TIKVAH-ETHIOPIA
#AgituGudeta #EthiopiaEmbassyRome በጣሊያን ውስጥ ከፍየል ወተት በምታዘጋጀው አይብና ለስደተኞች መብት ተቆርቋሪነቷ የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ አጊቱ ጉደታ ቤቷ ውስጥ ተገድላ መገኘቷን ፖሊስ ማሳወቁን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለቢቢሲ አረጋገጠ። የኤምባሲው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሠራተኛ የሆኑት አቶ ደሳላኝ መኮንን እንደተናገሩት ትናንት ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ማጣራትና…
የአጊቱ ጉደታ አስከሬን አዲስ አበባ ገባ።
የአጊቱ ጉደታ አስክሬን ዛሬ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን እና አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ቤተሰቦቿ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አስከሬኑን ተቀብለዋል፡፡
በጣልያን ሀገር ፍራሲሎንጎ ከተማ ፍየል እያረባች የፍየል ተዋጽኦዎችንና የቆዳ ቅባቶችን በመሸጥ የጠንካራ ሠራተኛነት ተምሳሌት የነበረችው አጊቱ ጉደታ መገደሏ ተገልጾ ነበር፡፡ ~ ኢብኮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ዳግም ያገረሸው ግጭት ...
በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ዳግም ባገረሸ ግጭት ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።
በኮንሶ ዞን የሰላም እና እርቅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በደቡብ ክልል የፌዴራል መንግስት የክልል አወቃቀር የሰላም አምባሳደር አባል የባላባት ካላ ገዛኸኝ፥ ጥቃት አድራሾቹ ሰገን ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ገብተው (መልካና ዱካያ፣ ሰገን ገነት፣ አዲስ ገበሬ፣ ገርጬ፣) ባሉት 9 ቀበሌዎች ውስጥ ሲያጠቁ ነበር ብለዋል።
ጥቃት አድራሾቹ ቤቶችን እያቃጠሉ፣ ሰው እየገደሉ ነው ያሉት ሲሉ ገልፀዋል።
በቾ፣ አዲስ ገበሬ፣ መለጋና ዱካያ፣ ገርጬ፣ ሰገን ገነት፣ ሉልቱ፣ ሌሎችም ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀሙን አስረድተዋል።
ካሉት 9 ቀበሌዎች ጥቃት ያልደረሰበት ብርብርሳ ብቻ ሳይሆን አይቀርምም ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በዞኑ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወረዳዎች እርቀ ሰላም ለማውረድ ቢሞከርም ለውይይት ፍቃደኛ ያልሆኑ አካላት መኖራቸው መሰናክል ሆኗል ብለዋል።
በተደጋጋሚ የሚያገረሸው ግጭት ዋነኛው መንስኤ "ልዩ ወረዳ" የመሆን ጥያቄ እንደሆነ ገልፀዋል።
የኮንሶ ዞን ከሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ወጥቶ ለብቻው ከተደራጀ በኃላ የመዋቅር እና የአስተዳደር ጥያቄ አለን የሚሉ አሉ።
በመዋቅር እና አስተዳደር ጥያቄ ምክንያት በአካባቢው በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰታሉ፣ ያገረሻሉ።
በዚሁ አካባቢ ከዚህ ቀደም በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ህይወት አልፏል፥ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። ~ ቢቢሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ዳግም ያገረሸው ግጭት ... በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ዳግም ባገረሸ ግጭት ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። በኮንሶ ዞን የሰላም እና እርቅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በደቡብ ክልል የፌዴራል መንግስት የክልል አወቃቀር የሰላም አምባሳደር አባል የባላባት ካላ ገዛኸኝ፥ ጥቃት አድራሾቹ ሰገን ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ገብተው (መልካና ዱካያ፣ ሰገን ገነት፣ አዲስ ገበሬ፣ ገርጬ፣) ባሉት 9 ቀበሌዎች ውስጥ…
የኮንሶ ዞን መንግስት ምን ይላል ?
ኮንሶ ሰገን ዙሪያ ወረዳ የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ የዞኑ መንግስት ትላንት ምሽት ባሰራጨው መግለጫ ቀጠናው እንዲተራመስ የተሳሳተና ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ የሚገኙ የፈጠራ ፌስቡክ አካውንቶች (በስም ጠቅሶ) አሉ ብሏል።
እነዚህ አካላት ሀሰተኛ መረጃዎችን በማደራጀት በቀጠናው ህብረተሰበሱ ሰላማዊ ኑሮ እንዳይኖር እርስ በእርስ እያጋጩት ነው ሲል ገልጿል።
ዞኑ በስም የጠቀሳቸውን የ1 የቴሌቪዥን ጣቢያ፣ 1 መፅሄት፣ 1 ድረገፅ (የፌስቡክ ፔጅ) እና 1 የሬድዮ ጣቢያ ፔጅ ሚዛናዊነቱን ያልጠበቀ መረጃ በማሰራጨት የተዛባ መረጃ በማሰራጨት ለኮንሶ ዞን እና ከደቡብ ክልል ውጭ ላሉ ህብረተሰቦች ተቆርቋሪ በመምሰል ለህገ ወጥ ስያሜ እውቅና በመስጠት ለ "ፀረ ሰላም ኃይል" ጉልበት እየሆኑ ነው ብሏል።
በአካባቢው ያለውን እውነታ በሩቅ ሆኖ ሳይሆን በአካል ቀርቦ መመልከት ተገቢ መሆኑን አስታውቋል ፤ ዞኑ በአካል ቀርበው እውነታውን መረዳት ለሚፈልጉ አካላት ሁሌም በሩ ክፍት መሆኑ ገልጿል።
(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#Ethiopia
"የሱዳን ሀይል ወደ ውስጥ የመግፋትና ወደ ኢትዮጵያ የመምጣት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው"- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ዛሬም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወደውስጥ የመግፋቱን እና በድንበር አካበቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን በማጎሳቆሉ ሕገ ወጥ ድርጊት እንደቀጠለ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው ሳምንታዊ መግለጫቸው የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በትግራይ የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሱዳን በኩል ድንበር ጥሶ መግባቱን አስታውሰዋል።
ይህ ድርጊት አሁንም ስለመቀጠሉ አንስተው ኢትዮጵያ ግጭቱን ቀጣናዊ ላለማድረግ ስትል መታገሷን ግን ደግሞ ትዕግሥትም ልክ እንዳለው አክለዋል።
ዓለም ዐቀፍ ሕጎችን የጣሰው የሱዳን ድርጊት ለአገሪቱ ሕዝብም ሆነ ለመንግሥት እንደማይጠቅምና የሚገፋውም በሌሎች ሦስተኛ ወገን ኃይሎች እንደሆነ እናምናለን ብለዋል። ~ AhaduTV
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

ኢትዮጵያ ጦርነት ትጀምራለች ?
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ : “ጦርነት አያስቸኩልም ፣ አፍንጫህን የመታህን ወዲያውኑ አፍንጫውን ላትመታው ትችላለህ ፤ ሌላ ጊዜ ግን አንገቱንም ልትቆርጠው ትችላለህ”
አምባሳደር ዲና ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የገባችበትን የድንበር ውዝግብን ተከትሎ " ኢትዮጵያ ጦርነት ትጀምራለች ወይ? " ተብለው ሲጠየቁ ነው። ~ አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ : “ጦርነት አያስቸኩልም ፣ አፍንጫህን የመታህን ወዲያውኑ አፍንጫውን ላትመታው ትችላለህ ፤ ሌላ ጊዜ ግን አንገቱንም ልትቆርጠው ትችላለህ”
አምባሳደር ዲና ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የገባችበትን የድንበር ውዝግብን ተከትሎ " ኢትዮጵያ ጦርነት ትጀምራለች ወይ? " ተብለው ሲጠየቁ ነው። ~ አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AAWSA
አዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የውኃ አገልግሎት መቋረጡን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ።
በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ስራ ምክንያት 700 ሚሊሜትር ስፋት ያለው የውሃ መስመር ላይ ጉዳት በመድረሱ ነው ስታዲየም ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት የተቋረጠው።
የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ግንባታን እያከናወነ ያለው የቻይናው #ሲሲሲሲ ስራ ተቋራጭ ለውሃ መስመሩ ጥንቃቄ ሳያደርግ የግንባታ ስራ ሲያከናውን ነው ውሃ በሚያስተላልፈው የውኃ መስመር ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
በዚህም ጋንዲ ሆስፒታል ፣ አምባሳደር አካባቢ ፣ ቦሌ ሮድ እስከ ደንበል በአጠቃላይ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት ተቋርጣል፡፡
መስመሩን ጠግኖ ወደ መደበኛ ስርጭት ለማስገባት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጾ ደንበኞች በትግስት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

#የፋኦ_ማስጠንቀቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ኬንያ የተከሰተው አዲስ የአንበጣ መንጋ በ ምሥራቃዊ አፍሪካአካባቢዎች እየተዛመተ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት አስጠነቀቀ።
ድርጅቱ ባወጣው መረጃ፤ አዲስ የተፈለፈሉ የአንበጣ መንጋዎች ከዚህ ቀደም ከተከሰተባቸው ምሥራቅ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ሶማሊያ በመሰደድ ወደ ኢትዮጵያ "ደቡብ ክልል" እና ወደ ሰሜን ኬንያና የባህር ዳርቻዎች አካባቢ እየተስፋፋ ነው ብሏል።
የአንበጣ ወረራ በቀጠናው ለምግብ ዋስትና ትልቅ ስጋት መሆኑን የጠቀሰው ድርጅቱ፤ ባለፈው ዓመት በቀጠናው የተከሰቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አንበጣዎች በሰብል ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጿል።
በመሆኑም አገራት ጥናት ለማካሄድ፣ የአንበጣ መንጋውን ፍልሰት ለመቀነስ እና የነፍሳቱን እርባታ ለመቆጣጠር አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርጉ ፋኦ ማሳሰቡን ቢቢሲ ዘግቧል።

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ባለፉት አራት ተከታታይ የችሎት ቀጠሮ ላይ ሳይቀርቡ የቀሩት አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም በ1ና 3 ችሎቶች ላይ ያልቀረቡት አቶ ሃምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የሚገኙ ሁሉም ተከሳሾች ዛሬ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡
አቶ በቀለ እና አቶ ጃዋር ባለፉት ችሎቶች ለምን መገኘት እንዳልቻሉ በዝርዝር አስረድተዋል።
አቶ በቀለ ፥ "ዛሬ ችሎት የቀረብነው ችሎቱ እና መንግስት ምንም አይነት አደጋ ላይደርስብን ኃላፊነቱን ወስደዋል ብለን በማመናችን ነው" ብለዋል፡፡
ዝርዝር የችሎት መረጃው : telegra.ph/DW-01-12-2
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የካፒቶል ፖሊስ አባላት እየተመረመሩ ነው።
2 የአሜሪካ ካፒቶል ፖሊስ ኦፊሰሮች ከስራ ገበታቸው ታግደዋል።
2ቱ የፖሊስ ኦፊሰሮቹ የታገዱት የካፒቶል ነውጥን ደግፈዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።
በተጨማሪ በርከት ያሉ የUS ካፒቶል ፖሊስ ኦፊሰሮች ነውጠኞችን ደግፈዋል (ተባብረዋል) በሚል ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
@tikvahethiopia

#EthiopianPoliceUniversity
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ፈቃድ በማግኘት ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉን አስታወቀ።
ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉን አስመልክቶ የማብሰርያ መርሐ- ግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አካሂዷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ፈቃድ በማግኘት ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉን አስታወቀ።
ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉን አስመልክቶ የማብሰርያ መርሐ- ግብር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አካሂዷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#UAE #SUDAN #ETHIOPIA
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኢትዮጵያና ሱዳን የገቡበትን ሰሞነኛ የድንበር ላይ ውዝግብ እንዲያረግቡ ጠየቀች፡፡
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አዲስ አበባ እና ካርቱም ከሰሞኑ በስፋት እየተወራ ያለውን የድንበር ላይ ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ እና በንግግር መፈታት አለበት ብሏል፡፡
ሁለቱ ሀገራት ለቀጣናዊ መረጋጋት እንዲሁም ብልጽግና ትልቅ ሚና እንዳላቸው የጠቀሰው መግለጫው የተፈጠረውን ችግር በንግግር መፍታት አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡
ዩኤኢ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የድንበር ላይ ግጭት መባባስ እንደሌለበት ገልጻ ሁለቱም ሀገራት ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም እና መረጋጋት አይነተኛ ሚና ስላላቸው የተፈጠረውን ነገር በሰከነ መንገድ ማየት አለባቸው ብላለች፡፡ ~ አል ዓይን ኒውስ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 4949 የኮሮና ቫይረስ ላብራቶሪ ምርመራ 376 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።
ባለፉት 24 ሰዓት የአንድ ሰው ሞት ሲመዘገብ ፤ 699 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን እስካሁን ከተደረገው ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የላብራቶሪ ምርመራ 128,992 ሰዎች ላይ ኮቪድ-19 ተገኝቷል ፥ ከነዚህ መካከል 2,004 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ፥ 114,262 ሰዎች አገግመዋል።

#Metekel
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ጥቃት አሁንም ቀጥሏል። የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው፥ንብረትም እየወደመ ነው።
• አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ታኅሳስ 26 በጭላንቆ ቀበሌ 7 ንፁሃን ዜጎች እና 4 የመከላከያ አባላት ለቡለን ወረዳ አጎራባች ከሆነው ካማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የገቡ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ መገደላቸውን በቅዳሜው እትሙ አስነብቧል።
• በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ቦታ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ 16 ሰዎች በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
• ጉባ ወረዳ ትናንት በደረሰ ጥቃት 11 ሰዎች ተገድለዋል።
• ትላንት ለሊት ድባጤ ወረዳ 'ቆርቃ ቀበሌ' በታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት ከ60 በላይ ንፁሃን መገደላቸውን የአይን እማኞች እና ከጥቃቱ ያመለጡ ሰዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ዘግቧል።
ከ25 በላይ ሰዎች ቆስለዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ንብረት እንደወደመ ተነገሯል።
ቪኦኤ ሬድዮ ፥አንድ የአካባቢው የኮማንድ ፖስት አባል ጥቃቱ መፈፀሙን አረጋግጠዋል ብሏል። ነገር ግን የደረሰውን ጉዳት መጠን አልገለፁም፤አላረጋገጡም፣ መረጃም አልሰጡም።
የአካባቢው የቲክቫህ አባላት በተፈፀመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከመቶ በላይ ነው ብለዋል።
• ትላንት እንዲሁም ዛሬ ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ በሚሄዱ መኪናዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ሁለት ሰው ሲገደል ሌሎች ቆስለዋል። ትላንት 1 ሰው ዛሬ 1 ሰው ተገድሏል።
አጠቃላይ ከላይ የተሰባሰቡት መረጃዎች የአይን እማኞችና ነዋሪዎች የሰጧቸው ሲሆኑ በመንግስት በኩል የተብራራ ዝርዝር መረጃ እስካሁን አልተሰጠም።
አሁንም አካባቢው ከፍተኛ የስጋት ቀጠና መሆኑን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው።
ምንጭ፦ቢቢሲ፣ቪኦኤ፣አዲስማለዳ፣ዶቼ ቨለ

ጎንደር ለአስመራ ጥሪ አደረገች።
በጎንደር በድምቀት ለሚከበረው የጥምቀት በዓል ለአስመራ ህዝብ ጥሪ መተላለፉን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መመሪያ አስታውቋል።
ጎንደር ከአስመራ ህዝብ ጋር የነበራትን ጥንታዊ የጠበቀ ግንኙነት ለማስቀጠል እና አብሮነትን ለማጠናከር አስመራ በበዓሉ እንድትታደም መጋበዟን ነው ከከተማ አስተዳደሩ ባህል ቱሪዝም ስፖርት መመሪያ የተገኘው መረጃ የሚገልፀው።
ባህረ ጥምቀቱን ምክንያት በማድረግ ወደ ጎንደር የሚሄዱ እንግዶችም በቦታው ሲገኙ ከሃይማኖታዊ ክዋኔ በተጨማሪ የጎንደርን ጥንታዊ፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶችን እንዲጎበኙ ዝግጅት ተደርጓል።
እንግዳ አክባሪው ፣ ፍጹም የኢትዮጵያዊነት እሳቤ እና አመለካከት ያለው የጎንደር ህዝብ እንግዶችን ለመቀበል ቅድም ዝግጀት ማጠናቀቁን ነው መምሪያው ያስታወቀው።
ባህረ ጥምቀቱን ለማክበር ሲደረግ የነበረው ሰፊ ዝግጅት መጠናቀቁን የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መመሪያ አስታወቋል። ~ AMMA

#DonaldTrump
የትራምፕ ደጋፊዎች ከፈጸሙት የአመጽ ድረጊት ጋር በተያያዘ ፣ የአሜሪካ ም/ቤት ፕሬዝዳንቱ በ25ኛው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ መሰረት ከስልጣን እንዲወርዱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ፣ ሀገሪቱን በአግባቡ መምራት ያልቻለ ፕሬዝዳንንት ከስልጣኑ ተነስቶ ምክትሉ መሪነቱን እንዲረከብ የሚደነግገውን 25ኛውን ማሻሻያ እንደማይተገብሩት ገልጸዋል፡፡
ይህንን ተከትሎም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንቱን በኢምፒችመንት ከስልጣን ለማውረድ ዝግጅት ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ አመጽ በመቀስቀስ ወንጀል ፕሬዝዳንቱን ለመክሰስ ዛሬ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ኢምፒችመንት የሚካሄድባቸው መሪ ያደርጋቸዋል፡፡
ትራምፕ ከኋይት ሀውስ ለመውጣት የቀራቸው 1 ሳምንት ቢሆንም ፣ ፕሬዝዳንቱ በኢምፒችመንት እንዲነሱ ባለቀ ሰዓት ሩጫ መጀመሩ ፣ በዋነኛነት ከዚህ በኋላ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይቀርቡ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ (አል ዓይን)
@tikvahethiopiaBOT