TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"አሜሪካ የሰሜን ኮሪያ ትልቋ ጠላት ናት" - ኪም ጆንግ ኡን

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ዩናይትድ ስቴትስ የአገራቸው 'ትልቋ ጠላት' መሆኗን በመግለጽ ማንም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢሆን ፒዮንግያንግን በተመለከተ ዋሽንግተን ፖሊሲዋን ትቀይራለች ብለው እንደማይጠብቁ ገልፀዋል።

ኪም በገዢው የሠራተኛ ፓርቲ ብዙም ያልተለመደ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ የሰ/ኮሪያን የኒውክሌር የጦር መሣሪያና የጦር አቅም እንደሚያሳድጉ ቃል ገብተዋል።

የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ ዕቅድ ለመጠናቀቅ ጫፍ ደርሷል ብለዋል።

ኪም ጆንግ ኡን ይህን የተናገሩት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት ነው።

ተንታኞች ኪም አስተያየት የሰጡት ባይደን በቅርቡ ቃለ መሃላ በመፈጸም በሚመሠርቱት በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ላይ ጫና ለማሳደር ነው ብለዋል።

በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ በተደረጉ ውይይቶች ብዙም ተጨባጭ ውጤት ባይመጣም ኪም ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር መልካም ወዳጅነት ነበራቸው።

ኪም ባደረጉት ንግግር ፒዮንግያንግ "የጠላት ኃይሎች" ቀድመው በአገራቸው ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ካላሰቡ ፒዮንግያንግ የኒውክሌር መሣሪያዎቿን ለመጠቀም አታስበም ብለዋል።

"አሜሪካ ለአገራቸን አብዮት ታላቋ ጠላታችን እና ትልቋ መሰናክል ነች ... ማንም ስልጣን ቢይዝ በሰሜን ኮሪያ ላይ ያለው የፖሊሲው አይቀየርም" ማለታቸውን የአገሪቱ መንግሥት ዜና ወኪል ዘግቧል። ~ BBC

@tikvahethiopiaBot
#Twitter

ትዊተር ላይ 88.7 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስከመጨረሻው ትዊተር እንዳይጠቀሙ አካውንታቸው ታገደ።

ትዊተር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ትራምፕ በአካውንታቸው ላይ 'በቅርቡ ያሰፈሯቸውን መልዕክቶች በደንብ ከመረመረ' በኋላ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProfessorBeyenePetros

ታዋቂው ፖለቲከኛ እና ምሁር ፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ በህይወት ዘመናቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ የምስጋና ስነ-ሰረዓት እየተካሄደላቸው ነው።

የምስጋና ስነስርዓቱ በአዲስ አበባ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የፕሮፈሰሩ 70ኛ አመት የልደት በአል እና የረጅም ጊዜ ፖለቲካዊ እና ምሁራዊ አገልግሎት ይዘከራል ተብሏል።

ፕሮፌስር በየነ ጴጥሮስ ለሰላማዊ የፖለቲካ ማጎልበት ያላቸው ሚና ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ ላይ በታዋቂ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፍ ይቀርባል።

ምንጭ፦ የደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች !

በትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ግጭት በርካታ ሰዎች በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለዋል።

66 ሺህ በላይ የሚሆኑትም ድንበር ተሻግረው ሱዳን ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል ምን ያህል ድጋፍ ፈላጊ ዜጎች አሉ ?

የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኣቶ ምትኩ ካሳ ለቢቢሲ የሰጡት መረጃ ፦

- ከኦፕሬሽኑ በፊት ከተለያዩ የክልሎች ተፈናቅለው ወደ ትግራይ የሄዱ 110 ሺህ ዜጎች አሉ። (እነዚህ በተለያዩ ጊዜት በተለያዩ ክልሎች በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለው ትግራይ ክልል የገቡ ናቸው)

- በአሁን ሰዓት የተፈናቀሉትን ለመለየት 3 ቡድን ተሰማርቷል። ቡድኑ ከኮሚሽኑ ፣ ከዓለም አቀፍ NGO የተውጣጣ ነው። ስራቸውን ሲጨርሱ በሚቀጥለው ሳምንት ቁጥሩ ይገለፃል።

- በመደበኛው ሰዓት (ከኦፕሬሽኑ በፊት) በትግራይ ክልል 1.8 ሚሊዮን ተረጂ ነው ያለው ፥ ከዚህ ውስጥ 1.1 ሚሊዮኑ ሴፍቲኔት ነው፣ 600 ሺህ የዕለት ደራሽ እርዳታ የሚቀርብላቸው ናቸው፣ 110 ሺህ ከላይ የተገለፁ ተፈናቃዮች ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅር በትግራይ ክልል 2.3 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደሚፈልጉ ገልጿል።

በሰሜናዊ ምዕራብ፣ ምስራቃዊ እና ማዕከላዊ ትግራይ በርካታ ቦታዎች እና የሽመልባ እንዲሁም ሒጻጽ ስደተኛ ጣቢያዎች አሁንም በጸጥታ ጉድለትና ቢሮክራሲ ሳቢያ ለዕርዳታ ተደራሽ አልሆኑም፡፡

በርካታ የጤና ማዕከሎች እና የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች እንደተዘረፉ እና ጉዳት እንደደረሰባቸው ሪፖርቱ ገልጿል።

https://www.unocha.org/story/daily-noon-briefing-highlights-ethiopia-9

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FreedomandEqualityParty

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምርጫ 2013 የሚያደርገውን ዝግጅት አካል የሆነው የቅድመ እጩ ምዝገባ በይፋ ጀምሯል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ሙሐመድ በአማራ ክልል የኦሮሞ ዞን ባቲ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር የቅድመ እጩነት ፎርም መሙላታቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EZEMA

ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)ን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎች ከዛሬ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ መታወቅ እንደሚጀምሩ ፓርቲው በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#GadaSystem የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የተመዘገበበትን አራተኛው ዓመት በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ይከበራል። ከ4 ዓመት ወዲህ የተከናወኑ ተግባራት የሚገመገሙበት መድረክ ጥር 1 እና 2 በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እንደሚካሄድ ተገልጿል። Via ENA @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የ "ገዳ ስርአት" ለአለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ አመት የመታሰቢያ በአል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የገዳ ፓናል ውይይት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች የፌዴራል መንግስት ኃላፊዎች ፣ የምእራብ ጉጂ ዞን ኃላፊዎች እና የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ የገዳ ስርአትን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል።

ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ይሆናል። ~ EPA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"ኢትዮጵያ ዳግም የህሊና እስረኞች ቤት እንድትሆን መፍቀድ የለብንም" - ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) 'ኢትዮጵያ ዳግም የህሊና እስረኞች ቤት እንድትሆን መፍቀድ የለብንም' በሚል የታሰሩ አመራሮቹ እንዲፈቱ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በዛሬው ዕለት እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

ፓርቲው በፌስቡክ እና በትዊተር ዓለም አቀፍ ዘመቻው አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው አመራሮች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ዘመቻ እንደሚያካሂድ ገልጿል።

በሌላ በኩል ለመጋቢት 29/2013 ዓ.ም ተቀጥረው የነበሩት እነ አቶ እስክንድር ነጋ ቀጥሮው ተሻሽሎ በመጭው ጥር 5/ 2013 ዓ/ም ፍ/ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DonaldTrump

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ በረቷቸው ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ እንደማይገኙ አሳውቀዋል።

ጆ ባይደን ጥር 12 ቀን በሚከናወነው በዓለ ሲመታቸው ቃለ መሐላ በመፈፀም 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከካፒቶል ነውጥ በኃላ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንደሚደረግ ማሳወቃቸው ይታወሳል።

ይሁንና ዘግየት ብለው "የምትጠይቁኝ ካላችሁ በመጪው ጥር 12 ቀን በሚከናወነው በዓለ ሲመት ላይ አልገኝም" ሲሉ አሳውቀዋል፡፡

Via Sheger FM 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትራምፕ የክብር ድግሪያቸውን ተነጠቁ።

"ሊሃይ ዩኒቨርሲቲ" ከ30 ዓመት በፊት ለዶናልድ ትራምፕ ሰጥቷቸው የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደሻረው አሳውቋል።

ይህ የሆነው ከካፒቶል ነውጥ በኃላ ነው።

ውሳኔው ትላንት በዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባላት ፀድቋል። ከዚህ ጋር የተያያዘም አጭር መግለጫ ዩኒቨርሲቲው በድረገፁ አሰራጭቷል።

ሊሃይ ዩኒቨርሲቲ ለዶናልድ ትራምፕ የክብር ዶክትሬት ድግሪ የሰጣቸው በእ.ኤ.አ 1988 ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AyatollahAliKhamenei

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ በአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም የተመረቱ ክትባቶች ኢራን ውስጥ እንደታገዱ በይፋ ተናገሩ።

አል ካሚኒ በክትባቶቹ ውጤታማነት ላይ እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በUK እና US ክትባት ላይ ያላቸውን ስጋት ለኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ካሳወቁ በኃላ በይፋ እንደተናገሩ ገልፀዋል።

አሊ ሃሚኒ "የነዚህ ሀገራት (US እና UK ማለታቸው ነው) ክትባቶች አላምናቸውም፤ ብዙ ጊዜ ውጤታማነታቸውን ለመሞከር በሌላ ሀገራት ሰዎች ላይ ነው የሚሞክሩት" ብለዋል።

በተጨማሪም ኣሊ ሃሚኒ ለፈረንሳይ ክትባትም በጎ ነገር እንደሌላቸው ገልፀዋል።

ከውጭ ሀገራት ከሚገቡት ይልቅ በሀገር ውስጥ የሚዘጋጅውን ክትባት እንደሚመርጡም አሳውቀዋል።

የኢራን መንግስት ከውጭ ክትባት ለማስገባት ጥረት እያደረገ ባለበት ውቅት ነው መንፈሳዊ መሪው ይህን ያሉት።

ባለፈው ወር የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገዥ አብዶለሳር ሃማቲ ክትባት ለመግዛት የመጀመሪያ ስምምነት እና ገንዘብ ለማዘዋወር ስምምነት መደረጉን ተናግረዋል፤ የክትባቱን ምንጭ ግን አልገለፁም።

ፕሬዝዳንት ሃሰን ሮሃኒ፥ "የኢራን የመጀመሪያ ምርጫ የሀገር ውስጥ ክትባት ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ከሌሎች ሀገራት ጋር በትብብር ለማዘጋጅት በመጨረሻም ከWHO መግዛት ነው" ብለው ነበር።

ኢራን ባለፈው ሳምንት በሰው ላይ የመጀመሪያው ምዕራፍ የክትባት ሙከራ ጀምራለች ፥ ለ3 ሰዎች ክትባቱ የተሰጠ ሲሆን 20 ሺህ ሰዎች ለሙከራው ተመዝግበዋል።

ኣናዱል የዜና ማሰራጫ ያነጋገራቸው ጤና ባለሞዎች ኢራን ካሳተናገደችው የወረርሽኙ ተፅእኖ እና ሀገሪቱ ላይ ከሚፈጠረው ጫ ጫ አንፃር የውጭ ክትባቶች ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ እና ጥቅም ላይ እንዲውሉ መክረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Breaking

ከ50 በላይ መንገደኞችን የጫነ የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) ጠፋ።

አውሮፕላኑ የተነሳው ከጃካርታ ሲሆን እስካሁን የደረሰበት አልታወቀም።

የኢንዶኔዢያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ከጃካርታ ከተነሳ በኃላ በደቂቃዎች ውስጥ ደብዛው የጠፋውን አውሮፕላን የመፈለጉ ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT