#የእሳት_አደጋ_በሀዲያ_ዞን
በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ በሶስት ቀበሌዎች ፦
- ኤራ ጌሜዶ፣
- ኩናፋ
- ጉና ሜጋቾ በደረሰ እሳት አደጋ 4 መቶ 36 የቤተሰብ አባላት መፈናቀላቸውን የዞኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት አሳውቋል።
ፅህፈት ቤቱ አደጋው የተፈጥሮ እሳት አደጋ ነው ብሏል።
በደረሰው አደጋ ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መዉደሙ ተጠቁሟል፡፡
በአደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
128 ዶሮዎች፣ 243 ኩንታል የተለያዩ የእህል ዘሮች ፣ 18 የንብ ቀፎዎች፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች እና በአካባቢው የነበሩ የጓሮ አትክልቶች በድምሩ ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል።
በሌላ መረጃ ፦
በምዕራብ ሶሮ ወረዳ በጃቾ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ250 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል።
አደጋው ታህሳስ 18 ከምሽቱ 2፡30 በመብራት ኮንታክት የደረሰ መሆኑን የወረደው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
አደጋው ህብረተሰቡና የፖሊስ አካላት ባደረጉት ርብርብ ወደ ሌሎች ሱቆችና መኖርያ ቤቶች ሳይሻገር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተገልጿል።
(ሀዲያ ዞን ኮሚኒኬሽን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ነገ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት #አስቸኳይ_ጉባኤ እንደሚካሄድ ተገለጸ። የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ እንዳሉት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል። በጉባኤው የመተከል ዞን የሠላም እና ጸጥታ ችግር ዋነኛው የምክር ቤቱ ትኩረት እንደሚሆን ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ አስታውቀዋል፡፡ ሌሎችም ክልላዊ እና…
#UPDATE
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመሯል፡፡
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባዔው ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ያነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዞኑ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ምስጋናው እንጅፈታ አረጋግጠዋል።
ም/ኮሚሽነሩ ፥ አቶ አትንኩት የተያዙት በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ችግር እጃቸው እንዳለበት ተጠርጥረው ነው ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ አትንኩት ዛሬ ረፋድ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

አቶ አብነት በዋስ እንዲፈቱ ተደረገ።
የአቶ ሴኩቱሬ የልጅ ባል አብነት ሃይሉሸዋ በዋስ እንዲፈቱ ተደረገ።
አቶ ኣብነት ሃይሉሸዋ ከህወሓት ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ተጠርጥረው ምርመራ ሲደረግቸው ቆይቷል።
ተጠርጣሪው በምስክርነት ዞረው በዋስ እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ነገር ግን ከሃገር እንዳይወጡ እግድ ተጥሎባቸዋል።
በሌላ በኩል ፦
የ "ማይካድራውን ጭፍጨፋ" #አስተባብራለች የተባለችው ወታደር ታጎስ ገ/ትንሳኤ ጉዳይዋ በሀገር መከላከያ የጦር ፍርድ ቤት እንዲታይ መዝገቡ ወደ መከላከያ የጦር ፍርድ ቤት መዞሩ ተገልጿል። #ኤፍቢሲ

#UPDATE የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመሯል፡፡ ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጉባዔው ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ያነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዞኑ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የ4 የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት ተነሳ !
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ 5 ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የ4 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡
በምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው ፡-
1. አቶ አድጎ አምሳያ
2. አቶ ሽፈራው ጨሊቦ
3. አቶ ግርማ መኒ
4. አቶ አረጋ ባልቢድ ናቸው፡፡
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የቀረቡትን የ4ቱን የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

#Egypt #Ethiopia #Sudan
በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል የሚደረገው ድርድር በሚቀጥለው #እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥልም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።
አምባሳደሩ ይህን የገለፁት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ነው።
ከታላቁ ህዳሴው ግድብ ድርድር ራሷን አግልላ የነበረችው #ሱዳን ወደ ድርድሩ እንደምትመለስ በቅርቡ ይፋ ማድረጓ ይታወቃል፡፡
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ ላይ ያነሷቸውን ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ : telegra.ph/ALAIN-12-29 (መረጃውን አዘጋጅቶ ያሰራጨው አል ዓይን ኒውስ ነው)
@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT

#FDREDefenseForce
የልዩ ዘመቻ ኮማንዶ 2ኛ ብርጌድ አንደኛ ወጋገን ሻለቃ የሕወሓት ቡድን ሲያስወነጭፋቸው የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በመቐለ ከተማ በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችቶ እንዳገኛቸው አሳወቀ።
በተደጋጋሚ ወደ ባሕር ዳር ፣ ጎንደር እንዲሁም አስመራ ሲወነጨፉ የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው መገኘታቸውን ነው ኮማንዶው ያስታወቀው።
የልዩ ዘመቻ ኮማንዶ 2ኛ ብርጌድ አንደኛ ወጋገን ሻለቃ አደረኩት ባለው አሰሳ እና ፍተሻ በመጋዘን ውስጥ ያልተተኮሱ 13 ሮኬቶች እንዳገኘ ገልጿል ፣ 7 ሮኬቶች ደግሞ ከማስቀመጫው ሳጥን ወጥተው ተተኩሰው እንደነበርም አስታውቋል።
በተጨማሪም የተተኳሽ ሮኬት ማስወንጨፊያ ከባድ ተሽከርካሪ ከመቐለ ከተማ ዳርቻ ባለ ስፍራ ተደብቆ መገኘቱን ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

"ሾላ ቀበሌ" በደረሰ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ።
በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ "ሾላ ቀበሌ" ትላንት ታህሳስ 19 ቀን 2013 ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።
የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ እንደማይታወቅ ተናግረዋል።
በእሳት አድጋው እካሁን መጠኑ ያልታወቀ ከፍተኛ ንብረት መውደሙን አባላቶቻችን በ www.tikvahethiopia.net ላይ አሳውቀዋል።
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ወደ ም/ኦሞ ዞን ፖሊስ ተደጋጋሚ ስልክ ብንሞክርም ስልኩ ሊነሳልን አልቻለም።
የቤሮ ወረዳ ገቢ/ባለ/ቅ/ፅ/ቤት በፌስቡክ ገፁ ትላንት በሾላ ቀበሌ መነሻው ያልታወቀ የእሳት አደጋ በግብር ከፋዮች እና አጠቃላይ በቀበሌው ህዝብ ላይ ውድመት ማስከሰቱን አሳውቋል።
ፅ/ቤቱ በተፈጠረው አደጋ ለተጎጂዎች መፅናናትን በመመኘት ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ እንደሚሰራ ገልጿል።

* ተጨማሪ
ቤሮ ወረዳ 'ሾላ ቀበሌ' ስለደረሰው የእሳት አደጋ የቤሮ ወረዳ ገቢ/ባለ/ቅ/ፅ/ ቤት ኃላፊን አነጋግረናቸዋል ፦
- ኃላፊው በአሁን ሰኣት የእሳት አደጋው ጉዳት ባደረሰበት አካባቢ ይገኛሉ።
- የመጀመሪያ እርዳት እየተሰጠ እንደሆነ ገልፀዋል።
- ብዙ ህፃናት ስላሉ ምግብ እንዲያገኙ እየተሰራ ነው።
- ቤት ንብረታቸው የተቃጠለባቸው ዜጎች የሚያድሩበትን ቦታ ለማመቻቸት እየተሰራ ነው።
- ወጣ ወጣ ያሉ ከአደጋው የተረፉ የተወሰኑ ተቋማት አሉ ፤ ትምህርት ቤት ፣ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፣ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ፣ መስጊድ ተጎጂዎች እዛ አርፈው የጋራ መመገቢያ ለማዘጋጀት እየተሰራ ነው።
- ምን ያህል ሰው በአደጋው ተጎጂ እንደሆነ ገና እየተመዘገበ ይገኛል። ዝርዝር መረጃ ተጣርቶ እንዳለቀ ለቲክቫህ አባላት እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

#Metekel
በመተከል ዞን ከ97 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
ከ58 ሺ በላይ ዜጎች ግልገል በለሰ ከተማ ይገኛሉ ፤ 39 ሺህ 679 ተፈናቃዮች በአማራ ክልል አዊ ብሔርስብ አስተዳደር በተዘጋጀው ጊዜያዊ መጠለያ ይገኛሉ።
ዜጎች ከተፈናቀሉበት ጊዜ አንስቶ ያተደረገ ድጋፍ ፦
• በግልገል በለሰ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ33 ሺ ኩንታል በላይ ስንዴ ፣ 4 ሺ 38 ኩንታል ዓልሚ ምግብ እና 187 ሺህ ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
• አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሚገኙ ተፈናቃዮች 3 ሺህ 404 ኩንታል ስንዴ እና 10 ሺህ 316 ሊትር ዘይት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
ይህ ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ የምግብ እህልና ቁሳቁስ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ለአብመድ አሳውቋል። #MinistryOfPeace

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሌተና ጀነራል አበባው ታደሰ እና በሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ስም #ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጽ ተከፍቶ የተዛባና የተሳሳተ መልዕክት እየተላለፈ እንደሚገኝ ገልጿል።
የመከላከያ ሰራዊት ሁለቱ ከፍተኛ ጀነራል መኮንኖች ምንም አይነት ማህበራዊ ገጽ በስማቸው ያልከፈቱ መሆኑን አሳውቆ ፣ ህብረተሰቡ በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይደናገር አሳስቧል።

"ሾላ ቀበሌ" በደረሰ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ። በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ "ሾላ ቀበሌ" ትላንት ታህሳስ 19 ቀን 2013 ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል። የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ እንደማይታወቅ ተናግረዋል። በእሳት አድጋው እካሁን መጠኑ ያልታወቀ ከፍተኛ ንብረት መውደሙን አባላቶቻችን በ www.tikvahethiopia.net ላይ አሳውቀዋል።…
#UPDATE
የቤሮ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ዶንቴስ ባይኬስ በሾላ ቀበሌ በደረሰው የእሳት አደጋ 586 ሚሊየን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ለኤፍ ቢ ሲ አስታወቁ።
የእሳት አደጋው መነሻ ከአንድ ጸጉር ቤት ውስጥ የተነሳ እሳት መሆኑን ነው የወረዳው አስተዳዳሪ ለኤፍ ቢ ሲ የተናገሩት።
በአደጋው ፦
• 1 ሺህ 840 መኖሪያ ቤቶች፣
• 547 የንግድ ቤቶች፣
• 37 የወርቅ ማህበራት፣
• 109 የወርቅ ማሽን #መውደማቸው ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የቤሮ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ዶንቴስ ባይኬስ በሾላ ቀበሌ በደረሰው የእሳት አደጋ 586 ሚሊየን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ለኤፍ ቢ ሲ አስታወቁ።
የእሳት አደጋው መነሻ ከአንድ ጸጉር ቤት ውስጥ የተነሳ እሳት መሆኑን ነው የወረዳው አስተዳዳሪ ለኤፍ ቢ ሲ የተናገሩት።
በአደጋው ፦
• 1 ሺህ 840 መኖሪያ ቤቶች፣
• 547 የንግድ ቤቶች፣
• 37 የወርቅ ማህበራት፣
• 109 የወርቅ ማሽን #መውደማቸው ተገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbabaPoliceCommission
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ትምህርት ቤት ጀርባ ዛሬ ከቀኑ በግምት 8:30 ሁለት ህፃናት ወድቆ ያገኙትን ቦንብ ሲነካኩ ፈንድቶ የአምስት ዓመት እድሜ ያለው ህፃን ፀጋዬ ተክለማርያም ህይወቱ ሲያልፍ የአምስት ዓመቱ ህፃን ግዛው አንተንአየሁ በእግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበት ህክምና እንደተደረገለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#DrLiaTadesse
ከኮቫክስ የተገኘውና ለ20 በመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሆን የኮሮና ቫይረስ ክትባት በቅርቡ ይመጣል።
ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት ለደሃ አገሮች በዕርዳታ መልክ ለማቅረብ ካቀደው የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ክትባት ውስጥ ፣ ኢትዮጵያ እስከ 20 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን ለመከተብ የሚያስችል የክትባት መጠን በጥቂት ወራት እንደምታገኝ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ
@TIKVAHETHIOPIA

አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ምስጋናው እንጅፈታ አረጋግጠዋል። ም/ኮሚሽነሩ ፥ አቶ አትንኩት የተያዙት በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ችግር እጃቸው እንዳለበት ተጠርጥረው ነው ሲሉ ተናግረዋል። አቶ አትንኩት ዛሬ ረፋድ ነው በቁጥጥር ስር…
ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በመተከል ዞን የጸጥታ ችግር እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው ዛሬ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገለፀ።
ይህን የገለፁት የክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ናቸው።
አቶ ሙሳ ፥ ሌሎችም ከፀጥታ ችግር ጋር እጃቸው ያለባቸውን አመራሮች እና ግለሰቦች የማደኑ ስራ መቀጠሉን ለኢዜአ ተናግረዋል።
ዛሬ ረፋድ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መገለፁ ይታወሳል።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,155
• በበሽታው የተያዙ - 243
• ህይወታቸው ያለፈ - 1
• ከበሽታው ያገገሙ - 893
አጠቃላይ 123,388 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,913 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 110,739 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
233 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።