TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Update

በኮልፌ አጠና ተራ የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር እንደተቻለ (እሳቱም እንደጠፋ) የኮልፌ አጠና ተራ ቲክቫህ አባላት ከቪድዮ ጋር አያይዘው አሳውቀዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ነጋዴዎች ከሱቆች እቃ በማውጣት ንብረት ለማትረፍ ጥረት ማድረጋቸውን አባላቶቻችን ገልፀዋል።

በእሳት አደጋው የደረሰውን ጉዳት ዝርዝር በሚመለከት በቀጥታ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ይፋ ሲደረግ እናሳውቃለን።

Video : Tewachew (TikvahFamily Kolfe) - 75 MB
@TikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KolfeAtenaTera #Efoyta

በኮልፌ አጠና ተራ የተነሳው የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተችሏል። አሁን ላይ በአካባቢ ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ፎቶ የቲክቫህ አባል (Tewachew) አጋርቷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በማይናማር ወታደሩ ስልጣን ተቆጣጠረ።

በቀድሞ በርማ በአሁኗ ማያንማር ወታደሩ ሥልጣን መቆጣጠሩ ተሰምቷል።

ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የኖቤል ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተለቅመው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል።

በሚየንማር በወታደሩ እና በሲቪሊያን አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት ተከስቶ ነበር።

እነ ሳን ሱ ቺ ከመታሰራቸው ቀደም ብሎ የመንግሥት ቴሌቪዥን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ ነበር።

ሚየንማር የዲሞክራሲያዊ ማሻሻያዎችን ማድረግ እስከጀመረችበት 2011 ድረስ በጥብቅ ወታደራዊ መንግሥት ነበር ስትመራ የቆየችው።

ባለፈው ሕዳር ወር በተደረገ ምርጫ የሳን ሱ ቺ ፓርቲ 'ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ' መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችለውን የመቀመጫ ቁጥር ማግኘት ችሎ ነበር። ሆኖም ወታደሮቹ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ቆይተዋል።

በዛሬው ዕለት የሀገሪቱ ወታደሮች የአገሪቱን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውና መሪያቸውም ኮማንደር ሚነ ኦንግ ሌይንግ መሆናቸው ተናግረዋል።

ወታደሩ ለአንድ ዓመት በስልጣን ላይ እንደሚቆይም ገልጿል።

በርካታ ወታደሮች በአገሪቱ ዋና ከተማ ናይፒታው እና በሌላኛዋ ዋንኛ ከተማ ያንጎን ይታያሉ።

የሞባይል እና ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም ስልክ በስፋት የተቋረጠባቸው ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሲሆን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ሥርጭት ለማድረስ እክል እንደገጠመው በመግለፅ ተቋርጧል።

በርካታ ወታደሮች በተለያዩ ቦታዎች እየሄዱ የሲቪል አስተዳደሩ ሚኒስትሮች የነበሩ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Maynmar

የማይናማር ሰራዊት የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠሩ እንዲሁም የሀገሪቱን የሲቪል መሪዎች ለቃቅሞ ማሰሩን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

እስካሁን አሜሪካ፣ ህንድ ፣ ሲንጋፖር፣ አውስትራሊያ በማይናማር ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

UN ፣ ሂውማን ራይትስ ዎች ድርጊቱን አውግዘዋል። ሂውማን ራይት ዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ የታሱሩ መሪዎች እንዲፈቱ ጠይቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ዓለም ስለማይናማር ምን አለ?

#Australia

የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ማራይዝ ፓይኔ ፤ በማይናማር ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣን መቆጣጠሩ እና ሲቪል መሪዎች መታሰራቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል። ወታደሩ የህግ የበላይነትን እንዲያከብር ፣ ችግሮችን በህግ ብቻ እንዲያስተካከል፤ በአስቸኳይ የሲቨል መሪዎችን እና ሌሎችንም ያለህግ አግባብ ያሰራቸውን አካላት እንዲለቅ ጥሪ አቅርበዋል።

#UnitedStates

አሜሪካ በማይናማር እየሆነ ያለውን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን ገልፃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጉዳዩ በጣም እንዳሳሰባቸውን ገልፀዋል፤ ወታደሩም ውሳኔውን በአስቸኳይ እንዲቀለብስ አሳስባዋል። የማይማር ወታደር ሁሉንም የሲቪል መሪዎች እንዲፈታ፣ የበርማን ህዝብ ፍላጎት እንዲያከብር (Nov 8 የተካሄደውን ምርጫ ማለታቸው ነው) አሳስበዋል። ብሊንከን አሜሪካ ከበርማ ህዝብ ጎም እንደምትቆም ገልፀዋል።

#UnitedNation

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴክሬተሪ ጀነራል አንቶኒዮ ጉተሬዝ የማይናማር የሲቪል መሪዎች መታሰራቸውን በእጅጉ አውግዘዋል። ወታደሩ ስልጣን ጠቅልሎ መያዙ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል። ድርጊቱ በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሪፎርም ላይ ችግር ሊያስከትል እንደሚችልም ጠቁመዋል።

#India

የህንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማይናማር ጉዳይ እንዳሳሰበው ገልጿል። ህንድ በማይናማር የዴሞክራሲያዊ ሽግግር እንደምትደግፍ ገልፃ ፤ የህግ በላይነት እና የዴሞክራሲያዊ ሂደት መከበር አለበት ብላለች፤ በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለች እንደሆነ አሳውቃለች።

#Singapore

ሲንጋፖር በማይናማር እየሆነ ያለው ጉዳይ እንዳሳሰባት የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጻል። ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለች እንደሆነም ገልፃለች።

#HumanRightsWatch

የHRW የኤዥያ ዳይሬክተር ብራድ አዳምስ በአስቸኳይ ያላምንም ቅድመ ሁኔታ ሳን ሱቺ እና ሌሎችም ያለህግ አግባብ የታሰሩ አካላት እንዲፈቱ ጠይቀዋል። የወታደሩ ድርጊት በህዳር ወር የተካሄደውን ምርጫ እና የማይናማር ህዝብ የራሱን መንግስት የመምረጥ መብት የሚጋፋ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#KolfeAtenaTera በአካባቢው ላይ በርካታ ሱቆች በመኖራቸው ምክንያት የዝርፊው ነገር እንዳሰጋቸው የቲክቫህ አባላት እያሳወቁ ነው። የእሳቱ መጠን ቀደም ብሎ ከነበረው በአንድ በኩን ትንሽ ቀንሷል። የእሳት አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን የቲክቫህ ኮልፌ አጠና ተራ አባላት ገልፀዋል። * ይህ ቪድዮ ከደቂቃዎች በፊት…
#update

ትላንት በኮልፌ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ መነሻ በማጣራት እርምጃ እንደሚወሠድና በቃጠሎው ለተጎዱ ነዋሪዎች ድጋፍ እንደሚደረግ ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ጠዋት በኮልፌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 "እፎይታ የገበያ ማዕከል" በመገኘት በእሣት ቃጠሎ የተጎዱ ነዋሪዎችን ማፅናናታቸውን እንዲሁም የደረሠውን ጉዳት በአካል ተገኝተው መመልከታቸው ተገልጿል።

በአደጋው የተቃጠሉ የሱቆች እንዲሁም የቤቶች ብዛት ፣ በጠቅላላው የደረሰውን ጉዳት በፖሊስ እየተጣራ መሆኑንም ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ገልፀዋል።

ወ/ሮ አዳነች ፥ የእሳት ቃጠሎው መነሻ ለማወቅ በሚደረገው ጥረት እና ለጋራ ሰላም ሲባል ምንም አይነት መረጃ ያለው ሰው ለህግ አስከባሪ እና ለፖሊስ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጠይቀዋል።

ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች መሰል አደጋ ዳግም እንዳይከሰት ለእሳት አደጋ መነሻ ከሆኑ ነገሮች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና አመራሩ ጉዳዩን በአፋጣኝ በማጣራት ርብርብ እንዲደረግ ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል።

VIA Addis Ababa Press Secretary
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DrArkebeOqubay

የኢኮኖሚ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ኣርከበ ዕቁባይ በአለም ባንክ አዘጋጅነት በተካሄደ “የምስራቅ ኤዢያ - አፍሪካ፡ የዌቢናር ውይይት ተሳትፈዋል።

በውይይቱ ላይ ዶ/ር ኣርከበ ፥ “የሚወጡ ዕቅዶችና የሚቀመጡ ግቦች እንደ ዶግማና ርዕዮተ ዓለም ሳይቆጠሩ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በማገናዘብ መስራት የኢኮኖሚ ዕድገት ያመጣል” ሲሉ ገልፀዋል።

ዘለቄታዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስመዝገብ የረጅም ጊዜ እቅድና ሰፊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል።

በአፍሪካ የሚፈለገውን የምጣኔ ሃብት እድገት እና ልማት ለማስመዝገብ የረጅም ጊዜ ራዕይ በማስቀመጥ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል” ብለዋል።

እቅዶቹን ከመመሪያ ባለፈ ሰፊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማካሄድ ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚያስፈለግ ነው ዶክተር ኣርከበ የጠቆሙት።

“በተለይም የሚታቀዱትን ዕቅዶችና የሚቀመጡ ግቦችን እንደ ዶግማና ርዕዮተ ዓለም ከመቁጠር ባለፈ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በማገናዘብ ተግራባራዊነቱ ላይ መስራት ይገባል” ሲሉ አመላክተዋል።

“ይህንንም ከቻይና እና ኤዢያ አገሮች መማር እንችላለን” ነው ያሉት።

ሁሉንም አዋጭ ፖሊሲዎችና መንገዶች በመጠቀም በየጊዜው ከሚከሰቱ ሁነቶች ጋር ተናባቢና ተዛማጅ የሆኑ ተግባራዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባም ዶክተር ኣርከበ ተናግረዋል።

Video : Doctor Arkeb Oqubay , ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FireAlert

በአዲስ አበባ ቦሌ ዘ ሃብ ሆቴል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከሰተ።

አደጋው ከደቂቃዎች በፊት ታምሪን መኪና መሸጫ አካባቢ ዘ ሀብ ሆቴል ፊት ለፊት ባለ አንድ መኖሪያ ቤት መድረሱን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ገልጿል።

አደጋውን በቁጥጥር ሰር ለማዋል የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም የአካባቢው ሰዎች የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ሲሆኑ የእሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች በቦታው ደርሰው አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል በጥረት ላይ ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

በአዲስ አበባ ኡራኤል አካባቢ በመኖርያ ቤቶች ላይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ደርሷል።

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በቦሌ ክፍለ ከተማ ኡራኤል አካባቢ በሚገኙ መኖርያ ቤቶች ላይ ድንገተኛ የእሳት አደጋ መድረሱን አስታውቋል።

ባሁኑ ሰአት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት ዛሬ ይፋ ያደርጋል !

የኢትዮጽያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፓለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የቦርዱ ኮሙኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ እንደገለጹት፤ እስካሁን መስፈርቱን አሟልተው ጠቅላላ የተመዘግቡት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል እስእካሁን የደረሷቸውን 48 የምርጫ ምልክቶች ናቸው።

እነዚህን ምልክቶችም አስቀድሞ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቦርዱ ዛሬ ይፋ ያደርጋል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Gofa

ጎፋ ዞን አስተዳደር በትግራይ ሰብዐዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ገለፀ።

የዞኑ አስተዳደር ፥ በትግራይ ክልል በተፈጠረው ፀጥታ ችግር እና አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው፣ ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ነው ያሳወቀው።

"ለወገን ደራሽ ወገን ነው" በሚል ለተጎዱት እና ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከ 7 ወረዳዎች እና ከ2 ከተማ አስተዳደሮች እርዳታውን እንዳሰባሰበ ገልጿል።

ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ያሰባሰበውን ጤፍ = 107.4 ኩንታል ፣ ስንዴ 12 ኩንታል ፣ ባቄላ 4 ኩንታል በድምሩ 123.4 ኩንታል እህል በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዲደርስ መላኩን አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT