#NEBE
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ እየተከናወነ ይገኛል።
እስከአሁን ድረስ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ማስገባታቸውን ታውቋል።
የሚከተሉት ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ እንደተደረገላቸው ቦርዱ አሳውቋል ፦
1ኛ. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ - የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
2ኛ. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
3ኛ. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) - የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
4ኛ. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ
5ኛ. የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ
6ኛ. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) - ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ የተጠየቁ (በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል።)
የምርጫ ምልክት ያላስገቡ፣ እንዲቀይሩ የተገለፀላቸው ወይም መቀየር የሚፈልጉ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቁ ቦርዱ አሳስቧል።
የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎች ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኮሎምቢያው መከላከያ ሚኒስትር በኮቪድ19 ሞቱ።
የኮሎምቢያው የመከላከያ ሚኒስትር ካርሎስ ሆልመስ ትሩሂዮ ዛሬ ጥዋት በኮቪድ-19 ምክንያት መሞታቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታውቀዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ከዛሬ 14 ቀን በፊት ነበር በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ፤ ከዛም ቦጎታ በሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲከታተሉ ነበር።
@tikvahethiopiaBot

#Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,342
• በበሽታው የተያዙ - 437
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 549
አጠቃላይ 134,569 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,075 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 120,748 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
219 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,342
• በበሽታው የተያዙ - 437
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 549
አጠቃላይ 134,569 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,075 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 120,748 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
219 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ethiopia
የአውሮፓ ህብረት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ2021 የመጀመሪያቸው የሆነውን ስብሰባ ትላንት አካሂደዋል።
በስብሰባው የሩስያ ፖለቲካ ጉዳይ፣ ኮቪድ19 ስጋት፣በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ሁኔታ ተነስቶ ውይይት ተካሂዶበታል።
የአፍሪካ ሁኔታን በሚመለከት፦
የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል፥ "የአፍርካ ቀንድን ሁኔታ በጥልቀት አይተናል። በአካባቢው ሌላ ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዳይፈጠር ጥረት ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑንም ተገንዝበናል። በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታና በኢትዮጳያና ሱዳን የደንበር ውዝግብ ላይ ለሚኒስትሮቹ ማብራሪያ ሰጥቻለሁ" ብለዋል።
ሁኔታውን በቅርብ ለማየትና ከሚመለከታቸው አክላት ጋር ለመወይየትም የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፔካ ሀቪስት የአውሮፓ ህብረትን ከፍተኛ ልኡክ በመምራት በዚህ ወር መጨረሻ ወደ አካባቢው የሚሄዱ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአውሮፓ ህብረት፣በትግራይ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችና የሰብዊ መብት ጥሰቶች የሚያሳስቡት መሆኑን በመግለጽ ተደጋጋሚ መገለጫዎችን ማውጣቱ ይታወሳል።
የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ገብተው የርዳታ ስራቸውን በነጻ እንዲያከናዉኑ እንዲፈቀድላቸው፣ጋዜጠኞችና የሰባዊ መብት ድርጅቶቸ ወደ ክልሉ ገበተው ያለውን ሁኔታ እንዲያዩና እንዲዘግቡ በአጠቃላይ በክልሌ የህግ የበላይነት እንዲከበርና የዜጎች መብት እንዲጠበቅ በመጠየቅ፣ ይህ መሆኑ እስከሚረጋገጥ ድረስ ለዚህ ወቅት የሚሰጠውን 90 ሚሊዮን ኢሮ የበጀት ድጎማ የሚያዘገይ መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።
መንግስት ግን የሚቀርብበትን ክስና ውንጀላ ሲያስተባብል መቆየቱን፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት የዕርዳታ ድርጅቶች ወደ ክልሉ ገብተው የተራዶ ስራቸውን በነጻ እያከናወኑ እንደሆነ እየገለጸ እንደሞገኝ #ዶቼቨለ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
በየሳምንቱ 1,000 ዜጎች ወደ ሀገር ሊመለሱ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ከሳዑዲ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በየሳምንቱ 1000 ተመላሾች ወደ አገር እንደሚገቡ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አስታውቋል። በመንግስት በኩል በሚሰጡ አቅጣጫዎች መሰረት የተመላሾች ቁጥርም ይጨምራልም ሲል ገልጿል። ወደ ሳዑዲአረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የስደተኞች…
#UPDATE
በጅዳ ሹሜሲ የስደተኞች ማቆያ የነበሩ ዜጎች በዛሬው ዕለት ወደ አገር ተመለሱ።
ወደ ሳዑዲ አረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ የሚገኙና ላለፉት ወራት ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ የነበሩ ዜጎችን ወደ አገር የመመለስ ስራ መጀመሩ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት በጅዳ "ሹሜሲ" የህገወጥ ስደተኞች ማቆያ ውስጥ የነበሩ የመጀመርያዎቹ 293 ኢትዮጵያውያን ወንድ ስደተኞች ዛሬ ማክሰኞ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

አጫጭር መረጃዎች ኮቪድ-19 ፦
- ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በመላው ዓለም 15,879 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲሞቱ 528,698 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።
- በአሜሪካ በ24 ሰዓታት 4,045 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞተዋል ይህም አጠቃላይ የሟቾችን ቁጥር 435,452 አድርሶታል።
- ብራዚል ውስጥ በ24 ሰዓት የ1,206 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ 63,626 ሰዎች በበሽታው ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።
- ዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 1,631 ዜጎቿን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አጥታለች። በሀገሪቱ የተመዘገበው አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 100,162 ደርሷል።
- ሩስያ 564 ፣ ፈረሳይ 417፣ ስፔን 591 ፣ ጣልያን 541፣ ጀርመን 988፣ ሜክሲኮ 659 ፣ ደቡብ አፍሪካ 680 ፣ ኮሎምቢያ 381 ዜጎቻቸውን በ24 ሰዓታት ውስጥ በኮቪድ-19 የተነጠቁ ሀገራት ናቸው።
- በአህጉራችን አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 1,027 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ ከነዚህ መካከል 680 ሰዎች ከደቡብ አፍሪካ፣ 83 ከቱኒዚያ፣ 55 ከግብፅ፣ 15 ከሞሮኮ፣ 15 ከናይጄሪያ ይገኙበታል። በአህጉሪቱ የተመዘገበው አጠቃለይ የሟቾች ቁጥር ወደ 90 ሺህ እየተጠጋ ነው።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 100,837,646 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 2,167,096 ሰዎች ሞተዋል፤ 72,864,912 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
* ውድ አባላት ኮቪድ-19 ዛሬም የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነውና ሳትዘናጉ እራሳችሁ፣ ቤተሰባችሁ ጠብቁ።
#Purpose #Tikvah

#Metekel
በመተከል ዞን የሽፍታ እንቅስቃሴ እያገዙ 'በሁለት ቢላዋ የሚበሉ' የጸጥታ መዋቅሩ አባላት አካሄዳቸውን ማስተካከል አለባቸው ሲል በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል አሳሰበ።
ማሰበቢያው የተሰጠው በፌዴራል መንግስት የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል በመተከል ዞን ለሚሰሩ የጸጥታ ሃይል አመራሮችና አባላት ስልጠና እየሰጠ ባለበት ወቅት ነው።
ግብረ-ሃይሉ በዞኑ ከሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ውይይት በዞኑ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ላይ አንዳንድ የጸጥታ ሃይል አባላት እጃቸው እንዳለበት መገንዘቡን አስታውቋል።
በዞኑ የሚሰሩ የጸጥታ ሃይል አመራሮችና አባላት እንዲገመገሙና ሥልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑንም አሳውቋል።
ከጋንታ መሪ እስከ ብርጌድ አዛዥ የነበሩ 109 ፀረ-ሽምቅ፣ ልዩ ጥበቃና አድማ ብተና ልዩ ኃይሎች እንዲሁም በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ 37 የፖሊስ አመራሮች ስልጠናውን መውሰድ ጀምረዋል።
የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥና የግብረ-ሃይሉ አባል ብ/ጄነራል ዓለማየሁ ወልዴ፤ የጸጥታ ኃይሉ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችን በእኩልነትና በተዓማኒነት የማገልግል ሃላፊነት አለበት ብለዋል።
ከዚህ በተቃራኒ የሚደረጉ ማናቸውንም አይነት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ በፍጥነት መቆም እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።
"የህዝብ አገልጋይ መስለው የሽፍታውን እንቅስቃሴ እያገዙ 'በሁለት ቢላዋ ለመብላት' ሲነቀሳቀሱ የነበሩ የጸጥታ መዋቅሩ አባላት አካሄዳቸውን ማስተካከል አለባቸው" ብለዋል።
"ማንኛውም የጸጥታ ኃይል ከህዝብ እና አገር በታች መሆኑን አስገንዝበው ፤ የተዘበራረቀ አስተሳሰብ የሚያራምዱ የጸጥታ መዋቅር አባላት ቆም ብለው መስመራቸውን ሊያጠሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ባለ 5 ሊትሩን ዘይት ከ360 ብር በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ተጀመረ !
በዘይት ዋጋ ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ አከበረኝ ውጋገን በቅርቡ በዘይት ዋጋ ላይ የተከሰተው የዋጋ ጭማሪ ምክንያታዊ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ዋጋውን ለማረጋጋት የንግድ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱም የዘይት ዋጋ ከ2 ወር በፊት ወደ ነበረበት የመሸጫ ዋጋ እንዲመለስ የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
ይሁን እንጂ በስምምነቱ መሰረት ዘይት ዋጋ ቅናሽ አለማሳየቱን በመዲናዋ ጉዳዩ ለመከታተል የተቋቋመው ግብረ ሃይል በዳረገው ቅኝት ማረጋገጡን አንስተዋል፡፡
በዚህ መሰረት ቢሮው ባለ 5 ሊትሩን ዘይት ከ360 ብር በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው የገለጹት፡፡
በዚህ መሰረት በትናንትናው ዕለት 240 በሚደርሱ የንግድ ተቋማት ላይ በተደረገ አሰሳ 10 የሚሆኑት ከስምምነቱ ውጪ ሲሸጡ መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
እነዚህ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን የገለጹት አቶ ወጋገን፣ ከዛሬ ጀምሮ 5 ሊትሩንን ዘይት 360 ብር በላይ በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ የማሸግ እርምጃ ይወሰዳል ነው ያሉት፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ነጋዴዎች ምርታቸውን ወደ ክልሎች ለማውጣት ሙከራ ያደርጋሉ የሚሉት ምክትል ሃላፊው ይህንን ለመቆጣጠር ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል የዘይት አስመጪዎች እና አከፋፋዮች በተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ ብቻ እንዲሰሩ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ አሳውቀዋል። ~ ኤፍ ቢ ሲ

ችሎት!
የእነ አቶ ጃዋር መሀመድን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሞ የነበረው የተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመመልክት ነበር።
ይሁንና ተከሳሾቹ ቤተሰቦቻቸን ችሎት ስላልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላቸንን መስጠት አንችልም ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል።
አቃቢ ህግም ጊዜው በተገፋ ቁጥር የተከሳሾችም ሆነ የኛንም ጊዜ እየተወሰደ ይሄዳል ስለዚህ ጊዜው ታሳቢ ቢደረግ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
አቶ ጃዋርም የፍርድ ቤቱን ጊዜ ለመውስድ አይደለም ቤተሰቦቻችን መግባት ስላለባቸው ነው ሲሉ በፍርድ ቤቱ ያላቸውን እምነት ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል።
አቤቱታውን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመመልከት ለጥር 27 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Mekelle
ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት ጀምሯል።
በመቐለ እና አዲሽሁ ከተማ መካከል የሚገኝ ፋይበር በመቆረጡ ምክንያት በትግራይ ክልል የስልክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጸዓሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።
የስልክ አገልግሎት የተቋረጠው ከትናንትና ማምሻ ጀምሮ ነበር።
በመቐለ እንዲሁም ሌሎች አቅራብያ አካባቢዎች ያሉ ቡድኖች ገብተው ጥገና አድርገው አገልግሎቱ ጀምሯል።
እንደ ወ/ሪት ፍሬህይወት ገለፃ ፥ ኢትዮ ቴሌኮም በአጣዳፊ ግዜ አገልግሎት እንዲሰጥ በሚያስችለው መሳሪያ ታግዞ ነው አገልግሎቱን መጀመር የቻለው።
ሙሉ ለሙሉ በአካባቢው መጨናነቅ እንዳይፈጠር የፋይበር ጥገናው እየተከወነ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለው ገልፀዋል።
ፋይበሩ የተቆረጠው በተፈጥሮ ምክንያት አልያም ሆን ተብሎ በሰው መሆኑን ገና አለመታወቁን ወ/ሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል።
መረጃው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ለBBC አማርኛው ክፍል እና ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት የተቀናጀ ነው።

የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ገለጸ፡፡
ከትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ12ኛ ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡
ፈተናው በበይነ መረብ (በኦንላይን) እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ገልጸዋል፡፡
ለፈተናው የሚያስፈልጉ የግብዓትና የስልጠና ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ዳይሬክተሩ መግለፃቸውን አሃዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ከትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ12ኛ ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡
ፈተናው በበይነ መረብ (በኦንላይን) እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ገልጸዋል፡፡
ለፈተናው የሚያስፈልጉ የግብዓትና የስልጠና ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ዳይሬክተሩ መግለፃቸውን አሃዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce
ከህወሓት የታጠቀ ሃይል ጋር በመሰለፍ ከመቐለ እስከ ቆላ ተንቤን ሲዋጉ እንዲሁም ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።
በቀጥጥር ስር ከዋሉት መኮንኖች መካከል ዘጠኙ የሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ፤ ሰባቱ የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ ያላቸውና ሁለቱ ደግሞ የፖሊስ ኮማንደሮች መሆናቸው ተገልጿል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከህወሓት ቡድን ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ በድጋሜ ጥሪ ማቅረቡን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክተር ሜ/ጄነራል መሀመድ ተሰማ ዛሬ ማምሻውን ለኢዜአ ተናግረዋል።

ለአክሱም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ፦
ለሁላችሁም የአክሱም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ወደ "ኲሓ ካምፓስ" እንድትገቡ የተገለፀ ቢሆንም በተደረገው ማስተካከይ ወደ ዋና ጊቢ እንድትገቡ ተወስኗል። ይህን ተገንዘባችሁ በዋናው ግቢ ተገኝታችሁ report እንድታደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
መልዕክቱን ያደረሰን የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለሁላችሁም የአክሱም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች ወደ "ኲሓ ካምፓስ" እንድትገቡ የተገለፀ ቢሆንም በተደረገው ማስተካከይ ወደ ዋና ጊቢ እንድትገቡ ተወስኗል። ይህን ተገንዘባችሁ በዋናው ግቢ ተገኝታችሁ report እንድታደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
መልዕክቱን ያደረሰን የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ፅ/ቤት ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,852
• በበሽታው የተያዙ - 476
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 846
አጠቃላይ 135,045 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,083 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 121,594 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
217 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,852
• በበሽታው የተያዙ - 476
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 846
አጠቃላይ 135,045 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,083 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 121,594 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
217 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት! የእነ አቶ ጃዋር መሀመድን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሞ የነበረው የተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመመልክት ነበር። ይሁንና ተከሳሾቹ ቤተሰቦቻቸን ችሎት ስላልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላቸንን መስጠት አንችልም…
የዛሬው የነአቶ ጃዋር የፍርድ ቤት ውሎ፦
(ጋዜጠኛ ስዩም ጌቱ~ዶቼ ቨለ ፣ ቪድዮና ፎቶ : OMN )
"...ቤተሰቦቻችን እንዳይገቡ በመከልከላቸውና ወንበሮቹ በደህንነት ሰዎች በመሞላታቸው ድርጊቱ ፍትህን የሚፈትንና እውነት እንዳይሰማ የሚደረግ ጥረት አድርገን ተረድተናል" -አቶ በቀለ ገርባ
"...መታወቂያ፣ቋንቋና የለበሱት ልብስ ታይቶ ቤተሰቦቻችን ወደ ችሎቱ እንዳይገቡ ተደርገዋል/ወደእስር ቤት ተወስደዋል"-አቶ ጃዋር መሃመድ
ዛሬ ጥዋት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ችሎቱ በሚሰየምበት አዳራሽ ውስጥ ተከሳሾች እና ጠበቆቻቸው ከፀጥታ አካላት ጋር ረዘም ላለ ደቂቃ ሲሟገቱ ነበር።
ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው በዚሁ ክርክር እና ውዝግብ ውስጥ እያሉ ከተባለው 3 ሰዓት ዘግይቶ የተሰየመው ችሎት ወደ ያዘው አጀንዳ ለመግባት ቢወጥንም ሁሉም ተከሳሾች ባሉበት ቆመው በችሎቱ ሂደት ቅሬታ እንዳላቸው ለፍርድ ቤቱ ያስረዳሉ።
ችሎቱ እንዳተሰየመ ቤተሰቦቻቸው ከችሎቱ ተሳትፎ መከልከላቸው ቅሬታ እንደፈጠረባቸው በመግለፅ ችሎቱ እንዴካሄድ ፍላጎት እንደሌላቸው በቆሙበት ለፍርድ ቤት አቤት ብለዋል።
አቶ በቀለ ገርባ፥"በታዘዝነው ሰዓት በአግባቡ ብንደርስም ክፍት መሆኑ የሚታወቀው ችሎት ቤተሰቦቻችን ውጪ በመከልከላቸውና ወንበሮቹ በደህንነት ሰዎች በመሞላታቸው ድርጊቱ ፍትህን የሚፈትን እና እውነት እንዳይሰማ የሚደረግ ጥረት አድርገን ለመረዳት ተገደናል" ሲሉ በነበረው ስሜት ችሎቱን ለማካሄድ በስነልቦና አለመዘጋጀታቸውን አስረድተዋል።
አቶ ጃዋር መሃመድ፥"መታወቂያ ቋንቋና የለበሱት ልብስ ታይቶ ቤተሰቦቻችን ወደ ችሎቱ እንዳይገኑ ተደርገዋል ወይም ወደእስር ቤት ተወስደዋል በዚህ አግባብ ችሎቱ መካሄድ የለበትም" ሲሉ ሞግተዋል።
ቀጣዩን ያንብቡ : telegra.ph/JM-01-27