የሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ መግለጫ ሲዳሰስ ፦
- በትግራይ ክልል ፥ በ8 ቡድን የተደራጀና በ8 የህወሓት ቡድን አመራሮች የሚመሩ ኃይሎች ላይ በተመሳሳይ ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ ዘመቻ መደረጉን ተናግረዋል።
- በዘመቻው መከላከያ ማንኛውም ሀገሪቱ ያላትን ኃይል በሙሉ፣ ወታደራዊ አቅምን በሙሉ መጠቀሙን ገልፀዋል።
- በቅርቡ መቐለን እንቆጣጠራለን፣ አዲስ አበባ እንገባለን፣ የሚባለውን ነገር በነሱ አቅም ፈፅሞ የሚሞከር እና የሚቀመስ አይደለም ብለዋል። "ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቐለ እና አዲስ አበባ እይገቡም" ሲሉ ተደምጠዋል።
- ቡድኑ በምስራቅ አልያም በምዕራብ በኩል ወደ ሱዳን ለመውጣት ዝግጅት እያደረገ ነው /እየተሰባሰበ ነው ብለዋል። ዝግጅቱ እዚህ ኢትዮጵያ ባለው የህወሓት ቡድን ብቻ ሳይሆን በውጭ በሱዳን በኩልም ዝግጅቶችን አሉ ሲሉ ተናግረዋል።
- መከላከያ ሰራዊት በህግ የሚፈለጉት አካላት ተይዘው ህግ ፊት እስኪቀርቡ ድረስ ወይም እስኪጠፉ ድረስ ስራውን መከላከያው እንቅልፉን አይተኛም ብለዋል።
በዝርዝር ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Ethiopian-National-Defense-Force-04-13

Telegraph
Ethiopian National Defense Force
የሌ/ጄነራል ባጫ መግለጫ ሲዳሰስ ፦ ዛሬ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዋነኝነት መግለጫውን የሰጡት የሰሞኑን የሰራዊቱን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ለህዝብ ለማሳወቅ እንደሆነ ተገልጿል ሌ/ጄኔራል ባጫ በቅርቡ ዶ/ር አብይ አህመድ በ8 ግንባሮች ውጊያ እየተደረገ እንደነበር መግለፃቸውን አስታውሰው ይህን ጉዳይ በተመለከተ ግልፅ ማብራሪያ መስጠት ማስፈለጉን ገልፀዋል። በትግራይ ክልል ፥ በ8 ቡድን…
#Ethiopia😷
ባለፉት 24 ሰዓት 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 7,601 የላብራቶሪ ምርመራ 1,568 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 1,838 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 232,512 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,230 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 173,818 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 967 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

TIKVAH-ETHIOPIA
ፔካ ሀቪስቶ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሀርቪስቶ የተመራው የአውሮፓ ህብረት ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል። ፔካ ሀርቪስቶ ወደኢትዮጵያ ከመምጣታቸው ከሰዓታት በፊት በትዊተር ገፃቸው ፥ በቆይታቸው በአዲስ አበባ እንዲሁም ትግራይ ክልል ጉብኝት እንደሚያደርጉ ገልፀው ነበር። በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ቀውስም ፈጣን መፍትሄ እንደሚፈልግ ፅፈዋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፔካ ሀቪስቶ : “በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ጥሰቶች አሁንም መሻሻሎች እየታዩ አይደለም”
[ALAIN , CNN]
የትግራይ ክልል የሰብአዊ ቀውስ ሁኔታው እየተባባሰ መምጣቱን ከቀናት በፊት ትግራይን የጎበኙት የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኛ የፊንላንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሀቪስቶ ለCNN ተናግረዋል።
ልዩ መልእክተኛ ሀቪስቶ፥ “በትግራይ ባለው የሰብዓዊ ቀውስ ሁኔታ መሻሻሎች እየታዩ አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሀቪስቶ በትግራይ ቆይታቸው ፥ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘውን ‘የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል’ን የመጎብኘት እድል እንደነበራቸው ያነሱ ሲሆን ሆስፒታሉ ጉዳት በደረሰባቸው ንጹሃን ዜጎች ተጨናንቆ መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡
More : https://telegra.ph/Al-AIN---CNN-04-13

የጥንቃቄ መልዕክት : እራሳችሁን ጠብቁ !
ኢትዮጵያ ሀገራችን ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ በየዕለቱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው።
በዕለታዊ ምርመራ ከሚመረመሩት ዜጎቻችን መካከል በርካቶች በኮቪድ-19 መያዛቸው እየተረጋገጠ ነው።
የኛ መዘናጋት ለወረርሽኙ በአደገኛ ሁኔታ መጨመር አስተዋፆ እያደረገ ነው እና ዘውትር እንቅስቃሴያቸውን ጥንቃቄ የተሞላበት በማድረግ የሰው ልጆችን ህይወት እናትርፍ።
በተለይም ሰዎች ከሚሰበሰቡበት በመራቅ ፣ ሁል ጊዜም የአካላዊ ርቀታችንን በመጠበቅ ፣ ማስክ በማድረግ ፣ የእጆችን ንፅህና በመጠበቅ እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ሁሉ ከዚህ አስከፊ ወረርሽኝ እንታደግ።
ሁላችንም ኃላፊነታችንን ከተወጣን ወረርሽኙ እየተዛመተበት ያለውን ፍጥነት መቀነስ እንችላለን።

የጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሀምዶክ ጥሪ : "በዝግ እንወያይ"
[Al AIN]
የሱዳን ጠ/ሚር ዶክተር አብደላ ሀምዶክ ለግብጽ ጠ/ሚር ሙስጠፋ ማድቦሊ እና ለኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ10 ቀናት ውስጥ “በዝግ እንወያይ” የሚል ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ከ10 ባልበለጡ ቀናት ውስጥ ተገናኝተን የድርድሩን ሂደቶች እንገምግም” ብለዋል፡፡
“በ2015ቱ የመርሆዎች ስምምነት መሰረት ወደፊት ለመራመድ በሚያስችሉን አማራጮች ላይ ተወያይተን እንስማማ፤ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነታችንንም እናድስ” ሲሉም ነው ሃምዶክ ጥሪ ያቀረቡት፡፡
ጥሪው የቀረበው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረጉት ተደጋጋሚ የሶስትዮሽ ድርድሮች “ውጤታማ ሳይሆኑና ስምምነት ላይ ሳይደረስ ዓመታት በመቆጠራቸው” ነው፡፡
ሃምዶክ ለኢትዮጵያና ለግብጽ አቻዎቻቸው ጉዳዩን የተመለከተ መልዕክት ልከዋል፡፡
More : https://telegra.ph/Al-AIN-04-14

"... ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ፤ ነገር ግን ዝግጁ አይደለንም ማለት አይደለም" - ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ
ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ትለንት በሰጡት መግለጫ ፥ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ጦርነት እንደማታደርግ ፥ ጦርነት ማድረጉ ምንም እነደማያደርግ ተናግረዋል።
ሌ/ጄነራሉ አሁን ሱዳኖች ያያዙትን መሬት በንግግር መጨረስ ይቻላል ፥ እምነታችንም እሱ ነው ብለዋል።
ስንት ጊዜ ነው በመሬት ችግር ዘራፍ ብለን ተዋግተን ወጣቶችን የምናስጨርሰው ? ብለው የጠየቁት ሌ/ጄነራሉ ፥ የመሬቱን ጉዳይ በቀላሉ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ መፍታት ይቻላል ፤ ግፋ ቢል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መፍታት ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።
በሱዳን እና በኢትዮጵያ ወንድማማቾች መካከል የገባ ሶስተኛ ወገን አለ ፤ ከሱዳን ወንድሞቻችን ጋር በጋራ ሆነን ይሄን ሶስተኛ ወገን ለማውጣት ጥረት ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።
ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ "ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ነገር ግን ዝግጅ አይደለንም ማለት አይደለም፤ ኢትዮጵያን ለመከላከል እኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምን ጊዜም ዝግጁ ነን" ሲሉ ገልፀዋል።

የማህበር ቤት ምዝገባ : የአ/አ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በማኅበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን በአማራጭ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ምዝገባ ነገ ይጀምራል። በምዝገባው የሚካተቱት ፦ - በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና 40 /60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ተጠቃሚ ለመሆን የተመዘገቡ - ስማቸው በምዝገባ ቋት የሚገኝ እና የቁጠባ ደብተር ሂሳብ…
የማህበር ቤት ምዝገባ ተራዘመ።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የማህበር ቤት ምዝገባ ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን አስታውቋል።
የማህበር ቤት ምዝገባ ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ከ8 ሺህ 500 በላይ የማህበር ቤት ፈላጊዎች ተመዝግበዋል፡፡
የምዝገባ ጊዜው ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም የተጠናቀቀ ቢሆንም ከተጠቃሚው ወደ ቢሮው በሚመጡ ጥያቄዎች በመነሳት ምዝገባው ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን ቢሮው አስታውቋል፡፡
መመዝገብ እየፈለጉ በተለያዩ ምክንያቶች ቀኑ ያለፋቸው ተጠቃሚዎች የምዝገባ ጊዜው ከሚያዚያ 6 እስከ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቀው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።
ተመዝጋቢዎች ወደ ቢሮ መምጣት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ /Online/ በቢሮው አድራሻ aahdab.gov.et አማካኝነት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ በምዝገባ ወቅት ችግር የገጠማቸውን የማህበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኃላ ከሚያዚያ 18-20/2013 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በቢሮው ቀርበው ቅሬታችውን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።
@tikvahethiopiaBOT

#Adwa
(ሰኞ ሚያዚያ 4 ቀን 2013 ዓ/ም)
• "...በመኪና ተጭነው ሲሄዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች አንድ የባጃጅ አሽከርካሪ መንገድ ዘጋብን በሚል ነው ጥቃት የፈፀሙት፤ ...አንድ ሰው ሞቷል" - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስገዶም ስዩም
• "...በተኩሱ 8 ሰዎች ሞተዋል" - የአድዋ ነዋሪዎች
• "...ወታደሮቹ ወደ ከተማዋ ሲገቡ፣ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት አድዋ ላይ ምንም አይነት ጦርነት አልነበረም" - የአድዋ ነዋሪ
• "...2 የኤርትራ ሠራዊት የጫኑ የጭነት መኪኖች አንበሳ ባንክ አካባቢ ሲደርሱ መተኮስ ጀመሩ። አጋጣሚ አጠገቤ አንድ ሱቅ ነበርና ወደ እዚያ ልገባ ስሮጥ 3 ጊዜ ተኮሱብኝ" - የጥቃቱ ሰለባ
• "...ሁለት ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እያከምን ነው" - የጤና ባለሞያ
• "... ሰኞ እለት 18 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አድዋ ኪዳነምህረት ሆስፒታል መጥተው እርዳታ እንደተደረገላቸው ነው ፤ 11 ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ አክሱም ሆስፒታል ተልከዋል" - MSF
ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-04-14
@tikvahaethiopiaBOT @tikvahethiopia

#ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
[ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 - የኔነህ ሲሳይ]
በዛሬው የውይይት መድረክ በምርጫ ቦርድ በኩል ተከታዮቹ ነጥቦች ተነስተዋል ፦
- ከ50,000 ያህል የምርጫ ጣቢያዎች የተከፈተው 25,000 ብቻ ነው።
- በሶማሌ ክልል እና አፋር ክልል በትራንስፖርት ፣ በሎጅስቲክ ፣ በፀጥታች ችግሮች ምክንያት የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም።
- በፀጥታ ችግር ምክንያት ከ4,000 በላይ የምርጫ ጣቢያ አልተከፈተም።
- በተለያዩ አካባቢዎች በትራንስፖርትና በሎጅስቲክ ምክንያት ያለተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች አሉ።
- በምዕራብ ወለጋ ፣ ምስራቅ ወለጋ ፣ በቄለም ወለጋ ፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ አንድም የምርጫ ጣቢያ አልተከፈተም። ምርጫ ጣቢያ ያልተከፈተው በፀጥታ ችግር ነው።
- ከአፋር እና ሱማሌ ፣ ኦሮሚያ ክልሎች አንዳንድ ቦታዎች በተጨማሪ በሌሎች አካባቢዎች እስካሁን ምንም አይነት ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች አሉ።
- እስካሁን የተመዘገበ የመራጭ ቁጥር በትክክል ይፋ አልተደረገም።
- በአዲስ አበባ በአካባቢዎች መቀያየር ምክንያት ምርጫ ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ጣቢያዎች አሉ።
- የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ስምንት ቀናት ብቻ ቀርቶታል። እስካሁን ምን ያህል ሰዎች እንደተመዘገቡ ባይታወቅም አጠቃላይ ሂደቱ በጣም አስቸጋሪ እና ፈታኝ ሆኗል።
- የምርጫ 2013 የመራጮች ምዝገባ በሚፈለገው መንገድ እንዲሄድ ለማድረግ ምርጫ ቦርድ ከቀደው እቅድ መካከል አጭር የፅሁፍ መልዕክት ማስተላለፍ ሲሆን ለ35 ሚሊዮን ዜጎች መልዕክት እንዲደርሳቸው እቅድ ተይዟል።

#ምርጫ2013 የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አካሂዷል። [ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 - የኔነህ ሲሳይ] በዛሬው የውይይት መድረክ በምርጫ ቦርድ በኩል ተከታዮቹ ነጥቦች ተነስተዋል ፦ - ከ50,000 ያህል የምርጫ ጣቢያዎች የተከፈተው 25,000 ብቻ ነው። - በሶማሌ ክልል እና አፋር ክልል በትራንስፖርት ፣ በሎጅስቲክ ፣ በፀጥታች ችግሮች ምክንያት የምርጫ ጣቢያዎች አልተከፈቱም።…
#ምርጫ2013 : ሊጠናቀቀ 8 ቀናት ብቻ በቀሩት የምርጫ 2013 የመራጮች ምዝግባ እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ መዲና አዲስ አበባ አነስተኛ መራጮች ናቸው የተመዘገቡት ተብሏል።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ፥ እስካሁን በአዲስ አበባ የተመዘገበው ሰው ብዛት 200,903 ብቻ እንደሆነ ዛሬ ስለመናገራቸው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ አስነብቧል።
ወ/ሪት ብርቱካን ፥ እስካሁን የተመዘገቡ የመራጮችን ቁጥር “አነስተኛ” ያሉ ሲሆን “በነበሩት ቀናትና በነበሩት ጣቢያዎች ላይ ይሄ ብቻ መመዝገብ አልነበረበትም” ሲሉ ተናግረዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ 24 ሺህ ገደማ ምርጫ ጣቢያዎች እስካሁን አልተከፈቱም።
በአዲስ አበባ ከተማ 1,848 የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሎ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ 186ቱ እንዳልተከፈቱ ምርጫ ቦርድ መግለፁን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።

የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦
#Purpose #Tikvah
- በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 732 የላብራቶሪ ምርመራ 63 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል ፤ 55 ሰዎች አገግመዋል።
- በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓታት ከተደረገው 17 የላብራቶሪ ምርመራ 7 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።
- በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 181 የላብራቶሪ ምርመራ 72 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
- አማራ ክልል በ24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገ 339 የላብራቶሪ ምርመራ 79 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል፤ 8 አገግመዋል።
- አፋር ክልል ከተደረገው 156 የላብራቶሪ ምርመራ መካከል 17 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጣል
- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 130 የላብራቶሪ ምርመራ 23 ሰዎች ላይ ቫይረዱ ተገኝቷል ፤ 14 ሰዎች አገግመዋል።
- ኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 897 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 264 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 5 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
- ሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 189 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 92 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 6 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
@tikvahethiopia

ሀገር አቀፍ የኮቪድ-19 ሪፖርት :
የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ወደ 1 ሺህ እየተጠጋ ነው። የዛሬው ዕለታዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው አሁን ላይ 995 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
ባለፉት 24 ሰዓት 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 8,705 የላብራቶሪ ምርመራ 1,893 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 863 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 234,405 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,252 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 174,591 ሰዎች አገግመዋል።
#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ወደ 1 ሺህ እየተጠጋ ነው። የዛሬው ዕለታዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው አሁን ላይ 995 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
ባለፉት 24 ሰዓት 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 8,705 የላብራቶሪ ምርመራ 1,893 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 863 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 234,405 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,252 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 174,591 ሰዎች አገግመዋል።
#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
አጭር ቁጥራዊ መረጃ ፦
የመራጮች ምዝገባ ማካሄድ የጀመሩና አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል :
1. አዲስ አበባ - 1,662 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 1,848 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
2. አፋር - 0 (የምርጮች ምዝገባ የጀመረ የምርጫ ጣቢያ የለም) ምክንያት : የቁሳቁስ ማሰራጨት ችግር ፤ አጠቀላይ ያሉ የምርጫ ጣቢያዎች 1,432
3. አማራ - 6,558 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 12,199 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ - 286 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 699 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
5. ጋምቤላ -383 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 431 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
6. ኦሮሚያ - 8,545 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 17,623 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
7. ሀረሪ - 120 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 285 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
8. ድሬዳዋ - 209 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 431 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
9. ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች - 5,271 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 8,281 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
10. ሲደማ - 2,117 የመራጮች ምዝገባ የጀመሩ ጣቢያዎች ፤ 2,247 አጠቃላይ የምርጫ ጣቢያዎች
11. ሶማሊ - 0 (የምርጮች ምዝገባ የጀመረ የምርጫ ጣቢያ የለም) ምክንያት : የቁሳቁስ ማሰራጨት ችግር ፤ አጠቀላይ ያሉ የምርጫ ጣቢያዎች 4,057
በአጠቃላይ ካሉት 50 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች በ25,151 የምርጫ ጣቢያዎች ብቻ ነው ምዝገባ እየተካሄደ የሚገኘው።

በመላው ዓለም በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሚሊዮን እየተጠጋ ነው !
- 138,899,975 በቫይረሱ የታያዙ
- 2,987,155 ህይወታቸው ያለፈ
- 111,678,970 ያገገሙ
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አሁንም አስከፊነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቀጠለ ሲሆን በየዕለቱ በአስር ሺዎች እየሞቱ ፣ በመቶ ሺዎችም በቫይረሱ እየተያዙ ነው።
ለምሳሌ ትላንት ሚያዚያ 6 ብቻ : ከዎርልዶሜትር ባገኘነው መረጃ 804,362 ሰዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረሰ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ 13,577 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
በትላንትናው ዕለት ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡት በህንድ ሲሆን 200 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ከፍተኛው ሞት ደግሞ የተመዘገበው በብራዚል ነው ,3,462 ሰዎች ሞተዋል።
በአፍሪካ ደረጃ ስንመለከት በቫይረሱ የተያዙ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የተመዘገበባቸው ሀገራት የሚከተሉት ናቸው ፦
1. ደቡብ አፍሪካ - 1,561,559 ሰዎች
2. ሞሮኮ - 503,664 ሰዎች
3. ቱኒዝያ - 276,727
4. ኢትዮጵያ - 234,405
በአፍሪካ ደረጃ በከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የሚከተሉት ሀገራት በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል ፦
1. ደቡብ አፍሪካ - 53,498
2. ግብፅ - 12,570
3. ቱኒዝያ - 9,480
4. ሞሮኮ - 8,920
5. ኢትዮጵያ - 3,252
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እኛ ብንዘነጋውም ዛሬም የሰው ልጆችን ህይወት እንደቅጠል እያረገፈ ነውና ጥያቄ አይለያችሁ።
[Purpose - Tikvah]

የ4G LTE አገልግሎት በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ተጀመረ።
ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ክልል የ4G LTE አድቫንስንድ አገልግሎት አገልግሎት በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ባሉ ስድስት ከተሞች በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
የ4G LTE አድቫንስንድ አገልግሎት የጀመረባቸው ከተሞች ፦
- ወላይታ ሶዶ፣
- አርባ ምንጭ፣
- ቡታጅራ፣
- ወልቂጤ፣
- ጂንካ እና ሆሳዕና ናቸው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ክልል የ4G LTE አድቫንስንድ አገልግሎት አገልግሎት በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ባሉ ስድስት ከተሞች በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
የ4G LTE አድቫንስንድ አገልግሎት የጀመረባቸው ከተሞች ፦
- ወላይታ ሶዶ፣
- አርባ ምንጭ፣
- ቡታጅራ፣
- ወልቂጤ፣
- ጂንካ እና ሆሳዕና ናቸው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ግዚያዊ ፕሬዘዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት የኃላፊነታቸው ጊዜ ስላበቃ በትላንትናው ዕለት ኃላፊነቱ እንደተነሳላቸው ይታወቃል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ተሹሞለታል።
ዶ/ር ፋና ሀጎስ ብርሃኔ ናቸው የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነዉ የተሾሙት።
ዶ/ር ፋና ሀጎስ ማንናቸው ? ከMoSHE ያገኘነው መረጃ ፦
- የመጀመሪያ ድግሪያቸዉን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህግ ትምህርት ተቀብለዋል። ሁለተኛ ድግሪያቸዉን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ፍሪስቴትና ሶስተኛ ድግሪያቸዉን በዋርዊክ ዩኒቨርስቲ(Warwick University, UK) ተምረዋል፡፡
- ኬኒያ ናይሮቢ በሚገኘዉ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ የፖስት ዶክተሬት ተመራማሪ ሆነዉ ሰርተዋል፡፡
- በትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ አቃቤ-ህግ በመሆን ፤ በመቐለ ዩኒቨርስቲ ለ12 አመታት የህግ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በመሆን አገልግለዋል፡፡
- በዩኒቨርስቲዉ የስርዓተጾታ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተርና የህግና ስነ-መንግስት/Governance/ ኮሌጅ ዲን በመሆን አገልግለዋል፡፡
- የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትንት ሆነው ከመሾማቸዉ በፊት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ነበር፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ካሉ የቤተሰብ አባለቱ እንደሰማው ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንትነት ውድድር ሲደረግ ነበር። ተወዳዳሪዎችም የተለያዩ ሃሳቦቻቸውን ሲያቀርቡ ነበር የቆዩት።
ዶክተር ፋና ፕሬዜዳንት ከመሆናቸው በፊት ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይ ጊዜያዊ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት በመሆን ሲሰሩ ነበር።
ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይ የኃላፊነት ቦታውን ተረክበው የነበረው ከግንቦት 28/2005 ጀምሮ እስከ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲውን የመሩት ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት የስራ ኃላፊነቱ ከተነሳላቸው በኃላ እንደነበር አይዘነጋም።

#UnitedNationsSecurityCouncil
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ባለው ጉዳይ ላይ ዛሬ በዝግ ይወየያል።
የተመድ፥ የእርዳታ ዘርፍ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ ለተፈናቃዮች እርዳታ ከማቅረብ አንጻር ያሉትን ችግሮች በተመለከተ ለ 15ቱ የፀጥታው ም/ቤት አባላት ገለጻ ያደርጋሉ፡፡
የዛሬው ስብሰባ በአሜሪካ የተጠራ ነው።
ከዚህ በፊትም የካቲት 25/2013 ዓ.ም በተመሳሳይ ጉዳይ ስብሰባ የተካሔደ ሲሆን ፣ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ አባላት ሩሲያና ቻይና እንዲሁም በተለዋጭ አባሏ ህንድ ተቃውሞ የጋራ መግለጫ ሳይወጣ መቅረቱ ይታወሳል ሲል አል ዓይን በድህረ ገፁ አስነብቧል።
@tikvahethiopia @tikavhethiopiaBOT

#Russia #Ethiopia
ኢትዮጵያና ሩስያ በሰላማዊ የኑክሌር ኃይል አጠቃቀም ዙሪያ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን በሞስኮ መፈራረማቸውን ተሰምቷል።
የመግባቢያ ስምምነቱ የኑክሌር ኃይል በተመለከተ አዎንታዊ የሕዝብ አስተያየትን ለማስያዝ እና በኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል መስክ በትምህርት እና በስልጠና ትብብር መሥራት ላይ ያተኮረ ነው።
ስምምነቱን የፈረሙት አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ እና የሩስያ የኑክሌር ኃይል ትብብር ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ መሆናቸውን በሩስያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ኢትዮጵያና ሩስያ በሰላማዊ የኑክሌር ኃይል አጠቃቀም ዙሪያ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን በሞስኮ መፈራረማቸውን ተሰምቷል።
የመግባቢያ ስምምነቱ የኑክሌር ኃይል በተመለከተ አዎንታዊ የሕዝብ አስተያየትን ለማስያዝ እና በኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል መስክ በትምህርት እና በስልጠና ትብብር መሥራት ላይ ያተኮረ ነው።
ስምምነቱን የፈረሙት አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ እና የሩስያ የኑክሌር ኃይል ትብብር ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ መሆናቸውን በሩስያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መሰጠት ተጀመረ። በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት "በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ጅዳ" እስከ አሁን ሳይሠጥ የቆየው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዛሬ 3/08/2013 መሠጠት ጀምሯል። ፈተናው የፊታችን ረቡዕ ይጠናቀቃል። በሀገር ውስጥ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከየካቲት 29 - መጋቢት 2 ድረስ መሰጠቱ ፤ በአጭር ጊዜም ፈተናው ታርሞ ውጤትና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ…
#Update
ሲሰጥ የነበረው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተጠናቀቀ።
በኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ ት/ቤት ለተማሪዎች ሲሰጥ የቆየውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተጠንቋል።
ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለተማሪዎቹ አዲስ ፈተና አዘጋጅቶ በመላክ ከሚያዚያ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከትላንት ሚያዚያ 6 ድረስ ፈተናው ሲሰጥ ቆይቷል።
ኤጀንሲው ኃላፊ መድቦ ፈተናውን እንደተቆጣጠረ ተገልጿል።
የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ አበበ ጫላ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ፈተናው ትላንት በሰላም ስለመጠናቀቁ ተናገረዋል።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
@tikvahuniversity @tikvahethiopia

"...ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ፈጣሪ በመቅረበ በይቅርታና በንስሃ የሚመላለሱ ልጆች ያስፈልጓታል" - ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከመጪው አርብ ጀምሮ ሃገር አቀፍ የጸሎትና ምህላ መርሃ ግብር ሊጀመር መሆኑን ዛሬ አስታወቀ። ጉባኤው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መስፋፋትን፣ መጪው ሀገራዊ…
#Update
ሀገራዊ የፀሎት እና ምህላ እወጃ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሀገራዊ ፀሎት እና ምዕላ ማስጀመሪያ እና ማወጃ መርሃ ግብር ዛሬ ሚያዚያ 7 እያካሄደ ነው።
በመርሀ ግብሩ ላይ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ ከሁሉም የቤተ እምነቶች የተወኩሉ የእምነት አባቶች ፣ ሁሉንም ማህበረሰብ ይወክላሉ የተባሉ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ፣ ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል ተብሏል።