#DrLiaTadesse
ከኮቫክስ የተገኘውና ለ20 በመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሆን የኮሮና ቫይረስ ክትባት በቅርቡ ይመጣል።
ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት ለደሃ አገሮች በዕርዳታ መልክ ለማቅረብ ካቀደው የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ክትባት ውስጥ ፣ ኢትዮጵያ እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት መጠን በጥቂት ወራት እንደምታገኝ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ
@TIKVAHETHIOPIA

TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ምስጋናው እንጅፈታ አረጋግጠዋል። ም/ኮሚሽነሩ ፥ አቶ አትንኩት የተያዙት በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ችግር እጃቸው እንዳለበት ተጠርጥረው ነው ሲሉ ተናግረዋል። አቶ አትንኩት ዛሬ ረፋድ ነው በቁጥጥር ስር…
ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በመተከል ዞን የጸጥታ ችግር እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው ዛሬ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገለፀ።
ይህን የገለፁት የክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ናቸው።
አቶ ሙሳ ፥ ሌሎችም ከፀጥታ ችግር ጋር እጃቸው ያለባቸውን አመራሮች እና ግለሰቦች የማደኑ ስራ መቀጠሉን ለኢዜአ ተናግረዋል።
ዛሬ ረፋድ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መገለፁ ይታወሳል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,155
• በበሽታው የተያዙ - 243
• ህይወታቸው ያለፈ - 1
• ከበሽታው ያገገሙ - 893
አጠቃላይ 123,388 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,913 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 110,739 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
233 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

#AviationAcademy
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የገፅ ለገፅ ትምህርት መስጠት ጀምሯል።
በክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር በግማሽ እንዲቀንስ ተደርጓል፤ የተግባር ስልጠናውም አካላዊ ርቀት ተጠብቆ እየተሰጠ ነው ብሏል።
አካዳሚው የገፅ ለገፅ ትምህርቱን በሚሰጥበት ወቅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዙ መንገዶችን የማይተገብሩ ሰልጣኞችን #እንከማባረር የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል።
አካዳሚው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የባከነውን የስልጠና ጊዜ ለማካካስ በሚል ተማሪዎቹን ጫና ውስጥ እንደማይከት ገልጾ ፤ በስልጠናው ተማሪዎች ማወቅ ያለባቸውን እውቀት ሁሉ እንዲያገኙ የስልጠና ጊዜው ወደፊት እንደሚገፋ አሳውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ፦
- በአውሮፕላን አካልና ሞተር ጥገና
- በአብራሪነት
- በበረራ አስተናጋጅነት
- በማርኬቲንግ እና ሊደርሺፕ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ታሳቢ በማድረግ ለ1 ሺህ 500 ሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ~(ኢቢኤስ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#WoalitaSodo በዎላይታ ሶዶ በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ለተጎዱ ነጋዴዎች ጊዜያዊ አማራጭ የገበያ ቦታ እየተዘጋጀ ነዉ፡፡ በተለምዶ መናፈሻ ተብሎ የሚጠራዉ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምድረ ግቢ ነዉ በአማራጭ ገበያ ቦታነት እየተዘጋጀ የሚገኘዉ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ እና የዞኑ መንግስት ከተጎጂዎቹ ጋር ተወያይተው በተስማሙት መሰረት ነው ስራው የተጀመረው። ነጋዴዎቹ በሚዘጋጅላቸዉ ጊዜያዊ…
#UPDATEWolaitaSodo
1. የጊዜያዊ ገበያዉ ሥራ መጀመር ፦
በዎላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ቃጠሎን ተከትሎ ጊዜያዊ አማራጭ የገበያ ቦታ መዘጋጀቱ ተገልጾ ነበር።
በጊዜያዊ ገበያዉ ከ1,200 በላይ ቦታ ተዘጋጅቶ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ቦታቸዉን ተረክበዉ ሥራቸዉን ጀምረዋል፡፡
ቦታቸዉን የተረከቡ ነጋዴዎች ለጊዜያዊ ጥላነት /ሼድ/ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በራሳቸዉ እያቀረቡ እየሠሩ ነው።
2. የፌደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ድጋፍ ፦
በመርካቶ ገበያ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የፌደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን 2 ሺህ 4 መቶ 93.6 ኩንታል ስንዴ እና ሌሎች አልሚ ምግቦች እርዳታ አደርጓል።
በተደረገው እርዳታ በቤተሰብ ደረጃ 16 ሺህ 626 ሰዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።
3. የዞኑ አመራሮች ድጋፍ ፦
በመርካቶ በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም አጠቃላይ የወላይታ ዞን አመራሮች የ1 ወር ደመወዝ ድገፍ አደረጉ።
በአጠቃላይ ቃል የተገባው የአንድ ወር የአጠቃላይ አመራር ደመወዝ 12 ሚሊዮን 97 ሺህ 519 ብር ነው ተብሏል።
ምንጭ፦ የወላይታ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ፣ ፌዴራል ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#Metekel
በድባጤ 'ዚጊ ቀበሌ' ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ንፁሃን ሲገደሉ አንድ ሰው ቆስሏል።
ጥቃቱ በትላንትናው ዕለት ማለዳ ላይ እንደተፈፀመ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ገልጿል።
የሟቾች የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት ተፈፅሟል።
በጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ አንደኛው ባለትዳር እና 5 ልጆች አባት እንደሆኑ ወንድማቸው ትላንት ምሽት በተሰራጨ መደበኛው የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ሲናግሩ ተደምጠዋል።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ ታደለ ተረፈ ጥቃቱን አረጋግጠዋል ፥ እሳቸውም በድባጤ ወረዳ በዚጊ ቀበሌ ወደ ማሳቸው በሚሄዱ 3 ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ 2ቱ መገደላቸውን አንደኛው መቁሰሉን መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ትላንት የመተከል ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር በዞኑ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

#SolianaShimeles
የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዝግጅት ፦
ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ (የምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ) ስድስተኛው (6) አገራዊ ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ምርጫዎች በእጅጉ ፍትሃዊ ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ ሆኖ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ቁሳቁሶች 90 በመቶ ተገዝተው መጠናቀቃቸውን ለኢፕድ ተናግረዋል።
ለምርጫው የተገዙት ቁሳቁሶቹ እንዲሁም ህትመቶች ከዚህ በፊት ምርጫ ከተደረገባቸው ቁሳቁሶች እና ህትመቶች የተለዩ እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው ብለዋል።
የድምጽ መስጫ ወረቀቶቹ እና የመራጭ ካርዶቹ ደግመው መታተም የማይችሉ ፣ ከተነካኩ የሚያስታውቁ፣ የራሳቸው የሆነ ቀሪ ያላቸው ፣ ኮፒ ለመደረግ የሚያስቸግሩ እንዲሁም የድምጽ መስጫ ሳጥኖቹ አስተማማኝ እና መራጩ ድምጽ ሲሰጥ በነጻነት ለመስጠት የሚያስችል መከለያዎች ያሉት እንደሆነ ጠቁመዋል።
ከዚህ ቀደም በተካሄዱት ምርጫዎች ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ የተለያዩ ማጭበርበሮችን የሚያስቀሩ የምርጫ ቁሳቁሶች መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል። ~ EPA

#EthioTelecom
ኢትዮ ቴሎኮም የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ለደንበኞቹ እያቀረበ ይገኛል።
አገልግሎቱን ለማግኘት A ፣ C ወይም L ወደ 810 መላክ ወይም *810# ላይ መደወል እንደሆነ ገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችሉ መስፈቶች ተከታዮቹ እንደሆኑ አሳውቋል ፦
• የቅድመ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ጊዜ ያላለፈባቸው።
• የሞባይል አገልግሎታቸው በማንኛውም ምክንያት ያልተቋረጠ።
• ከአሁን በፊት የወሰዱትን ክሬዲት በሙሉ አጠናቀው የከፈሉ።
• ከ3 ወራት ያላነሰ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ የቆዩ እንዲሁም በየወሩ የ30 ብር የሞባይል አየር ሰዓት በመሙላት ሲጠቀሙ የነበሩ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።
ለክሬዲት አገልግሎት የተዘጋጁ የሞባይል ድምፅ እና ኢንተርኔት ጥቅሎች ዝርዝር ከላይ ባሉት 2 ምስሎች ተያይዟል።
* ኢትዮ ቴሌኮም 10% የአገልግሎት ክፍያ ቀጣይ ከሚሞሉት የአየር ሰዓት እንደሚቀንስ አስገንዝቧል።

#Tigray
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የአሮጌ ብር ቅየራ ድጋሚ ተጀምሯል፡፡
የብር ቅየራው ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ከዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ አስታውቋል።

#AgituGudeta #EthiopiaEmbassyRome
በጣሊያን ውስጥ ከፍየል ወተት በምታዘጋጀው አይብና ለስደተኞች መብት ተቆርቋሪነቷ የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ አጊቱ ጉደታ ቤቷ ውስጥ ተገድላ መገኘቷን ፖሊስ ማሳወቁን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለቢቢሲ አረጋገጠ።
የኤምባሲው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሠራተኛ የሆኑት አቶ ደሳላኝ መኮንን እንደተናገሩት ትናንት ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ማጣራትና ምርመራ በአጊቱ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ተጠርጣሪ ስደተኛ ወንጀሉን መፈጸሙን እንዳመነ ገልጸዋል።
በሮም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም የአጊቱ ጉደታን ሞት በተመለከተ በፌስቡክ ገጹ ላይ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፤ ግድያውን በተመለከተም ኤምባሲው ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በቶሎ ተጣርቶ ይፋ እንዲደረግና ወንጀለኛው ለፍርድ እንዲቀርብ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አመልክቷል።
የአጊቱ ግድያ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቻ ሳይሆን በጣሊያኖችም ላይ ትልቅ ድንጋጤና ሐዘን የፈጠረ መሆኑን የገለጹት አቶ ደሳለኝ በተለይ በስደት ወደ ጣሊያን የሚመጡ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያንን በመርዳት ስለምትታወቅ ወንጀሉ በስደተኞች ዘንድ ታላቅ ሐዘንን አስከትሏል ብለዋል።
ፖሊስ እንዳለው አጊቱ ጉደታ ትሬንቲኖ ውስጥ በሚገኘው ፍራሲሎንጎ በተባለው ስፍራ ባለው መኖሪያ ቤቷ ውስጥ ጭንቅላቷ ላይ ጉዳት ደርሶባት አስከሬኗ አግኝቷል።
ምርመራ እያደረገ እንደሆነ የገለጸው ፖሊስ የአጊቱ ጉደታ ሞት ጭንቅላቷ ላይ በመዶሻ በመምታት የተፈጸመ የግድያ ወንጀል ሳይሆን እንዳልቀረ ገልጿል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopia

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ድጋፍ አደረገ።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ግምታቸው ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ከ350 ሺህ በላይ ደብተሮች እና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች አበረከተ።
ደብተሮቹ ላይ የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ፎቶግራፍ እና የክለቡ አርማ ያረፈባቸው ሲሆኑ መታሰቢያነቱም ለእሳቸው እንደሆነ ተገልጿል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ማህበር ያሰባሰበው ቁሳቁስ ከፍተኛ መጠን ያለው በመሆኑ በአዲስ አበባ፣ በማይካድራ፣ በመቐለ ፣ በመከተል እና በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ለተቸገሩ ተማሪዎች ተደራሽ ይሆናል ብሏል።
እንዲሁም ለተመረጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና የተለያዩ ተቋማት ልገሳ አድርጓል ፦
- ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
- ለተስፋአዲስ የህጻናት ካንሰር መርጃ ድርጅት (TAPCCO)
- ለመከላከያ ሰራዊት
- ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ
- ለትኩረት በጎአድራጎት ማህበር
- ለህይወት የተቀናጀ የልማት ማህበር
- ለትምህርት ሚኒስቴር
መልዕክቱን የላከልን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ነው።