TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#China #SouthKorea #Russia

- ባለፉት 24 ሰዓት በቻይና አስራ አራት (14) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ ፤ ሁለቱ ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ተገልጿል። በቻይና በአንድ ቀን ከ10 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ9 ቀናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

- በደቡብ ኮሪያ በ24 ሰዓት 34 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በደቡብ ኮሪያ ከአንድ ወር በኃላ በአንድ ቀን ከ30 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

- ሩሲያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 11,012 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በተጨማሪ 88 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#SouthKorea

ደቡብ ኮርያ በተተናቀቀው 2020 በአገሪቷ ውስጥ ከውልደት ምጣኔ ይልቅ የሞት ቁጥር አሻቅቦ መገኘቱ እንዳሳሰባት ተገለፀ።

ይህ የሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በ2020፣ 275,800 ሕጻናት የተወለዱ ቢሆንም ከ2019 ጋር ሲነጻጸር በ10 % ቀንሷል።

በዚሁ ዓመት ከተወለዱት ይልቅ በሞት ያጣቻቸው ዜጎቿ ቁጥር ከፍ ብሏል። 307,764 ዜጎቿ ሟተዋል።

የሕዝብ ቁጥር መቀነስ በአገሪቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮባታል።

የወጣቶች ቁጥር መቀነስ የአምራች ኃይል በመቀነስ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ የሚፈጥር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ጡረታ እና የጤና እንክብካቤ ፍላጎት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል።

ባለፈው ወር ፕሬዝዳነት ሙን ዤ ኢን የውልደት መጠን እንዲጨምር በማሰብ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ያስተዋወቁ ሲሆን ለመውለድ ለሚወስኑ ቤተሰቦች የገንዘብ ድጎማ ማድረግ ከእቅዶቻቸው መካከል ነው።

በዚህ እቅድ መሰረት ከ2022 ጀምሮ የሚወለድ እያንዳንዱ ልጅ የቅድመ ወሊድ ወጪውን ለመሸፈን 2 ሚሊዮን ዩዋን (የኮሪያ ገንዘብ) ወይንም 1,850 ዶላር ይቀበላል።

ይህ ገንዘብ ከ2025 ጀምሮ ለመተግበር ከታሰብው ልጁ 1 ዓመት እስኪሞላው ድረስ በየወሩ ለቤተሰቡ የሚሰጠውን 300,000 ዩዋን አይጨምርም።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopia