TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአሜሪካ የቪዛ እቀባ የሚመለከተው ማንን ነው ?

አሜሪካ በኢትዮጵያ "ትግራይ ክልል ግጭት" ሳቢያ በተለያዩ የግጭቱ ተሳታፊ ናቸው ባለቻቸው አካላት ላይ የቪዛ እቀባ ማድረጓ አይዘነጋም።

አሜሪካ እገዳውን ለመጣል የወሰነችው የትግራዩ ጦርነት እንዲቆም፣ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል እንዲሁም ተፋላሚ ወገኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ ያቀረብኩት ሀሳብ ተቀባይነት አላገኘም በሚል እንደነበር ይታወሳል።

የቪዝ ክልከላ የተጣለባቸው አካላት በግልፅ የስም ዝርዝራቸው ይፋ ባይሆንም እቀባው ግን የሚመለከተው ፦

- የቀድሞ እና የአሁን የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት
- የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወታደራዊ እና የፀጥታ ሹማምንት
- የአማራ ክልል የፀጥታ አካላት
- የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (TPLF) አባላትን ነው።

ትላንት መግለጫ ያወጣው በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከላይ ከተገለፁት ውጭ ሌሎች ለትምህርት፣ ለስራ፣ ለሌላም ጉዳይ ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ሰዎችን የቪዛ ጥያቄ እንደሚያስተናግድ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 ጀምሮ እንደሚሰጥ የአ/አ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ።

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 23-25/2013 ድረስ እንደሚሰጥ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ፦

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ፣ ከአሜሪካ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት የመግለጫቸው ዋነኛ አጀንዳ ነበር፡፡

ቃል አቀባዩ ምን አሉ ?

- አሜሪካ የጣለችውን እገዳ በማስመልከት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት ሽመልስ አብዲሳ “የነቀዘ ስንዴ ነው የሚቀርብን” ማለት ያሰሙትን ንግግር በተመለከተ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ “ግለሰቦች የመናገር መብት አላቸው ፤ ይህም የግል አስተያየትና ስሜታቸው ነው” ብለዋል፡፡

- የኦሮሚያ ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ “የነቀዘ ስንዴ” ሲሉ የተናገሩት ንግግር የመንግስት አቋም ሳይሆን የግላቸው አስተያየት መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልፀዋል።

- በውጭ ጉዳይ ደረጃ “ጉዳዩን የማጋጋል ፍላጎት የለንም” ብለዋል ፤ “የተፈጠረው ጉዳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈታ በጋራ ወዳጆቻችን በኩል እየተነጋገርን ነው ያለነው” ሲሉ አሳውቀዋል።

- የሴናተር ጂም ኢንሆፌ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል የተፈጠረውን ጉዳይ ለመፍታት እየተኬደ ያለበት የዴፕሎማሲ መንገድ አካል ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል ፤ "የአሜሪካ አቋም ይቀየራል ብለን ነው የምናምነው ፣ መቼና እንዴት የሚለው ግን እነሱን የሚመለከት ነው” ብለዋል።

- ሴናተር ጂም ኢንሆፌ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መገናኘታቸውን እና “ውጤታማ ጉብኝት” አድርገዋል ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-06-02

#አልዓይን

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ በሁለት ቀን ብቻ 743 ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ አስወጥታለች።

ኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን በስፋት ወደ ሀገራቸው መመለስ ከጀመረች ወራት ተቆጥረዋል።

አሁንም ዜጎችን ወደሀገራቸው የመመለስ ስራ ተጠባክሮ የቀጠለ ሲሆን በሁለት ቀን ብቻ 743 ዜጎቿን ወደሀገራቸው መልሳለች።

አገራቸው ከተመለሱት ከ 743 ኢትዮጵያውያን መካከል 334ቱ #ከሪያድ ትላንት የተመለሱ ሲሆኑ 409ኙ ደግሞ በዛሬው ዕለት #ከጅዳ የተመለሱ ናቸው።

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

ኮቪድ-19 ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው አገሮች መካከል አንዷ በሆነችው #ብራዚል የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ ሆኖ በነበረበት ጊዜ እና ሀገሪቱ የበሽታውን ስርጭት ለመዋጋት በክትባት እጥረት በተጨነቀችበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3.5 ሚሊዮን የሲኖቫክ ክትባቶችን በሚያዝያ ወር ብቻ ከሻንጋይ፣ ቻይና ወደ ብራዚሏ ሳኦ ፖሎ በማጓጓዝ አስረክቧል።

የአየር መንገዱን ስራ በተመለከተ "ፋይናንሺያል ታይምስ/ Financial Times/" ያወጣው ዘገባ : t.co/cJ5DvWRW30

@tikvahethiopia
በተለያዩ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ተቀጥረው ለአጭር ግዜ የሰበዓዊ አገልግሎት ስራ ለሚሰሩ ግለሰቦች የሚሰጠው የቪዛ ጊዜ ተራዘመ።

ከዚህ ቀደም ለ1 ወር ይሰጥ የነበረ የNGO ቪዛ ከትላንት ጀምሮ ለ3 (ሦስት) ወር እንደሚሰጥ የኢሚግሬሽን እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አሳውቋል።

ለተጨማሪ ግዜ ቪዛቸው እንዲራዘም ለሚጠይቁ ድርጅቶች ለኤጀንሲው ጥያቄ ሲያቀርቡ የሚራዘም ይሆናል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም የሰብዓዊ አገልግሎት ስራ የሚሰሩ ግለሰቦች የ1ወር የቪዛ ጊዜ ይዘው ገብተው ስራቸውን ካልጨረሱና የይራዘምልን ጥያቄ ባቀረቡ ወቅት ይራዘምላቸው ነበር።

@tikvahethiopia
ዘምዘም ባንክ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነጻ ባንክ በመሆን አገልግሎት መጀመሩን ዛሬ አበሰረ።

ባንኩ የሸሪአን መርህን መሰረት ባደረገ መልኩ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን አገልግሎቱን የሚሰጡት በባንክ ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላቸው ስመጥር ባለሞያዎች ናቸው ብሏል፡፡

ዘምዘም ባንክ ፥ የኮር ባንኪነግ ሲስተሙ ዘመናዊ እንደሆነ ገልፆ በሲስተም አቅራቢዎችና በሸሪአ ባለሞያዎች በኩል ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንዳለው አሳውቋል።

ባንኩ ነገ ከጥዋት 3:30 ጀምሮ የመክፈቻ ስነስርአት እንዳለው ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,003 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 246 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 272,036 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 7 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,178 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,838,569 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
#TigrayRegion

በትግራይ ክልል 23,066 ዜጎች የኮቪድ-19 ክትባት መከተባቸውን የትግራይ ጤና ቢሮ ገልጿል።

ሁሉም ክትባቱን የወሰዱ ዜጎች በመቐለ ብቻ የሚገኙ እንደሆኑ ተነግሯል።

አሁን ላይ ወደሌሎች የትግራይ ከተሞች፦ ማይጨው ፣ ውቕሮ ፣ ዓዲግራት፣ ኣክሱም ክትባቱ እንዲሰጥ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ክትባቱን ለማስጀመር አስፈላጊው ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ክትባቱ ወደከተሞቹ ተልኳል።

ዓዲግራት፣ ወቕሮና ማይጨው ከሳምንት በፊት ክትባቱ ተልኮላቸው ክትባቱ መሰጠት ተጀምሯል።

አጭር መረጃ፦

- በትግራይ 5 ወር ያህል ተቋርጦ የነበረው የኮቪድ-19 ምርመራ ከሁለት ወር በፊት የጀመረ ሲሆን በቫይረሱ ተጠርጥረው ምርመራ ከተደረገላቸው መካከል 37% በቫይረሱ ተይዘው ተገኝተዋል።

- አስቀድሞ የሚሰሩት የኮቪድ-19 መከላከል ስራዎች የሉም።

- በተፈናቃይ ካምፖች የኮቪድ-19 ስርጭት እጅግ አሳሳቢ ነው። እንደምሳሌ፦ ሽረ ላይ ባለየተፈናቃይ መጠለያ በአንድ ክፍል ውስጥ እስከ 4 ቤተሰብ መሪ በተጨናነቀ ሁኔታ ይኖረል።

- ክትባት ከአንድ ወር በፊት ተጀምሮ በዝቅተኛ ደረጃ እየተሰጠ ነው።

- 119 ሺ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ትግራይ የተላከላት ሲሆን ከ23 ሺህ በላይ ጥቅም ላይ ውሏል።

- በጦርነት ምክንያት የኮቪድ-19 ጉዳይ ትኩረት በማጣቱ ፣ በህብረተሰቡ ዘንድ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬ በመኖሩ ክትባቱ የተቀዛቀዘ ነበር ፥ የተከታቢ ቁጥር አነስተኛ ስለነበር የክትባቱ አገልግሎት ጊዜ ወደማብቃት ተጠግቷል፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን መነቃቃት እያሳየ ነው።

- ቅድሚያ 55ና በላይ እድሜ ያላቸው፣ እንዲሁም ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው እየተሰጠ ሲሆን ከሚቀር ተብሎም ዕድሜያቸው 40 ለሆናቸውም እየተሰጠ ነው።

- በተፈናቃይ ካምፖች ክትባት መሰጠት አልተጀመረም። #ከዶቼቨለ

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#GERD🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማከናወን ሁለት ወር ቀርቷታል።

በግድቡ አጠቃላይ አሁናዊ ሁኔታ ላይ እና በየዘርፉ ያሉ ምዑራን በግድቡ ላይ ያላቸውን ተሰትፎ ማሳደግ በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጉባኤ ተካሂዷል።

በዚህ ጉባኤ ላይ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተው ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ አጭር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ምን አሉ ? ግድባችን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል ? ከላይ በተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

© ፋና ብሮድካስቲንግ (25 MB)

@tikvahethiopia
#Election2013

የሀገር መከላከያ ሰራዊት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ምርጫው #ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ገልጸዋል፡፡

ከምርጫው በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት እንዲከናወን እና በመላው ሀገሪቱ ወንጀለኛን አድኖ ለመያዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምርጫው በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲጠናቀቀቅ ሁሉም የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ መቅርረቡን አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 ዘግቧል።

PHOTO : FILE
@tikvahethiopia
ጋዜጠኛ እና ደራሲ አባተ ማንደፍሮ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ አባተ ለረጅም ጊዜ ከከፍተኛ የህመም ስቃይ ጋር እየተጋለ መቆየቱ ተገልጿል።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ አባተ ማንደፍሮ ማን ነው ?

- ከውትድርና ጀምሮ የወሎ ባህል ኪነት ቡድን ውስጥ በመድረክ አስተዋዋቂነት ሰርቷል።

- በጋዜጠኝነት በአገሪቱ ወስጥ አሉ በተባሉ ጋዜጦች እና መፅሔቶች እንዲሁም በ96.3 ኤፍ አም አቢሲኒያ ኢንተርቴይንመንት በተሰኘ አዝናኝና ቁምነገር አዘል መሰናዶ ሰርቷል።

- በ96.3 የሬዲዮ ፕሮግራሙ ላይ የቀጥታ ባለተሰጥኦዎች የድምፅ ውድድር በማዘጋጀት ለአሸናፊዎች ግጥምና ዜማ በመፃፍ እና አቀናባሪ በማፈላለግ በነፃ ነጠላ ዜማ እንዲሰሩ አድርጓል።

- የጄቲቪ ኢትዮጵያ በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ ስራ አስኪያጅ ሆኖ አገልግሏል።

- በአዋሽ ኤፍ ኤም ሬዲዮ በጋዜጠኝነቱ ቀጥሎ ነበር።

- በቅርቡ በድርሰት ሁለተኛ ስራው የሆነውን "ታልከል"የተሰኘ መፅሐፍ አስመርቋል።

- ለረጅም ጊዜ ከከፍተኛ የህመም ስቃይ ጋር እየተጋለ ስራውን ሲሰራ የነበረ ባለሞያ ነው።

- ጋዜጠኛ እና ደራሲ አባተ ማንደፍሮ ባለትዳር እና የአንድ ወንድ እና አንድ ሴት ልጅ አባት ነበር።

(ከጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ)

@tikvahethiopia
19,739 የቱርክ ሽጉጥ ተተኳሽ ጥይት ተያዘ።

19,739 ተተኳሽ ጥይቶቹን በ ሰሌዳ ቁጥር " ኮድ 1-43622 (አማ) " በሆነ ባጃጅ ተሽከርካሪ ጭነው ወደ ባህር ዳር ለማስገባት የሞከሩ 2 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

2ቱ ግለሰቦች የቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ጥይቶቹን ከምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ከገለጎ ከተማ ወደ ባህር ዳር ለማስገባት ሲሞክሩ ነው ትላንት ከቀኑ 9 ሰዓት በሻውራ ጉምሩክ ሰራተኞች እና በፌደራል ፖሊስ ትብብር በተደረገ የኬላ ፍተሻ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው ይገኛል።

መረጃው የጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia