TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኤርትራ ጦሯ ድንበር ተሻግሮ ስለመግባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አምናለች ፤ ለማስወጣት መስማማቷንም ለተመድ አሳውቃለች!

[አል ዓይን ኒውስ]

የኤርትራ ጦር ድንበር ተሻግሮ ትግራይ እንደገባ ሪፖርቶች በተደጋጋሚ ሲወጡ መቆየታቸው ይታወሳል።

ነገርግን የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ውስጥ መግባታቸውን አምኖ እንዲወጡ መስማማቱን ከመግለጹ ውጭ በኤርትራ በኩል ወታደሮቹ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው ስለመግባታቸው ያለው ምንም ነገር አልነበረም።

አሁን ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ባካሄደው ውይይት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ባለስልጣን የሆኑት ማርክ ሎውኮክ እና በም/ቤቱ የአሜሪካ መልዕክተኛ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ላደረጉት ንግግር፤ ኤርትራ በተወካይዋ አማካኝነት ምለሽ ሰጥታለች፡፡

በተመድ የኤርትራ አምባሳደር እንዲሁም ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ሶፊያ ተስፋማሪያም ለጸጥታው ጥባቃ ም/ቤት ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡

አምባሳደሯ በፃፉት ደብዳቤ የኤርትራ ሠራዊትን በሚመለከት "አንዣቦ የነበረው ስጋት በአብዛኛው በመወገዱ ኤርትራና ኢትዮጵያ የኤርትራ ኃይሎችን ለማስወጣትና የኢትዮጵያ ሠራዊት በድንበር ላይ እንዲሰማራ ለማድረግ በከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው አማካይነት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል" በማለት አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ሶፊያ፥አክለው በዝግ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የአሜሪካዋ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በሰነዘሩት "ተገቢ ያልሆነ" መግለጫ ላይ የኤርትራ መንግሥት ተቃውሞ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ተመድ "በተደጋጋሚ ከተሰጠው ድርሻ ባሻገር በመሄድ ተቀባይነት የሌለው ገንቢ ያልሆነ ተግባራት ውስጥ ገብቷል" ሲሉ ከሰዋል።

More : telegra.ph/Al-AIN-News-Agency-04-17-2

Pic-ADDIS STANDARD
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...በአጣዬ የሆነው ከዚህ በፊት እንኳን ሆኖ የማያውቅ ነው" - የአጣዬ ቲክቫህ አባላት በአጣየ ዳግም የተፈፀመው ጥቃት / የፀጥታ ችግር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን የቲክቫህ አባላት በላኩት መልዕክት አሳውቀዋል። ሁኔታው እጅግ ከሚባለው በላይ ከባድ ነው ፤ ቁጥራቸውን በውል ያልታወቀ ዜጎች ሞተዋል ፣ ንብረት ወድሟል ፣ በርካቶችን የሚሰነዘረውን ጥቃት ለማምለጥ ቤታቸውን ጥለው ሸሽተዋል ፣…
"...ባለው ስጋት ምክንያት ከተማችንን ጥለን ወጥተናል" - የሸዋሮቢት ቲክቫህ አባላት

በአጣየ እና አካባቢው ባለው ፀጥታ ችግር በርከቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሸሻሸውን የአጣየ አባላት ሪፖርት ማድረጋቸው ይታወቃል።

ከጥቂት ደቂቃዎችን በፊት መልዕክት ያስቀመጡ የሸዋሮቢት ቲክቫህ አባላት ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት ቤታቸውን ጥለው ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ለመሸሽ መገደዳቸውን ገልፀዋል።

"በአጣየ የተፈፀመው እንዚህ እንዳይደገም በሚል ስጋት ፈርተን ወደ ደብረብሃን ሄደናል" ያሉት አባላቶቻችን ፥ ባለው ሁኔታ ሁሉ ክፉኛ እንዳዘኑና ሰላም እንዲመለስ ሁሉም እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

ሌሎች አባላትም ሸዋሮቢት ባለው ድባብ ምክንያት ሰላም ፍለጋ ወደ ደብረሲና መሸሻቸውን ገልፀዋል።

የዙጢ ቲክቫህ አባላት በበኩላቸው በአካባቢያቸው ንብረት መውደሙ አሳውቀወል። ለደህንነታቸው ሰግተው በመሸሻቸው የሰው ህይወት ይጥፋ አይጥፋ በቂ መረጀ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

በአጠቃላይ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር ከተፈጠረባቸው አካባቢዎች የሚመጡት መልዕክቶች ቀጠናው መረጋጋት እንዳልቻለ፣ የሚፈፀመው ጥቃትም ከባድ እና ከአቅም በላይ መሆኑ፣ የሰው ህይወት እየተቀጠፈ መሆኑን፣ ንብረት በከፍተኛ ደረጃ እየወደመ መሆኑን፣ አሁን ባለው ሁኔታ የፀጥታ መዋቅሩም ሁኔታዎችን መቆጣጠር ፈታኝ እንደሆነበት የሚገልፁ ናቸው።

አባላቶቻችን ፥ ፌዴራል መንግስት የፀጥታ ኃይሉን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ ሁኔታውን መቆጣጠር ካልቻለ ከዚህ የከፋም ጉዳት እንዳይደርስ ያሰጋል ፥ ሁሉም የመፍትሄው አካል በመሆን የንፁሃንን ህይወት መታደግ አለባቸው ሲሉ አሳሰባል።

@tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia😷

ባለፉት 24 ሰዓት 28 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,307 የላብራቶሪ ምርመራ 1,709 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,076 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 240,236 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,328 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 178,705 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 1,027 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
አጭር መረጃ ለቲክቫህ አባላት ፦

- የፀጥታ ችግር ያለባቸው ቦታዎች ፦ አጣዬ ፣ ካራቆሬ ፣ ማጀቴ ፣ አንፆኪያ ፣ መኮይና ፣ ሸዋሮቢት ሲሆን በርካቶች ሰላም ፍለጋ ሸሽተዋል፤ በርካቶችም በሰላም እጦት በጭንቅ ውስጥ ናቸው።

- ጥቃት በተፈፀመባቸው ቦታዎች ህፃናት፣ እናቶችና አዛውንቶች መገደላቸው ተሰምቷል።

- በአጣዬ የነበረው በጣም የከፋ ነው ፤ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል ፣ ንብረት ወድሟል ፣ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ዝርፊያ ተፈጽሟል፤ ከተማዋ ክፉኛ ተጎድታለች ፤ እስረኞች ተለቀው በከተማይቱ ተበትነዋል።

- ልክ እንደ አጣየ ካራቆሬ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

- በሸዋሮቢት እስረኞችን የማስለቀቅ እንቅስቃሴ ተደርጓል።

- ችግር ወዳለባቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የፀጥታ ሃይሎች እየተሰማሩ ነው ብሏል የክልሉ መንግስት።

- አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ፣ የስንት ዜጎች ህይወት እንደጠፋ ፣ ምን ያህል ዜጎች ንብረት አልባ እንደሆኑ ንብረታቸው እንደወደመ አይታወቅም ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በነበረው ችግር የደረሰው ጉዳት እንኳን በአግባቡ ተለይቶ ይፋ ሳይደረግ ነው ይህ የተደረበው።

@tikvahethiopia
"... በደብረ ብርሃን የስጋት ቦታዎች ላይ ጥበቃ እና ፓትሮል እየተደረገ ነው፤ የኬላ ፍተሻ በአድማ መከላከል እና በልዩ ሃይል በጥብቅ እየተካሄደ ነው" - የከተማው ሰላምና ህዝብ ደህንነት ጽ/ቤት

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ህዝብ ደህንነት ጽህፈት ቤት ፥ የከተማውን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የጸጥታ ሃይሉ ማለት ልዩ ሃይል አድማ መከላከል ፣ ሚሊሻ እና ሰላም አስከባሪ በመቀናጀት የስጋት ቦታዎች ላይ ጥበቃ እና ፓትሮል እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የኬላ ላይ ፍተሻ በአድማ መከላከል እና በልዩ ሃይል በጥብቅ እየተካሄደ መሆኑንም ገልጿል።

በተጨማሪም ፅህፈት ቤቱ ፤ በከተማው ውስጥ የሚስተዋሉ የጸጥታ ስጋቶችን ለመቀነስ የከተማው ማህበረሰብ በተለይ ወጣቶች ከጸጥታ ሃይሉ ጎን በመሆን የተለየ እንቅስቃሴ ሲመለከቱ መረጃ በመስጠት እንዲሁም ለግጭት መንስዔ የሚሆኑ ተግባራት እንዳይፈጸሙ በመከላከል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ከሸዋሮቢት እና አካባቢው በርካታ ተፈናቃዮች ወደ ደ/ብርሃን እየገቡ በመሆኑ የከተማው ማህበረሰብ እና ወጣቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Tigray

በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች መኖሪያቸውን ጥለው ሲሰደዱ ተነጣጥለዋል፡፡

የግንኙነት መስመሮች ወደስራ የተመለሱ ቢሆንም አሁንም በርካቶች የሚወዷቸው ሰዎች ምን እንደገጠማቸው አያውቁም፡፡

ICRC ኢትዮጵያ የተጠፋፉ የቤተሰብ አባላት እንደገና እንዲገናኙ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ከሱዳን ቀይ ጨረቃ ማህበር ጋር በቅርበት እየሰራን እንደሚገኝ አሳውቋል።

እ.ኤ.አ ከህዳር 2020 እስከ የካቲት 2021 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ 17,400 የሚሆኑ ተፈናቃይ እና ስደተኛ ቤተሰቦች በነጻ የስልክ ጥሪዎች እና ‹የደህና ነኝ› መልእክቶች እንደገና እንዲገናኙ ማገዙን ከICRC ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የሴናተር ክሪስ ኩንስ የኢትዮጵያ ቆይታ ማብራሪያ ፦ By : Al Ain News Agency ከአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ወደ ኢትዮጵያ ተልከው ፣ በኢትዮጵያ የነበሩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ የኢትዮጵያ ቆይታቸው ስኬታማ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ሴናተር ኩንስ ወደአሜሪካ ከተመለሱ በኋላ ከአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ላይ ፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች…
#SnatorChrisCoos

ከሳምንታት በፊት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ ፥ "ጠ/ሚ ዐብይ የኤርትራን ኃይሎች ለማስወጣት ፣ በሰብዓዊ ተደራሽነት ላይ እንቅፋቶችን ለማስወገድ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድራሾችን ተጠያቂ ለማድረግ የገቡትን ቃል አለመፈጸማቸው ቅር አሰኝቶኛል።" ሲሉ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

ይህን የፃፉት ከሁለት ቀናት በፊት አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ የፃፉትን መልዕክት ባጋሩበት የትዊተር መልዕክት ላይ ነው።

ሴናተር ክሪስ ኩንስ አሁንም በኢትዮጵያ በትግራይ ውስጥ እና ከትግራይ ውጪ የቀጠለው ግፍ ያሳስበበኛል ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ፥ "ኢትዮጵያ ዓባይ ወንዝን ለልማቷ ስታውል ፣ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት የማስከተል ፍላጎትም ዕቅድም የላትም" ብለዋል።

ዶክተር አብይ ይህን ያሉት ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ነው።

ጠ/ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት የተገኘው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የሕዳሴውን ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት እውን ያደረገ መሆኑን አስታውሰው ፥ "የግድቡ መኖር በራሱ ጎረቤት ሀገራችን ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ በአስተማማኝ ሁኔታ ተከላክሎላታል" ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ሁለተኛው የውኃ ሙሌት ከመቀጠሉ በፊት ፣ አዲስ በተጠናቀቁት የውኃ መውረጃዎች አማካኝነት ባለፈው ዓመት ከተገደበው ተጨማሪ ውኃን የምትለቅቅ መሆኑን እና መረጃንም እንደምታጋራ ገልፀዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ "ሁለተኛው ሙሌት የሚከናወነው ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚገኝባቸው የሐምሌ/ነሐሴ ወራት በመሆኑ፣ ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ ለመከላከል ይጠቅማታል" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...በመሳሪያ እያስፈራሩ ፣ በገጀራ ፣ በሽጉጥ እያስፈራሩ መዝረፍ ይሄ ከበደልም በላይ በደል ነው" - ኮማንደር አብርሃ ጎደፋይ

የፀጥታ አካላትን ልብስ በመልበስ በመቐለ ከተማ አይደር ክፍለ ከተማ መንግስታዊ ባልሆነ ተቋም ውስጥ ባለ መጋዘን የተቀመጠ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን እና መድሃኒቶችን ለመዝረፍ ሙከራ ያደረጉ ግለሰቦች በጥበቃ ሰራተኛ ጥቆማ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር አውለዋቸዋል።

የመቐለ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አብርሃ ጎደፋይ ፥ ግለሰቦቹ የመከላከያ ፣ የፌዴራል ፖሊስና ፀጥታ ኃይሎችን ዩኒፎርም አድርገው የመጋዘኑን በር ሰብረው ሲዘርፉና በአይሱዚ ሲጭኑ ተደርሶባቸው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት ብለዋል።

ግለሰቦቹ የተለያዩ መሳሪያዎችን ጩቤ፣ ገጀራ፣ ሽጉጥ ይዘው እንደነበር የሚገልፁት ኮማንደር ኣብርሃ ግብረመልስ ሲሰጣቸው እጃቸውን እንደሰጡ ገልፀዋል።

የፀጥታ ኃይሎችን ዩኒፎርም አድርገው ሲዘርፉ የተያዙት 3 ግለሰቦች ናቸው፥ ጥቆማውን የሰጠው ደግሞ የድርጅቱ የጥበቃ ሰራተኛ መሆኑ ኮማንደሩ አሳውቀዋል።

ኮማንደር አብርሃ ፥ "... እነኚህ ወጣቶች ህዝቡን ሊደግፉት እየተገባ ለህዝቡ የገባውን መድሃኒት ፣ በየመኖሪያው እየዘለሉ እየገቡ በመሳሪያ እያስፈራሩ ፣ በገጀራ ፣በሽጉጥ እያስፈራሩ መዝረፍ ይሄ ከበደል በደል ነው፤ ስለዚህ ህዝቡ ማወቅ ያለበት ማንኛውም ችግር እራሳችን ነው የምንፈታው ፥ በተለይ የፀጥታ ችግር ሺ ፖሊስ ብናሰልፍ ፖሊስ ብቻውን ሊወጣው አይችልም ህዝቡ እርስ በእራሱ ተደራጅቶ እውቅና ተሰጥቶ በየመንደሩ ተደራጅቶች መጠበቅ አለበት...የመቐለ ወጣት ከፖሊስ ጎን መቆም አለበት" ብለዋል።

@tikvahethiopia
"...የመንግስት ተቀደሚ ስራው የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ መሆን አለበት" - ሰላም ፍለጋ ቤታቸውን ጥለው የሸሹ የቲክቫህ አባላት

የፅሁፍ መልዕክት ያስቀመጡ የቲክቫህ አባላት የመንግስት ተቀዳሚ ስራው የዜጎችን ደህንነት እና ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሰላም እና ደህንነት በሌለበት እንዴ መኖር ይችላል ? እንዴት ነው ሀገር አለኝ ብሎ ሰርቶ ፣ ለፍቶ ፣ ቤተሰብ መስርቶ የወደፊት ተስፋን ሰንቆ መኖር የሚቻለው ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ እጅግ ሰፊ ሀገር ናት የሚሉት የሰላም እጦት ገፈጥ ቀማሽ ነን ያሉ አባላቶቻችን ፦
- በተደጋጋሚ ሰላም የሚናጋበት ፣
- ፀጥታ የሚደፈርስበት ፣
- ዜጎች በግፍ የሚገደሉበት ፣
- ዜጎች፣ ንብረታቸውና ቤታቸው የሚወድምበት አካባቢዎች ይታወቃሉ ፤ የስጋት ቀጠናዎች በደንብ ይለያሉ በነዚህ አካባቢዎች ችግሮች ሳይፈጠሩ መከላከል ይገባል ፤ ችግሮች ከተፈጠሩ በኃላ እንዳይሰፋና ጥፋተኞች ተለይተው ሌላው እንዳይደግመው አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ብለዋል።

ችግር አለባቸው በሚባሉባቸው ቦታዎች ቀድሞ በቂ የፀጥታ ኃይል በመመደብ ፣ ቀድሞ በመዘጋጀት ፣ ከምንም በላይ ደግሞ አንድም ሳይቀር ጥፋተኛን በመያዝ ለፍርድ ማቅረብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

መንግስትም እራሱ ውስጡን ፈትሾ በተደጋጋሚ ጊዜ ችግር በሚፈጠርባቸው ቦታዎች ተሳትፎ ያላቸውን አካላት መለየት ይኖርበታል ፤ ተቀዳሚ ስራው የህዝብ ደህንነት ማስጠበቅ ነው ብለዋል።

ስርዓትና ህግ የሌለበት ሀገር እስኪመስል ከተሞች ሲወድሙ ፣ ዜጎች ሲገደሉ ፣ ቤቶች ሲቃጠሉ ፣ ድርጊት ፈፃሚዎችን መቆጣጠር ሳይቻል ቀርቶ የለየለት ስርዓት አልበኝነት ነግሶ ማየት ለነገ የሀገሪቱ ህልውና እጅግ አደገኛ ምልክት ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፦

[ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ - የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር]

- ሁለት የውሃ ማስተንፈሻዎች ግንባታ ተጠናቋል ፥ ሙከራውም ተጠናቆ ስራ ጀምረዋል።

- 2ቱ የውሃ ማስተንፈሻዎች አጠቃላይ ዓመታዊውን የዓባይ ፍሰት የማሳለፍ አቅም ያላቸው ሲሆን ፥ በግድቡ ሙሌት ወቅት የዓባይ ውሃ ወደ ታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ያለውን ፍሰት እንዲጨምር የሚያስችሉ ናቸው። ይህም ወደ ታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚኖረው የውሃ ፍሰት እንደማይስተጓጎል ማረጋገጫ ነው።

- ሌሎች 13 የውሃ ማስተንፈሻዎች በመገንባት ላይ ናቸው ፥ ይህም ለታችኛው የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ከፍተኛ ውሃ እንዲለቀቅ የሚያስችል ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
"...በአንደኛው ሟች ኪስ ውስጥ ተጨማሪ ያልፈነዳ ቦንብ ተገኝቷል" - ፖሊስ

[አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን]

በልደታ ክ/ከተማ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ግለሰቦች ህይወት ማለፉን የአዲስ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው "ከሚትሮሎጂ ፊት ለፊት"ለልማት በተዘጋጀ ቦታ ላይ በተከሰተ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈው።

በፍንዳታው አንድ ግለሰብ በፅኑ ተጎድቶ ወደ ሆስፒታል መሄዱን ፖሊስ አሳውቋል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ኢንስፔክተር ዳንኤል ታፈሰ የምርመራ መዝገብ ዋቢ አድርገው ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል ፦

"ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ አንድ በግምት ዕድሜው ከ50 እስከ 55 የሚገመት ግለሰብ ከሁለት በተመሳይ የዕድሜ ደረጃ ላይ ከሚገኙ 2 ሴቶች ጋር እየተገፈታተረ ወደቦታው ከገባ በኋላ ፍንዳታ ተሰምቷል ጉዳት ደርሷል። የግለሰቦቹ ማንነት እና የፍንዳታው ምክንያት ለማወቅ በምርመራ ሂደት ላይ ነው።"

በሠዓቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ የቴክኒክ እና የፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች ቦታው ላይ ፈጥነው በመድረስ ተጨማሪ ፍንዳታ እንዳይከሰት አካባቢውን ነፃ የማድረግ ስራ መስራታቸው ተገልጿል።

ፖሊስ በአንደኛው ሟች ኪስ ውስጥ ተጨማሪ ያልፈነዳ ቦንብ መገኘቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT