TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ቡናው ታዋቂ ደጋፊ ጥቃት ተፈፅሞት ህይወቱ አለፈ።

በኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊነቱ የሚታወቀው ቴዎድሮስ አበባው ወይም ደግሞ በቅፅል ስሙ "ቴዲ ቡናማው" ጥቃት ተፈፅሞበት ህይወቱ አልፏል።

ቴዎድሮስ ላይ እነማን ጥቃት እንደሰነዘሩ እና ህይወቱን እንዳጠፉ አልታወቀም።

ጥቃት አድራሾቹ ስለመያዛቸውም የተባለ ነገር የለም።

ኢትዮጵየ ቡናዎች እንዲህ ይላሉ ፦ "ቴዎድሮስ ክለቡ በሚፈልገው ቦታ ሁሉ ቀድሞ የሚገኝ እና በሁሉም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የሚወደድ ቅን ደጋፊያችን ነበር።"

የኢትዮጵያ ቡና በስራ አመራር ቦርድ ፣ በፅህፈት ቤት ሰራተኞች ፣ በአሰልጣኞች እና በተጫዋቾቹ ስም የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

ከስርዓተ- ቀብሩ ጋር እና ተያያዥ መረጃዎችን ክለቡ በቀጣይ እንደሚያሰውቅ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የትራፊክ ደንብ ተላላፊዎች በእርከን አንድ ተቀጥተን 100 ብር መክፈል ሲገባን 309 ብር ክፈሉ ተባልን በሚል ላነሱት ቅሬታ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ማብራሪያ ሰጥቷል።

ለ2ኛ ጊዜ እና ከ2ኛ ጊዜ በላይ ጥፋት ሲፈፀም የሚያስከትለው ቅጣት እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• 2 - 6 የገንዘብ ቅጣት 300 ብር

• 7 - 11 የገንዘብ ቅጣት 350 ብር

• 12 - 16 የገንዘብ ቅጣት 400 ብር

• 17-21 የ3 ወር የአሽከርካሪ ብቃት መረጋገጫ ፈቃድ እገዳ እና የተሃድሶ ስልጠና

• 22 - 27 ለ6 ወር የአሽከርካሪ ብቃት መረጋገጫ ፈቃድ እገዳ እና የተሃድሶ ስልጠና

• 28 እና ከዛ በላይ የአሽከርካሪ ብቃት መረጋገጫ ፈቃድ ለአንድ ዓመት ይታገድና የተሃድሶ ስልጠና ነው።

የትራፊክ ደንብ ተላላፊዎች የተጣለባቸውን ቅጣት በወቅቱ ባለመክፈል ምክንያት ከፍተኛ ወለድ እየተጠየቁ መሆን በተለያዩ አግባቦች ቅሬታ እያቀረቡ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ክፍያውን በወቅቱ ባለመክፈል የሚወልድባቸው የገንዘብ መጠን ከላይ በተያያዘው ሁለተኛው ምስል ተመልከቱ።

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ በእንግሊዝ "ቁዩ ዝርዝር" ውስጥ ተካተተች።

እንግሊዝ በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ4 አገራት ወደ ግዛቷ የሚገቡ ተጓዦች ላይ ከመጪው አርብ ጀምሮ እገዳ መጣሏን አስታወቀች።

ከዚህ ቀደም 30 አገራት ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳለች።

አሁን ከዝርዝሩ ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ኳታርን፣ ኦማንንና ሶማሊያን ማካተቷን አስታውቃለች።

እንግሊዝ ሀገራቱን ያገደችው የወረርሽኙ ክትባት መስጠት ዘመቻ ወሳኝ ደረጃ ላይ ባለበት ወቅት በደቡብ አፍሪካ እና በብራዚል የተገኙትን የመሰሉ አዲስ አይነት የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎችን ለመከላከል ነው ተብሏል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በእንግሊዝ 'ቀዩ ዝርዝር' ውስጥ ከተካተቱት ከኢትዮጵያ እና ከሦስቱ አገራት ከአርብ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ቀደም ብሎ ካሉት 10 ቀናት ጀምሮ ጉዞ ያደረጉ ወይም በዚያ ያለፉ ሰዎች ወደ እንግሊዝ እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም።

ተጓዦቹ የብሪታኒያ ወይም የአየርላንድ ዜጎች ወይም የረጅም ጊዜ ቪዛን ጨምሮ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ከሆኑ ግን እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።

የሚገቡት ሰዎች ግን በመንግሥት እውቅና ባላቸው ማቆያዎች ውስጥ ለ10 ቀናት ተለይተው እንዲቆዩና በሁለተኛና በ8ኛ ቀናቸው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ከተጓዦች በተጨማሪም ከተጠቀሱት አገራት በሚመጡ የንግድና የግል አውሮፕላኖች ላይም እገዳ ይጣላል። ይህ ግን የጭነት አውሮፕላኖችን እንደማይመለከት የወጣው መግለቻ አመልክቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"...ክትባቱን መስጠታችንን እንቀጥላለን" - ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ከኮቪድ-19 ክትባቱ ጋር ተያይዞ በኢትዮጰያ እስካሁን የገጠመ ችግር የለም ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ሊያ ፥ "የትኛውም ክትባት መጠነኛ የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ይችላል ፤ በተከተቡትና ባልተከተቡት መካከል እምብዛም ልዩነት የለም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ ከአስትራዜኔካ ክትባት ጋር ተያይዞ ወደ ፊት አዲስ ነገር ካለ እናሳውቃለን ያሉ ሲሆን ከክትባቱ ጋር ተያይዞ እስካሁን የገጠመ ችግር ባለመኖሩ ክትባቱን መስጠታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ክትባቱን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ብዥታዎችን ለማጥራት የማስተማሪያ ግብዓቶች በተለያዩ ቋንቋዎች እየተዘጋጁ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

ጀርመን ፣ ፈረንሳይ ፣ ጣሊያን፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና ስፔንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት የደም መርጋት ያስከትላል በሚል ስጋት አስትራዜኔካ የተሰኘው ክትባት እንዲቋረጥ አድርገዋል፡፡ ~ አል ዓይን

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
“ኢትዮጵያ ለድርድር ሁሌም ዝግጁ ናት ፤ ሙሌቱም ይቀጥላል" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብጽ የሶስትዮሽ ድርድር የሚቋጨው በሶስቱ አገሮች እንጂ በአደራዳሪዎች አይደለም ብለዋል።

“የአደራዳሪ ሚና ማስተባበር እንጂ ማጉረስ አይደለም” ያሉት አምባሳደር ዲና ፤ ሱዳንና ግብጽ አራት አደራዳሪ ወገኖች ይግቡ በሚል ያቀረቡት ሃሳብ ለኢትዮጵያ በይፋ እንዳልቀረበ ገልጸዋል።

አደራዳሪነት ማስተባበር እንጂ ውይይቱ የሚቋጨው በሶስቱ ተደራዳሪዎች እንደሆነ በስምምነት ሰነዱ መቀመጡን ገልጸዋል።

“ለአፍሪካ ህብረት ትልቅ ክብር አለን ፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካን ችግር በአፍሪካ የመፍታት ፅኑ አቋም አላት” በማለት ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ለድርድር ሁሌም ዝግጁ ናት። ሙሌቱ ይቀጥላል። ድርድሩ ግን ከሙሌቱ በፊትም ቢሆን ቢቋጭ ኢትዮጵያ ችግር የለባትም” ብለዋል።

በሌላ በኩል ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ አምባሳደር ዲና ፥ “በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ጉዳይ ኢትዮጵያ ዝም አላለችም፣ ውስጥ ለውስጥ ዲፕሎማሲዊ ስራ እየሰራች ነው” ሲሉ ገልፀዋል - ENA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የጎረቤት ሀገራት መሪዎች የኮቪድ- 19 ክትባት ተከተቡ።

የሱማሊያ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መከተባቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንቱ የተከተቡት የኦክስፎርድ አስትራዜኔካ ክትባት ነው።

የሱማሊያ የጤና ሚኒስትር የሆኑት ዶክተር ፋውዚያ አቢካርም የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወስደዋል፤ በሀገሪቱ የመጀመሪያ ክትባት የወሰዱ ሰው ናቸው።

ከፕሬዜዳንት ፈርማጆ በተጨማሪ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱት የጎረቤት ሀገር መሪ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌህ ናቸው። ባለቤታቸውም ካድራ ሞሃሙድ ሃይድ ክትባት መውሰዳቸው ተሰምቷል።

የአስትራዜኔካ ክትባት በርከት ባሉ የአውሮፓ ሀገራት ከደም መርጋት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ቢታገድም በሌሎች በርካታ ሀገራት ክትባቱ እየተሰጠ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሃላይደጌ ፓርክ በተከሰተ የእሳት አደጋ እስካሁን ከ100 ኪሎ ሜትር እስኩየር በላይ ሳርና ቁጥቋጦ ወድሟል ! ባለፈው ሀሙስ ቀትር ላይ በፓርኩ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተውን የእሳት አደጋ በአብዛኛው መቆጣጠር እንደተቻለ የፓርኩ አስተባባሪ አቶ መሐመድ እድሪስ ተናግረዋል። አደጋውን ለመቆጣጠር ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል። የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ፦ - የአፋር ክልል…
የእሳት አደጋው ከ4 ቀናት በኃላ በቁጥጥር ስር ዋለ።

በሃላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሄራዊ ፓርክ ተነስቶ የነበረውን የእሳት አደጋ ከአራት ቀናት ጥረት በኋላ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል።

በፓርኩ ሰሜናዊ ክፍል መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ/ም የተቀሰቀሰው የእሳት አደጋ መንስኤው #ሰው_ሰራሽ መሆኑ ከዚህ ቀደም መገለፁ አይዘነጋም።

ለአራት ቀናት የቆየው የእሳት አደጋ ከ100 ኪሎ ሜትር ስኩየር በላይ የሚሸፍን ቦታ ላይ በነበረ የፓርኩ ሳር ፣ ቁጥቋጦ ፣ የዱር እንስሳትና አእዋፍ ላይ ጉዳት ማድረሱን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
1 ዓመት ከትምህርት ገበታቸው የራቁት የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕጣፋንታ ምንድነው ?

By : Sheger FM 102.1 (ትዕግስት ዘሪሁን)

ለአንድ ዓመት ያህል ከትምህርት ርቀው የሚገኙት የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና መዳረጋቸውን እያሳወቁ ይገኛሉ።

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በደረሰበት ውድመት ጥገና እየተካሄደለት እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም መግለፁ አይዘነጋም።

ተማሪዎቹ መቼ ወደ ትምህርት እንመለሳለን ? ከሚለው ጥያቄ ባሻገር ብንጠራ እንኳን የፀጥታው ሁኔታ፤ ለደህንነታችን ምን ዋስትና አለ የሚለው ጉዳይ በእጅጉ እንደሚያስጨንቃቸው ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በተመራቂዎች ላይ ጥቃት ተከፍቶ ጓደኞቻችን አጥተናል፤ እኛም አካባቢው ሰላም ካልሆነ እና አስተማማኝ ሰላም ካልተረጋገጠ መሄድ አንፈልግም የሚል ሃሳብ አንስተዋል።

ተማሪዎቹ ካለብን ስጋት ነፃ ያደርገናል ያሉትን ሃሳብ የገለፁ ሲሆን ይኸውም፥ ሰላም ወዳለባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንበተን/ባለንበት አካባቢ ይመቻችልን/ ይህ ካልሆነ ደግሞ ወደ ሰፋፊ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተሸጋሽገን እንግባ የሚል ነው።

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ምን ይላል ?

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአስተዳደርና መሰረት ልማት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን አብርሃም፥ "ዩኒቨርሲቲው መልሶ ግንባታ ላይ ነው መልሶ ግንባታውን እንደጨረሰ ጥሪ ያደርጋል" ብለዋል።

እንደ አቶ ሰለሞ ገለፃ ዩኒቨርሲቲው መጋቢት አጋማሽ ተማሪዎች ይጠራል የሚል እቅድ መያዙን አሳውቀዋል።

ከዋስት እና ደህንነት ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ጥያቄ እንዲሁም ተማሪዎቹ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንመደብ ላሉትም አቶ ሰለሞን ፥ "ይሄ የኔ ውሳኔ አይደለም፤ በመንግስት የሚወሰን ነው ፤ አሁን መንግስት የያዘው ፕሮግራም ተማሪዎች ይሄዳሉ የሚል ነው" ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ቡናው ታዋቂ ደጋፊ ጥቃት ተፈፅሞት ህይወቱ አለፈ። በኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊነቱ የሚታወቀው ቴዎድሮስ አበባው ወይም ደግሞ በቅፅል ስሙ "ቴዲ ቡናማው" ጥቃት ተፈፅሞበት ህይወቱ አልፏል። ቴዎድሮስ ላይ እነማን ጥቃት እንደሰነዘሩ እና ህይወቱን እንዳጠፉ አልታወቀም። ጥቃት አድራሾቹ ስለመያዛቸውም የተባለ ነገር የለም። ኢትዮጵየ ቡናዎች እንዲህ ይላሉ ፦ "ቴዎድሮስ ክለቡ በሚፈልገው ቦታ ሁሉ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የቴዎድሮስ አበባው ገዳዮች ዙሪያ ምርመራ እየተደረገ ነው።

የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊ በሆነውን ቴዲ ቡናማው ገዳዮች ዙሪያ መንግስት ምርመራ እያደረገ መሆኑን ጓደኞቹ ተናግረዋል።

እንደ ጓደኞቹ ገለፃ ቴዲ ቡናማው የትራንስፖርት ሰራ እየሰራ እያለ ሶስት ሰዎች ናቸው ጥቃት ፈፅመው የገደሉት።

ጓደኞቹ እንደተናገሩት ይህን የትራንስፖርት አገልግሎት የመስጠት ስራ ከጀመረ አንድ ወር እንኳን አልሞላውም።

የቴዲ ሞት የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ደጋፊዎችን ብቻ ሳይሆን የመላው የኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰቦችን ያስደነገጠ፣ ያሳዘነ እና በቁጭትም ያንገበገበ ነው።

ሁሌም በተጠራበት የሚገኘው ፥ የታመሙት ለማሳከም የሚሮጠው፣ ሰዎችን ለመርዳት ዘውትር የማይደክመውን ቴዲን በዚህ አሳዛኝ ግድያ በማጣታቸው ጓደኞቹ እና የክለቡ ደጋፊዎች ልብ ተሰብሯል።

ቴዲ ኑሮውን ሊቀልስ እየተዘጋጀ እያለ ነው ህይወቱን የተቀጠፈው።

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች ምሽት ላይ ተገደሉ/ተዘረፉ የሚሉ ወሬዎች በተለያየ ጊዜ ይሰማሉ ፤ አምሽቶ መስራትም እጅግ አደገኛ እንደሆነ አገልግሎት ሰጪዎቹ የሚያነሱት ጉዳይ ሲሆን በማንኛውም ሰዓት የዜጎች በሰላም ወጥቶ የመግባት ደህንነት ሊረጋገጥ ይገባል ይላሉ።

Video : Nahoo Television (16 MB)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አሜሪካ በሰላም መተኛት ካሻት ከጦርነት ጨዋታዎች እራሷን ታቅብ" - ሰሜን ኮሪያ

አሜሪካ በሰላም መተኛት ካሻት ከጦርነት ጨዋታዎች እራሷን ታቅብ ስትል ሰሜን ኮሪያ አስጠነቀቀች።

የሰሜን ኮሪያ መሪ እህት ኪም ዮን ጆንግ የአሜሪካ አስተዳደር እንቅስቃሴን በኮሪያ ድንበር አካባቢ "የሚሰነፍጥ የባሩድ ሽታ ነው" ሲሉ ኮንነዋል።

እንቅስቃሴው በአካባቢው ሰላም ለማምጣት የሚረዳ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።

ኪም ዮ ጆንግ ይህን ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ወደ ደቡብ ኮሪያ ሄደው ለመወያየት መወሰናቸውን ካሳወቁ በኃላ ነው።

2ቱ የአሜሪካ ከፍተኛ ከፍተኛ ባለስልጣናት የፓሲፊክ ተሻጋሪ አጋርነትን ለማጠናከር በታለመ ጉዟቸው ጃፓንን እየጎበኙ ናቸው።

የመጀመሪያቸው በሆነው ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጉዞ፣ በቶኪዮ ከጃፓን አቻዎቻቸው ጋር ተነጋግረዋል።

የጉዟቸው ዓላማ "ቻይና አቋሟን እያፈረጠመች ባለችበት እና ሰሜን ኮሪያ ጠብ አጫሪነቷን እያባባሰች ባሉበት በዚህ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስን ፓሲፊክ ተሻጋሪ አጋርነት ይበልጡን አስረግጦ ለማሳየት" መሆኑ ተገልጿል።

ሁለቱ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶሽሚትሱ ሞቴጊ እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ኖቡ ኮሺ ጋር የተወያዩ ሲሆን ነገ ደግሞ ለተመሳሳይ ተልዕኮ ወደደቡብ ኮሪያ ሶል እንደሚያመሩ ታውቋል።

ምንጭ፦ Deutsche Welle & Voice Of America
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Alert😷

በኢትዮጵያ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 591 ደረሰ።

ዛሬም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ ጊዜ አንስቶ #ከፍተኛው የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ተመዝግቧል።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 5,338 የላብራቶሪ ምርመራ 1,490 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 18 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 660 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 178,108 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,573 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 144,488 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች 'በጥይት ተመትቶ' ህይወቱ አልፏል። አርቲስት ሃጫሉ በዛሬው ዕለት ምሽት 'ገላን ኮንዶሚኒየም' አካባቢ በጥይት መመታቱንና ህይወቱ ማለፉን በኦሮሚያ ክልል ያሉ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን 'ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር' #አረጋግጠዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግራሚ አዋርድ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን አስታውሷል።

Grammy Award እ.አ.አ 2020-2021 የዓለም የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ካጣቸው አርቲስቶች እና የሙዚቃ ሰዎች ዝርዝር ዉስጥ የሀገራችንን ድምፃዊ አርቲስት ሃጫሉን ሀንዴሳን አካቷል።

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ያለፈው ዓመት ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትቶ መገደሉ አይዘነጋም።

አርቲስት ሃጫሉን ሚሊዮኖች እንደ ድምፃዊ ብቻ ሳይሆን እንደነፃነት ታጋይ ፣ እንደጭቁን ህዝቦች ድምፅ፣ እንደሰብዓዊ መብት ተሟጋችም ጭምር ነው የሚያዩት።

በህይወት እያለ ለህዝብ ያቀረባቸው ሙዚቃዎቹ በሀገሪቱ ውስጥ ሲደረግ ለነበረው የፖለቲካ ፣ የነፃነት ትግል እና ጥያቄ ሚሊዮኖችን ለለውጥ እንዳነሳሳ ይታመናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ፆታዊ ጥቃቶች በትግራይ ፦

- እንደ ሆስፒታል ምንጮች በመቐለ ዓይደር ሆስፒታል ሪፈራል ሆስፒታል በየቀኑ በአማካኝ ከ3 የማያንሱ ሴቶች በተለያዩ አካላት ተደፍረው መጥተው ሪፖርት ያደርጋሉ።

- የትግራይ ክልል ሴቶች ቢሮ ከታህሳስ እስከ የካቲት ወር ባለው 3 ወራት 524 ሴቶች መደፈራቸውን በመቐለ እና ዓዲግራት ጤና ተቋማት ሪፖርት ተደርጓል።

- ከመቐለ ፣ እና ለመቐለ በቅርብ ርቀት ላይ ካሉ ወረዳዎች ፣ ከዓዲግራት ከተማ እና አካባቢው የተሰበሰበው ሪፖርት ውጭ በአብዛኛው የትግራይ ክፍል ስለተፈፀመው ጥቃት በተለያየ ምክንያት ሪፖርት ማግኘት አልተቻለም።

- በአይደር ሆስፒታል ብዙ ጥቃት ተፈፅሞባቸው አልጋ ይዘው የተኙ ሴት እህቶቻችን አሉ።

- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሴቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት አሳሳቢ ነው ብሏል።

- የትግራይ አስተዳደር ፆታዊ ጥቃቶቹን እንደሚቃወም፣ አጥብቆ እንደሚኮንን ፤ ድርጊቱን የፈፀሙ ለህግ መቅረብ አለባቸው የሚል አቋም መያዙን አሳውቋል።

ሰፋ ያለውን ሪፖርት ይመልከቱ👇
https://telegra.ph/Tigray---Ethiopia-03-16
Audio
"...የትግራይ ህዝብ በታሪኩ እንደዚህ ያለ ውስብስብ ነገር ገጥሞት አያውቅም"-ጄነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል (የትግራይ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ)

በቅርቡ በነበረ አንድ የትግራይ ድጋፍ ማድረጊያ መድረክ ላይ ጄነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል ባደረጉት ንግግር በግጭቱ የትግራይ ህዝብ ዋጋ እየከፈለ ነው ብለዋል።

ጄነራሉ የትግራይ ህዝብ በታሪኩ አሁን እንደገጠመው ያለውስብስብ ታሪክ ገጥሞት አያውቅም ሲሉ ህዝቡ ያለበትን ሁኔታ ሁኔታ ገልፀዋል።

አሁን ህዝቡ ያለበትን ሁኔታ እንደጥሩ አጋጣሚ ሊወስደው የሚፈልግ ኃይል አለ የሚሉት ጄነራል ዮሐንስ ነገር ግን ይህ የትም አያደርስም ሲሉ ተደምጠዋል።

መንግስት በትግራይ ያለውን ችግር አስተባብሮ ለማቆም ኃላፊነት አለበት የሚሉት ጄነራሉ በትግራይ ጦርነት የጫረው ወንጀለኛ ተጠያቂነት ይኖረዋል ብለዋል።

በዚህ መኃል ግን ህዝቡን የማዳን ስራ የሁሉም ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በትግራይ ካለው ግጭት አፍታት ጋር በተያያዘ ጄነራል ዮሐንስ፥"የግጭት አፈታትን በተመለከተ የዓለም ታሪክ የሚያስተምረን በጦርነት ከተጀመረ በጦርነት ያልቃል የሚባል ነገር የለም። አምልጦ ከተጀመረ በሂደት ደግሞ አቁመህ፣ተኩስ አቁም ብለህ ምህረት ሰጥተህ አጀንዳ ያለው ቁጭ ብሎ እንዲነጋገር አርገህ ለህዝቡ ሰላም ሲባል እንደዚህ ነው መቋጨት ያለበት" ብለዋል።

በተጨማሪ ከጥቂት ቀናት በፊት የትግራይ አመራሮች ከአምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር በነበራቸው መድረክ አንድ አምባሳደር በትግራይ ያለው ሁኔታ ማብቂያ እንዲኖረው ምን አይነት መንገድ ትከተላላችሁ ሲሉ ጥያቄ አቅርበው ነበር።

በወቅቱ ጄነራል ዮሐንስ፤ በመንግስት፣በTPLFና በነሱ በኩል ግልፅ የሆነ ተጨማሪ የመፍትሄ ሃሳብ እንደሌለ ገልፀው በግላቸው ግን ወታደራዊ አማራጭ ብቻ ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወስዱ እንዲያበረታቱ ተጠየቁ ! ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎችቸውን የኮቪድ-19 ክትባት እንዲወስዱ እንዲያበረታቱ ጠየቁ። ዶ/ር ፋውቺ ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ትራምፕ "በሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ዘንድ በጣም ታዋቂ ነው" በማለት የፕሬዝዳንቱ ቃል የበርካቶችን ሃሳብ እንደሚለውጥ ተናግረዋል። ትራምፕ ወጥተው…
ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ክትባት እንዲወስዱ መልዕክት አስተላለፉ።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን ደጋፊ የሆኑ ሰዎች ክትባት እንዲወስዱ ጥሪ አደረጉ፡፡

ትራምፕ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ክትባቱ አስተማማኝና ጥሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የዶናልድ ትራምፕ ይህ ያሉት ጽንፈኛ እና አክራሪ ደጋፊዎቻቸው በኮሮና ዙርያ የተዛባ አመለካከት ይዘው መቆየታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል።

በርካታ የትራምፕ ደጋፊዎች የኮሮና ቫይረስ መኖርን የማያምኑ ናቸው ፤ ክትባቱም ሌላ ዓላማ አለው ብለው ያስባሉ፡፡

በርካታ የዶናልድ ትራምፕ ነጭ አክራሪ ደጋፊዎች ክትባት አንከተብም ሲሉ የሚፎክሩ እንደነበሩ ዘገባዎች ማረጋገጣቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia