#MoSHE
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በ2013 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና በሠላማዊ መንገድ ለማስቀጠል እንደሚሠራ ገልፀዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ትላንት ባቀረቡት በዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ የሠላም ተግዳሮቶች ዳሰሳ ሪፖርት በ2013 በተቋማቱ ሠላም ለማስፈን በልዩ ሁኔታ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባለፉት የትምህርት ዘመናት በተለይም ደግሞ በ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሲገጥሙ የነበሩትን ውጫዊና ውስጣዊ የሠላም ፈተናዎችን ለመቅረፍ ዝግጅት መደረጉን ዶ/ር ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡
ጽንፍ የረገጡ የፖለቲካ አቋሞች ፣ ሚዛናዊ ያልሆኑ ውስን ሚዲያዎች ፣ አክትቪስቶች ፣ አሁን ባለዉ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ምክንያት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ፣ የተቋማቱ አቅም ውስንነትና መሰል ጉዳዮች ሠላማዊ መማር ማስተማርን እንዳያዉኩ ብዙ ስራዎች እየተሠሩ እንደሆነ በገለጻው ቀርቧል፡፡
በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በቀጣይነት የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ በየደረጃው ካሉት ባለድርሻ አካት ጋር እንደሚሠራና ለተቋማቱም የተደራጀ ችግር ፈቺ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ተጠቅሷል፡፡ (MoSHE)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#JacindaArdern በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምላሽ አሠጣታቸው እጅግ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፉት የኒውዚላንድ ጠ/ሚር ጀሲንዳ አርደን የኒውዚላንድን ምርጫ ዳግም አሸንፈዋል። ጠ/ሚር ጀሲንዳ አርደን ትላንት በተካሄደው አጠቃላዩ ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ ነው ማሸነፍ የቻሉት። ሁለት ሶስተኛው የመራጭ ድምፅ ተቆጥሮ ከወዲሁ የሳቸው ሌበር ፓርቲ 49% እንዳሸነፈ ተረጋግጧል። ከፓርላማው 120 መቀመጫ 64…
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን የኒውዚላንድ ጠቅላላ ምርጫ በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዶክተር ቴድሮስ ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምላሽ አሰጣጥ ሂደት ላሳዩት የላቀ አመራር ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ከእሳቸው እና ከመንግስታቸው ጋር በጋር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።
በነገራችን ላይ ኒውዚላንድ ካላት 5,000,000 ህዝብ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው 25 ሰዎች ብቻ ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶክተር ቴድሮስ ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምላሽ አሰጣጥ ሂደት ላሳዩት የላቀ አመራር ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ከእሳቸው እና ከመንግስታቸው ጋር በጋር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።
በነገራችን ላይ ኒውዚላንድ ካላት 5,000,000 ህዝብ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው 25 ሰዎች ብቻ ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ጎርጎራ_ፕሮጀክት
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የጎርጎራ ፕሮጀክት ተሳታፊ ለመሆን ያቀዱ ባለሀብቶች ከ80 እስከ 300 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የፕሮጀክት ሐሳብ እያቀረቡ መሆናቸውን አስታውቋል።
"የጎርጎራ ፕሮጀክት" በአገር ደረጃ ሊሠሩ በእቅድ ከተያዙት ሀገር አቀፍ ፕሮጀክቶች መካከል ነው፡፡
የቦታውን አመቺነት የተመለኩቱ እስካሁን ድረስ ከ100 በላይ ባለሀብቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን የማከላዊ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገልጿል። (AMMA)

በወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ የተመራ ቡድን በኦሞ ወንዝ ሙላት የተፈናቀሉ ወገኖችን እየጎበኘ እንደሚገኝ ደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አሳውቋል።
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከ62,000 በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ይታወሳል።
በዛሬው ጉብኝት ላይ የተሳተፉ አርቲስቶችና የዳያስፖራ አባላት ተፈናቃዮቹን ለመርዳት ሁሉም ኢትዮጵያዊ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪ አቅርበዋል። እነሱም ህዝቡን ለማስተባበር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከ62,000 በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ይታወሳል።
በዛሬው ጉብኝት ላይ የተሳተፉ አርቲስቶችና የዳያስፖራ አባላት ተፈናቃዮቹን ለመርዳት ሁሉም ኢትዮጵያዊ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪ አቅርበዋል። እነሱም ህዝቡን ለማስተባበር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
የጤና ተማሪዎችን ጉዳይ በሚመለከት ለኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበናል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ አጭር ማብራሪያ ሰጥተውናል።
የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ (1.5 MB)
@TIKVAHETHIOPIA

በዛሬው ዕለት ማለትም በ8/02/2013 በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በመረጃ ባለሙያነት ሲሰራ የነበረው አቶ ጀግናው አሳየ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቱ አልፏል።
"አስከፊው የኮሮና ቫይረስ በሽታ ዛሬም መሀላችን ላይ አድፍጧል። እባካችሁ እራሳችሁን ጠብቁ መዘናጋቱ ዋጋ እያስከፈለን ነው" ሲል የባህር ዳር ኮሚኒኬሽን መልዕክት አስተላልፏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አስከፊው የኮሮና ቫይረስ በሽታ ዛሬም መሀላችን ላይ አድፍጧል። እባካችሁ እራሳችሁን ጠብቁ መዘናጋቱ ዋጋ እያስከፈለን ነው" ሲል የባህር ዳር ኮሚኒኬሽን መልዕክት አስተላልፏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከነገ ጥቅምት 9 ጀምሮ በአዲስ አበባ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት ይገባሉ ተብሏል።
እነዚህ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት የሚገቡት የከተማውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ነው።
የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከግል የትራንስፖርት ማህበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ የተጠቆመው፡፡
በአሁን ሰዓት በመስቀል አደባባይ ከፍተኛ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የስምሪት ፕሮግራሙ ይፋ በመደረግ ላይ ነው። (ENA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እነዚህ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት የሚገቡት የከተማውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ነው።
የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከግል የትራንስፖርት ማህበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ የተጠቆመው፡፡
በአሁን ሰዓት በመስቀል አደባባይ ከፍተኛ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የስምሪት ፕሮግራሙ ይፋ በመደረግ ላይ ነው። (ENA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ONLF
የቀብሪደሃር ነዋሪዎች በኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ሁለተኛ (2) ዓመት አክበረዋል።
በኦብነግ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የሰላም ስምምነቱ የተደረገው እንደእኤአ ጥቅምት 21/2018 በአስመራ ነበር።

ዛሬ እስራኤልና ባህሬን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው በይፋ ይጀመራል፡፡
የእስራኤል “የሰላም አውሮፕላን” የእስራኤልን እና የአሜሪካን ልዑካን ጭኖ በባህሬን ማናማ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል፡፡
የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ባህሬን UAE ተከትላ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ መስማማቷን ተከትሎ የመጣ ነው።
PHOTO : ALAIN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእስራኤል “የሰላም አውሮፕላን” የእስራኤልን እና የአሜሪካን ልዑካን ጭኖ በባህሬን ማናማ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል፡፡
የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ባህሬን UAE ተከትላ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ መስማማቷን ተከትሎ የመጣ ነው።
PHOTO : ALAIN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከነገ ጥቅምት 9 ጀምሮ በአዲስ አበባ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት ይገባሉ ተብሏል። እነዚህ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት የሚገቡት የከተማውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ነው። የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከግል የትራንስፖርት ማህበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ የተጠቆመው፡፡ በአሁን ሰዓት በመስቀል አደባባይ ከፍተኛ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ…
560ዎቹ አውቶብሶች ለ1 ሳምንት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ይሰጣሉ !
የአ/አ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኪራይ ወደ ስምሪት የሚገቡ 560 አውቶብሶች ስራ አስጀምረዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በየወሩ ለብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት 121 ሚሊዮን ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ምክትል ከንቲባዋ አመልክተዋል፡፡
የትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከአውቶብስ አቅርቦት በተጨማሪ ዘመናዊ የትራንስፖርት የመሰረተ ልማት ስርዓት እንዲዘረጋ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በቀጣይ ሁለት ዓመታት በ12 ቢሊዮን ብር ወጪ 3 ሺህ የሚሆኑ አውቶብሶችን በግዢ ለማስገባት በሂደት ላይ ነው ብለዋል።
በኪራይ ወደ ስምሪት የሚገቡት 560 አውቶብሶች ነገ ስራ የሚጀምሩ ሲሆን ለ1 ሳምንት ያህል ለሁሉም የከተማዋ ነዋሪ የነፃ አገልግሎት እንደሚሰጡ ምክትል ከንቲባዋ መግለፃቸውን ከአ/አ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ የ28 ሺህ አባወራዎች ሰብል ሙሉ በሙሉ መውደሙን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በሀብሩ ወረዳ ውስጥ 39 ቀበሌዎች ሲኖሩ 17 ወረዳዎች ላይ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ 9 ሺህ 100 ሄክታር ሰብል ፣ 60 ሺህ ሄክታር ግጦሽ ፣ 53 ሺህ ሄክታር ደን እና 60 ሺህ ቁጥቋጦ መውደሙን ወረዳው ገልጿል።
አንበጣዉ መንጋው ሙሉ በሙሉ ውድመት ባደረሰባቸው 17 ወረዳዎች 141 ሺህ 240 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
Via Addis Maleda Newspaper
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀብሩ ወረዳ ውስጥ 39 ቀበሌዎች ሲኖሩ 17 ወረዳዎች ላይ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ 9 ሺህ 100 ሄክታር ሰብል ፣ 60 ሺህ ሄክታር ግጦሽ ፣ 53 ሺህ ሄክታር ደን እና 60 ሺህ ቁጥቋጦ መውደሙን ወረዳው ገልጿል።
አንበጣዉ መንጋው ሙሉ በሙሉ ውድመት ባደረሰባቸው 17 ወረዳዎች 141 ሺህ 240 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
Via Addis Maleda Newspaper
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ሀብሩ_ወረዳ
በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል የስራ ሃላፊዎች በሀብሩ ወረዳ በአንበጣ መንጋ ሰብላቸው የወደመባቸው የአርሶ አደር ማሳ ጎብኝተዋል።
የዚህ ጉብኝት አላማ በአንበጣ መንጋ የተጎዱ አካባቢዎችን በማየት የጉዳት መጠናቸውን ለሚመለከታቸው አካላት በመግለጽ ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል ለማሳወቅ ነው።
በወረዳው የደረሰው ጉዳት በጣም ከፍተኛ በመሆኑ እና አሁንም የአንበጣ መንጋው እየጨመረ ስለሆነ መነሻው ከሆነው አጎራባች ወረዳ አሰሳ መደረግ እንዳለበት የሀብሩ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት ሃላፊ አቶ ተመቸ ሲሳይ ገልፀዋል።
በአንበጣ መንጋው ሰብላቸው የወደመባቸውን አካባቢዎች የዞን አመራሮችም ጎብኝተዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION📣
በኦሮሚያ ክልል ጭሮ እና አካባቢው የበረሃ አንበጣ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ የጭሮ ቲክቫህ አባላት መልዕክት አድርሰዋል።
Video : CNSRTC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል ጭሮ እና አካባቢው የበረሃ አንበጣ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ የጭሮ ቲክቫህ አባላት መልዕክት አድርሰዋል።
Video : CNSRTC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ፦
• ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ብዛት ደቡብ አፍሪካ ፣ ሞሮኮ እና ግብፅን ተከትላ ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ከመላው ዓለም ደግሞ 49ኛ ላይ ትገኛለች።
• በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ40 ሚሊዮን በልጠዋል ፤ ከነዚህ መካከል ከ30 ሚሊዮን በላዩ አገግሟል፤ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

በደራ ወረዳ ነገ ተማሪዎች ትምህርት ይጀምራሉ !
በደራ ወረዳ ውስጥ በባለፈዉ ዓመት 12ኛ እና 8ኛ ክፍል የነበሩ ተማሪዎች ነገ ጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ትምህርት ይጀምራሉ።
ቀሪዎቹ ከ1ኛ -11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ደግሞ ጥቅምት 16/2013 ዓ/ም ትምህርት እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
በተጠቀሡት ቀናት ተማሪዎች በሚማሩበት ትምህርት ቤት ተገኝተው ትምህርታቸው እንዲከታተሉ የደራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በደራ ወረዳ ውስጥ በባለፈዉ ዓመት 12ኛ እና 8ኛ ክፍል የነበሩ ተማሪዎች ነገ ጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ትምህርት ይጀምራሉ።
ቀሪዎቹ ከ1ኛ -11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ደግሞ ጥቅምት 16/2013 ዓ/ም ትምህርት እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
በተጠቀሡት ቀናት ተማሪዎች በሚማሩበት ትምህርት ቤት ተገኝተው ትምህርታቸው እንዲከታተሉ የደራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ማስክ በጊዜ ባለመድረሱ ምክንያት በጋሞ ዞን ነገ ትምህርት አይጀምርም ተብሏል።
ጋሞ ዞን ነገ ጥቅምት 9/2013 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ተብሎ ቢጠበቅም የማስክ አቅርቦት በተባለው ጊዜ ባለመድረሱ ምክንያት ትምህርት እንደማይጀምር ተገልጿል።
የማስክ አቅርቦት ተሟልቶ ጥቅምት 16 የመማር ማስተማሩ ሂደት እንደሚጀምር የዞኑ ትምህርት መምሪያ አሳውቋል።