TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Asmera

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ አስመራ መግባታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው እንዳሉት በመሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ የተመራ ልዑክ አባላት ዛሬ አስመራ ገብተው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

አቶ የማነ እንዳሉት ከሆነ ጉብኝቱ የኤርትራ እና የሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ በከፍተኛ የሀገራቱ ባለሥልጣናት መካከል የሚደረገው ምክክር አካል ነው። ~ AL AIN

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሺጂያዡዋንግ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ።

ቻይና በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ በምትገኘውና የ11 ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ በሆነችው ሺጂያዡዋንግ ከተማ ውስጥ ከ100 በላይ አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ስላገኘች የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች።

ነዋሪዎች ከተማዋን ለቅቀው እንዳይወጡ የተከልክለዋል፤ ትምህርት ቤቶችም ተዘግተዋል።

ነዋሪዎች ተመርምረው ውጤታቸውን ማወቅ እንዲችሉ ከ500 በላይ የመመርመሪያ ቦታዎች ተከፍተዋል።

በከተማዋ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር በቻይና ለተከታታይ አምስት (5) ወራት ከተመዘገበው አሃዝ ውስጥ ከፍተኛው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅማ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት ወደመ !

በጅማ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ዛሬ ንጋት አካባቢ 11 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ነው።

በከተማው በቦቾ ቦሬ ቀበሌ መናኸሪያ አካባቢ በሚገኝ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ወጤቶች ማምረቻና መሸጫ የግል ድርጅት ላይ አደጋው መድረሱ ተገልጿል።

በአደጋው በድርጅቱ ተመርተው ለገበያ የተዘጋጁ ዘመናዊ የእንጨት ስራ ውጤቶች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል።

የወደመው ንብረት 6 ሚሊዮን ብር ግምት አለው እንደሆነ የተነገረ ሲሆን በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በጸጥታ አካላትና በእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ትብብር በተደረገ ጥረት ቃጠሎው ወደ ሌሎች የንግድ ተቋማት ሳይዛመት በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው። ~ENA

PHOTO : JIMMA TIKVAH FAMILY
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#OBN

የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በአራት ተጨማሪ ቋንቋዎች ስርጭት ሊጀምር ነው።

OBN Horn Of Africa በቅርቡ በአፋርኛ ፣ በኑዌር ፣ በአኙዋክኛ እና በመጃንግ ቋንቋዎች ስርጭት ለመጀመር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ተገለፀ።

OBN አሁን ላይ በ8 ቋንቋዎች በአፋን ኦሮሞ ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ ፣ ሓዲይኛ ፣ ሃላቢኛ ፣ ሶማልኛ ፣ ሱዋሂሊ ፣ አረቢኛ እና ኢንግልዝኛ ቋንቋዎች ዜናዎች እና ፕሮግራሞችን እያሰራጨ ይገኛል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የህወሓት አመራር አቶ ስብሃት ነጋ ይገኙበታል።

በተጨማሪ ፦

- ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤት እና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበሩ፣ በኋላ በጡረታ የተገለሉ

- ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዱ

- ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመለካከያ የከዱ

- አስገደ ገ/ ክርስቶስ- ከመሃል ሀገር ተጉዘው ቡድኑን የተቀላቀሉና ለጊዜው ሃላፊነታቸው ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሌላ በኩል ፦

የሜ/ጀነራል ሃየሎም አርአያ ባለቤት የነበሩና ኑሮዋቸውን በአሜሪካ አድርገው የቆዩ በኋላም ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት ወደ ህወሓት ተቀላቅለው የነበሩ ፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ ህወሓትን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ሲሞክሩ ገደል ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አልፏል ሲል ሀገር መከላከያ ገልጿል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት አቶ ስብሃት ነጋን በቁጥጥር ስር ያዋልኳቸው ከተደበቁበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ ነው ብሏል።

አቶ ስብሃትን ፥ የህወሓት ቡድን አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀዋቸው ነበር ሲል ገልጿል ሀገር መከላከያ በሰጠው መግለጫ።

የመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻ እና አሰሳ፣ ከተደበቁበት በማውጣት በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ገልጻል።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር የዋሉ አመራሮችን ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የታጠቅ ሀይል መደምሰሱን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#UPDATE

የ6ተኛው አገር አቀፍ የመጨረሻ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ ተደረገ።

* የመጨረሻው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,240
• በበሽታው የተያዙ - 161
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 345

አጠቃላይ 127,572 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,974 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 113,182 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

208 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የህወሓት አመራር አቶ ስብሃት ነጋ ይገኙበታል። በተጨማሪ ፦ - ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤት እና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበሩ፣ በኋላ በጡረታ የተገለሉ - ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዱ - ኮሎኔል የማነ…
#FDREDefenseForce

የወ/ሮ አልጋነሽ መለስ ገደል ውስጥ ገብተው ህይወታቸው ማለፉን እዛው የነበሩ ሰዎች ለመከላከያ ሰራዊት መረጃውን እንደሰጡ ብ/ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ተናገሩ።

ብ/ጄኔረሉ ይህን የተናገሩት በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በሰጡት አጭር ማብራሪያ ላይ ነው።

ሌሎች በህይወት እያሉ እንዴት እሳቸው ብቻ ህይወታቸው ሊያልፍ ቻለ ? ስለሚለው ጉዳይ በቦታው የነበሩ ሰዎች "ወደገደል ገብተው ሞቱ" የሚል መረጃ ብቻ እንደሰጧቸው አሳውቀዋል።

ወ/ሮ አልጋነሽ ህይወታቸው ካለፈ በኃላ አለመቀበራቸውን ገልፀዋል።

እንደ ብ/ጄነራል ተስፋዬ ገለፃ ፥ ወ/ሮ ኣልጋነሽ ህይወታቸው ያለፈው በጦርነቱ ምክንያት አይደለም።

ጦርነቱ ሲደረግ የነበረው አመራሮች ከነበሩበት ስፍራ ራቅ ባለ ተራራ ላይ ከህወሓት ቡድን አመራር ጠባቂዎች ጋር ነበር ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ850 በላይ ተማሪዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል።

ዛሬ መቐለ ዩኒቨርሲቲ የዓዲግራት ተማሪዎችን ሲቀበል ውሏል።

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ መልዕክት መተላለፉ ይታወቃል።

ዛሬ እና ነገ ተማሪዎች የሚገቡ ሲሆን ጥር 2 ቀን 2013 ትምህርት ይጀመራል።

እስካሁን ድረስ ከ850 በላይ ተማሪ ግቢ ገብቷል።

ለተማሪዎች ትራንስፖርት / መኪና ለመመደብ እንቅስቃሴ እንደነበር ቢገለፅም ምንም የተመደበ መኪና የለም።

ወደ ግቢ የገቡ ተማሪዎች እንደገለፁት ከአዲስ አበባ በባስ 850 ብር ትኬት ቆርጠው ነው መቐለ የደረሱት።

ከአዲስ አበባ ውጭ ከመቐለ በቅርብ ርቀት ያሉ ከተሞች (ወልዲያ፣ ደሴ) የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ኮንትራት መኪና በራሳቸው ይዘው መቐለ እንደገቡ ተሰምቷል።

የትራንስፖርት ክፍያው ውድነት እንዲሁም ትራንስፖርት አጥተው የተቸገሩ የቲክቫህ አባላት ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ገንዘቡ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑና የትራንስፖርት እጥረት በመኖሩ ጉዟቸውን ፈታኝ እንዳደረገው አሳውቀዋል።

ምንም እንኴን እጥረት ቢኖርም ከአዲስ አበባ - መቐለ ትራንስፖርት አለ፤ መንገድ ላይም ምንም አይነት ችግር እንደሌለ ዛሬ መቐለ የገቡ ተማሪዎች ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ለፖለቲካ ችግሮቻችንም ሆነ ለነፃ፣ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋቱ ወሳኝ ነው"-ኦፌኮ

ኦፌኮ ትላንት ባወጣው መግለጫ ለሀገራችን የፖለቲካ ችግሮችም ሆነ ለነፃ ፣ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝቧል።

የፌዴራል ስርዓቱ ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲተገበር የክልሎች የራስን አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ ገብነት እና የሞግዚት አስተዳደር እንዲወገድ በኢህአዴግ በሚመራው መንግስት ላይ ለዓመታት የመረር ትግል በማድረጉ አያሌ አባላቱ ፣ ደጋፊዎቹ ላይ ግድያ ፣ ማሰር ፣ ማሰቃየት፣ ማፈናቀል፣ እና ማሳደድ ወንጀሎች እንደተፈፀመባቸው አስታውሷል።

ዛሬም በርካታ የኦፌኮ አባላትና ደጋፊዎች ከከፍተኛው አመራር እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ለህዝብ ነፃነትና መብት ፀንተው በመቆማቸው የውሸት እና የፈጠራ ወንጀል ተለጥፎባቸው በተለያዩ ማጎሪያ ካምፖች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ልዩ ኃል ካምፖች፣ በድርጅት ፅ/ቤቶች በመደበኛ እስር ቤቶች እና በመማሪያ ክፍሎች ሳይቀር ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብሏል።

ኦፌኮ መንግስት በኢፌዴሪ ህገ መንግስት እና በዓለም አቀፍ ህጎች የተደነገጉ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማክበር በተለያዩ አካባቢዎች በፖለቲካ አቋማቸው ያሰራቸውን አመራሮች እና አባላት፣ ደጋፊዎች በአስቸኳይ እንዲፈታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቋል።

በኃይል የተዘጉ ፅ/ቤቶች ተከፍተው ስራ እንዲጀምሩ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቋል።

ምርጫ የሚያስተባብሩ፣ የሚወዳደሩ እና የሚታዘቡ የፓርቲው አመራሮች፣አባላት እና ደጋፊዎች ታስረው ሌሎችም ከደረሰባቸው ማስፈራሪያ ተሰደው ፅ/ቤቶች በኃይል ተዘግተው ምርጫ ለመሳተፍ እንደሚቸገር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ፤ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም እንዲያውቁት እንፈልጋለን ብሏል።

#OFC
"አሜሪካ የሰሜን ኮሪያ ትልቋ ጠላት ናት" - ኪም ጆንግ ኡን

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ዩናይትድ ስቴትስ የአገራቸው 'ትልቋ ጠላት' መሆኗን በመግለጽ ማንም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢሆን ፒዮንግያንግን በተመለከተ ዋሽንግተን ፖሊሲዋን ትቀይራለች ብለው እንደማይጠብቁ ገልፀዋል።

ኪም በገዢው የሠራተኛ ፓርቲ ብዙም ያልተለመደ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ የሰ/ኮሪያን የኒውክሌር የጦር መሣሪያና የጦር አቅም እንደሚያሳድጉ ቃል ገብተዋል።

የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ ዕቅድ ለመጠናቀቅ ጫፍ ደርሷል ብለዋል።

ኪም ጆንግ ኡን ይህን የተናገሩት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት ነው።

ተንታኞች ኪም አስተያየት የሰጡት ባይደን በቅርቡ ቃለ መሃላ በመፈጸም በሚመሠርቱት በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ላይ ጫና ለማሳደር ነው ብለዋል።

በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ በተደረጉ ውይይቶች ብዙም ተጨባጭ ውጤት ባይመጣም ኪም ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር መልካም ወዳጅነት ነበራቸው።

ኪም ባደረጉት ንግግር ፒዮንግያንግ "የጠላት ኃይሎች" ቀድመው በአገራቸው ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ካላሰቡ ፒዮንግያንግ የኒውክሌር መሣሪያዎቿን ለመጠቀም አታስበም ብለዋል።

"አሜሪካ ለአገራቸን አብዮት ታላቋ ጠላታችን እና ትልቋ መሰናክል ነች ... ማንም ስልጣን ቢይዝ በሰሜን ኮሪያ ላይ ያለው የፖሊሲው አይቀየርም" ማለታቸውን የአገሪቱ መንግሥት ዜና ወኪል ዘግቧል። ~ BBC

@tikvahethiopiaBot