TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ExitExam 

የህግ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam ) ከዛሬ ጀምሮ መውሰድ ይጀምራሉ።

በኮቪድ ምክንያት የትምህርት ተቋማት ከተዘጉ በኋላ ወደ 2013 የተዛወረው ፈተና ቀጥሎም በሀገሪቱ በተፈጠረው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ዳግም ሊራዘም ችሏል።

በዚህ ምክንያት በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በትግራይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፈተናውን አይወስዱም።

በአስፈታኝ ዩኒቨርሲቲዎች ለማስፈተን አመቺ ሁኔታዎች ከሌሉ በአጭር ጊዜ የድጋሚ ፈተና በልዩ ሁኔታ በማዘጋጀት እንዲፈተኑ ይደረጋል ተብሏል።

የፍትሕ እና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢኒስትቲውት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ፈተናው ከታህሳስ 13-16 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወሳል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የትምህርት ሚኒስቴር " የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ " ን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አሰራጭቷል። በ2015 የትምህርት ዘመን ገቢራዊ የሚሆነው መመሪያው፤ የከፍተኛ ትምህርት የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ወሳኝ ነው ተብሏል። መመሪያ ቁጥር 919/2014 ሆኖ በፍትህ ሚኒስቴር የጸደቀውን መመሪያ የከፍተኛ…
#ExitExam

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ዓመት 2015 ትምህርት ዘመን የሚጀምረውን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአፈፃፀም መመሪያን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማሰራጩት ይታወቃል።

ለመሆኑ መመሪያው ምን ይላል ?

- የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያ ዲግሪ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ይመለከታል።

- መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚከወኑ የማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው።

- የመውጫ ፈተናውን ወስዶ 50 በመቶ ውጤት ማምጣት ያልቻለ ተማሪ መመረቅም ሆነ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ የዲግሪ ሰርተፊኬት ማግኘት አይችልም።

- በመውጫ ፈተና 50 በመቶ ማምጣት ያልቻለ ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ በአግባቡ አጥንቶ ፈተናውን 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥቶ ማለፍ እንዲችል ለሁለት ተጨማሪ ጊዜ የመፈተን እድል ይሰጠዋል። ተፈታኙ እድሉን መጠቀም ያለበት የመጀመሪያውን ፈተና ከወሰደ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው።

- አንድ ተማሪ ለምርቃት ብቁ የሚሆነው የመውጫ ፈተናውን ካለፈ ብቻ ሲሆን 3 ጊዜ ተፈትኖ የማለፊያ ነጥብ ያላገኘ ተፈታኝ ከብሄራዊ የብቃት ማዕቀፍ ተገቢው ማስረጃ ይሰጠዋል።

- የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና እንደየትምህርት ፕሮግራሙ ባህሪ በዓመት ሁለቴ እና ከዛም በላይ ሊሰጥ ይችላል።

- የመውጫ ፈተና የሞያ ማህበራት ተጠናክረው የሞያ ፍቃድ ፈተና መስጠት እስከሚጀምሩ በትምህርት ሚኒስቴር ወይም ውክልና በሚሰጠው ተቋም ይዘጋጃል።

መውጫ ፈተና ላይ ሚካተቱ ኮርሶችን በተመለከተ በመጪው ጊዜ በየትምህርት መስኩ በሚዘጋጁ የማስፈፀሚያ ዝርዝር መመሪያዎች ይለያል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ካሰራጨመው ዘገባ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።

ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦

" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።

በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።

ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።

ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።

በጥሩ ግብዓት ከተደገፈ እና ጥሩ ሂደት ካለው በውጤቱ ማረጋገጥ ይገባል ከሚል መነሻ የተጀመረ የሪፎርም ስራ ነው "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

በ2015 የትምህርት ዘመን ከሚጀምረው የመውጫ ፈተና (ለመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ብቻ) ጋር በተያያዘ ከፈተናው በፊት ሊቀድሙ የሚባቸው ነገሮች አሉ በሚል የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ።

የግብዓት አቅርቦት ችግር ባለበት ሁኔታ ፣ የትምህርት ተቋማት አቅም በሚፈለገው ደረጃ ባልሆነበት ፣ የመምህራን ብቃት በራሱ ሳይመዘን / መምህራን ሳይመዘኑ ተማሪዎችን መመዘን እንዴት ይሆናል ፤ እንዴትስ ውጤት ያስገኛል በሚል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።

የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ላይ ምላሽ አለኝ ብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) ከተናገሩት ፦

" አቻ ምሳሌ ላይሆን ይችላል ግን አንድ ምሳሌ ላንሳ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አሉ ከሺህ በላይ የሚሆኑ በሁሉም ት/ቤቶች ያለው አቅም ፣ የመምህራን፣ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰረተ ልማት አቅም እና መምህራኑ የተመዘኑ / ምዘናውን ያለፉ መሆን አለመሆናቸው ያለው ምጣኔ በጣም የተለያየ ነው። እንደዛም ሆኖ ግን አንድ ወጥ የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ያስፈልገናል እንደ ሀገር።

የ2ኛ ደረጃ ፈተና የምንሰጠው አንድ ሰው በሁለተኛ ደረጃ የሚሰጠውን ትምህርት በእርግጥ አጠናቋል ለሁለተኛ ደረጃ አጠናቃቂ ነው ተብሎ በቅቷል ወይ ለማለትና ለመለካት ነው።

ይሄ ፈተና ስታንዳርድ ፈተና ነው። በየሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አቅም አይደለም የሚዘጋጀው ፣ በሁለተኛ ደረጃ ያሉ መምህራንን አቅም ብቻ አይደለም ታሳቢ የሚያደርገው፤ እንደ ሀገር ሁለተኛን ደረጀን የጨረሰ ሰው ምን አይነት እውቀት እና ስብዕና ሊኖረው ይገባል የሚለውን የሚፈትሽ ነው።

መምህራኑ ሁሉም ተፈትነው ብቁ ሆነው እስኪያልፉ ፣ ያለን መሰረተ ልማት በትምህርት ቤቶች ወይም በዩኒቨርሲቲዎች ያለን አቅም ተመጣጣኝ እስክናደርግ ድረስ አንድን ሪፎርም አንጀምርም ካልን ዝንተዓለም ያንን ሪፎርም አናደርግም።

ሪፎርሙ መጀመር አለበት የሆነ ጊዜ ላይ መጀመር አለበት የተባሉ ጉድለቶች እንዳሉ አውቃለሁ፤ እንደ ትምህርት ሴክተርም እንደትምህርት ሚኒስቴርም እንገነዘበዋለን።

የመምህራኖቻችንን ብቃት ለማሳደግ በየአመቱ ከልማት አጋሮችም ፣ ከመንግስትም ግምጃ በሚሊዮኖች እያፈሰስን መምህራን በ2ኛ ፣ 3ኛ ዲግሪ እናስተምራለን።

እንደሚታወቀው መንግስት ለትምህርት በሰጠው ልዩ ትኩረት በሀገራችን 4ኛው ትልቁ በጀት የሚመደብለት ሴክተር ነው ሰፊውን የሚወስደው የከፍተኛ ትምህርት ነው የውስጥ መሰረተ ልማታቸውን፣ አደረጃጀታቸውን ለማሳደግ የሚውል ሀብት አለ እነዚህ ቁርጠኝነቶች በመንግስት በኩል የውስጥ ችግሮችን ለመፍታት የሚውል ነው።

መምህራኖቻችን በቀጣይነት እያበቃን መሄድ አለብን እርግጥ ነው እንደዛም ሆኖ ግን ይሄ ስራ መጀመር አለበት ፤ አሁን ካልጀመርነው ከበቂ በላይ ጉዳት ደርሷል የትምህርት ጥራቱ ላይ።

በፈተና ብቻ አይደለም ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮ በትኩረት በመለየት ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ፣ የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና በጥራት በመስጠት ፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን አነስተኛውን መስፈርት በፖሊሲው መሰረት 50 ፐርሰንት በማድረግ እነኚህ ሪፎርሞች መምህራን ልማት ላይ የምንሰራውን ፤ የዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያን ገድበን የወሰድናቸውን ሪፎርሞች ድምር ውጤት ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ነው ፤ ይሄንን ማድረግ ተገቢ ነው ጊዜው አሁን ነው ብለን ነው የገባንበት። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና  በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። መውጫ ፈተና በሁሉም  መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሀግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከትና ፈተናውን   በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል። የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ  ተማሪዎች ባሻገር  #የማታና #የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን…
#ExitExam

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  ፦

" የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣ የማታ እና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ  በመንግስትና ግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና #በኦንላይን ለመስጠት ታቅዷል ።

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል ።  "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

ምን ያህል ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ?

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወቅር ህዝቅኤል በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ፣ ዝግጅት እና ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ተማሪዎችን በተመለከተ) ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ፦

" አሁን የለየናቸው አሉ ፤ የደረሰን መረጃ አለ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎች ናቸው እጃችን ላይ ያሉት።

ነገር ግን ጥር ላይ በተለያየ ምክንያት ያላጠናቀቁ ልጆች በአንደኛ ሴሚስተር የሚያጠናቅቁና ወደ ምዘናው ሊመጡ የሚችሉ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ።

ከዛ ባሻገር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ System ውስጥ የሚያልፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የደረሱን መረጃዎች አሉ።

አሁን በቁጥር ነው የተቀበልነው ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስም እያንዳንዱ ስም በሚመጣ ሰዓት የተወሰነ የቁጥር ለውጥ ሊኖረው ይችላል አሁን ባለንበት ሁኔታ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለን እናስባለን።

ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው የሚገኘው። ከዛ ባሻገር አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል ፈተናዎች እንዲፈተኑ በማድረግ፣ psychologically እንዲዘጋጁ እንዲያጠኑ እየተሰራ ነው ተማሪዎችን በዛ ልክ አውቀው እየሰሩ ነው።

ፈተናው እንዴት manage ይደረጋል በሚለው ላይ የተለያዩ ማስፈፀሚያዎች ወደ ታች ወርደዋል በዚያ መሰረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደርጉ ነው የሚገኙት። "

የመጀመሪያውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?

" ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ።

ይሄ የሚሆነው እንዴት ነው የመጀመሪያው ዙር መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ነው ከዛ በኃላ ልክ 12ኛ ክፍል Private እንደሚፈተነው ሁሉ መውጫ ፈተና ላይም ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

እስከዛ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ የመውጫ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የሚያስገኘውን ፈተና ማለፍ ባይችሉ እንኳን ዝቅ ባሉ ደረጃዎች በLevel ደረጃ ባሉት (ከዲግሪ በታች ባሉ መመዘኛዎች) ተፈትነው ልክ COC እንደሚፈተነቱ ተፈትነው ማለፍ የቻሉበት ደረጃ ላይ Certify ይደረጋሉ በዛ ስራ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ይኖራቸዋል። "

@tikvahethiopia
#MoE #ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች #በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። 

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።

ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
#ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ " የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ይረዳኛል ፤ ትውልድ እና ሀገርንም ከውድቀት ይታደጋል " በሚል ዘንድሮ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መስጠት ይጀምራል።

ለዚህ ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች በኦንላይን ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናው ላይ ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተቋማት ለፈተናው ተማሪዎቻቸውን ዝግጁ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከዚህ የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ፈተናውን የማለፍ የማይችሉ ተማሪዎች ፈተናውን ደጋግመው እንዲወስዱ ዕድል ያላቸው ሲሆን በተማሪዎች ምረቃ ላይ ግን የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው።

ይህን የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ሁሉም ተቋማት ለማስፈፀም እየሰሩ ይገኛሉ።

ለአብነት ፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ " የመውጫውን ፈተና ያለፉ ብቻ " የመመረቂያ ጋዎን እንዲሰጣቸው ክትትል እንዲደረግ አሳስቧል።

የተቋሙ የሬጅስትራር እና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን በሚመለከት ለሁሉም የተቋሙ አካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራሮች በፃፈው ደብዳቤ የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው " የመውጫ ፈተና አፈፃፀም መመሪያ " መሰረት ፤ ኮርስ አጠናቀው ያልተመዘገቡ እንዲሁም ያልተመዘገቡትና ያልፋቁት " F " ያላቸው ተማሪዎች በስህተት ለመውጫ ፈተና ዝርዝራቸው የተላኩ ካሉ የመውጫ ፈተናውን እንደማይፈተኑ ከወዲሁ እንዲነገራቸውና የመውጫ ፈተና ኮርስም እንዳይመዘገቡ አዟል።

የመውጫ ፈተና " መመዝገብ የሚችሉት " ብቻ ኮርሱን እንዲመዘገቡና የምዝገባ ስሊፕ ለመውጫ ፈተና መግቢያ እንዲያገለግላቸው ከወዲሁ ለተማሪዎች እንዲሰጣቸውም ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ዳይሬክቶሬቱ ፤ ለምረቃ መሟላት ከሚገባቸው መመዘኛዎች በተጨማሪ የመውጫ ፈተና ያለፉ (50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ) ብቻ ለምረቃ እንዲቀርቡ ፤ የምረቃ መስፈርቱን ያሟሉና የመውጫ ፈተና ያለፉ ብቻ የመመረቂያ ጋዎን እንዲሰጣቸው ክትትል እንዲደረግ ዳይሬክቶሬቱ አሳስቧል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዘንድሮ የተማሪዎችን ምረቃ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ ይችላሉ።

More : @tikvahUniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይደመጥ የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የ " መውጫ ፈተና " ን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ከላይ ተያይዟል። በዚህ ማብራሪያ ፦ - የፈተናውን አይነት - የውጤት አገላለፅ - የጤና ተማሪዎች ፈተና / የሙያቸው እና የመውጫው - እንደው ተማሪዎች ፈተናውን ባያልፉ መቼ እና የት ? እስከ ስንት ጊዜ ድረስ ድጋሚ መውሰድ እንደሚችሉ - የፈተናው…
#ExitExam

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ምን አሉ ?

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው ምን አሉ ?

- የፈተናው አይነት " የምርጫ ጥያቄ " መሆኑን ገልፀዋል።

- የፈተናው ጥያቄ ብዛት በተመለከተ ጊዜው ሲደርስ እንደሚገለፅ፤ የጥየቄው ብዛት ግን ከ50 በላይ እንደሆነ ፤ በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ እንደሚኖር አሳውቀዋል።

- በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ ነው ፈተናው ፤ በተወሰኑ መስኮች ምርጫውን ለመሙላት ብዙ ሂሳብ ስለሚሰሩ የጥያቄ ቁጥሩ ከ100 ሊያንስ ይችላል።

- ተማሪዎች ፈተናውን እንደተፈተኑ ውጤታቸውን ወዲያው መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ቢሮርም የመጀመሪያ ቀን የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤት ቢገለፅ ሌሎች ላይ ከሚያሳድረው ጫና አንፃር ወይም ፈተናው ቀለል / ከባድ ነው ብሎ እንዳይዘናጋ / እንዳይጨነቅ ወዲያው አይገለፅም። የፈተናው ውጤት የሚገለፀው የመጨረሻው ፈተና ከተሰጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው።

- ውጤት አልፏል ወድቋል ብቻ ሳይሆን ተማሪው ያመጣው ውጤት ይገለፃል።

- የጤና ተማሪዎች ፈተና ሰኔ 30 ይጀምራል እስከ ሐምሌ 8 ድረስ ይዘልቃል። የጤና ተማሪዎች ቀድመው የሚፈተኑበት ምክንያት ቀኑን ሙሉ ፈተናውን ስለሚወስዱ ነው። ጥዋት ላይ ከሙያቸው ጋር የተያያዘውን ይፈታናሉ ፤ ከሰዓት ላይ የመውጫውን ፈተና ይወስዳሉ / በተቃራኒው / ።

- ፈተናው በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የተዘጋጀው ፤ በውስን ኃላፊዎች ብቻ እንዲታወቅ ተደርጓል፤ ስለማይታተም፣ እጅም ስለሌለበት ደህንነቱ አያሰጋንም።

- ፈተናውን ከመስጫው ሰከንድ በፊት ማየት የሚችል ሰው አይኖርም። ፈተናው ካለቀበት ሰከንድ በኃላ መስራት የሚችል ሰው አይኖርም። ይህ በማዕከል ነው ቁጥጥር የሚደረገው።

- የማለፊያው ነጥብ 50 % እና በላይ ሲሆን ይህን ያላለፉ (ኮርስ ያልጨረሱ) ከ5 / ከ6 ወር በኃላ ጥር እና የካቲት ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና መውሰድ ይችለሉ። በዚህም ከለተሳካ ከቀጣይ አመት ተፈታኞች ጋር መውሰድ ይቻላል። በዓመት ሁለት ጊዜ ለመስጠት ታቅዷል።

- አብዛኛው ተማሪ በመጀመሪያው ዙር ያልፋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፤ ካልሆነ ግን በሁለተኛው ዙር ተፈትኖ ያልፋል። ሁለቴ ተፈትኖ ማለፍ ያልቻለ እስከሚያልፍ / 50 % እና ከዚያ በላይ ማምጣቱ እስኪረጋገጥ ፈተናውን መውሰድ ይችላል።

- ፈተናው ተማሪዎች አልተሳካላቸውም ብሎ የማሸማቀቅ ዓለማ ስለሌለው እስኪያልፉ ድረስ መፈተን ይችላሉ።

- ምናልባት ያላለፉ ተማሪዎች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ አይጠበቅባቸውም ፤ ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል።

- ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች በምረቃ ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ ? ትምህርት ሚኒስቴር የምረቃ ፕሮግራም በተመለከተ በፖሊሲው ላይ እንደማይፅፍ ገልፀዋል። ጉዳዩ የተቋማት ነው ብለዋል። ሚኒስቴሩ በፖሊሲ የሚያስገድደው ግን የመውጫ ፈተናው የስርዓተ ትምህርቱ አካል ስለሆነ ይህን ያላለፈ ዲግሪ/ጊዜያዊ ጭምር፣  ትራንስክሪብት አይሰጠውም። የምረቃ ፕሮግራም ከማዕከል አይመራም ይህ የተቋማቱ ጉዳይ ነው። እኛ የምንከታተለው ፈተናውን ሳያልፉ ዲግሪ እንዳይሰጣቸው ነው።

- የምረቃ ጉዳይ እና በዕለቱ በምረቃ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ጉዳይ የሴኔት ነው ትምህርት ሚኒስቴር አይመለከተውም። ነገር ግን የመውጫ ፈተናው እየተሰጠ/ ሳይሰጥ በፊት ምረቃ ማድረግ በፍፁም አይቻልም።

- የመውጫ ፈተና ያላለፈ ተማሪ በፍፁም ዲግሪ፣ ቴምፖራሪ ዲግሪ፣ ሰርተፊኬት እንደማይሰጠው አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
#ExitExam

" የሚሰጠው ሞዴል ፈተና በጥያቄ ክብደቱም ሆነ በብዛቱ ከዋናው የመውጫ ፈተና ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ለሁሉም የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 29/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የሙከራ ፈተናው ከ168 ሺህ ለሚበልጡ ዕጩ ምሩቃን እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና በመስጠት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

የሙከራ ፈተናው ተማሪዎች የራሳቸውን መለያ ቁጥር እና የይለፍ ቃል ተጠቅመው በቀላሉ መፈተን እንዲችሉና ከፈተና ስርዓቱ ጋር እንዲተዋወቁ የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል።

ለሁሉም የግልና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጥያቄ ክብደቱም ሆነ በብዛቱ ከዋናው የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሞዴል ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 29/2015 ዓ.ም በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚሰጥም ኃላፊው ገልጸዋል።

የ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል። ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ዕጩ ምሩቃን ላይ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ይህ የመውጫ ፈተና ከቀናት በፊት ለጤና ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በተለያዩ የትምህርት መርሀግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ዕጩ ምሩቃን ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ። የመውጫ ፈተናው እስከ ሐምሌ 8 /2015 ድረስ መሰጠቱን የሚቀጥል ሲሆን የፈተናው ውጤት በአጭር ጊዜ…
#ExitExam

በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙና የመውጫ ፈተና የወሰዱ የ " መካኒካል ምህንድስና " የትምህርት ዘርፍ ተማሪዎች በተፈተኑት የፈተና ይዘት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልእክት አሳውቁ።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ለየሚማሩበት ተቋማት የሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ጥያቄ እና ቅሬታ የተቀበለ ሲሆን ተማሪዎቹ ምንም እንኳን የትምህርት ሚኒስቴር ብቁ ዜጋን ከማፍራት አንጻር እና የት/ት ጥራትን ለማሻሻል እየተገበረ ያለውን የመውጫ ፈተና የሚደግፉት ቢሆን የተፈተኑት የፈተና ይዘት ከተነገራቸው መመዘኛ ነው ተብሎ ከቀረበው ሀሳብ ጋር የማይገጥም መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ ለመመዘኛ የቀረበው የፈተናው ክብደት እና ብሉ ፕሪርት ተብሎ ከተሰጣቸው ጋር እንዳልተጣጣመ ፤ ለፈተናው የተሰጣቸው ሰዓትም ከጥያቄው አንፃር እዚህ ግባ የማይባል መሆኑ በማስረዳት ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የወጡ ፈተናው ጥያቄዎች ተከልሰው እንዲታዩ የጠየቁ ሲሆን በተማሪዎች ዘንድ ያሉ ጥያቄዎች የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ በማጤን የፈተናው ውጤት ከመገለፁ በፊት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎችን ጥያቄ በተመለከተ የሚመለከተውን አካል ለማነጋገር ጥረት ያደርጋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጉዳዮችን በ @tikvahUniversity ይከታተሉ።

@tikvahethiopia