸም የማይችሉ አመራሮችም ሆኑ የግንባሩ አባል ፓርቲዎች መቀጠል #የለባቸውም የሚል #ቀይ_መስመር ተለይቷል

▪️የኢሕአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የጥልቅ ተሃድሶ ያለበትን ደረጃና የመጀመሪያ ደረጃ ትሩፋቶችን በማድነቅ እየገመገመ መሆኑንና ቀጣይ የለውጡ አቅጣጫን በተመለከተ በመወያየት ላይ እንደሚገኝ የጉባዔው ቃል አቀባይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ፡፡

በተለይም ኢሕአዴግ የአመራር ለውጥ ከማድረጉ በፊት ራሱ ግንባሩና አገሪቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደነበሩ፣ በአገሪቱም #የመበተን አደጋ ተጋርጦ እንደነበር መገምገሙን አክለዋል፡፡
የአመራር ለውጥ ከተደረገ በኋላ ግን ብዝሃነትን፣ #ኢትዮጵያዊነትንና በማኅበረሰቡ ላይ ተስፋን የሚጭሩ የፖለቲካ ተግባራት መፈጸማቸውን፣ ይህም በአገሪቱ የፖለቲካ መረጋጋት መፍጠሩ በጉባዔው እንደተገመገመ ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ጉዳይ ላይ ግምገማው እንደቀጠለ የወደፊት የፖለቲካ ሪፎርሙ አቅጣጫ ተቋማዊ መልክ እንዲይዝና በግምባሩ አባል ድርጅቶችና አመራሮች መካከል መልካም ግንኙነትና የዓላማ አንድነት መፍጠር የጸጸት ዶሴውን መዝጋት፣ በይቅርታና ቅን ልቦና ወደፊት መሄድ እንደሚገባ መገምገሙንና ውይይቱም መቀጠሉን ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡

በመደመር ፍልስፍና ላይ ግልጽነት የፈጠረ ውይይት መደረጉንና የማይታለፉ ቀይ መስመሮችን በተመለከተ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከቀይ መስመሮቹ መካከል መፈጸም የማይችሉ አመራሮችም ሆኑ የግንባሩ አባል ፓርቲዎች እንደማይቀጥሉ፣ ሥርዓት
አልበኝነትን አለመታገስ እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡ ቃል አቀባዩ በጉባዔው ላይ የተነሱ የልዩነት ሐሳቦችን ሳይጠቅሱ ያለፉ ሲሆን፣ ከጋዜጠኞች ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎችን #እንደማይቀበሉ በመግለጽ መግለጫውን አጠናቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DrHagosGodefay

በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሶስቱ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ነግረውናል።

ሁለቱ (2) ከማይካድራና ሰቲት ሁመራ ለይቶ ማቆያ ፣ አንድ (1) ሰው ከመቐለ ላይቶ ማቆያ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አሳውቀውናል።

ዛሬ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሶስቱም (3) ሰዎች ምንም አይነት ምልክት #የለባቸውም

ዶክተር ሓጎስ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አሁንም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ፤ ዜጎችም በመንግስት የሚስጡ መመሪያዎችንና በጤና ባለሞያዎች የሚተላለፉ ምክሮችን ሳይዘናጉ እንዲተገብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia