TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀለኞች መሸሸጊያ የላቸውም...

#በኢትዮጵያ_ወንጀል_ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የትም ሆነ የት መሸሸጊያ ያላቸውን እጃቸውንም #አንጠልጥዬ ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክባለሁ ሲል አለም አቀፍ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ማስተማመኛ ሰጠ፡፡

ትናንትና አዲስ አበባ የመጡት የኢንተርፖል ዋና ሀላፊ ዶ/ር ጀርጋን ስቶክ ከፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው ወሬው የተሰማው፡፡

ከንግግሩ በኋላ መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ጀነራል #እንዳሻው_ጣሰው በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያንን ኢንተርፖል ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ ማስተማመኛ ሰጥቷል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙና ሀገር የዘረፉ ሰዎች ግማሾቹ በሀገር ውስጥ ግማሾቹ ደግሞ ባህር አቋርጠው በውጭ አገር እንደሚኖሩ ታውቋል ብለዋል፡፡

ይህንን ወንጀል ፈፃሚዎቹ የትም ይደበቁ የትም ይኑሩ ኢንተርፖል እጃቸውን አንጠልጥሎ ለኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያስረክብ ሀላፊው አረጋግጠውልናል ሲሉ መናገራቸውን ከመንግስታዊ ምንጮች ስምቻለሁ ብሎ ሸገር ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሰሞኑ ባስተላለፉት መልዕክት በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ማንም ይሁን ማን ከየትኛውም ብሔር ገብተው ይደበቁ፣ የትኛውም ወገን ይጩህላቸው በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ ካሉበት አድነን ለህግ እናቀርባቸዋልን ማለታቸው
ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia