TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"እንዲህ አዝኜ አላውቅም" - አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ

ሱሌይማን ደደፎ በተባብሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፤ የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ "በመደመር ፍልስፍና አልስማማም፤ የኢሕአዴግንም ውሕደት አላምንበትም" ማለታቸውን አሳዝኝ እንደሆነ አስታወቁ።

አቶ ለማ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል በሰጡት ቃለ ምልልስ "ከመጀመሪያው ጀምሮ የፓርቲዎችን መዋሃድ በተመለከተ የማላምንበት መሆኑን ለሥራ አስፈጻሚውና ለሁሉም በስፋት ገልጫለሁ። መዋሃዱ ትክክል አይደለም፤ ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም። ወቅቱ አይደለም" ብለዋል።

አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎም በበኩላቸው አቶ ለማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ጋር ያላቸውን ልዩነቶች እንደሰሙበት ወቅት አዝነው አንደማያውቁ በቲዊተርና ፌስቡክ ገጾቻቸው ላይ አኑረዋል።

#SBS

@tikvahethiopia @tsegabwolde
"በማናቸውም የኦዲፒ እና የኢሕአዴግ ስብሰባዎች ላይ ውህደቱንና የመደመር ዕሳቤን አስመልክቶ ከአቶ ለማ የልዩነት ሃሳብ አልሰማንም፤ የተለየ አማራጭ ሃሳብም አላቀረቡም!" - አቶ ታየ ደንደኣ(የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

አቶ ታየ ደንደኣ ስለ ብልፅግና ፓርቲ አመሠራረት ሂደት፣ ፋይዳዎቹና የአቶ ለማ መገርሣ በውህደቱ አላምንም ማለትን አስመልክተው ከSBS አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፦ "አቶ ለማ በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ውህደቱ አስፈላጊ እንደሆነና የመደመር ዕሳቤ ከኢትዮጵያ ዐልፎ ለምሥራቅ አፍሪካም ጠቃሚ ሃሳብ እንደሆነ ተስማምተው ነው ያጸደቁት፤ የልዩነት ሃሳብ አልሰማንም። ከዚያም ዐልፎ በኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴና ጉባኤ፣ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ ሁሉ የተለየ አቋም አላንጸባረቁም። በዚህ መሄድ አለብን የሚል የተለየ አማራጭ ሃሳብም አላቀረቡም" ብለዋል።

#SBS
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ኮሮና ቫይረስ ለተራራ ጎሪላዎች ሕይወት አስጊ ሆኗል!

የኮሮና ቫይረስ አስጊነት ተከትሎ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ቨሩንጋ ብሔራዊ ፓርኳን እስከ ወርኃ ጁን ለቱሪስት ዘግታለች።

ሩዋንዳም በተመሳሳይ ሶስት ብሄራዊ ፓርኮችን ለቱሪስቶች እንዲሁም ለጥናት ስራዎች ዘግታለች። ኡጋንዳ ግን እንደ ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተመሳሳይ እርምጃ አልወሰደችም።

በኡጋንዳ ፣ ሩዋንዳና ኮንጎ ጥበቃ በሚደረግላቸው ሥፍራዎች የሚገኙት የተራራ ጎሪላዎቹ ቁጥር ከ1,000 ያልበለጠ ነው።

#AP #SBS
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia