TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

የሰኞው የአድዋ ከተማ ግድያ :

• "የኤርትራ ወታደሮች ሰኞ ዕለት በአድዋ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍተው 3 ሰዎች ገድለዋል ፤ 19 አቁስለዋል" - አምነስቲ ኢንተርናሽናል

• "... የኤርትራ ወታደሮች በአድዋ ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል ፥ በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጣልቃ ባይገባ ኖሮ ተጨማሪ ሰላማዊ ዜጎች ይገደሉ ነበር" - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለስልጣን

• የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ፤ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ መኖር አለመኖራቸውን በተመለከተ በቀጥታ ምላሽ ባይሰጡም በአጠቃላይ "የኤርትራ ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎችን በፍፁም አይገድሉም" ብለዋል።

• “የህወሃት ደጋፊዎች እና ምንጮች የሚናገሩትን ማረጋገጥ አልችልም” - ቢለኔ ስዩም

የፔካ ሐቪስቶ ቃለምልልስ :

• "...በጉብኝቴ ወቅት የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣታቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ማየትም ሆነ መስማት አልቻልኩም" - ፔካ ሐቪስቶ

የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ :

• "...የኤርትራ ወታደሮች መውጣታቸውን የሚያመለክት ነገር የተባበሩት መንግሥታት ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ከእኛ ጋር አብረው የሚሰሩ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች አላዩም" - ማርክ ሎውኮክ

• በትግራይ የአስገድዶ መድፈርና ጾታዊ ጥቃቶችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች 'በአስቸኳይ' ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ጠይቀዋል።

• አምባሳደር ታዬ ትላንት በፀጥታው ም/ቤት ስለቀረበው ገለፃ ፥ “ገለጻው የመንግስትንና የሌሎች ሰብዓዊ አጋሮችን ጥረት ዝቅ ያደረገ እና የሚያደናቅፍ” ነው ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-Report-04-16

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የ20 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች።

አሜሪካ ያደረገችው የ20 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ እንደሚውል ተሰምቷል።

ይህ ከአሜሪካ የበሽታዎች መከላከል ማዕከል (CDC) ይፋ የተደረገው ድጋፍ ኮቪድ -19ን ለመከላከል እና የአገሪቱ የህብረተሰብ ጤና አቅምን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ነው የተገለፀው።

መረጃው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AtoLidetuAyalew

አቶ ልደቱ አያሌዉ ለሕክምና ወደ አሜሪካ እንዳይሔዱ በድጋሚ መከልከላቸዉን ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

አቶ ልደቱ ፥ ወደአሜሪካ ለመብረር አስፈላጊውን ሰነድ አሟልተዉ ትናንት ማታ ቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ ተናግረዋል።

የኤርፖርቱን የመጀመሪያውን የፍተሻ ካለፉ በኃላ ከአየር መንገዱ የበረራ ሰነድ ወይም ቦርዲንግ ፓስ ወስደው ፣ ሻንጣቸውን ልከው የመጨረሻው ኬላ ሲደርሱ ግን «ሲስተሙ የፍርድ ቤት እግድ እንዳለብህ ያሳያል» በሚል ከጉዞአቸው መሰናከላቸውን ገልፀዋል።

ምንም የፍርድ ቤት እግድ እንደሌለባቸው ለማስረዳት ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ተናገረዋል።

አውሮፕላን ላይ የተጫነው ሻንጣቸዉ ወርዶ ለሊት 6 ሰአት ወደ ቤታቸዉ ቢመለሱም፣ ፓስፖርታቸው ግን እንዳልተመለሰላቸው አስታዉቀዋል።

አቶ ልደቱ ፥ የደረሰባቸዉን በደል በተለይ ለሕክምና እንዳይጓዙ መከልከላቸዉን «የሞት ፍርድ» ብለውታል።

አቶ ልደቱ ፥ ወደ ዉጪ ሀገር እንዳይሄዱ ሲከለከሉ የትናንቱ የመጀመሪያዉ እንዳልሆነ ሬድዮ ጣቢያው በዘገባው ላይ አስታውሷል።

@tikvahethiopiaBOT
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ስያሜውን ወደ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ቀየረ።

አዲሱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በስራ ላይ ውሏል።

ከዚህ በፊት በስራ ላይ ሲውል የነበረው የብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 533|1999 ተሽሮ ወደ 1238\2013 ተለውጧል።

የኢትዮጵያ ብሮድካሰት ባለስልጣን ስያሜም ወደ "ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን" መለወጡ ተገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#አጣዬ

አጣዬ ዳግም ሰላም ርቋታል፤ የአጣዬ ቲክቫህ አባላት በላኩት የፅሁፍ መልዕክት ዳግም በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ሰዎች ሞተዋል ፣ ንብረት ተቃጥሏል፣ ሰዎች ሰላምን ፍለጋ ከገዛ ቤታቸውን ተፈናቅለው ሸሽተዋል።

ረቡዕ በአጣዬ ቤቶች መቃጠላቸውን ተከትሎ ከአምስት ሰዓት ጀምሮ የተኩስ እሩምታ የነበረ ሲሆን በሰዓት መከላከያ እና ፌዴራል ሁኔታውን መቆጣጠር ችለው ነበር።

አንድ የቲክቫህ አባል በአጣዬ ባለው ሁኔታ ሁለት በቅርብ የሚያውቃቸው ሰዎች መሞታቸውን ቢያረጋግጥም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር በትክክል እንኳን እንደማይታውቀ ተናግሯል።

ሌላ የቲክቫህ አባል ፥ በቅድሚያ ወደዳር አካባቢ የነበረው የተኩስ እሩምታ ወደ መሃል ክፍልም ይሰማ እንደነበረ ተናግሮ በአካባቢው የሚኖሩ ቤተሰቦቹ ሰላምን ፍለጋ ቤታቸውን ጥለው ሸሽተዋል።

የፀጥታ ኃይሎች ያሉ ቢሆንም፥ በቂ አይደለም በታጠቁ ኃይሎች የሚፈፀመው ጥቃት / የሚሰማው ተኩስ በርካቶችን በደህንነት ስጋት ውስጥ ከቷቸውን ቤታቸው ለቀው እየሸሹ ናቸው።

በተጨማሪ በአንጻኪያ ወረዳ ውስጥ ባሉቱ የተለያዩ ቀበሌዎች ዳግም ግጭት ተቀስቅሶ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል።

በእነዚህ አካባቢዎች በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ዋናው ዳግም መንገድ ተዘግቷል፤ወደ እና ከ አ/አ መሄድ አይቻልም መኪናዎችም ሸዋሮቢት ላይ ቆመዋል።

የሸዋሮቢት ቲክቫህ አባላት እንዴት ናችሁ ብለን ጠይቀናቸው ነበር?

ዛሬ በሸዋሮቢት ሁሉም መደበኛ እንቅስቃሴ መቀጠሉን አረጋግጠውልን፤ አጣዬ ላይ የተፈፀምጠረውን ሁኔታ ግን እንደሰሙት ገልፀዋል።

የአካባቢው አስተዳደር የጸጥታ ኃይል ችግር ቢፈጠር እንኳን ለመጠበቅና ለመከላከል ቦታ መያዙን፤ ምንም የሚያሳስብ ነገር እንደሌለ መግለፁን ነገርውናል።

ከሀሰተኛ መረጃና ውዥንብር ማህበረሰቡ እንዲቆጠብ ጥሪ መቅሩብን ነግረውናል።

@tikvahethiopia
ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ተከታዮቹን መረጃዎች ሰጥተዋል ፦

[ኤፍ ቢ ሲ & Purpose]

- እስካሁን ከ430,000 በላይ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት ወስደዋል።

- ክትባት የወሰዱ ጤና ባለሞያዎች፣ ሰራተኞች እድሜያቸው ከ65 አመት በላይ ለሆኑ፣ እድሜያቸው 64 እና ከዚያ በላይ ሆነው ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸው ዜጎች ናቸው።

- ከ5 ሚሊየን በላይ ተጨማሪ ከትባት ለማግኘት ከአፍሪካ ህብረትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየተሰራ ነው።

- ኮቪድ-19 ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን ከማስተግበር አንጻር የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል ፥ በአዲስ አበባ ብቻ ከ73 ሺ በላይ ግለሰቦች ማስክ ባለማድረግና አካላዊ ርቀት ባለመጠበቅ የማስተማሪያ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። ደንቦችን የተላለፉ ከ400 በላይ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው፥ 30 ግለሰቦችና 16 ተቋማት ጉዳያቸው በህግ እየታየ ነው።

- የኦክስጅን አቅርቦትን አሁን ላይ በ2 ሺህ 500 ሲሊንደር ማሳደግ ተችሏል። ይህም የቀን ሲሊንደር የመሙላት መጠኑን ከ4 ሺህ ወደ 6 ሺ 500 አሳድጎታል።

- እስካሁን በሀገሪቱ ለኮቪድ -19 ብቻ 258 የመተንፈሻ ማሽኖች ነበሩ ያነሱት፥ ተጨማሪ 215 የመተንፈሻ ማሽኖች ስርጭት እየተደረገ ነው።

- ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘም እስካለፈው ቅዳሜ በነበሩት 10 ቀናት ከ20 ሺ 600 በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝንቶብቸዋል። ይህ አሃዝ ከወር በፊት በነበሩት 10 ቀናት ቫይረሱ ከተገኘባቸው 10 ሺ 800 ሰዎች ጋር ሲነጻጸር የ91 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

- በአዲስ አበባ የመቃብር ስፍራ አጠቃላይ የሞት መጠን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ተደርጎ ባለፈው መጋቢት ወር የነበረው የሞት መጠን ከዘንድሮው መጋቢት ሲነፃፀር የ37 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

@tikvahethiopiaBOT
"...ባለፉት 3 ቀናት 25 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል" - ዶ/ር መንግስቱ በቀለ

በኦሮሚያ ክልል ከዕለት ወደዕለት / ከሳምንት ወደሳምንት ሪፖርት የሚደረጉ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር በ40% መጨመሩን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በቀለ ገለፁ።

በሌላ በኩል በህክምና ማዕከላት ህክምና እየተደረገላቸው እየዳኑ የሚወጡ ሰዎች ከሳምንት ወደ ሳምንት በ11% ቀንሷል።

በኦሮሚያ እስካሁን በአጠቃላይ 377 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ባለፉት 3 ቀናት ብቻ 25 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ዶ/ር መንግስቱ ፥ "በአንድ አመት ከአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በ3 ቀን 25 ሰው የሚሞት ከሆነ በእንዲህ ያለው ሁኔታ ቢቀጥል ከአንድ አመት በኃላ የክልሉ እና የሀገሪቱ እጣፋንታ ፣ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ሲታይ እጅግ አሳሳቢ ነው።" ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ በተሰራ ጥናት የእጅና የግል ንፅህና መጠበቅ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ወይም "የለም" የሚባልበት ደረጃ ላይ መድረሱ ገልፀዋል።

የማስክ አጠቃቀም በዋና ዋና የኦሮሚያ ከተሞች ሲሰራ 30 % እንደሚያሳይ የተገለፀ ሲሆን የእጅ ንፅህና ግን 1.7% ብቻ ነው የሚያሳየው ሲሉ ዶ/ር መንግስቱ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሱዳን ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ ከፍራንስ 24 [The Interview] ጋር :

- ከትላትን በስቲያ ለኢትዮጵያ እና ግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ያቀረቡት ጥሪ እስካሁን ከሁለቱም በኩል ምላሽ እንዳላገኙ ተናግረዋል ፤ ነገር ግን በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ ምላሽቸውን እንደሚጠባበቁ ገልፀዋል።

- በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ የወታደራዊ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት እንደሌላቸው ተናግረዋል። ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት ጉዳዩን የUN ፀጥታው ም/ቤት እንዲይዘው ሊጠይቁ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

- በኢትዮዮጵያ እና ሱዳን ድንበር መካከል ያለው ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል ፤ በድንበር ጉዳይ ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው ገልፀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia😷

ባለፉት 24 ሰዓት 15 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,480 የላብራቶሪ ምርመራ 1,973 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,750 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 238,527 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,300 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 177,629 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 1,013 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
"የ7 ወር ደመወዝ አልተከፈለንም" - የወላይታ ሶዶ ከነማ ተጫዋቾች

በወላይታ ሶዶ ከነማ የሚጫወቱ ተጫዋቾች የሰባት (7) ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው እና እስካሁን መፍትሄ እንዳላገኙ በፁህፍ መልዕልት አሳውቀዋል።

በቡድኑ ውስጥ ያሉ የቲክቫህ አባላት በላኩት መልዕክት ላለፉት 7 ወራት ደሞዝ ባለማግኘታቸው እንደተቸገሩ ገልፀዋል።

የአበላይ አካላትን እንድናገኝ አይፈለግም፤ ለችግሩ መፍትሄ ይሰጡናል ብለን ብንጠብቅም ሊሆን አልቻለም፤ ጉዳዩን ወደ ፌዴሬሽን ብንወስደው በቀጥታ ክለቡ ላይ ነው እርምጃ የሚወሰደው ይህ ደግሞ እንዲሆን ባለመፈለጋችን እስካሁን ታግሰናል ብለዋል።

እኛ ክለቡን ማገልግለን ፥ የወጣንበትን አካባቢ እና ማህበረሰብ በእግር ኳሱ መወከል ነው ፍላጎታችን ነገር ግን ምንም ደመወዝ ሳናገኝ በዚህ መልኩ መቆየታችን አሳዝኖናል ሲሉ አስረድተዋል።

ችግሩ ዛሬም ድረስ ሊፈታና ከአቅማችን በላይ በመሆኑ ነው ወደሚዲያ ለመውጣት የተገደድነው የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ይህን ተረድተው አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አጣዬ አጣዬ ዳግም ሰላም ርቋታል፤ የአጣዬ ቲክቫህ አባላት በላኩት የፅሁፍ መልዕክት ዳግም በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ሰዎች ሞተዋል ፣ ንብረት ተቃጥሏል፣ ሰዎች ሰላምን ፍለጋ ከገዛ ቤታቸውን ተፈናቅለው ሸሽተዋል። ረቡዕ በአጣዬ ቤቶች መቃጠላቸውን ተከትሎ ከአምስት ሰዓት ጀምሮ የተኩስ እሩምታ የነበረ ሲሆን በሰዓት መከላከያ እና ፌዴራል ሁኔታውን መቆጣጠር ችለው ነበር። አንድ የቲክቫህ አባል በአጣዬ…
"...በአጣዬ የሆነው ከዚህ በፊት እንኳን ሆኖ የማያውቅ ነው" - የአጣዬ ቲክቫህ አባላት

በአጣየ ዳግም የተፈፀመው ጥቃት / የፀጥታ ችግር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን የቲክቫህ አባላት በላኩት መልዕክት አሳውቀዋል።

ሁኔታው እጅግ ከሚባለው በላይ ከባድ ነው ፤ ቁጥራቸውን በውል ያልታወቀ ዜጎች ሞተዋል ፣ ንብረት ወድሟል ፣ በርካቶችን የሚሰነዘረውን ጥቃት ለማምለጥ ቤታቸውን ጥለው ሸሽተዋል ፣ በአጠቃላይ ከዚህ በፊት ታይቶ የማታወቅ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክታቸውን ከላኩ የቲክቫህ አባላት መካከል ፥ በቅርብ የሚያውቁትን ወዳጃቸውን ያጡ እና ሸሽተው ወደ ሌላ ቦታ የሄዱ አባላችን በታሪካቸውን እንዲህ ያለው ነገር ይሆናል ብለው እንዳልጠበቁ ፣ እንደአሁኑ ያለው አይነት የከፋ ጉዳት አይተው እንደማያውቁ አስረድተዋል ፥ አጣዬ እንዳልነበረች ነው የሆነችው ፣ ከፍተኛ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፣ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል።

አሁንም ቀጠናው በውጥረት የተሞላ መሆኑን አባላቶቻችን ያሳወቁ ሲሆን የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የፀጥታ ኃይሎችን መድቦ በፍጥነት መቆጣጠር ካልተቻለ አሁን ካለው በላይ ተስፋፍቶ ሌሎች ቦታዎችንም ሊያዳርስ ይችላል እና ጥንቃቄ ይደረግ ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
በፎኖተ ሰላም ከተማ አንድ ፖሊስ ሲገደል፥ አንድ የአማራ ክልል አድማ ብተና አባል ቆስሏል !

የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ ፤ በፍኖተ ሰላም ከተማ አንድ የፖሊስ አባል መገደሉን እና አንድ የአማራ ክልል አድማ ብተና አባል መቁሰሉን ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ገልጿል።

ትላንት ከቀኑ ወደ 7:30 አካባቢ "በወለጋ የሚኖሩ ወገኖቻችን እየተገደሉ እየተጨፈጨፉ ነው እየሞቱ ነው" በሚል ጉዳት ደረሰብን የሚሉ ህብረተሰቡን እና የአካባቢውን ወጣት በማስተባበር ተቃውሟቸውን በሰላማዊ ሰልፍ እንገልፃለን በማለት ወደ አደባባይ ወጥተው እንደነበር ተገልጿል።

ፖሊስ ፥ "ሰልፈኞቹ ተቃውሟቸውን እየገለፁ በነበረበት ወቅት ሰላማዊ ተቃውም ወደ ህገወጥ ነውጥ በማምራቱና በመሸጋገሩ በፍኖተ ሰላም ከተማ ፓሊስ እና የፀጥታ ሀይል የክልሉ አድማ ብተና ፓሊስ ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ነውጥነት ባህሪ ሲያሳይ የፀጥታ ሀይሉ ነውጡን እያረጋጋ ባለበት ጊዜ የተለያየ ተልዕኮ ባነገቡ አካላት ከሰልፉ በስተጀርባ በመሆን ማህበረሰቡን በቅንነት በታማኝነት ሲያገለግል የነበረን የፍኖተ ሰላም ፓሊስ ላይ ጥይት በመተኮስ የገደሉ ሲሆን አንድ የአድማ ብተና ፖሊስ አባል ላይም አቁስለዋል" ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

ከፍኖተሰላም ከተማ በመውጣት ከደብረማርቆስ ወደ ባህር ዳር ድንች ጭኖ ሲጓዝ በነበረ FSR የጭነት መኪና የተቃጠለ ሲሆን በሹፌሩ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ፖሊስ ገልጿል።

* የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ኤርትራ ጦሯ ድንበር ተሻግሮ ስለመግባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አምናለች ፤ ለማስወጣት መስማማቷንም ለተመድ አሳውቃለች!

[አል ዓይን ኒውስ]

የኤርትራ ጦር ድንበር ተሻግሮ ትግራይ እንደገባ ሪፖርቶች በተደጋጋሚ ሲወጡ መቆየታቸው ይታወሳል።

ነገርግን የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ውስጥ መግባታቸውን አምኖ እንዲወጡ መስማማቱን ከመግለጹ ውጭ በኤርትራ በኩል ወታደሮቹ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀው ስለመግባታቸው ያለው ምንም ነገር አልነበረም።

አሁን ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ባካሄደው ውይይት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ባለስልጣን የሆኑት ማርክ ሎውኮክ እና በም/ቤቱ የአሜሪካ መልዕክተኛ የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ላደረጉት ንግግር፤ ኤርትራ በተወካይዋ አማካኝነት ምለሽ ሰጥታለች፡፡

በተመድ የኤርትራ አምባሳደር እንዲሁም ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ሶፊያ ተስፋማሪያም ለጸጥታው ጥባቃ ም/ቤት ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡

አምባሳደሯ በፃፉት ደብዳቤ የኤርትራ ሠራዊትን በሚመለከት "አንዣቦ የነበረው ስጋት በአብዛኛው በመወገዱ ኤርትራና ኢትዮጵያ የኤርትራ ኃይሎችን ለማስወጣትና የኢትዮጵያ ሠራዊት በድንበር ላይ እንዲሰማራ ለማድረግ በከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው አማካይነት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል" በማለት አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ሶፊያ፥አክለው በዝግ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የአሜሪካዋ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በሰነዘሩት "ተገቢ ያልሆነ" መግለጫ ላይ የኤርትራ መንግሥት ተቃውሞ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ተመድ "በተደጋጋሚ ከተሰጠው ድርሻ ባሻገር በመሄድ ተቀባይነት የሌለው ገንቢ ያልሆነ ተግባራት ውስጥ ገብቷል" ሲሉ ከሰዋል።

More : telegra.ph/Al-AIN-News-Agency-04-17-2

Pic-ADDIS STANDARD
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...በአጣዬ የሆነው ከዚህ በፊት እንኳን ሆኖ የማያውቅ ነው" - የአጣዬ ቲክቫህ አባላት በአጣየ ዳግም የተፈፀመው ጥቃት / የፀጥታ ችግር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን የቲክቫህ አባላት በላኩት መልዕክት አሳውቀዋል። ሁኔታው እጅግ ከሚባለው በላይ ከባድ ነው ፤ ቁጥራቸውን በውል ያልታወቀ ዜጎች ሞተዋል ፣ ንብረት ወድሟል ፣ በርካቶችን የሚሰነዘረውን ጥቃት ለማምለጥ ቤታቸውን ጥለው ሸሽተዋል ፣…
"...ባለው ስጋት ምክንያት ከተማችንን ጥለን ወጥተናል" - የሸዋሮቢት ቲክቫህ አባላት

በአጣየ እና አካባቢው ባለው ፀጥታ ችግር በርከቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሸሻሸውን የአጣየ አባላት ሪፖርት ማድረጋቸው ይታወቃል።

ከጥቂት ደቂቃዎችን በፊት መልዕክት ያስቀመጡ የሸዋሮቢት ቲክቫህ አባላት ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት ቤታቸውን ጥለው ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ለመሸሽ መገደዳቸውን ገልፀዋል።

"በአጣየ የተፈፀመው እንዚህ እንዳይደገም በሚል ስጋት ፈርተን ወደ ደብረብሃን ሄደናል" ያሉት አባላቶቻችን ፥ ባለው ሁኔታ ሁሉ ክፉኛ እንዳዘኑና ሰላም እንዲመለስ ሁሉም እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

ሌሎች አባላትም ሸዋሮቢት ባለው ድባብ ምክንያት ሰላም ፍለጋ ወደ ደብረሲና መሸሻቸውን ገልፀዋል።

የዙጢ ቲክቫህ አባላት በበኩላቸው በአካባቢያቸው ንብረት መውደሙ አሳውቀወል። ለደህንነታቸው ሰግተው በመሸሻቸው የሰው ህይወት ይጥፋ አይጥፋ በቂ መረጀ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

በአጠቃላይ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር ከተፈጠረባቸው አካባቢዎች የሚመጡት መልዕክቶች ቀጠናው መረጋጋት እንዳልቻለ፣ የሚፈፀመው ጥቃትም ከባድ እና ከአቅም በላይ መሆኑ፣ የሰው ህይወት እየተቀጠፈ መሆኑን፣ ንብረት በከፍተኛ ደረጃ እየወደመ መሆኑን፣ አሁን ባለው ሁኔታ የፀጥታ መዋቅሩም ሁኔታዎችን መቆጣጠር ፈታኝ እንደሆነበት የሚገልፁ ናቸው።

አባላቶቻችን ፥ ፌዴራል መንግስት የፀጥታ ኃይሉን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ ሁኔታውን መቆጣጠር ካልቻለ ከዚህ የከፋም ጉዳት እንዳይደርስ ያሰጋል ፥ ሁሉም የመፍትሄው አካል በመሆን የንፁሃንን ህይወት መታደግ አለባቸው ሲሉ አሳሰባል።

@tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia😷

ባለፉት 24 ሰዓት 28 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,307 የላብራቶሪ ምርመራ 1,709 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,076 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 240,236 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,328 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 178,705 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 1,027 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
አጭር መረጃ ለቲክቫህ አባላት ፦

- የፀጥታ ችግር ያለባቸው ቦታዎች ፦ አጣዬ ፣ ካራቆሬ ፣ ማጀቴ ፣ አንፆኪያ ፣ መኮይና ፣ ሸዋሮቢት ሲሆን በርካቶች ሰላም ፍለጋ ሸሽተዋል፤ በርካቶችም በሰላም እጦት በጭንቅ ውስጥ ናቸው።

- ጥቃት በተፈፀመባቸው ቦታዎች ህፃናት፣ እናቶችና አዛውንቶች መገደላቸው ተሰምቷል።

- በአጣዬ የነበረው በጣም የከፋ ነው ፤ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል ፣ ንብረት ወድሟል ፣ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ዝርፊያ ተፈጽሟል፤ ከተማዋ ክፉኛ ተጎድታለች ፤ እስረኞች ተለቀው በከተማይቱ ተበትነዋል።

- ልክ እንደ አጣየ ካራቆሬ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

- በሸዋሮቢት እስረኞችን የማስለቀቅ እንቅስቃሴ ተደርጓል።

- ችግር ወዳለባቸው አካባቢዎች ተጨማሪ የፀጥታ ሃይሎች እየተሰማሩ ነው ብሏል የክልሉ መንግስት።

- አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ፣ የስንት ዜጎች ህይወት እንደጠፋ ፣ ምን ያህል ዜጎች ንብረት አልባ እንደሆኑ ንብረታቸው እንደወደመ አይታወቅም ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በነበረው ችግር የደረሰው ጉዳት እንኳን በአግባቡ ተለይቶ ይፋ ሳይደረግ ነው ይህ የተደረበው።

@tikvahethiopia