TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አማራ🕊ትግራይ!

የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በሁለቱ ክልሎች #ሰላም ዙሪያ ተወያዩ።

በሁለቱ ክልሎች ሰላም ላይ ያተኮረው ውይይት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ መካሄዱን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ #አልማዝ_መኮንን፥ በየትኛው የታሪክ አጋጣሚ ህዝብ ከህዝብ #ተጣልቶ አያውቅም ብለዋል።

የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ህዝቦች ለዘመናት የኖረ #አብሮነት ያላቸው ተመሳሳይ ባህል የሚጋሩና የተዋለዱ ህዝቦች ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰለም ለማሰፈን ችግሮችን ተሸክሞ የሚቆዝም ሰው ሳይሆን የይቅርታ ልብ ይዞ ህዝብን የሚያቀራርብ የሀገር ሽማግሌና የሀይማኖት አባቶች ያስፈልጉናልም ብለዋል።

ሚኒስቴር ዴኤታዋ የሀይማኖት አባቶች ከፖለቲካ ነፃ በመሆን መንግስት ሲሳሳት አደብ ግዛ ሊሉት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የሁለቱ ክልሎች የሀገር ሽማግሌዎች ሰፊ የሃሳብ ለውውጥ ካደረጉ በኋላ እርስ በእርሳቸው በመተቃቀፍ በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና ወንድማማችነታቸውን ለማጠናከር ቃል በመግባታ ተለያይተዋል።

በውይይቱ ላይ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፣ ፓስተር ዳንኤልና እና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
 
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራና ቅማንት ሕዝቦችን #አብሮነት ለማጠናከር የሚያስችል የእርቀ-ሰላም ኮንፈረንስ በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንደ ውሃ ከተማ እተካሄደ ነው። በኮንፈረንሱ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ወጣቶች እየተሳተፉ መሆኑን ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ኮንፈረንሱ በአካባቢው በሁለቱ ህዝቦች መካከል ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ለመፍታትና አብሮነትታቸውን ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬ❤️

"ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ከቶ አይዘነጋም ድሬ ላይ መሆኑ! "

በድሬዳዋ ሁሌም ቢሆን የነዋሪዎቿ #ፍቅር#አንድነት እና #አብሮነት ብሎም አሁናዊ የከተማዋ ሰላም ለሌሎች ምሳሌና ማሳያ ነው መባሉ በምክንያት ነው።

በጥምቀት ከተራ በዓል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድምና እህቶች በቀፊራ ፣ በለገሀሬ ፣ ኮኔል ፣ በድልድይ መጋላ እና በሌሎችም አካባቢዎች ለህዝበ ምእመኑ ውሀ፣ ኩኪሲችና ጣፍጭ ምግቦችን በማቅረብ እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ ወንድማዊና ቤተሰባዊ ፍቅራቸውን ገልፀዋል።

ፎቶ ፦ ድሬ ፖሊስ ሚዲያ

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያሽከርክሩ፤ እድልዎን ይሞክሩ!

የዓመቱ ስኬታችንን ደስታ ለመጋራት፤ ስለ አብሮነታችሁ ምስጋና በቴሌብር ሱፐርአፕ የተዘጋጀው የዕጣ ሽልማት እስከ ፊታችን ዓርብ ሐምሌ 21 ይቀጥላል፤

🎁 10 ላፕቶፖች
🎁 10 ታብሌቶች
🎁 10 ስማርት ስልኮች
🎁 10 ስማርት ሰዓቶች
🎁 50 ኢርበድስ
🎁 50 ሺህ የ100 ብር ሽልማቶች

በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ተጫውተው ያሸንፉ/ Play and win የሚለውን ይጫኑ፤ ያሽከርክሩ፤ በየቀኑ እድልዎን ይሞክሩ!

#አብሮነት በላቀ አገልግሎት
#ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ