TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

ዛሬ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ 4 ወረዳዎች እና 1 ከተማ አስተዳደር የ "ክላስተር" አደረጃጀትን በየም/ቤቶቻቸው ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አፅድቀዋል።

የመስቃን እና ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እና የቡታጅራ ከተማ ማዕከሉን ቡታጅራ ያደረገ አዲስ ዞን ለመመስረት በተጨማሪነት የወሰኑ ሲሆን የማረቆ እና ቀቤና ወረዳዎች ደግሞ ወደ ልዩ ወረዳነት ለማደግ ውሳኔ አሳልፈዋል።

የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ም/ ቤቶች፤ በ" ክላስተር" የሚደራጀውን አዲስ ክልል የመቀላቀል ውሳኔን ያጸደቁት በሙሉ ድምጽ መሆኑን ተነግሯራ።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን የሚል ስያሜ ያለው አዲስ ዞን ለመመስረት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብም በተመሳሳይ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን ተነግሯል።

የ4ቱ ወረዳዎች ም/ቤቶች ዛሬ የወሰኗቸውን ውሳኔዎች ለፌደሬሽን ም/ቤት ያስገባሉ ተብሏል።

የፌዴሬሽን ም/ቤት ወረዳዎች እንደዚህ አይነት ውሳኔዎች የማሳለፍ ስልጣን አላቸው ወይ ? በሚል ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።

የም/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ " ምክር ቤቶቹ ስለ ህዝብ ጥያቄ የመወያየት፤ ተወያይተውም ውሳኔ የማሳለፍ ስልጣን አላቸው፤ ሆኖም ጥያቄው የሚቀርበው #በዞን እና #በክልል ምክር ቤቶች አልፎ ነው " ሲሉ ማስረዳታቸውን #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር ዘግቧል።

ከቀናት በፊት የጉራጌ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ዞኑን ከአጎራባች ዞኖች እና ልዩ ወረዳ ጋር አንድ ላይ በክልል እንዲደራጅ በመንግስት የቀረበውን ምክረ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎ ነበር።

በምክር ቤቱ ከተገኙ 92 አባላት ውስጥ 40ዎቹ የ " ክላስተር " አደረጃጀት ምክረ ሃሳብ የደገፉ ቢሆንም 52 አባላት ክላስተርን በመቃወማቸው ነው ምክረ ሀሳቡ ውድቅ የተደረገው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ። ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው። በዚህም መሠረት :- - የም ዞን - ምስራቅ ጉራጌ ዞን - ጠምባሮ ልዩ ወረዳ - ቀቤና ልዩ ወረዳ - ማረቆ ልዩ ወረዳ ሆነው…
#NewsAlert

የደቡብ ኢትያጵያ ክልላዊ መንግስት አዲስ ዞን እና የወረዳ አስተዳደር መዋቅርን ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት ፦

- የአማሮ ፣ የደራሼ ፣ የባስኬቶ፣ የቡርጂ፣ የአሌ ልዩ ወረዳዎች እያንዳንዳቸው እራሳቸውን ችለው #በዞን ይደራጃሉ።

- በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ እንዲደራጅ ተወስኗል።

- የደቡብ ኦሞ ዞን በሁለት ዞን እንዲደራጅ ተወስኗል።

• ከደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ፣ የሐመር፣ የበና ጸማይ ፣የሰላማጎ፣ የኛንጋቶም የዳሰነች ወረዳ እና የቱርሚ ከተማ አስተዳደር በጋራ #በዞን የሚደራጁ ይሆናል።

• ከደቡብ ኦሞ ዞን የደቡብ አሪ፣ የወባ አሪ የባካ ዳውላ ፣ የሰሜን አሪ ወረዳዎች እንዲሁም የጂንካ ከተማ አስተዳደር እና የገሊላ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በጋራ ሆነው #በዞን ይደራጃሉ ተብሏል።

መረጃ የክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia