TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SuperSport

ዓለም አቀፍ የሆኑ የስፖርት ውድድሮች በሱፐር ስፖርት በአማርኛ ቋንቋ መቅረብ ጀመሩ።

በመልቲቾይስ አፍሪካ እህት ኩባንያ " ሱፐርስፖርት " አማካኝነት በDSTV ቻናል 240 አዲሱ ቻናል ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ የስፖርት ክንውኖችን በአማርኛ ቋንቋ ከመጋቢት 9 ጀምሮ ማስተላለፍ መጀመሩን ዛሬ ባዘጋጀው ይፋዊ የማሳወቂያ መርሐግብር ላይ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዋናነት በዚህ የሱፐር ስፖርት ልዩ ቻናል 240 ይተላለፋል ነው የተባለው።

ሱፐርስፖርት ልዩ በአማርኛ ቋንቋ የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ቻምፒየንስ ሊግ፣ ኤፍ ኤካፕና ሌሎች የስፖርት ውድድሮችን የሚያቀርብ ሲሆን የአትሌቲክስ፣ UFC & Boxing፣ WWE እንዲሁም የቴኒስ፣ ጎልፍ፣ የሞተር ውድድር፣ ራግቢና ክሪኬት በአማርኛ ቋንቋ ይተላለፋሉ ተብሏል።

በዕለቱም የ " አቦል ቴሌቪዥን " አንደኛ ዓመት የተከበረ ሲሆን የቴሌቪዥን ቻናሉ በተለይ በፊልም ኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረው ጉልህ ድርሻ ተነስቷል።

በመድረኩ የአማርኛ ይዘቶች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የግርጌ የትርጉም ጹሑፍ (Subtitles) ታክሎባቸው ለዕይታ ይበቃሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia