#ProfessorBeyenePetros
ታዋቂው ፖለቲከኛ እና ምሁር ፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ በህይወት ዘመናቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ የምስጋና ስነ-ሰረዓት እየተካሄደላቸው ነው።
የምስጋና ስነስርዓቱ በአዲስ አበባ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
የፕሮፈሰሩ 70ኛ አመት የልደት በአል እና የረጅም ጊዜ ፖለቲካዊ እና ምሁራዊ አገልግሎት ይዘከራል ተብሏል።
ፕሮፌስር በየነ ጴጥሮስ ለሰላማዊ የፖለቲካ ማጎልበት ያላቸው ሚና ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩ ላይ በታዋቂ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፍ ይቀርባል።
ምንጭ፦ የደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በፕሮፌሰር በየነ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር በየነ ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውንም ጠቁመዋል። " በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ " ሲሉም ገልጸዋል። @tikvahethiopia
#ProfessorBeyenePetros
" ከጠዋቱ 2 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል " - ሀድያ ዞን
የጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል።
የፕሮፌሰሩ አስክሬን በህክምና ሲረዱ ከቆዩበት ኬንያ ናይሮቢ ትላንት ምሽት ነው አዲስ አበባ የገባው።
የቀብር ስርዓቱን ለማስፈጸም የተቋቋመ አብይ ኮሚቴ ሊኢብኮ በሰጠው ቃል ፤ የፕሮፌሰሩ ስርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የሙያ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም አሳውቋል።
በሌላ በኩል በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ነገ ሐሙስ ከጠዋቱ 2 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል።
መላው የዞኑ ነዋሪ ሕዝብ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ በመገኘት በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን እንዲገልጽ ጥሪ ቀርቧል።
ፕሮፌሰር በየነ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ዕንቁ ምሁራን መካከል ከቀዳሚቹ ተርታ ይጠቀሳሉ። ከዚህ ባለፈ በሀገሪቱ የፖለቲካ ውስጥ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት ነበሩ፡፡
ነፍስ ይማር !
@tikvahethiopia