መሀመድ አል-አሩሲ ለፌዴራል ፓርላማ ለመወዳደር እጩ ሆኖ ቀረበ።
በመካከለኛው ምስራቅና በአረቡ አለም የኢትዮጵያን ገፅታ ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ያለው መሀመድ አል አሩሲ በምርጫ 2013 ላይ ለመወዳደር መዘጋጀቱ ታወቀ፡፡
መሀመድ አል - አሩሲ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በግብፅ ወገን የተሰረጩ የተሳሳቱ አስተሳሰቦችን ለማረም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ኢትዮጵያዊ ግዴታውን በመወጣት ይታወቃል።
መሀመድ አል - አሩሲ "የብልፅግና ፓርቲን" በመወከል በአዲስ አበባ ከተማ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ሆኖ መቅረቡ ተረጋግጧል ሲል የደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ከትግራይ ክልል ሁኔታ ጋር በተገናኘ የታሰሩ ተጠርጣሪዎች አያያዝ - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እና የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በሚገኘው እስር ቤት የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በመገኘት በታሳሪዎች አያያዝ ሁኔታ ላይ ክትትል አድርገዋል፡፡
በጉብኝቱ በትግራይ ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙትን እነ ዶ/ር አብረሀም ተከስተ ፣ አምባሳደር አባይ ወልዱ ፣ አቶ ስብሀት ነጋ ፣ አምባሳደር አባዲ ዘሙ ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሀጎስ ፣ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ፣ ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ ፣ ሜ/ጀነራል ይርዳው ገብረ መድኅን ፣ ሜ/ጀነራል ገብረ መድኅን ፍቃዱ ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋን ጨምሮ በአጠቃላይ 21 ታሳሪዎች የሚገኙበትን የእስር ሁኔታ ጎብኝተው ታሳሪዎችን አነጋግረዋል።
ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡
* ከላይ በተያያዘው መግለጫ ዝርዝሩን ያንብቡ።

ባለስልጣኑ ስልጣን ሊለቁ የፈለጉበት ምክንያት ምንድነው ?
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጠን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ በፍቃዳቸው ኃላፊነታቸውን እንደሚለቁ ገልፀዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ከስልጣን ሊለቁ የፈለጉበት ምክንያት ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጀ ግን ሀሰት መሆኑን ኢብባ አሳውቋል።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱአለም ፥ በቅርቡ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የተቋሙን ሰራተኞች ሰብስበው ተቋሙን እንደማይመሩና ኃላፊነታቸውን በፍቃዳቸውን ለመልቀቀ መወሰናቸውን አሳውቀዋል ሲሉ ገልፀዋል።
ዶክተር ጌታቸው ኑሯቸውን በአሜሪካ አድርገው ለማስተማር እና ለመርምር ስራ ወደኢትዮጵያ መመለሳቸው የተገለፀ ሲሆን ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ወንድወሰን ፥ ዋና ዳይሬክተሩ ወደኃላፊነት ሲመጡ ለ2 ዓመት ብቻ ለመስራት እንደሆነ ተናግረዋል ብለዋል።
በማስተማር እና በምርምር ስራ ጊዜያቸውን ማሳለፍ የበለጠ እንደሚወዱ የተናገሩት ዶ/ር ጌታቸው ለሰራተኞችም ያሳወቁት ይህንኑ ነው ፤ ከዛ ውጭ የሚናፈሰው በሙሉ ሀሰተኛ መረጃ ነው ሲሉ አቶ ወንድወሰን አሳውቀዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን (ኢብቦ) ተጠሪቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን ጉዳዩ በቦርድ ውሳኔ እስከሚፀድቅ መልቀቂያቸው ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ ተብሎ መናገር እንደማይቻል ተገልጿል።
Via Sheger FM 102.1

በመተማ ወረዳ ተላላፊ የውሻ በሽታ ተከሰተ።
በምዕራብ ጎንደር በመተማ ወረዳ ተላላፊ የውሻ በሽታ መከሰቱን የወረዳው እንሰሳት ሀብት ልማት ጽ/ቤት አስታውቋል።
በሽታው በተለያዩ ቀበሌዎች የተከሰተ ሲሆን በሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ በጽ/ቤቱ በኩል የእብድ ውሻ ተላላፊ በሽታ/Rabbies/ ክትባት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
አስካሁን ሸመለጋራ ቀበሌ፣ ኩመር አፍጥጥና ገንዳውሀ ብርሽኝ ቀበሌ ከ600 በላይ ወሻዎች ክትባት የተደረገላቸው መሆኑን የመተማ ወረዳ እንስሳት ሀብት ልማት ጽ/ቤት አሳውቋል።
ማህበረሰቡ በሽታው ከፍተኛ ጉዳት ሳያደርስ መከላከል እንዲቻል ወደ ተቋሙ በመምጣት ለውሻዎቹ ክትባቱን እንዲያደርግ ጥሪ እየቀረበ እንደሚገኝ የመተማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።

TIKVAH-ETHIOPIA
የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈው የሰንዓው እሳት ፦ የመን ሰንዓ በርካታ ኢትዮጵያውያን በነበሩበት አንድ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተነሳ እሳት በርካቶች ሞተዋል። በርካታ ከአፍሪካ ቀንድ በተለይም ደግሞ ከሀገራችን #ኢትዮጵያ የሄዱ ስደተኞች በተጠለሉበት በዚህ ስፍራ የተነሳው እሳት 30 ሰዎችን ሲገድል 170 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል ሲል ዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (አይኦኤም) ገልጿል። ከስደተኞቹ…
"በየመን በርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አልፏል" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
በየመን በደረሰው የእስር ቤት ቃጠሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው ማለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው ሳምንታዊ መግለጫ ፥ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያውያን ትክክለኛ ቁጥር እየተጣራ ነው ብለዋል።
በኦማን መዲና ሙስካት የሚገኘው የኢትዬጵያ ኤምባሲም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።
ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ከአደጋው የተረፉትን ከአካባቢው ለማስወጣት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ማብራራታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በሐይቅ ከተማ የእሳት አደጋ ተከሰተ።
በሐይቅ ከተማ አስተዳደር ምክኒያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የእሳት አደጋ ተከሰተ።
በቀበሌ 2 ከረሞፋ መስጅድ ግቢ ውሥጥ የእስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ግቢ የልጆች ቁርአን መቅሪያ መድረሳ ቦታ ቃጠሎ ደርሶበታል።
ህብረተሰቡ ቃጠሎውም ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳይሰራጭ በመከላከል ላይ ይገኛል።
የቃጠሎውን መንስኤ የሐይቅ ከተማ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

#ምርጫ2013 አዲስ አበባ ፦
- ኢዜማን ወክለው በአዲስ አበባ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች ታውቀዋል።
- ባልደራስ ከመኢአድ እና አብን ጋር በምርጫው እርስ በእርስ ላለመፎካከር ስምምነት አድርገዋል።
በምርጫ 2013 #ኢዜማን ወክለው በየወረዳው ለፓርላማ ከሚወዳደሩት 23 እጩዎች መካከል የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፣ የፓርቲው ም/መሪ አንዷለም አራጌ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ የኢኮኖሚ ምሁሩ ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌና አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን ተጠቃሽ ናቸው።
ኢዜማ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ካቀረባቸው 138 እጩዎች መካከል ታዋቂው የኢኮኖሚ ተንታኝና የፓን አፍሪካ ንግድ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ፣ አቶ ክቡር ገና ይጠቀሳሉ።
ባልደራስ ፣ መኢአድ እና አብን በምርጫ 2013 እርስ በእርስ ላለመፎካከል ስምምነት አድርገዋል።
የኢዜማ 23ቱ እጩዎች እነማን ናቸው ?
(በInstant View ይመልከቱ-በአዲስ አድማስ)
https://telegra.ph/Ethiopia-Election-2013-AA-03-08

Telegraph
Ethiopia Election 2013 AA
#ምርጫ2013 ከፍተኛ ፉክክር የሚጠበቅባት አዲስ አበባ ፦ - ኢዜማን ወክለው በአዲስ አበባ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች ታውቀዋል። - ባልደራስ ከመኢአድ እና አብን ጋር በምርጫው እርስ በእርስ ላለመፎካከል ስምምነት አድርገዋል። በምርጫ 2013 ኢዜማን ወክለው በየወረዳው ለፓርላማ ከሚወዳደሩት 23 እጩዎች መካከል የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የፓርቲው ም/መሪ አንዷለም አራጌ፣ አቶ…
2 የቢራ ፋብሪካዎች ታሸጉ።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒድቴር አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ባላቸው 2 የቢራ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ዛሬ አስታወቀ።
2ቱ የቢራ ፋብሪካዎች ስማቸውን አልተገለፀም።
ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን በዓለም ዓቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ዘርግቼ እየተንቀሳቀስኩ ብገኝም አንድአንድ የማኑፍክቸሪንግ ተቋማት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ብሏል።
ይህንንም ተከትሎ በተደረገ ክትትል ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በተገኙ 2 የቢራ ፋብሪካዎች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።
አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት ቢዝነስ ፕላን ማዘጋጀት ሲኖርባቸው የራሳቸውን የትርፍ ህዳግ ለማስፋት ሲሉ እንደፈለጉ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ተገቢነት የሌለው እና ወንጀል መሆኑ ተገልጿል።
ሁሉም የማምረቻ ተቋማት እንደዚህ ያለህገወጥ ተግባር ከመፈጸም መቆጠብ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
@tikvahethiopia

የታለ (Yet’Ale) ፤ አሁን ሁሉን አቀፍ ፤ ፈጣን፤ አንድ የገበያ ቦታ በእጅዎት ላይ አለ::
ይግዙ:: ይሽጡ፤ ያትርፉ፤ተጨማሪ ገንዘብ ይሥሩ::
መተግበሪያውን አሁኑኑ ይጫኑ!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.inmp.yetale
በኢትዮጵያ ብቻ። Only in #Ethiopia.

#NationalBankofEthiopia
ብሔራዊ ባንክ ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉን የገንዘብ መጠን በድጋሜ ዝቅ ማድረጉ ተገለፀ።
ባንኩ ትናንት ካቲት 29 ጀምሮ ይህንንና መሰል ጉዳዮችን የያዙ መመሪዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
በማሻሻያዉ መሰረት ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉ የገንዘብ መጠን ለድርጅቶች ወደ 200,000 ብር እንዲሁም ለግለሰቦች ወደ 100,000 ብር ዝቅ እንዲል አድርጓል።
ባንኩ ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ገደብ የሚጥል መመሪያ ሲያወጣ በ6 ወራት ዉስጥ ለ2ተኛ ጊዜ ሲሆን ከ6 ወራት በፊት የወጣዉና እስካሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆዬዉ መመሪያ ከባንክ ዉጭ ሊኖር የሚችለዉ የገንዘብ መጠን 1.5 ሚሊዮን ብር የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በተመሳሳይም የዳያስፖራ አካዉንት ባለቤቶች የገቢ ንግድ ላይ የሚሳተፉበት አካሄድ እንዲሁ ማሻሻያ ተደርጎበታል።
በዚህ መሰረት እነዚሁ ደንበኞች በአስመጭነት መሳተፍ የሚችሉት ባንኩ ቅዲሚያ ትኩረት እንዲያገኙ መርጫቸዋለሁ ባላቸዉ ዘርፎች ላይ የተወሰነ የዉጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንደሚኖር ተገልጿል፡፡
እነዚህ ለተለያዩ የፋብሪካ ምርቶች በግብዓትነት የሚያገለግሉ ጥሬ እቃዎች ፣ መድሃኒቶች ፣ እንዲሁም በተለዬ አስፈላጊ የተባሉ የምግብ እና ምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ብቻ እንዲሆን ታስቦ መመሪዉን ማሻሻል እንዳስፈለገ የባንኩ ምክትል ገዥ አስረድተዋል፡፡
ምንጭ፦ አሀዱ ቴሌቪዥን

14 አፍሪካዊያን ስደተኞች ባህር ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።
ወደ ጣልያን ሀገር ለመሻገር የሞከሩ 14 አፍሪካዊያን ስደተኞች ባህር ውስጥ ሰጥመው ህይወታቸው ማለፉን Al Ain News (አል ዓይን) CGTN አፍሪካን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ስደተኞች በጣልያኗ ላምፔዱሳ ደሴት በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር በማሰብ በሁለት አነስተኛ መጓጓዣ መርከቦች አማካኝነት ሲጓዙ ነበር በሜድትራኒያን ባህር ላይ አደጋ የደረሰባቸው።
በዚህ የመስጠም አደጋ ምክንያት 4 ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 14 ስደተኞች ሲሞቱ 139 ያህሉ ደግሞ የቱኒዝያ ብሔራዊ ዘብ እንደታደጋቸው ተዘግቧል።
ነገር ግን ወደ በጣልያን አድርገው ወደ አውሮፓ ለመግብት በመርከቦቹ ምን ያህል ስደተኞች ጉዞ አንደጀመሩ እስካሁን አልታወቀም።
ተጨማሪ የሞቱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ በሚልም አስከሬን ፍለጋው እንደቀጠለ ተጠቁሟል።
ባሳለፍነው ሳምንት ከ 20 በላይ ስደተኞች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለመግባት በሚል ጉዞ የጀመሩ ስደተኞች ጅቡቲ ላይ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተገፍትረው እንዲሰጥሙና እንዲሞቱ መደረጉ የሚታወስ ነው።

የ2ተኛው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ተሰጥቷል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ትላንት የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም መጀመሩ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለት የ2ኛው ቀን ፈተና በመላ ሀገሪቱ ሲሰጥ ውሏል።
ከፈተናው ሂደት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች ከተማሪዎች እና ከተማሪ ወላጆች እያደረሱን ይገኛሉ።
አንዳንድ ተማሪዎች ስልክ ይዞ የመገኘትም ነገር እንደነበረ ተፈታኞች ለቲክቫህ እያሳወቁ ነው።
በተለያዩ የቴሌግራም ግሩፖች ላይ ሞባይል ስልክ ይዘው የሚገቡ ተማሪዎች ፈተናውን በማንሳት እያሰረጩ እንደሆነና ይህንንም የሚገልፅ በቂ ማስረጃ እንዳላቸው የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተፈታኞች እየገለፁ ነው።
እኛም ጉዳዩ ለትምህርት ሚኒስቴር አካላት ለማሳወቅ ጥረት አድርገናል።
በቀጣይ ቀናት ፈተናዎች በሞባይል ስልክ ዙሪያ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ እያሳሰቡ ነው።
ባደረግነው ማጣራት ፈተና ይሰራጭባቸዋል ከተባሉት እንዲሁም ቴሌግራም ላይ ካየናቸው ግሩፖች አንደኛው ሙሉ በሙሉ ሲጠፋ ፣ አንደኛው ግሩፕ ስሙ ተቀይሯል ፤ ሌላኛው ደግሞ በውስጡ የነበሩት መልዕክቶች ጠፍተዋል።
ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ስለሁለቱ ቀናት ስለነበረው የፈተና ሂደት በተመለከተ በአስተያየት መስጫው ላይ መልዕክት ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

የዝሆን ሎተሪ ወጣ!
ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ዝሆን ሎተሪ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል ፦
1ኛ. 7,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0348349
2ኛ. 4,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 1523600
3ኛ. 2,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 1707653
4ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0042287
5ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0404416
6ኛ. 200,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 1669816
7ኛ. 100,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 1565394
8ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 13294
9ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 86624
10ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 3,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 63652
* ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮችን ከላይ በተያያዘው ምስል ይመልከቱ !
ምንጭ፦ የብሄራዊ ሌተሪ አስተዳደር

አቶ ልደቱ ከፖለቲካ ተሰናበቱ።
አቶ ልደቱ አያሌው በጤናዬ ላይ የተሰጠኝ የሀኪም ምክርና ትዕዛዝ እንዲሁም የሀገሪቱ አጠቃላይ የፖለቲካ ሁኔታ ለተሳትፎ የሚጋብዝና አበረታች ባለመሆኑ ፤ በተለይ የገዥው ፓርቲና መንግስት አፋኝነት እና ከፍተኛ የአምባ ገነንነት መንፈስ መላበስ የሚጠበቀውን ለውጥ ለሀገሪቱ የማያመጣ ከመሆኑ ባሻገር ለመግባባት ፍላጎት የሌለው በመሆኑ ከፖለቲካ ለመሰናበት ምክንያት ሆኖኛል ብለዋል።
አቶ ልደቱ በህይወት ለመቆየት የግድ ይህንን ውሳኔ መወሰን አለብኝ ብለዋል።
አቶ ልደቱ ፥ "ወደፊት የጤና ሁኔታዬ ተሻሽሎ እስከመጨረሻው በፖለቲካ ሒደቱ ለመቀጠል ለራሴ የገባሁትን ቃል ለመፈጸም ፈጣሪ ዕድል እንደሚሰጠኝ ተስፋ እያደርጋለሁ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማት ያለኝን ልባዊ ምኞት እገልጻለሁ" ብለዋል።
አቶ ልደቱ የስንብት መልዕክታቸውን በዝርዝር ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Ato-Lidetu-Ayalew-03-09

Ato Lidetu Ayalew
ስንብት፣ ለመሰንበት ! (ልደቱ አያሌው፣ የካቲት 29/2013 ዓ.ም.) ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የሕልውና አደጋ ውስጥ ትገኛለች። ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ የሆነ የዕውቀት፣ የአቅምና የቅንነት ድክመት ያለበት በመሆኑ ሀገሪቱ የገጠማትን ችግር ከማቃለልና ከመፍታት ይልቅ የበለጠ እያባባሰውና እያወሳሰበው ይገኛል። በዚህም ምክንያት ሀገራችን ሕልውናዋን የሚፈታተን አሳሳቢ የርስ በርስ ግጭት ውስጥ…
ዶ/ር አብይ የአፍሪካ የመብት ተቋም በትግራይ ያለውን ሁኔታ እንዲመረምር ኢትዮጵያ ፍቃደኛ ናት አሉ።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ የመብት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል ለሚቀርብ ቅሬታ የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የሰዎች መብቶች ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ሆኖ እንዲያጣራ መፍቀዳቸውን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአፍሪካ ሕብረት ሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ባቀረቡት ሀሳብ እንዳሉት ለአፍሪካውያን ተብለው በተቋቋሙ ተቋማት መጠቀም እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡
በዚህም መሰረት በትግራይ ክልል ተፈጽሟል በሚል ለሚወራው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አፍሪካዊ ተቋም እንዲመረምር ኢትዮጵያ መፍቀዷን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በራሷ ግዛት ውሰጥ ሕግ ማስከበሯ ዓለም አቀፍ ተግሳፅ እንዳስከተለባት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው ለመፍታት እና ለማሸነፍ መነሳት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡ (AlAIN News)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia