TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle

አሜሪካ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዜጎቿን ለማስወጣት ጥረት እያደረገች ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በትዊተር ገጹ ባሰራጨው "የጥንቃቄ መልዕክት" መቐለ የሚገኙ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ዜጎች ለማስወጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

በመቐለ የሚኖሩ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ለደኅንነታቸው ተጠልለው እንዲቆዩ መስሪያ ቤቱ መክሯል።

በክልሉ ያሉ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ወይም በመቐለ የሚኖር #አሜሪካዊ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች ከመስሪያ ቤቱ ጋር ግንኙነት እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

#WazemaRadio #USEmbassyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US : አሜሪካ TPLF ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጣ በድጋሚ አሳሰበች። ዛሬ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ከአማራ እና አፋር ክልል እንዲወጣ፤ ወደ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ የሚያደርገውን ግስጋሴ እንዲገታ አሳስቧል። ሚኒስቴሩ TPLF በከተሞች ላይ ከባድ መሳሪያዎችን ከመተኮስ እንዲቆጠብ ያሳሰበ ሲሆን ሁሉም ወገኖች ያለ ምንም…
#US #EU #USEmbassyAA

አሜሪካ በድጋሚ ተኩስ እንዲቆምና ድርድር እንዲጀመር ጠየቀች (ይህን ስትል በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለተኛዋ ነው)

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ የቀጠለው ጦርነት አሜሪካን እጅግ እንዳሳሰባት አሳውቀዋል።

ብሊንከን ጦርነቱ በስፋት መዛመቱ ሰብዓዊ ቀውሱን እንደሚያከፋው ጠቁመዋል።

ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በድርድር ላይ የተመሠረተ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉም በመግለጫቸው ላይ አሳስበዋል።

ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነር ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ሁሉም ወገኖች ያለ ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቱን እንዲያቀላጥፉ እና የጥላቻ ንግግሮችን እንዲያቆሙም አሳስበዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሌሴጎን ኦባሳንጆ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ህብረቱ እምነቱን ገልጿል።

በሌላ መረጃ ፦

አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ በሰሜን ኢትዬጵያ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጿል።

በአማራ ክልል፤ ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ ግጭት ተባብሷል ብሏል።

በአማራ እና በአፋር የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንን መከታተል እንዳለባቸው ፤ ግጭት በሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ካሉም ለመጠለል መዘጋጀት እንዳለባቸውና እነዚህን አካባቢዎች መልቀቅ ሊያስቡበት እንደሚገባ አብቆ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USEmbassyAA

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለDV (ዲቪ) መመረጥ ለቪዛ ወይም ለቃለ መጠይቅ ዋስትና እንደማይሰጥ አስገንዝቧል።

ካለፈው ቅዳሜ ምሽት አንስቶ የ2024 የDV ተመራጮች የታወቁ ሲሆን ለዚህ ዕድል ያመለከቱ በድረገፅ ow.ly/rJuC50OhWuz ላይ በመግባት የማረጋገጫ ቁጥር በማስገባት መመረጥ አለመመረጣቸውን ማወቅ ይችላሉ።

ይህ ብቸኛው የማወቂያው መንገድ መሆኑን ኤምባሲው ገልጿል።

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ፥ የዲቪ (DV) ተመራጭ መሆን ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና እንደማይሆን አስገንዝቧል።

እንደ ኤምባሲው ማብራሪያ ፤ የዲቪ (DV) ሎተሪ ተመራጭ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ሲሆን በቀጥታ ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሰጥም።

@tikvahethiopia