#MinistryOfEducation
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሁሉም አካባቢ እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዛሬ እንደተናገሩት በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀመር ከ700,000 በላይ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ተዘጋጅቷል።
ከዚህ በተጨማሪ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን 50 ሚሊዮን ብር መያዙን አሳውቀዋል።
በአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በህግ ማስከበር ሂደቱ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለመጠገን እና ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነው ብለዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም ተባለ።
በዚህ ጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበይነ መረብ መክረዋል።
ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ ድጋሚ የተጀመረ ሲሆን አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ተነስቷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አሳስበዋል።
ትምህርት ላይ የሚሰሩ አጋር አካላት እንዲሁም ከትምህርት ዘርፍ ውጭ ያሉ ተቋማትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር "ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ" በሚል ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የመመለስ ዘመቻም እንደሚጀመር አሳውቋል።

#MinistryofEducation
ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡
በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ባሉ የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ትምህርት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡
በ2015 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ህፃናት ወይም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቻ እንዲማሩ የሚያዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አሁን ግን በመጭው የትምህርት ዘመን ህፃናት ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መማር እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው 31ኛውን ጉባኤ ላይ ነው።
" ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቁ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲማሩ እናደርጋለን ያሉት " ሚኒስትሩ ብርሀኑ (ፕ/ር) " ተማሪዎቹ የትምህርት ደረጃቸው ከፍ ሲል የሚማሯቸው ትምህርቶች በእንግሊዘኛ ቋንቋ ስለሚሆኑ ከልጅነታቸው ጀምሮ ቋንቋውን እንዲያውቁት ማድረግ አስፈላጊ ነው " ብለዋል፡፡
አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ወደ ትግበራ ከገባት 2015 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲማሩ የቆዩት በአፍመፍቻ ቋንቋቸው ነው አሁን ደግሞ በመጭው የትምህርት ዘመን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራሉ ተብሏል። #ሸገርኤፍኤም
@tikvahethiopia