ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ሃዋሳ ገብተዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ሀዋሳ ከተማ የገቡ ሲሆን በሲዳማ ክልል አመራሮች እና በሲዳማ አባቶች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ በሚመረቀው የይርጋለም ከተማ አግሮ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ምረቃ ስነ ስርኣት ላይ ይገኛሉ፥ ፓርኩንም ያስመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ሌሎች የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም ሀዋሳ ገብተዋል።
PHOTO : Sidama Media Network & Dr. Abiy Ahmed
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Attention😷
በ24 ሰዓታት ውስጥ የ27 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 6,985 የላብራቶሪ ምርመራ 1,361 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 27 ሰዎች ሞተዋል።
ትላንት 355 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 172,571 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,510 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 141,195 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 454 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የኢትዮጵያ እና የሱዳን ድንበር ውጥረት ጦሱ ሱዳን ውስጥ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እየተረፈ ነው!
By : Almneh Mekonnen(ዶቼ ቨለ)
ሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ውስጥ ሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሱዳን ታጣቂዎች እንደሚዘርፏቸው፣ እንደሚደበድቧቸው፣ ከመኖሪያቸው አካባቢ እያባረሯቸውን እንደሆነ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያኑ እየተደበደቡ፣እየተዘረፉ፣ እየተባረሩ ያሉት የድንበር ውዝግቡ ከተባባሰ በኃላ መሆኑን ገልፀዋል።
እንደ ምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር መረጃ ባለፉት ወራት ከሱዳን በታጣቂዎች የተባረሩ 230 ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ተገደዋል።
አሁንም ሱዳን ውስጥ የሚኖሩን ኢትዮጵያውያን ችግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
ከሱዳን ከተባረሩት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዳንዶቹ እስከ 30 ዓመት ሱዳን ውስጥ የኖሩ ናቸው።
ተባረው ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት መካከል አንዳዶቹ የሱዳን ታጣቂዎች ማንነት/ዘርን መሰረት አድረግው የአማራ ተወላጆችን ተከታትለው ያጠቀሉ ሲሉ ከሰዋል።
ሱዳን ውስጥ ከዚህ ቀደም ዘር እና ሃይማኖትን ሳንለይ አብረን እንኖር ነበር አሁን ላይ ግን ሱዳን መሬት ላይ የአማራ ተወላጅ ሆኖ መኖር ፈተና ሆኗል ሲሉ ያለውን ሁኔታ አስረድተዋል።
መተማ ዮሐንስ አካባቢ የሰፈሩት ተባራሪዎች የመጠለያ እና የመሰረታዊ አገልግሎት ችግር እንዳለባቸው እያሳወቁ ነው።
የምዕራብ ጎንደር ዞን በበኩሉ ከሱዳን ለመጡት ዜጎች የተወሰነ ድጋፍ ቢደረግም የተደራጀ ባለመሆኑ የተሟላ አይደለም፤ ነገር ግን ትኩረት እንዲደረግ ከበላይ አመራር ጋር እየሰራን ነው ብለዋል።
እንደ ዞኑ አስተዳደር ፥ በድንበር አካባቢ ባለው ችግር በየዕለቱ ከሱዳን ከ8 እስከ 10 ሰዎች ወደሀገር እየገቡ ነው፤ በሀገር ውስጥም በድንበር አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተዘርፈዋል፣ ንብረታቸው ወድሟል ተገናቅለዋል።
@tikvahethiopia

አሜሪካ ስለህዳሴው ግድብ ፦
ኢትዮጵያ ፣ ግብጽ እና ሱዳን የታላቁ የኅዳሴ ግድብን (GERD) በተመለከተ ያላቸውን አለመግባባት በትብብር እና ገንቢ በሆነ ጥረት እንዲፈቱ አሜሪካ ድጋፍ መስጠቷን እንደምትቀጥል ማስታወቋን #ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።
ሦስቱ ሃገሮች ውጤታማ ወደሆነ ውይይት እንዲመለሱ እናበረታታለን ሲል የዋይት ሃውስ የብሄራዊ ጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ቢሮ አስታውቋል።
ውዝግቡ ገንቢ መፍትሄ እንዲያገኝ እና በክልሉ ያለው ውጥረት እንዲረግብ ለመርዳት በምንሰጠው ድጋፍ ከግድቡ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መያዛቸውን በማረጋገጥ መስራታችንን እንቀጥላለን ብሏል መግለጫው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ኢትዮጵያ በአየርላንድ የሚገኙትን አምባሳደሯን ጠራች !
By : Selam Mulgeta
የኢትዮጵያ መንግስት በአየርላንድ የሚገኙትን አምባሳደር እሸቱ ደሴን ወደ ሃገር ቤት መጥራቱን ከዲኘሎማቲክ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያ አምባሳደሯን የጠራችው ለምክክር እንደሆነ ነው የተገልፀው።
አየርላንድ ተመድ እና የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ግንባር ቀደሙን እንቅስቃሴ እያደረገች እንደሆነ ይነገርላታል።
አየርላንድ በጀመረችውን ተግባር የምትቀጥል ከሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ኤምባሲውን ሙሉ ለሙሉ እስከመዝጋት የሚደርስ ውሳኔን ሊያሳልፍ ይችላል ተብሏል።
አየርላድ የሁለቱን ሃገራት ነባር ወዳጅነት በማይመጥን እንቅስቃሴ ውሰጥ ናት ያሉት ዲኘሎማቲክ ምንጮች ወቅታዊ ተግባሯ በወደፊቱ የሃገራቱ ግንኙነት ላይም ቀላል የማይባል አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብለዋል።
* አየርላንድ ከሰሞኑን የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ጉዳይ እንዲመክር ጥሪ እንዳቀረበች መነገሩ በኃላም ስብሰባው ያለምንም ስምምነት መበተኑ አይዘነጋም።

#NewsAlert
አቶ አገኘሁ የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ!
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወሰዱ፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ ክትባቱን የወሰዱት ዛሬ በክልሉ በተጀመረው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡
ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ክትባቱን ወስደዋል፡፡ (AMMA)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አቶ አገኘሁ የመጀመሪያውን የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ!
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወሰዱ፡፡
ርዕሰ መስተዳደሩ ክትባቱን የወሰዱት ዛሬ በክልሉ በተጀመረው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡
ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ክትባቱን ወስደዋል፡፡ (AMMA)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#WHO #DrTedrosAdhanom
የአስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋትን ስለማስከተሉ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ በዚህ ስጋት አገሮች ክትባቱን ከመስጠት መቆጠብ የለባቸውም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
በትንሹ 5 የአውሮፓ ሀገራት አይስላንድ፣ ቡልጋሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ክትባቱን መስጠት አቁመዋል ፤ ይህ የሆነ አንዲት የዳኒሽ ሴት ከደም መርጋት ጋር በተገናኘ እንደሞተች ከተነገረ በኃላ ነው።
ይህንን በተመለከተ የዓለም ጤና ድርጅት በክትባቱ እና በደም መርጋት መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም ብሏል።
እስካሁን ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ አውሮፓውያን የአስትራዜኔካ ክትባትን ወስደዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም በበኩላቸው ፥ እስካሁን በመላው ዓለም 335 ሚሊዮን በላይ የኮቪድ-19 ክትባት መሰራጨቱን የገለፁ ሲሆን እስካሁን ከክትባቱ ጋር በተገናኘ ምንም ሞት አለመመዝገቡን አሳውቀዋል።

የኮቪድ-19 ክትባት በአማራ ክልል፦
- ባህርዳር ከተማ ፈለገህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል፡፡
- የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ፣ የጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ እና ሌሎች አመራሮች እና የጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ወስደዋል፡፡
- በሀገር አቀፍ በተሰጠው ኮታ መሰረት 108 ሺህ ዶዝ ክትባት ለአማራ ክልል ተሰጥቷል።
- በአማራ ክልል 251 ሺህ 597 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተመረምረው 7 ሺህ 392 ቫይረሱ ሲገኝባቸው 6 ሺህ 826 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡ 140 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። (ኤፍ ቢ ሲ)

የኮቪድ-19 ክትባት በአዲስ አበባ ፦
- በአ/አ የኮቪድ-19 ክትባት መሰጠት ተጀምሯል።
- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ ጤና ጣቢያ ነው የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር የተጀመረው።
- ክትባቱን በይፋ ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው።
- የኮቪድ -19 ክትባት በቅድሚያ ለጤና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል፤ ሌላው ህብረተሰብ ክትባቱ እስኪደርሰው ድርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
- እንደ አዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ ፥ የኮቪድ-19 ክትባት በዛሬው ዕለት በከተማዋ በሁሉም ጤና ተቋማት ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ፣ በእድሜና ለበሽታው ተጋላጭ ጤና ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሠብ ክፍሎች ይሰጣል።
- በአ/አ የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር ማስጀመሪያ ላይ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከገባ ጀምሮ በሽታውን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ግንባር ቀደም ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች ምስጋና ቀርቦላቸዋል።
Via Addis Ababa Press secretary

ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ።
By : EPA
የአ/አ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ዛሬ በአ/አ በተጀመረው የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር ክትባቱን ወስደዋል።
ዶክተር ዮሀንስ ፥ በክትባቱ ዙርያ የሚናፈሱት አሉባልታዎች ሁሉ ከእውነታ የራቁ ናቸው ብለዋል። ለዚህም ምስክርና ማሳያ ይሆን ዘንድ ራሳቸው የመጀመሪያውን ክትባት ወስደዋል።
ክትባቱ በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ክትባት የመጀሪያዉ ክትባት በተሰጠ ከ 8-12 ሳምንት ድረስ እንደሚሰጥ ነው ዶክተር ዮሀንስ ያስታወቁት።
ክትባቱ ቅድሚያ ለጤና ባለሞያዎች ይሰጣል ፤ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውንና እድሜያቸው የገፉ ሰዎች ደግሞ ከጤና ባለሞያዎች ቀጥሎ ክትባቱ እነደሚሰጣቸው ተገልጿል።

የኮቪድ-19 ክትባት በትግራይ ፦
የኮቪድ-19 ክትባት በአገር አቀፍ ደረጃ በመቐለ መሰጠት ተጀምሯል።
መርሐ ግብሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በመቐለ አጠቃላይ ሆስፒታል አስጀምረውታል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋና የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት ተከትበዋል።
ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች እና ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል። - ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኮቪድ-19 ክትባት በአገር አቀፍ ደረጃ በመቐለ መሰጠት ተጀምሯል።
መርሐ ግብሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በመቐለ አጠቃላይ ሆስፒታል አስጀምረውታል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋና የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት ተከትበዋል።
ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች እና ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል። - ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#NewsAlert
የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ለመቀየር የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ።
በቀጣይ 6 ወራት በጥናት ላይ ተመስርቶ የአማራ ህዝብን ታሪክና ስነ ልቦና የሚያንፀባርቅ ሰንደቅ ዓላማ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውልም ምክር ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል ነው የተባለው።
ነባሩ ሰንደቅ ዓላማ አንድን ፓርቲ የሚወክል እንጂ የአማራ ህዝብን ስነ ልቦና የማያንፀባርቅ በመሆኑ በህዝቡ ተቀባይነት ማጣቱም በምክር ቤቱ ተገልጿል። (AMMA)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ለመቀየር የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ።
በቀጣይ 6 ወራት በጥናት ላይ ተመስርቶ የአማራ ህዝብን ታሪክና ስነ ልቦና የሚያንፀባርቅ ሰንደቅ ዓላማ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውልም ምክር ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል ነው የተባለው።
ነባሩ ሰንደቅ ዓላማ አንድን ፓርቲ የሚወክል እንጂ የአማራ ህዝብን ስነ ልቦና የማያንፀባርቅ በመሆኑ በህዝቡ ተቀባይነት ማጣቱም በምክር ቤቱ ተገልጿል። (AMMA)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱት የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ ፦
ፖል ካጋሜ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ ሆነዋል።
የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ጃኔት ክትባቱን ሲወስዱ የሚያሳይ ፎቶግራፍም በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ይፋዊ ትዊተር ገጽ ላይ ተለቋል።
ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የኮሮና ክትባት የወሰዱ የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ ሆነዋል፡፡
እስካሁንም በሩዋንዳ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባን መውሰዳቸው ተገልጿል።

አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ።
የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ የኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ ክትባት በሶማሌ ክልል በይፋ አስጀምረዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በጅግጅጋ በሚገኘው የካራማራ ሆስፒታል በመገኘት ነው ክትባቱን ያስጀመሩት።
በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ገራዶች እና የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
የሶማሌ ክልል 108 ሺህ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክትባት መረከቡን ያስታወቁት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የሚገኙ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦች በተቻለ ፍጥነት ክትባቱን እንዲያገኙ ይደረጋል ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦ - የትግራይና አማራ ክልል አስተዳደር እና ወሰን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ የትግራይ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑን መግለፁ። - በ3 ቀናት ብቻ ከ70 ሺ በላይ ሰዎች ከምዕራብ ትግራይ መፈናቀላቸውን የትግራይ አስተዳደር ማሳወቁ። - የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሕወሓት የሚያሰራጫቸው የውሸት መረጃዎች ለአስተዳደሩ ፈተና እንደሆኑበት ማሳወቁ። - አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ…
#NewsAlert
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ተፈጽሟል ተብሎ ለቀረበው ውንጀላ ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው የቀጠናውም ሆነ ዓለም አቀፍ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ከቀናት በፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል «የዘር ማጥፋት/ማፅዳት» ተፈፅሟል ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም።
ብሊንከን በንግግራቸው በክልሉ የተፈጠረው ቀውስ እንዲመረመር እና የኤርትራ ወታደሮች እንዲሁም የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ግፊት እንዲደረግ መጠየቃቸው ይታወሳል።
የብሊንከንን ንግግር ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፡፡
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያቀረቡት ውንጀላ መሬት ላይ የሌለ እና ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መሆኑንም መግለጫው አንስቷል፡፡
መንግስትም ተፈጽሟል ለተባለው ማንነትን መሰረት ያደረገ የጥቃት ውንጀላ ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካባቢያዊም ሆኑ ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላትና አጣሪ ባለሙያዎች ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ዝግጁነት አስታውቋል፡፡
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም በጉዳዩ ላይ ከዘርፉ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር አስፈላጊውን ምርመራ ለማድረግ ስለመዘጋጀቱም ነው የገለጸው፡፡
https://telegra.ph/Tigray-03-13

Telegraph
#Tigray
በትግራይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ስለመፈፀሙ ከዓለም አቀፍ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት የኢትዮጵያ መንግስት ዝግጁ መሆኑ አሳወቀ ፦ መንግስት በትግራይ ክልል ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ተፈጽሟል ተብሎ ለቀረበው ውንጀላ ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው የቀጠናውም ሆነ ዓለም አቀፍ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጀ ብሊንከን…
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
በሲዳማ ክልል ይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ተመርቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የሲዳማ ክልል ባለስልጣናት ተገኘተው ነበር።
የኢንዱስትሪ ፓርኩ በ294.5 ሄክታር ላይ የተገነባ ሲሆን እምቅ የእሴት ጭማሬ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን፣ የወተት ተዋጽኦዎችን፣ ስጋ፣ የዶሮ እርባታ፣ ቡና እና ጥራጥሬዎችን እንደሚያጠቃልል ተገልጿል።
* ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይርጋለም የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ምዕራብ አርሲ ዞን ኤበን ወረዳ አርሲ ወረዳ ተጉዘው ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።